የፍቅር ጥግ
ክፍል 5
ጥሩ በቃ ተጫወቱ እማዬ እኔ ልተኛ ነው ብያት ብድግ አልኩ እናቴ ግን እጄን ያዘችና አስቀመጠችኝ።
ምነው እማ ፈለግሽኝ አልኳት።
አዎ አንድ ነገር ልነግርህ ነው ባንተ ፊት ቃል ላስገባት ነው አለችኝ።
ማንን???
እስካሁን ስሟን እንኳን አታቀውም አደል ልእልት ትባላለች ።
ልጄ እኔ አንድ ቃል የማስገባችሁ ነገር ቢኖር እኔ የሆነ ነገር ብሆን አይበለውና ብሞት እሷን ጓደኛ ጎረቤት እናት አድርገህ ትከሻዋን ተደገፋት አንቺም ልእልቴ በምትወጃት እናትሽ ይዤሻለሁ ልጄን ተቆጣኝ ገላመጠኝ ብለሽ ፊቲሽን እንዳታዞሪበት ምንም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን አደራዬን ላንቺ ነው የሰጠሁት በምድር የሰጠሁሽን ቃል በሰማይ እቀበልሻለሁ ይሄንን ቃሌን እንዳትረሱ አለች።
እናቴ ተናግራ እስክትጨርስ እኔ ቀድሞ እንባዬ ፈሶ አለቀ።
በጣም ስለተናደድኩ ተነስቼ ተቻት ወጣሁና አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ አላስችልህ ሲለኝ ደሞ ተመልሼ ሄድኩና እማዬ ሁለተኛ ይሄ እኔ ብሞት ወይ የሆነ ነገር ብሆን የምትይውን ነገር ደግመሽ ከተናገርሽው እንጣላለን ሁለተኛ እንደዚህ ስትይ ከሰማሁሽ ደግመሽ ፊትን አታይውም ቆይ እኔ ተጨንቄ እንድሞት ነው እንዴ ምትፈልጊው ደሞስ ቆይ ካልጠፋ ሰው ለዚች ዘገምት ነው አደራ ምትሰጭኝ እእ እኔኮ ፍቅረኛ አለኝ በቅርቡ ሚስቴ ላደርጋት ነው ታዲያ ይቺ ምን ቤት ናት ደሞ እሷን ብሎ ልእልት በስርአት ማውራት እራሱ አትችልምኮ ብያት ተመልሼ ወጣሁና ሳሎን ቁጭ ብዬ ቴሌቪዥን መመልከት ጀመርኩ።
ትንሽ ቆየት ብለው እናቴና ልጅቷ ተያይዘው መጡ እናቴ ተነስና ትምህርት ቤት አድርሰሀት ና አንተጋ መኪና እያለ ለምን taxi ትጠብቃለች አለችኝ።
ውስጤ ቅጥል እያለ ቢሆንም እሺ ብያት ቁልፈን አንስቼ ወጣሁ ።
ልጅቷ ቅርፍፍ እያለች መጣችና ጋቢና ገብታ ቁጭ አለች።
ልክ ከግቢ እንደወጣን ውረጂና በእግርሽ ሂጂ ልላት ፈልጌ ነበር ግን እናቴ ስትሰማ ምን እንደሚሰማት አሰብኩና እዛው ትምህርት ቤቷ አደረስኳት።
ስትወርድ ፊቴን እንኳን አላየችውም ቻው ወይም አመሰግናለሁ እንኳን አላለችኝም።
ይባስ እየተናደድኩ ወደቤት ለመመለስ መኪናውን እያዞርኩ እናቴ ደወለችና አንድ ክላስ ብቻ ነው ያላት ቢበዛ 45 ደቂቃ ነው በዛው ይዘሀት ና አለችኝ ።
እየማልኩ አላረገውም እማዬ አልኳት።
እሷ ግን ግግም አለች ልጄ ትራንስፖርት የያዘችውን ብር ቅድም ለኔ ቡና ገዛዝታበት መጣች እሰጥሻለሁ ብያት እረስቼውኮ ነው አለችኝ።
እየሳኩ አይ እማ ቤቱን የሞላው ቡና አደል እንዴ ያ ሁሉ ቡና እያለ ለምንድነው ምትገዛልሽ ብዬ መለስኩላት።
አደለምኮ ልጄ የሌለኝ መስሏት ነው እንጂ እኔ አጥቼ አደለምኮ አሁን 45 ደቂቃ መጠበቅ ከብዶህ ነው ይሁን በቃ አንተ እንደፈለክ አላስቸግረህ ተወው አለችኝ።
እንደከፋት ስለገባኝ እሺ በቃ እማዬ በሰው መኪና እኔ ምን እንቢ አስባለኝ በቃ ይዣት እመጣለሁ ቻው ብያት ስልኩና ዘጋሁትና ተመልሼ ያወረድኳት ቦታ ላይ ቆምኩኝ።
ፋኖስጋ ደውዬ ማውራት ጀመርን እንደለመድነው ምን እንዳወራን እንኳን በቅጡ ሳላውቅ 1ሰአት ከሀያ አውርተናል እኔ 10 ደቂቃ እራሱ ያወራኋት አልመሰለኝም ነበር።
ልክ ልጅቷ መጥታ መኪናዬ ፊት ለፊት ስትቆም ነው ያወራነውን ሁላ የተመለከትኩት።
ፋኖስን ተሰናብቻት ስልኩና ዘጋሁትና ከፍቼ አስገባኋት ።
እየተመለስን ምነው 45 ደቂቃ ነው ምትቆየው ብላኝ ነበርኮ እማ አንቺ ስንት ሰአት እንደቆየሽ ታውቆሻል አልኳት።
ዝም አለችኝ።
ንቀቷ ከምንም በላይ አናደደኝና ጥጌን ይዤ ቆሜ ውረጂ ከመኪናው ጭራሽ እኔን ማውራት እየደበረሽ ነው አብረሽኝ ምቴጂው አልኳት።
እንዳጎነበሰች ይቅርታ አለችኝ።
በፈጣሪ ስም ስንት አይነት አድርቅ ሰው አለ የሷ ግን ይለያል ።
ቤት ስንደርስ ከመቼው ከመኪናው ወረዳ እናቴጋ ሄዳ መሳሳቅ እንደጀመሩ አላውቅም ብቻ ግን መኪናውን እንኳን በስርአት እስካቆም የጠበቀችኝ አይመስለኝም ።
እኔም ችግሯ በትክክል ከኔጋ እንደሆነ ስለገባኝ ትቻቸው ገብቼ ለጥ አልኩኝ ።
ተኝቼ ሳስበው የነበረው ለፋኖስ ቀለበት ማስርላት መቼ ነው እንዴት አድርጌ ግሮግራሙን ላዘጋጀው ሚለውን እያሰብኩ ነበር እንቅልፍ የወሰደኝ።
ይቀጥላል...