ፅጌሬዳ
ክፍል 28
በነጋታውም ደገመችው ሳታናግረኝ ቀድማ ወደስራ ሄደች ።
ነገሩን እንዳመረረችው ገባኝ ።
እውነት ለመናገር ከሷጋ ስጣላ ስራ ቦታ ሄጄ ንጭንጭ ነው ምለው አንዳንዴ ማወራውን ምሰራውን ሁላ አላቀውም ልክ ጎዳና ላይ እንደነበርኩባቸው ጊዚያት ባዶነት ይሰማኛል ልክ ማረባ ሰው የሆንኩ ያህል ነው ሚሰማኝ።
ግን ደሞ በቃ ከመሬት ተነስታ እንደዚህ ምትሆን ከሆነ ምን ማድረግ እችላለሁ ብቻዬን እየተብሰለሰልኩ ስልኬ ጠራ ሳላስበው ፈገግ አልኩ።
ሄሎ ማሂ አልኳት ደስታ ውስጤን ውርር እያደረገው
ሰላም እንዴት ነህ ዛሬም order የተደረጉ እቃዎች አሉ ሲመችህ ናና አድርሳቸው ብላ ምላሼን ሳጠብቅ ስልኩን ዘጋችው ይሄ እሳት ላይ ውሀ የመከለስ ያህል ነበር ባንዴ ደስታዬ ጥፍት ያለው ።
ስራዬን ጨራረስኩ መሄድ አልፈለኩም ግን ግዴታ ብሩ እንደሚያስፈልገኝ ስለማቅ ብቻ ማሂጋ ሄድኩ።
ገና ሱቋጋ ሳልደርስ ፊቴን ክስክስ አደረኩትና ወደሱቋ ገባሁ ሰላምታ እንኳን ሳልሰጣት እቃዎቹን ስጭኝ አልኳት ሰጠችኝ ከሱቁ እየተቻኮልኩ ወጣሁ ብዙ እቃ ስለነበር ማደርሰው መሸብኝ።
አንዱን ካሳንቺስ ካደረስኩ ቀጣዩ ወሎ ሰፈር ሊሆን ይችላል ከዛ ስመለስ ወደ ጣፎ ልሄድ እችላለሁ በዛው ሰሚት ያዘዘም ይኖራል ብቻ ጡዘት ቢበዛውም ግን ብሩም አሪፍ ነው።
ማታ 2.30 አካባቢ ነበር ቤት የደረስኩት ስደርስ አቶ ሳሙኤል ቁጭ ብለው በር በሩን እያዩ ነበር ማሂ ግን ተኝታለች።
ሰላምታ ሰጠኋቸውና አጠገባቸው ሄጄ ቁጭ አልኩኝ ና እስቲ ልጄ ሰሞኑን ፊትህ ልክ አደለም ህይወት እንደሰለቸችው ሰው እየሆንክ ነው የቤተሰቦችህ ነገር እያስጨነቀህ ይሆን እንዴ ምንድነው የደበረህ ያስከፋህ ስራህ ላይ አልሳካ ያለህ ነገር አለ እንዴ አሉኝ።
አይ የለም ብቻ አልኳቸው።
አይዞህ የኔ ልጅ ትንሽ ጊዜ ነገሮች እስኪስተካከሉ ብቻ ነው እሺ እኔ ምን አይነት ስራ እንደምሰጥህ ታያለሀ ግን እስከዛው ወጣት ስለሆንክ በአዲስ ጉልበት በደንብ ተንቀሳቀስ የኔና ያንተ አባትና ልጅነታችን መቼም አይፋቅም እሺ አሉኝ።
የዛኔ እንባዬ መጣ አቀፍኳቸው በእውነት እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ያለው ደግ ልበ ቀና ሰው ያለ አይመስለኝሥ ነበር።
አመሰግናለሁ አባት በሌለኝ ሰአት አባት
ቤተሰብ በሌለኝ ሰአት በረተሰብ ስለሆናችሁኝ አባቴን በኔ ምክንያት ያጣውን ክብሩን ስለመለሳችሁልኝ ብቻ አመሰግናለሁ ፈጣሪ ይሄንን ውለታ ምመልስበትን እድሜ ብቻ ይስጠኝ አልኳቸው።
ጀርባዬን መታ መታ እያደረጉ አየህ ውስጥህ ልክ አደለም ብዬሀለሁኮ እቀፈኝና በደንብ አልቅሰህ ይውጣልህ ነገሮችን በውስጥህ እንዳታስቀምጥ በሽታ ነው ወይ አልቅሰህ ይውጣልህ ወይ ተናገረው አሉኝ።
ዝም ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ ምን ማልቀስ ብቻ ተንሰቀሰኩ ማለት እችላለሁ እንጂ።
አልቅሼ ስጨርስ ቀና ብዬ አይናቸውን ለማየት እያፈርኩ ገብቼ ተኛሁ።
ስላለቀስኩ ትንሽም ቢሆን ቀለል ብሎኝ ነበር ግን ረሀቡ በተራው አላስተኛም አለኝ።
ጠዋት ቁርስ እንደበላሁ ነው ለካ የዋልኩት በጣም ብዙ ቦታ ስለዞርኩም የበላሁት ተራግፏል ።
ተመልሼ ተነስቼ አልበላ ነገር ደበረኝ እየራበኝ እንዳልተኛ ደሞ ራበኝ
ለትንሽ ደቂቃ በእንቅልፍ ለማሳለፍ ትግል ጀመርኩ ግን አቃተኝ።
ኤጭጭ አሁንስ ቆይ በረሀብ ከመሞት መብላት አይሻለኝም እንዴ
