የፍቅር ጥግ
ክፍል 1
እነሆ የመጀመሪያ ክፍል 👇👇👇
በጠዋቱ ከእንቅልፌ ተነስቼ እየተጣደፍኩ መለባበስ ጀመርኩ እማዬ ከስር ከስሬ እየተከተለች ታጎርሰኛለች እኔ አንዱን እቃ ሳነሳ አንዱን ስጥል እንደልማዴ እየተርበተበትኩ እማዬ ያጎረሰችኝ አጣጥሜ በልቼ ወጣሁ።
ገና ትንሽ ከመራመዴ ከኋላ ከኋላዬ እማዬ እየጠራች ትከተለኛለች ድምጿን ስሰማው ወደኋላ ዞርኩኝና ደንግጬ ወደሷ ተመለስኩ
ልጄ ምን ሆነህ ነው ምሳህን እረስተህ ምትወጣው በል እንካ ብላ ትንሿን ቦርሳዬን አቀበለችኝ።
እኔም አመስግኛት መልሼ ወደቤት አስገብቻት ስሚያት ወደስራ ቦታዬ ሄድኩ።
ትናት ጀምሬ የተውኩትን መኪና ወደመጠጋገኑ ገባሁ ።
ወዲያው አለቃዬ ከውስጥ ወጣና አንተ ወመኔ በቃ ይሄ ማርፈድህን እንቢ አልክ አደል አለኝና ተሳስቀን አብረን መስራት ጀመርን።
ወዲያው እማዬ ደወለችና እንደለመደችው አለቃህ ምን አለህ እረፈደብህ ስንት ሰአት ደረስክ ብላ ጠየቀችኝ ሁሉንም ነገርኳትና ከአልጋ እንዳትወርድ ምግቧን ብቻ በልታ እንድትተኛ ቃል አስገብቻት ስልኩ ተቋረጠ።
ምሳ ሰአት ላይ ሁሉም ምግብ አዞ ሲበላ እኔ የራሴን ምሳ በላሁ።
ትኩስ ነገር ለመጠጣት ወጣንና ጠጥተን እየተመለስን ገራጁ በርጋ አንዲት ልጅ መጥታ ገጨችኝና እራሷ መሬት ላይ ወደቀች ትኩር ብዬ አየኋትና ያምሻል እንዴ የተገጨሁት እኔ የወደቅሽው አንቺ ምን ሆነሻል ብዬ እዛው በወደቀችበት አልፊያት ወደገራጁ ገባሁ።
ይኸው ከዛን ቀን አንስቶ ለድፍን አንድ ወር ያህል ያለምንም ማቋረጥ ጠዋት ስራ ከመግባቴ በፊት ከስራ ቦታዬ አጠገብ ቆማ ጠብቃ አይታኝ በፍጥነት ከዛ አካባቢ ትሰወራለች።
አንዳንዴ ማናስታውላቸው ግን ውስጣችን ተላምደው ሚቆዩ ነገሮች አሉ አደል ብቻ ሳላስበው ሁሌ ጠዋት ጠዋት እሷን ማዬቴን ተላምጄው ነበር።
ልክ ድፍን አንድ ወር ሲሞላት የመጀመሪያ የተገናኘን ቀን እንደተጋጨነው ምሳ ሰአት ላይ መጣችና አውቃ ገጭታኝ እራሷ ወደቀች ሳያት አላስቻለኝም አይቻት ፈገግ አልኩ ...ከኔ በላይ ከት ብላ ሳቀችና ወይኔ ጉዴ አንተ ስቀህ ታቃለህ እንዴ ልክ በወሩ ታምር አየሁ ማለት ነው ፈገግ ስትል ነው ያየሁህ አደል አለችኝ።
አንቺ ጤነኛ አትመስይኝም እብድ ብያት አሁንም ትቻት ገባሁ።
ወደውስጥ ገብቼ ዞር ብዬ ሳያት ብቻዋን እየሳቀች እንደ እብድ እየሮጠች ሄደች።
ምኗን ነው የጣለብኝ እንዴ ምን ሆና ነው ብዬ ከጓደኞዬጋ ተሳስቄ ወደስራ ገባሁ።
እማዬ ህመሟ ትንሽ እየባሰባት ስለነበር በየደቂቃው ነው ስልክ ምደውልላት
በነጋታው ደገመችና ጠዋት በር ላይ ጠበቀችኝ ስተየኝ ብቻዋን ሳቀችና ተመልሳ ሄደች።
ያ ነገር ያለማቋረጥ ድጋሜ ለ15 ቀን ቀጠለ።
የሆነ ቀን ጠዋት ላይ እማዬ በጣም ስላመማት ከስራ ቀረሁ።
ጓደኞዬ ደጋግመው እየደወሉ ሲጨቀጭቁኝ ስልኬን አጠፋሁት።
ለእናት ቡና አፈላልቼ ምግብ ሰርቼላት አበላኋትና አለባብሻት ወደሀኪም ቤት ይዣት ሄድኩ እንደተለመደው ምንም በሽታ የለባትም።
እረፍት ታድርግ እራሷን እንዳታስጨነቅ ብለው መለሱን።
ሁኔታው ሰላም ስለነሳኝ ቁጭ አድርጌ አወራኋት ምንሽን ነው ሚያምሽ ምንሽጋ ነው የሚሰማሽ ብዬ ጠየኳት እናቴ ነገሩን ቀለል አድርጋው አረ ልጄ እኔ በሽታዬ ይሄ ነው አልልህም በቃ እዚህጋ ነው ስል ሌላጋ ያመኛል ልቤን ስል ኩላሊቴን ኩላሊቴን ስል ጨጓራዬን ጨጓራ ስል እራሴን በቃ ግራ ነው ሚገባኝኮ አለችኝ።
በቃ ዛሬ ቤት ውለን እረፍታችንን እናጣጥም ብያት ስልካችንን ዘጋግተን ከእናቴጋ ፈታ ስንል ዋልን ማታ ላይ ተያይዘን ቤተክርስቲያን ሄድን ስንመለስ እማዬ በዛው ጎረቤት ገብታ ወሬ ስትጀምር እኔ ትቻት ወደቤት ገባሁና ስልኬን ከፈትኩት ብዙ ያልተሳካ ጥሪ ገባልኝ ከፍቼው ደቂቃ ሳልቆይ ማላቀው ቁጥር ተደወለልኝ አነሳሁት።
ሄሎ!
