🔸🔸🔺🔺🔹🔸
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ ማኔ
ክፍል 7️⃣
ከፊት ለፊቷ ሄጄ ቁጭ ስል እልህ ውስጤን ተናንቆኝ ሰውነቴ መንቀጥቀጥ ጀመረ።
ምንም ሌላ ነገር ልልሽ አደለም ግን ምክንያትሽን ብቻ ንገሪኝ አልኳት።
የፌዝ ሳቅ ፈገግ አለችና ታስታውሳለህ ከአመት በፊት የሆነች ቀይ እንቡጥ ለማየት ምታሳሳ ፀጉሯ በጀርባዋ የተነሰነሰ አደለም ለመምታት ለማየት ምታሳሳ ያያት ወንድ ሁሉ የሚመኛት አንዴ በሳቀች ብሎ ሰው ሁሉ የሚጠብቃት ልጅ እእ ለኛ ቤተሰብ ደሞ የመሳቃችን ምክንያት እሷ ነበረች።
እናትና አባቴ ለመፋታት ጫፍ ደርሰው እሷ በመረገዟ ምክንያት ትዳራቸው ስለቆየ ስጦታ ብለው ስም አወጡላት በቃ ለቤታችን ስጦታ ናት እሷ ከተወለደች ጀምሮ ቤታችን በረከት በበረከት ሆኖ ነበር።
ያ ለመፍረስ ጫፍ የደረሰው ትዳር እንዳዲስ የሰው ምሳሌ የሚያስቀና ትዳር ሆኖ ነበር።
ሁሉም ነገር ግን ነበር ለምን አትለኝም ባንተ ምክንያት ነው ለችኝ የሚፈሰውን እንባዋን ካይኗ ላይ እየጠረገች።
እንዴት??? ነገሮች ይበልጥ ተወሳስበውብኝ በአግራሞት እየተመለከትኳት ነበር።
ጥሩ እንዴት ማለት አሪፍ ነው ምን መሰለህ እህቴ ምትማረው ከእናት መስሪያ ቤት አስፋልት ተሻግሮ ያለው የሀብታም ትምህርት ቤት ነው ።
እና እሷ ወደትምህርት ቤት ባባቴ መኪና እየሄደች አንተ ከtaxi ወርደህ ወደስራ ቦታህ እየሄድክ ታይሀለች ምንህን እንደወደደችው ባላቅም ብቻ ባንድ እይታ ፍቅር ያዛት አባቴ ትምህርት ቤት በር ላይ አድርሷት ሲመለስ እሷ ተደብቃ አስፋልት ተሻግራ ቆማ አንተ ስራ ቦታህ እስክትመጣ ቆማ ትጠብቅሀለች አንተ ወደስራ ቦታ ለመግባት ስለምታረፍድ አንተን ጥበቃ እየቆየች እሷም ክላስ አርፍዳ ትገባለች ተደጋጋሚ ጊዜ በማርፈዷ ምክንያት ለአባቴ ተደውሎ ለምን እንደምታረፍድ ጥያቄ ቀረበበት አባቴ ደሞ ሁሌ በጊዜ ነው ክላስ አድርሷት የሚመመለሰው በዛ ምክንያት ግራ ስለገባው እህቴን አብዝቶ ተቆጣት ድጋሜ በማርፈድ ቅሬታ ከቀረበባት እዚሁ ለቤታችን ቅርብ የሆነ ሌላ ትምህርት ቤት እንደሚያስገባት ሲነግራት ሁለታችንም ደነገጥን ምክንያቱም እኔ ስላንተ ሁሉንም ነገር ጠንቅቄ ስለማቅ ነው። ለህቴ ከኔ በላይ ቅርብ ሰው የላትም ምንም ነገር ሳደብቅ ትነግረኛለች ስምህን እንኳን ሳታቀው ስላንተ ስታወራ አይኗ ይበራ ነበር አንዴ በሳቀች ብለን ምጠብቃት ልጅ ስላንተ ስታወራ ግን ፊቷ እንደፀሀይ እያበራ ሳቅ በሳቅ ሆና ነበር ምታወራኝ።
በመጨረሻም ሁሉንም እውነት ላንተ ነግራህ ሰአት አመቻችታችሁ እንድትገናኙ እሷም ክላስ ሳታረፍድ ወይ ስትወጣ እንድታይህ ካልሆነም ማታ ላይ ከስራ ሰአትህ ቡሀላ እየመጣን ልናገኝህ ወሰንና ለእህቴ ሁሉንም እውነት አፍረጥርጣ እንድትነግርህ ሌሊቱን ሙሉ ስመክራት አደርኩ እሷም ተስማማች ።
