ፅጌሬዳ
ክፍል 25
አልተከተልኳትም ብቻዬን እየሳኩኝ ካባቴጋ ተሰብስበው ወደ ሚጫወቱት ሰዎችጋ ተቀላቀልኳቸው።
አጠቃላይ የሰርጉ ድግስ እስኪያልፍ ድረስ ሁላችንም እዛው ቆየን።
እህቴን በክብር ከዳርን ቡሀላ አባቴ የመሬቱን ሽያጭ እንዲጨራርስ እዛው ቀረ እኔ ማሂና አቶ ሳሙኤል ወደ አዲስ አበባ ተመለስን ።
ወደ አዲስ አበባ ከተመለስን ቡሀላ ማሂም ወደ ስራዋ ገባች ።
እኔም ወደ ጋራዤ ሄጄ ስራዬን ጀመርኩ ቀኑን ሙሉ ከዛ እዚህ ስሯሯጥ አንዱን መኪና ስንፈታ ሌላኛውን ስንገጥም እቃ ለማምጣት አንዴ እዚህ አንዴ እዛ ስል ድክም ብሎኝ መሸልኝ።
ማታ ላይ ማሂ ደወለችልኛና ሱቅ ጠራችኝ ሄድኩኝ።
ፊቷን ጥላዋለች ምነው የኔ ጥንቸል ፊትሽን ጣልሽው አልኳት።
አንሳልኛ ከጣልኩት አለች እንዳኮረፈች።
የዛኔ ደንገጥ ብዬ ማሂ የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ ምን ሆነሻል አልኳት።
አዎ ባክህ አሁን ቤት ምን ብዬ እንደምሄድ ጨንቆኛል ሰርጉጋ ከመሄዳችን በፊት ባለቤቴ ወደ ውጪ ሄዷል ብዬ አባቴን ዋሸሁት።
ዛሬም ተመልሼ ስሄድ መጠርጠሩ አይቀርም ቢጠይቀኝ ምንድነው ምለው አለች እንደጨነቃት ፊቷ ይናገራል።
መልስ አጥቼ ዝም አልኳት!!
እሺ ምን እናድርግ ዞሮ ዞሮኮ ማወቃቸው አይቀርም እስከመቼ ለመደበቅ ነው ያሰብሽው እውነቱን ብትጋፈጪ አይሻልሽም ደሞኮ ገና በፍርድ ቤት መፋታት አለባችሁ እሱን ሁላ ነገር ብቻሽን ማድረግ አትችይም ስለዚህ ካሁኑ እውነቱን ተናገሪና ተገላገይ አልኳት።
ትኩር ብላላ አየችኝና ቆይ ግን አሁን እንዳወራኸው ቀላል ይመስልሀል እእ ቆይ በምን ተፋታችሁ ቢለኝስ ምን መልስ ልሰጠው ነው ከሌላ ሴትጋ አልጋዬ ላይ ያዝኩት ነው ምለው ወይስ ከመጀመሪያውም ከሱ ፍቅር አልያዘኝም ነበር ልለው ነው እእ ቆይ እስቲ ንገረኝ ልጄ ተሞሸረች አገባች ወግ ማእረግ ያዘችልኝ ብሎ ተደስቶ ሳይጨርስ ደስታውን ላጨልምበት አለችኝ በጥያቄ አይን እያየችኝ ውይ ማሂ እኔ እንደዚህ ስታይኝ ይጨንቀኛል እሺ እኔ ምን ላድርግልሽ በምንድነው ላግዝሽ ምችለው አልኳት።
ጥያቄዬን በጥያቄ ትመልስልኛለህ እንዴ እኔምኮ ምን እንደማደርግ ስለጨነቀኝ ነው አንተን የጠራኹህ በናትህ የሆነ ነገር ማድረግ አለብን አሁን ቤት ስሄድ ለሚጠይቀኝ ጥያቄ መልስ የለኝም በቃ ወደ ቤት አልሄድም room ይዤ አድራለሁ አለች እንባ እየተናነቃት።
