🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟
⭐️ክፍል 🟰1️⃣0️⃣
እስከ አምስት ሰአት ድረስ እያሱ ከደወለ ብዬ እየጠበኩ ስለነበር ምንም አልተኛሁም ።
እንደጠበኩትም አምስት ሰአት ላይ ደወለልኝ አወራን ለእናቴ ሽልማቱን እስክነግራት አላደርስ ብሎኝኮ ነው ወደቤት የመጣሁት ዛሬ እንዴት ደስ ብሏት እንደዋለች ብታይ አለኝ የእናቱ ደስታ እንደተጋባበት ግልፅ ነው።
እና ይሄን እድል የሰጠሽኝ አንቺ ስለሆንሽ እናቴ ልታመሰግንሽ ትፈልጋለች አናግሪያት አለኝ።
አረ በፈጠረህ እኔ ምን አደረኩና ነው እኔ አልፈልግም ቀስ ብሎ ይደርሳል ብዬ እያወራሁ
ከወዲያኛው መስመር ሄሎ የኔ ልጅ የሚል ድምፅ ሰማሁ ምን ላውራ ምን ልመልስ እእእእ ሄሎ ሰላምኖት አልኩኝ እየተንተባተብኩ እንዴት ነሽ ልጄ መሰረት እባላለሁ የእያሱ እናት ነኝ አለችኝ ።
ኤልዳና እባላለሁ እኔ ደሞ የእያሱ የክላስ ልጅ ነኝ እንዴት ኖት ማዘር አልኩኝ በተራዬ።
ኤልዳና በጣም ቆንጆ ስም ነው ያለሽ እኔ አሮጊት መስዬሽ ነው አንቱ ምትይኝ ገና ልጅ ነኝኮ መሰረት ብለሽ ጥሪኝ ፈጣሪ ስላደረግሽው ነገር ስለቀናነትሽ በእጥፉ ይክፈልሽ እያሱ ይሄንን እድል በማግኘቱ በጣም ነው ደስ ያለን አለችኝ።
እሺ መሰረት ጎበዝ ልጅ ነው ያለሽ ይሄ እድል ለሱ ነው ሚገባው እድሉን የሚጠቀም አይነት ልጅ ነው እንደጠበኩት ትምህርት ቤቱንም መምህራኖቹንም አኩርቷል እንኳን ደስ ያላችሁ አልኳት ንግግሬ ከልቤ ነበር።
አዎ ብቻ መቼ ነው ታዲያ በአካል የምተዋወቅሽ ለነገሩ እኔኮ በስልክም ስታወሩ እዩዬ ስላንቺ ሲነግረኝም ስለምሰማ በቃ በአካል የማቅሽ ያህል ነው ሚሰማኝ አንድ ቀን ደሞ ቁጭ ብለን እንጨዋወታለን እሺ በሉ እኔ ልተኛ እናንተ አውሩ አለችኝ።
እሺ አይቀርም አንድ ቀን እንገናኛለን ተባብለን ስልኩን ለእያሱ ሰጠችው።
እያሱ በጣም ደስ ብሎት መሲን ነው አንቱ ያልሽው አርጅተሻል እያልሻት ነው አለኝ።
አረ እንደዛ አደለም ያው ከአክብሮት አንፃር ነው እንጂ አልኩትና ማውራት ጀመርን።
በወሬያችን መሀል የሚመጣው ቅዳሜ እንደምንገናኝ ቃል አስገባኝ እርግጠኛ ሆኜ እንደምንም አመቻችቼ እንደማገኘው ነገርኩት በደስታ እሺ አለኝ።
በነጋታው ትምህርት ቤት ገባንና ወደቤት ሰአት ላይ ሁለቱን የክላስ ጓደኞቼን ወሰድኩና ለዴቭ በጣም የምወዳቸው የረጅም አመት ጓደኞቼ እንደሆኑ ነገርኩት እሱን ያስተዋወኳቸው ቅዳሜ እነሱጋ ልሄድ ነው ብዬ ለመሸወድ እንዲመቸኝ አስቤ ነው።
