🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟
⭐️ክፍል 🟰9️⃣
ከስንት ጊዜ ቡሀላ ለመጀመሪያ ቀን በአካል ቆመን አወራን ።
አይኑን ቀና ብሎ ማየት የሞት ሞት ነው የሆነብኝ።
ማታ ቤት ስገባ ቴሌግራም ላይ መልእክት አስቀመጠልኝ።
ብታይ ለናቴ ያደረግሽውን እየነገርኳት እንዴት ደስ እንዳላት እስክተዋወቃት ቸኩያለሁ እያለችኝ ነበር ይላል።
አይቼው ፈገግ አልኩኝና እኔና አንተ በደንብ እንተዋወቅና ከዛ ከእናትህጋ እተዋወቃለሁ አልኩት።
እኔና አንቺማ በደንብ እንተዋወቅ ስልሽ ኮራሽብኝ ቆይ ዛሬማ 5 ሰአት ስደውልልሽ ለምን እንደዛ እንዳደረግሽ ምክንያትሽን እፈልጋለሁ ቻው በቃ ማታ እናወራለን ብሎኝ ከonline ወጣ
ማታ በተለመደው ሰአት ደወለ አወራን።
ነገርኩት ከዚህ በፊት ስለነበረኝ ህይወት ብቻዬን እሱን ለማግኘት መውጣት ትልቅ ሀጥያት መስሎ እንደተሰማኝ አባቴ ምን ያህል ሀይለኛ እንደሆነ አጫወትኩት ይሄን ሁሉ ሳልረዳሽ ስላኮረፍኩሽ ይቅርታ አለኝ።
በተለመደው ሰአት ስልኩ ተዘጋ ።
ከቀናቶች ቡሀላ የውድድሩ ቀን ደረሰ።
ተወዳዳሪዎቹ ጠዋት ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ መጡና በጭብጨባና በሞራል ወደ ውድድሩ ቦታ ከተወሰኑ አስተማሪዎቻችንና ከዳሬክተሯጋ ተላኩ።
እኛ ወደተለመደው የትምህርት ገበታችን ተመለስን ቀኑን ሙሉ ለምን እንደጨነቀኝ ባላውቅም ተጨንቄ ነበር የዋልኩት።
ከትምህርት ቤት ዴቭ መጥቶ ሲወስደኝ ሁላ ሁኔታሽ ልክ አደለም ምን ሆነሻል ብሎ እየጠየቀኝ ነበር።
ቤት ከገባሁ ቡሀላም ቢሆን እንደወትሮው አልሳኩም አልተጫወትኩም ለፅጌ ክፍሌ ሻይ አፍልታ እንድታመጣልኝ ነገርኳትና ወደክፍሌ ገብቼ የእያሱን ስልክ መጠበቅ ጀመርኩ ።
ቴሌግራም ገባሁ ምንም መልእክት የለም ውስጤ ምን እያሰበ እንደነበር እራሱ ተደበላለቀብኝ ።
እኔን እያሳሰበኝ የነበረው የእያሱ የውድድር ውጤት ነበር ።
ወደ 12 ሰአት አካባቢ እያሱ ደወለልኝ አሁን ገና ቤት ገባሁ ከውድድሩ ቡሀላ በአስተማሪዎቻችን ግብዣ ተደርጎልን ነው እስካሁን የቆየሁት አለ።
እኔ ቀጥታ ውጤቱ እንዴት ነበር ብቻ አልኩት።
አሪፍ ነው ትምህርት ቤታችን ሁለተኛ ነው የወጣው አለኝ።
ትንሽ ንዴት ቢጤ ተሰማኝ ተበለጣችሁ ማለት ነው አልኩት።
ያው ምን ታደርጊዋለሽ በትንሽ ነጥብ ነው የተበለጥነው በቃ ስለደከመኝ እረፍት ላድርግ ነገ እንገናኛለን ደና ደሪ ብሎኝ ስልኩ ተዘጋ።