አይ ማሂ እንደሱማ አይሆንም በቃ ዞሮ ዞሮ መሰማታቸው አይቀርም አደል መጀመሪያ እንደደረስን ትንሽ ከባልሽጋ ሰላም እንዳልሆናችሁ ትነግሪያቸዋለሽ ከዛን ቡሀላ ቁጭ አድርገው ከጠየቁሽ ሁሉንም በግልፅ መናገር ነው እንዴ ስለምን ውጭ ስለማደር ነው ምታወሪው እንደትልቅ ሰው አስቢ እንጂ ብዬ ተቆጣኋት ።
ሁለታችንም ቁርጥ ያለውን ነገር መወሰን አቅቶን ሱቅ ቀምጠን አንዱን ሀሳብ ስናነሳ ሌላኛውን ስንጥል 3 ሰአት ሆነ።
አቶ ሳሙኤል ደወሉና ምነው ቆየህ ማሂም ስልክ አታነሳም አላገኘሀትም እንዴ አሉኝ።
አረ አብረን ነን ዛሬ በጣም ብዙ ምናስረክበው እቃ ነበረን እና እሱን ስናደርስ መሸብን መንገዱ ደሞ ዝግ ነው አሁን እራሱ ማሂን ቤትሽ እስክቴጂ ይመሽብሻል እኛጋ እደሪ እያልኳት ነው የደወሉት እኛጋ ትደር አይሻልም አልኳቸው።
አረ ልጄ እውነትህን ከዚህ ሰአት ቡሀላ ብቻዋን እንዳትልካት ባይሆን ባለቤቷን እኔ አወራዋለሁ በዚሁ ኑ በቃ መሽቷል አሉን
እኔና ማሂ ተያየንና እፎይ አልን።
ስልኩን ዘጋነውና ወደ ቤታችን ለመሄድ ሱቃችንን ቆልፈን ወጣን
ወደ ቤት እየሄድን እኔ መንገድ ላይ ከምገለብጥህ መኪናውን አንተ ንዳ አለችኝና ቁልፍ ሰጠችኝ።
መንገድ ላይ እየተጓዝን ግን ነገስ ምን እለዋለሁ አለችኝ በጥያቄ አይን እያየችኝ።
በቃ ነገን ነገ ያውቃል እንዳትጨናነቂ ደሞ ሰላም ያለው እንቅልፍ ተኚ እሺ ይሄንን እያሰብሽ አፍጠሽ እንዳይነጋ አልኳት።
ቤት ስንደርስ አቶ ሳሙኤል እራት እንኳን ሳይበሉ ቁጭ ብለው እየጠበቁን አገኘናቸው ።
ምነው አባቴ አትበላም ነበር እንዴ ለምን እስካሁን ቆየህ አለች ማሂ እየሳመቻቸው።
ምን ባክሽ ልጄ በፊትም አንቺ ስትወጪ ናታኔምን ተካሽልኝ ከዛ ደሞ አባቱን
ዛሬ ከቤቱ ሰው ሲጠፋ ጨነቀኝኮ አስኪመጣ እየጠበኩ አንቺም መጣሽልኝ ሰብሰብ ብለን እንብላ በቃ አሉን።
ተሰብስበን እራታችንን እየበላን ባልሽጋ ደውለሽ አሳወቅሽው አደል አሏት ፈጠን ብላ አዎ አባዬ አለች ።
በነጋታው ቁርሳችንን በላልተን እኔን ጋራዥ አድርሳኝ እሷ ወደ ሱቋ ሄደች።
እስከምሳ ሰአት ሰራራሁና ምሳ አብረን እንበላለን ስለተባባልን ማሂጋ ሄድኩ እዛ ስደርስ ሱቋ ዝግ ነበር።
ደወልኩላት ውስጥ ነኝ ብላ ሱቁን ከፈተችልኝ
አንቺ ያምሻል እንዴ እዚህ ቁጭ ብለሽ እንዴት ሱቅ ትዘጊያለሽ አልኳት ??