ያ የተጠበቀው ቅዳሜ ደረሰ ከእያሱጋ 9 ሰአት ላይ ለመገናኘት ተነጋገርን ዴቭን ደሞ ሰባት ሰአት ላይ መጥቶ እንዲወስደኝ ነገርኩት ከአባቴ ፍቃድ መጠየቅ እራሱ አይጠበቅበትም በፈለገው ሰአት መጥቶ ይወስደኛል።
ልክ ዴቭ ሲመጣ ያዘጋጀሁትን ልብስ ለባብሼ ፀጉሬን በስርአት አሲዤ ወጣሁ ዴቭ እንደተለመደው አይቼ ማላቀው ቤት ወሰደኝ ታዲያስ አዲስ ይባላል ቤቱ ፀጥታው መስተንግዷቸው ብቻ ሁሉ ነገራቸው ደስ ይላል ሁሉም couple ሆነው ተቃቅፈው ነው ሚስተናገዱት አንድቀን ከእያሱጋ እዚህ ብንመጣኮ ብዬ እያሰብኩ ነበር ካለወትሮዬ እያሱ መልእክት እስኪልክልኝ ተረጋግቼ ቁጭ አልኩ።
8.30 ላይ ከቤት እንደወጣ ሲነግረኝ ተነስቼ ወደሽንት ቤት ሄድኩኝና ተመልሼ መጣሁ ዴቭ እነዛ ጓደኞቼኮ እንገናኝ እያሉኝ ነው ቢያንስ ለአንድ ሰአት ያህል ላግኛቸው እንዴ በዛውም ለኔ ትንሽ መዝናኛ ይሆነኛል አልኩት እሺ ኤልዱ እንደተመቸሽ መጀመሪያ ግን አባትሽን አሳውቂው ወይ እኔ ላሳውቀው እሱ ካልፈቀደ አአይቻልም አለኝ።
አረ ዴቭ እሱማ እሺ እንደማይለኝ ታውቅ የለ ቢያንስ አንድ ሰአት ብቻኮ ነው አልቆይም እስኪ አንተ እንኳን ፍቀድልኝ አልኩት በተማፅኖ ።
አይ ኤልዱ እኔ ባንቺ ምክንያት ችግር ውስጥ መግባት አልፈልግም ካጠገብሽ ዞር ስል ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም እራሴ ከቤት እንዳወጣሁሽ እራሴ ለቤተሰቦችሽ ማስረከብ አለብኝ እኔ እንድጠብቅሽ ነው የታዘዝኩት አለኝ
እሱ እያወራ የኔ እንባ ከየት መጣ ሳይባል ግልብጥ ብሎ ፈሰሰ እየተንሰቀሰኩ እንዴ ቆይ አላሳዝንህም አንተ እንኳን አትረዳኝም እንደሰው ጓደኛ የለኝ አልዝናና ቤት ውስጥ ታስሬኮ ነው እየኖርኩ ያለሁት ምናለበት ለአንድ ሰአት እንኳን ከጓደኛጋ መጫወት መሳሳቅ አብሮ ጊዜ ማሳለፍ ስሜቱ ምን እንደሆነ ባውቀው ምናለበት ።
ለነገሩ ሁላችሁም ያው ናችሁ አልኩት ደንግጦ አጠገቤ መጥቶ አቀፈኝና በቃ እሺ ኤልዱ በማዬ ሞት እኔ እንደዚህ ስታለቅሺ ማየት አልችልም አባትሽኮ ይሄን ቢያውቅ እስከዘላለሙ አጠገብሽ እንዳልደርስ ነው ሚያደርገኝ አለኝ።
እኔኮ ህፃን አደለሁም እዛው አካባቢ ትጠብቀኝና ትንሽ አውርቻቸው መምጣት ነው ስለው እሺ በቃ ተነሽ የት ነው ማደርስሽ እኔ አብሪያችሁ መሆን እችላለሁ እንዴ አለኝ??