እውነት ለመናገር እንዴት ይበለጣሉ ብዬ ተናድጄ ነበር።
በነጋታው ትምህርት ቤት ስገባ ግን ጠዋት ወደ ክላስ ከመግባታችን በፊት ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ነበር ስለውድድሩ የነበረውን ነገር ነገሩን ትምህርት ቤቱ በራሱ ከአንድ አስከ ሶስት ደረጃ ሰቷቸው ሽልማት አዘጋጅቶላቸው ነበር።
አይገርም እያሱ ለካ ውድድሩን በአንደኝነት ነበር ያጠናቀቀው አንዷ ተማሪ ናት ያስበለጠቻቸው እንጂ አንደኛ ነበር ሚወጡት።
እያሱ ከውድድሩ ቦታም ትልቅ ሽልማት እንደተሰጠው ትምህርት ቤቱም በራሱ የዋንጫና የገንዘብ ሽልማት እንደሚያበረክትለት ነገሩን በሰአቱ የተሰማኝ ደስታ ወደር አልነበረውም እያሱ ስሙ ሲጠራ መድረክ ላይ ወጣ ሽልማቱን ሲቀበል ፈገግ አለ እኔም አብሬው ፈገግ አልኩ በሰአቱ ደስታ መልክ ቢኖረው እኔን ይመስል ነበር።
ከመድረክ ላይ ቆሞ ከሰዎች መሀል አሻግሮ አየኝና አመሰግናለሁ አይነት ነገር አለኝ።
ልቤ በደስታ ብዛት ዘላ ልትወጣ የደረሰች ያህል ነው የተሰማኝ ተራ በተራ ሽልማታቸውን ተቀበሉና ሶስቱም መድረክ ላይ ቆሙ ።
ዳሬክተራችን ንግግር ለማድረግ ማይኩን ተቀበለች።
አጨብጭቡላቸው ሞራል ይገባቸዋል በጣም ነው ያስደሰቱኝ በተለይ እያሱ እንዳንተ አይነት ተማሪ በማስተማራችን ኩራት ይሰማናል ውጤትህ ከጠበኩት በላይ ነበር በጣምምም ደስ ስላለኝ በግሌ የ20ሺ ብር ሽልማት አበርክቼልሀለሁ ይሄ ጅማሬው ነው ቀጣይ ብዙ ውድድሮቻችን ላይ ትምህርት ቤታችንን በኩራት እንደምታስጠራው አምናለሁ አለች በደስታ እያቀፈችው።
በቃ ከዛ ቡሀላማ ምን ውስጥ ልግባ ፈጣሪዬ ሆይ ቆይ ምን ሆኜ ነው በዚህ ልክ ደስ ያለኝ መረጋጋት ሁላኮ እያቃተኝ ነው ደስታ ለካ ከልክ በላይ ሲሆን ስሜቱ ይሄ ነው እንዴ አልኩኝ ለራሴ በዛን ሰአት ላይ ብጮህ ብዘል እንደሌሎች ተማሪዎች እብድ ብል ብዬ ተመኘሁ ግን ደስታዬን ዋጥ አድርጌ ዝም አልኩኝ።
ፕሮግራሙ ሲያልቅ ተማሪዎች ወደክፍላችሁ ግቡ ተባለ ሁሉም ተማሪ ወደየክላሱ መግባት ጀመረ አብዛኛው ተማሪ እያሱን ያየው የዛኔ መሰለኝ እኔ ከሁለቱ ልጆችጋ ወደክላስ እየሄድኩ ከፊት ለፊታችን ሶስት ሆነው ተያይዘው እየሄዱ ወይኔ በናትሽ ልጁ እያሱ ነዋ ስሙ እንዴት አስከዛሬ አላቀውም እንዴት አባቱ ነው ሚያምረው በዛ ላይ ጉብዝናው ታድሎ ግን እያሉ ያወራሉ የነሱ አልበቃ ብሎ ሁለቱ ጓደኞቼ ልበላቸው እንጂ ብቻ እነሱም ቀጠሉ ስለ እያሱ ማውራት ጀመሩ ኤልዱ ግን ይሄ ልጅ አይመችሽም እእ ለነገሩ አንቺ መልአክ እራሱ ፊት ለፊትሽ ቢቆም ቼክ ምታደርጊው አይመስለኝም እኔ ግን ተመችቶኛል ቆይ ቴሌግራም ላይ አሰማምጠዋለሁ አለች አንድኛዋ ሌላኛዋም ቀጠለች አረ አይሰማሽም ሲጀመር ጎበዝ ተማሪዎች ለእንደዚህ አይነት ነገር ጊዜ የላቸውም አርፈሽ ተቀመጪ አለቻት እኔ ዝም ብዬ ሚያወሩትን እሰማለሁ።
ውስጤ የሆነች ቅናት ይሁን ንዴት ጫር አድርጋኝ አለፈች።
ወደ ክላስ ከገባን ቡሀላ እያሱን ክላስ እስኪመጣ እየጠበኩት ነበር ግን ሳይመጣ ቀረ ።
ለካ በዛው ሽልማቱን ተቀብሎ ወደቤቱ ሄዶ ኖሯል።
ማታ ቤት እንደገባሁ ቀጥታ ወደስልኬ እሮጥኩ ምናልባት text ካደረገልኝ ብዬ ለማየት ነበር።
ግን ምንም የለም ።
ልብሴን ቀያይሬ ከእናቴጋ ትምህርት ቤት ውስጥ ስለተፈጠረው ነገር አጫወትኳት ቀጣይ ደሞ አንቺንም ውድድር ውስጥ ማየት እፈልጋለሁ አለችኝ።
ግድ ነው ታይኛለሽ እያልኳት እየተሳሳቅን አባቴ እሳት ጎርሶ እሳት ለብሶ ከየት መጣ ሳይባል ድንገት ደረሰ እኔና እናቴ ደንግጠን ከተቀመጥንበት ተነሳን ።
ምነው የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ አለች እናቴ በፍራቻ ውስጥ ሆና አው ከኤልዳናጋ ማውራት ያለብኝ ጉዳይ አለ ተቀመጡ አለ ንዴቱ እየባሰበት ።
እኔ ፍራቻዬን ዋጥ ለማድረግ እየሞከርኩ ተቀመጥኩና ምነው ችግር አለ እንዴ ምን ሆነህ ነው አልኩት።
አዎ በጣም ትልቅ ችግር አለ ትምህርት ቤቱ ጎበዝ ተማሪዎችን መርጦ ሲያወዳድር አንቺ ምን ስራ ኖሮብሽ ነው ከውድድሩ ውጪ የሆንሽው እእ እኔማ መጀመሪያ አስተማሪዎችሽ ሳይመርጡሽ ቀርተው ነው ብዬ ሄጄ ጉሮሯቸውን ልይዛቸው ነበሮ ጉዴን ስሰማ ግን ጭራሽ አንቺው ነሽ አልፈልግም ያልሽው አሉ አለኝ።
መጀመሪያ ተረጋጋ ምን እንደተፈጠረኮ ስላልገባህ ነው ከአስረኛ ክፍል አንድ ተማሪ ብቻ መመረጥ ስለሚችል ነው እንጂ እኔ አልፈልግም ብዬኮ አደለም ደሞ ባሁኑ በደንብ ላጥናና በቀጣዩ ውድድር ትምህርት ቤቱንም አንደኛ የሚያስወጣ ውጤት አመጣለሁ ብዬኮ ነው አባ አልሰማህም እንዴ ትምሀርት ቤታችንኮ ሁለተኛ ነው የወጣው እኔ እዚህ ውድድር ላይ ተወዳድሬ ቢሆንኮ እናደድ ነበር ተረጋጋ እንጂ አልኩት ምናልባት ንዴቱን ትንሽ ካበረድኩለት ብዬ ነበር።
💗 ኤልዳና 💗