አንዴ እነሳለሁ አንዴ እቀመጣለሁ በዛ መሀል ሰራተኛዋ በሰሀን ምግብ ይዛ መጣችና ጋሼ ናቸው እራት ሳይበላ እንዳይተኛ ያሉት አለችኝ።
ከሰማይ መና እንደወረደለት ሰው በውስጤ ፍንድቅ እያልኩኝ ተቀበልኳትና ጥርግ አድርጌ እራቴን በልቼ ተኛሁ።
በነጋታው ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ አባቴጋ ደወልኩና እሁድ ወደ ሀዋሳ እንደምመጣ ነገርኩት ።
ለምን ልጄ በሰላም ነው ተጣላህ እንዴ ከነሳሙኤልጋ አለኝ።
አጋጣሚ እናቴም አብራው ነበረች ልጄ ከመጣህ ቡሀላ ናፍቆትህ ብሶብኛል እባክህ ና ባይሆን ትመለሳለህ አለችኝ።
እሺ እናቴ እመጣለሁ እኔም ናፍቃችሁኛል አልኳትና ወዳባቴ ተመለስኩ
አባቴ ከነሱጋ ተጣልቼ ሳይሆን እዛው ሆኜ ያለውን ነገር በደንብ ብናወራ ብዬ አስቤ ነው አልኩት ።
እሺ ልጄ ናልኝ እኔም ወደዛ መምጣቴ ስለማይቀር ባይሆን አብረን እነመለሳለን አለኝ።
እኔ እንኳን ስለመመለሴም እርግጠኛ አደለሁም ግን በቃ ስመጣ ሁሉንም እናወራዋለን ወደስራ ልሄድ ነው አይርፈድብኝ ብያቸው ስልኩን ዘጋሁትና ተነስቼ ለባበስኩና ከአቶ ሳሙኤልጋ ቁርሳችንን መብላት ጀመርን ።
ማሂ ሰሞኑን ሌሊት ሹልክ እያለች ነው ምትወጣው ሰላም ነው አደል ካንተጋም ታወራላችሁ አደል?? አሉኝ
አረ አዎ ሰላም ነን ስራ በዝቶባት ይሆናል አልኳቸው ምንም እንዳልተፈጠረ ነገር አድርጌ።
የኛ ስራ ዛሬ በጣም ቢዚ ከሆንን ነገ ሊጠፋ ይችላል ዛሬ ስራ ጠፍቶ ቁጭ ብለን ከዋልን ደሞ በሚቀጥለው ቀን የትኛውን መኪና እንደምንሰራ እስኪቸግረን ድረስ ስራ ሊበዛ ይችላል ዋናዎቹ መካኒኮች ወይም chif መካኒክ የሚባሉት አንዳንዴ አስከሌሊቱ 6 ሰአት እየሰሩ ሊቆዩ ሁላ ይችላሉ።
እኔ ወደስራ ስገባ በጣም በስራ ተወጥረው ነበር እኔም ልብሴን ቀያይሬ ተቀላቀልኳቸውና ከሁሉምጋ እየተሳሳቅሁ መስራት ጀመርኩ ምሳም ከነሱጋ አብሬ በላሁ።
ማታ ላይ ወደቤት ከመሄዴ በፊት ለማሂ text አደረኩላት ።
አባትሽ መጠርጠር ሳይጀምሩ አይቀሩም ከቻልሽ ዛሬ በጊዜ ነይ አይዞሽ ምንም አላወራሽም ግን ሁሌ ድብብቆሽ ስንጫወት መጠርጠራቸው የማይቀር ነው አልኳት።
እሺ አለችኝ።
ቤት ስሄድ ቀድማ ገብታ ጠበቀችኝ እንደኖርማል ሰላም አልኳትና እራት አብረን በላን ።
ትንሽ ሰብሰብ ብለን አወራንና ሁላችንም ወደመኝታችን ሄድን።
ያች ሶስት ቀን እንደምንም አለፈችና ቅዳሜ ማታ ማሂ ከመምጣቷ በፊት ለአቶ ሳሙኤል ወደ ሀዋሳ ልሄድ እንደሆነ ቤተሰቦቼ እንደናፈቁኝ ስራም ለተወሰነ ጊዜ ብቻ እረፍት እንደሰጡኝ የትምህርት ማስረጃዬንም ማስተካከል እንዳለብኝ መታወቂያም እንደሚያስፈልገኝ ብቻ ብዙ ሰአት ብቻዬን ለፈለፍኩኝ።
ፈገግ አሉና እሺ ልጄ አንተ ሚበጅህን መች አጣኸው ሰላም ግባ ሰላም ተመለስ አሉኝ።
እሺ ብዬ ጉልበታቸውን ስሜ ወደመኝታ ቤት ገባሁ ሰሞኑን የሰራሁትን ብርና እራሴ በእጄ የገዛሁትን ልብስ ብቻ ያዝኩኝ ማሂ የገዛችልኝን እየመረጥኩ አስቀመጥኳቸው በኔ ቤት እኔን ቅጥል እንዳደረገችኝ እሷም ቅጥል እንድትል ብዬ ነበር።
አቶ ሳሙኤል አሁን ባልነገሯት ከሄድኩ ቡሀላ ባወቀች እያልኩ ፀሎት ማድረግ ጀመርኩ።
ልብሶቼን እያስተካከልኩ 3 ሱሪና ሁለት ቲሸርት አንድ ሸሚዝ ብቻ ያዝኩኝ በትንሽዬ ቦርሳ ውስጥ ከተትኳት ሻወር ወሰድኩኝ ምለብሰውን ልብስ አዘጋጀሁኝና ተኛሁ ።
✎ክፍል 29 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️ ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333