አይ እነሱ ነፃነታቸውን ከሚያጡ አንተ እራቅ ብለህ ትጠብቀኛለህ አልኩትና ከእያሱጋ ወደተቀጣጠርንበት ካፌ ሄድኩኝ ዴቭ እስኪመለስ ድረስ ቆሜ አየሁት ስደውልልህ እዚሁ መጥተህ ውሰደኝ ስላልኩት ሀሳብ አልገባኝም ነበር ስልኬን አንስቼ እያሱጋ ደወልኩ እያየሁሽ ነው እሱ እስኪሄድ ብዬ ነው መጣሁ አለኝ።
ወዲያው ከኋላዬ መጥቶ ቆመና ሰላም አለኝ ሳቁ እየተናነቀው አቀፈኝና እኔ የምር የተገናኘን አልመሰለኝም ህልም እየመሰለኝ ነው አለ.....በፈገግታ አየሁትና መልሼ አቅፌው የምር ነው የተገናኘነው አሁን ወዴት ነን አልኩት።
መናፈሻ አለ እዛ እንሂድ ከዚህ ጀርባ ነው አለኝ እሺ አልኩት ነይ በቃ ብሎ እጄን ያዘኝ ሙቀቱ ልቤ ድረስ ተሰማኝ ከእጁ ወጥቼ እሮጥ ይመስል ጥብቅ አድርጎ ያዘኝ ለምንድነው ደስ ያለኝ ብዬ ግራ እስክጋባ ድረስ ደስታ ተሰማኝ።
ሲሄድ ተከተልኩት መናፈሻውጋ ደረስን ገባን ገንጠል ብለን ተቀመጥን።
አንዲት ልጅ መጣችና ምን ልታዘዝ አለችን ታዘዣት አለኝ አይ እኔ ምንም አልፈልግም ከዴቭጋ ምሳ በልተን ነው የመጣሁት አንተ ታዘዛት አልኩት እሱም ምንም አልፈልግም እናመሰግናለን አላት ከዚህ በፊት እንደሚተዋወቁ ግልፅ ነው ።
እሺ እና እንዴት ነሽ አለኝ ወሬ ማስጀመሪያ መሆኑ ነው በሱ ቤት።
ደና ነኝ አልኩት ፊቱን ቀና ብዬ ለማየት ድፍረቱ አልነበረኝም መሬት መሬት እያየሁ ነበር ሳወራው የነበረው ።
የሆነ ነገር ላወራሽ ፈልጌ ነበር ግን የመስማት ሙድ ላይ አደለሽም መሰለኝ አለ ።
አረ ንገረኝ እኔ ማለት በቃ እእ አለ አደል ቀና ብዬ አይን አይንህን ማየት ስላልቻልኩ ነው አልኩት።
ወዲያው ብድግ ብሎ ቆመና እሺ እንደ አዲስ እንተዋወቅ እያሱ እባላለሁ አለኝ እጁን ዘርግቶ ጨበጥኩትና ኤልዳና አልኩት ሳቄ እየተናነቀኝ።
ጥሩ እሺ ቀለል እንዲልሽ እራሴን ላስተዋውቅሽ ግን አይን አይኔን ካላየሽኝ ማውራት አልችልም አለኝ።
እሺ አልኩት።
ስሜ እያሱ ነው ተወልጄ ያደኩት እዚሁ አዲስ አበባ ነው።
እናቴ እኔ ከመወለዴ በፊት በጣም የተደላደለ ምቹ ኑሮ ነበራት ከአባቴጋ እስከምትተዋወቅ ድረስ ህይወቷ ማንም ሰው በኖርኩት ብሎ ሚመኘው አይነት ህይወት ነበር።
በአጋጣሚ ከአባቴጋ ትተዋወቅና በፍቅር ትከንፋለች እሱም ቢሆን ሁሌ ምድር ላይ በሷ ልክ ሰው እንደሌለ ይነግራታል ።
💗 ኤልዳና 💗