በቃ ባክህ አስጠላኝ ሰው ማናገር ማየት ሁላ ነው የደበረኝ እራሴን ላዳምጥ ብዬ ነው ለነገ ትዛዝ ተቀብዬልሀለሁ ሸቀል ሸቀል አድርገህ ትመጣለህ አለችኝ።
ነይ በቃ ብያት ለምሳ ይዣት ወጣሁና ምሳችንን በላን ስንጨርስ ትንሽ ምክር ቢጤ ከለገስኳት ቡሀላ ወደ ሱቅ ተመለስን ከመጀመሪያው ትንሽ ቀለል ብሏት ነበር ።
እኔ ከሰአት ጋራዥ ብዙም ስራ ስላልነበር ወደ ቤት ሄድኩ።
የጋራዥ ስራ ደስ ሚለው ጥሩ አለቃ ካለ በፈለጋችሁበት ሰአት መስራት መቻላችሁ ነው።
እንደምንም ደፈር ብዬ ስለማሂ ነገርኳቸው ቀለል አድርጌ ትንሽ ከባሏጋ እንደተጣላችና ለትንሽ ጊዜ እኛጋ እንደምትሆን ይሄንን ለሳቸው ለመናገር እንደፈራች እንዳይሳቀቁ ብላ እንደተጨነቀች ነገርኳቸው።
አይ የኔ ልጅ እውነት ለመናገር የባሏ ሁኔታ ብዙም ደስ አይለኝም ነበር ።
እሷ ከወደደችው ካፈቀረችው የሆነ ጥሩ ነገር ብታይበት ነው ይሁን ብዬ ተቀበልኩት እንጂኮ ፊቱ ላይ ምንም ደና ነገር አይነበብም ለሷም ሆነ ለኔ አክብሮት የለውም ።
ሲሆን ሲሆን የልጄ ባል ማለትኮ ለኔም ልጄ ነበር ግን እንደምታየው ነው አንድም ቀን እንደትልቅ ሰው ቁጭ ብለን እንኳን አውርተን አናቅም ተደዋውለን ስለጤንነታችን ተጠያይቀን አናቅም ልጄን አስከፍቷት ይሆን እንዴ በምን እንደተጣሉ ነግራሀለች አንዴ ልጄ እባክህ ንገረኝ አስከፍቷት ልቧን ሰብሮት ይሆን ??!
አረ ጋሽ ሳሙኤል ለኔ ምንም አልነገረችኝም አሁን ሄጄ አመጣትና ከሷጋ ሁሉንም ታወራላችሁ እሷ ለመንገር ስለተጨነቀችኮ እኔ ነገሩን ቀለል ላድርገው ብዬ ነው አልኳቸው።
ወደ ማታ አካባቢ እራሳቸው ደወሉና እቤት እንድትመጣ እየጠበቋት እንደሆነ ነገሯት እኔ የሚያወሩበትን ሰአት ልስጣቸው ብዬ ማሂ ቤት ስትመጣ እኔ ወደቤተክርስቲያን ሄድኩ ።
ማታ ላይ ማሂ ደወለችና አውርተው እንደጨረሱና ቤት እንድመጣ ስትነግረኝ ወደቤት ተመለስኩ ።
ወደ ቤት ስገባ ውጪ ተቀምጣ አገኘኋት ያወሩትን ጠየኳት በቃ ከመጀመሪያውም ለሱ ፍቅር እንዳልነበረኝና አባቴን ለማስደሰት ብዬ እንዳገባሁት ከዛ ቡሀላ ግን ፀባዩ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ከሱጋ መቀጠል እንደማልፈልግ ነገርኩት
አዎ በጣም አመሰግናለሁ ኑርልኝ ብላ አቀፈችኝ ።
በይ አታካብጂ ነገሮችን ከስር ከስር መፍታት መልመድ አለብሽ ከኔ ህይወት ተማሪ አልኳትና ወደ ውስጥ ገባን እየተሳሳቅን እራታችንን በላን ።
ይቀጥላል ...
✎ክፍል 26 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️ ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333