ሄሎ አንተ በሰላም ነው ዛሬ ከስራ የቀረኸው አለችኝ።
ማን ልበል አልኳት።
ውይ እራሴን ሳላስተዋውቅ ፋኖስ ነኝ አለችኝ።
እሺ እኔ ደሞ ጨለማ ነኝ እንዴ... ፋኖስ ማነሽ አቅሻለሁ አልኳት
አዎ ታቀኛለህ ጠዋት ጠዋት አንተን ጥበቃ ብርድ እየጠጣሁ እየጠበኩህ እንዴት አታቀኝም ዛሬኮ ጠዋት ስትቀር ጓደኞችህን አልቅሼ ለምኜ ነው ስልክህን የሰጡኝ አለችኝ።
ማን እንደሆነች ሳውቅ እሺ ፋኖስ አሁን አወኩሽ ምን ፈልገሽ እንደደወልሽ ንገሪኝ ሰአት የለኝም አልኳት።
እእ ያው ዛሬ በሰላም ነወይ የቀረኸው ልልህና ድምፅህን ልሰማው ነው አለችኝ።
ስትሟዘዝ ነገረ ስራዋ አስጠላኝ
እንደውም ከቻልሽ ካሁን ቡሀላ ጠዋት ጠዋት እንዳላይሽ እያጨናነቅሽኝ ነው እኔ ሰላሜን ሚነሳኝ ሰው አልወድም አትከታተይኝ ስልኬ ላይም ደግመሽ እንዳትደውይ ብዬ ዘጋሁባት
ስልኳንም ብሎክ አደረኩት።
በነጋታው እንደለመደችው ከበሩ ፊት ለፊት ቆማለች እንደሌላ ጊዜው ፈገግ አላለችም አኩርፋ ነበር ባላየ አልፊያት ገባሁ።
የእማዬም ህመም ግራ እያጋባኝ ስራውም ትንሽ ቀዝቅዞ ስለነበር አንዳንድ ቀን ስራ እየገባሁ አንዳንድ ቀን ደሞ እየቀረሁ ሶስት ወራቶች ቆየን።
ሶስት ወር ሙሉ ፋኖስ አንድም ቀን ከመምጣት ተቆጥባ አታቅም ታየኝና እየሮጠች ትሄዳለች።
የቀረሁ ቀን በማይታወቅ ስልክ ትደዎልና ድምፅህን ልስማው ብዬኮ ነው በቃ ቻው ብላ ስልኩን ትዘጋዋለች እኔም የደወለችበትን ስልክ ብሎክ ማድረግ ሳይደክመኝ እሷም ስልክ እየቀያየረች መደወል ሳይደክማት ነው የቆየነው።
ጠዋት እንደተለመደው የስራ ቦታዬ በር ላይ ስደርስ ከሩቅ አንዴ አንዴ ጠብቀኝ እያለች እየሮጠች መጣች ።
ተኮሳትሬ ቆሜ ጠበቋት
ጥቁር ፌስታል አንጠልጥላለች እንካ ስጦታ ገዝቼልህ ነው እያለፍኩ ሳየው በጣም ስለወደድኩት ላንተ ገዛሁልህ እንካ አለችኝ።
አልፈልግም ሲጀመር አንድ ነገር ልንገርሽ ሴት ልጅ እራሷን ስታከብር ነው ደስ የሚለው በዚህ ልክ እራስሽን አታውርጅ እኔ ደሞ እንዳንቺ አይነት ሰው ምርጫዬ አደለም አትከታተይኝ ድጋሜ እዚህ ቦታ ቆመሽ እያየሽኝ ካገኘሁሽ አስቀይምሻለሁ ስጦታውን ደሞ ሂጅና ለሚፈልግ ሰው ስጭው ብያት ገፍትሬ ጥያት ገባሁ።
ንግግሬ ልኮ እንዳልሆነ ውስጤ ቢነግረኝም ግን ስላደረኩት አልፀፀተኝም ነበር።
ይቀጥላል....
✎ክፍል 2 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️ ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333