በነጋታው ስልኳን ይዛ ወደትምህርት ቤት መጣች ያንተን ስልክ ተቀብላ በዛውም ለኔ ምን እንዳልካት ደውላ ለመናገር ስለፈለገች ነበር ስልክ የያዘችው።
አይገርምም አንተ ጢባራሙ እእ አንተ ብቻ ወንድ የተፈጠርክ የሚመስልህ አንተ ግን እንደምትወድህ ስትነግርህ በጥፊ ብለህ ሸኘሀት።
እህቴ በሰአቱ እያለቀሰች እጅህን እንዳነሳህባትና በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተመታች በዛም ምን ያህል እንደከፋት እያዞራት እንደሆነና ትምህርት ቤት መጥቼ እንድወስዳት እየነገረችኝ ነበር ንግግሯን እንኳን ሳትጨርስ እህቴ የመኪና ሰለባ የሆነችው የቤታችንን ድመቀት ነው የቀማኸን ሳቃችንን ነው ያሳጣኸን የናትና አባቴን ትዳር ነው የበተንከው ገባህ ባይኔ ሙሉ ስላየኋት ምትሟሟብኝ የሚመስለኝን እህቴን በመኪና አደጋ እንዳጣት ያደረከኝ ታስታውሳለህ አደል አስክሬኗ እንኳን ከመሬት ተለቅሞ ነው የተቀበረችው የሚሰቀጥጥ የመኪና አደጋ ነው የደረሰባት እሷን ካጣሁ ቡሀላ ከልቤ ስቄ አላቅም ከእናትና አባቴ ቤት ወጥቼ ነው ምኖረው እናቴ ጤነኛ አደለችም ባንዴ ልጇንም ትዳሯንም ነው ያጣችው አባቴ ከስንት አንዴ ነው ስልክ እንኳን ሚያነሳልን የት እንዳለ የት እንደሚኖር አናቅም።
አንተ ካደረከን ነገር አንፃር እኔ ምንም አላደረኩህም ሰው ፊት ብቻ ነው ያዋረድኩህ ማፍቀር እንዴት እንደሆነ ስቃዩ እንድትረዳ ስለምፈልግ ነው እስካሁንም የታገስኩህ እንጂ እንደኔማ ቢሆን ገና የመጀመሪያ የተገናኘን ቀን መጥህ ውስጥ መርዝ አድርጌ ብገልህ ምኞቴ ነበር ስታቅፈኝ እንዳባ ጨጓሬ ነው ምትኮሰኩሰኝ ሳይህ ፊቴ ላይ ቀድሞ ሚመጣው ነፍሰገዳይነትህ ነው ምን ያህል ትግስተኛ እንደሆንኩ የገባኝ አንድ አመት ሙሉ አንተን መታገሴን ሳስበው ነው።
እህቴ ምን ጥሎባት አንተን እንደወደደችህ አላቅም አንተን እንኳን ማፍቀር ለትንሽ ቀን አብሮ ጊዜ ማሳለፍ እራሱ ይከብዳል ምትቀፍ ሰው ነህ ምንህም አይስብም።
ይታይሀል ከነሱጋ የተቀመጠው ሰው ፍቅረኛዬ ነው የአራት አመት ፍቅረኛዬ አሁን አብረን ነው ምንኖረው በከፋኝ ሰአት ከጎኔ የነበረው እሱ ነው አለችኝ።
አንዳንዴ የምንሰማውን ነገር ማመን አቅቶን ፈጣሪን በቃ ከህልሜ ቀስቅሰኝ እንጂ እስካሁንኮ አልነቃንም ብለነው አናቅም እኔ በሰአቱ እንደዛ ነው ያልኩት።
ፋኖስ ይሄን ሁላ ነገር ስትነግረኝ እያለቀሰች ስለነበር አሳዘነችኝ ውስጤ ተላወሰ እራሴን ጠላሁት በእህቷ ፈንታ እኔ በነበርኩ ብዬ ተመኘሁ።
ምንም ነገር ሳልነግራት ዝም ብዬ ተነስቼ መውጣት ፈልጌ ነበር ግን ለማንም አውርቼ ማላቀውን ሚስጥሬን ለመንገር ወሰንኩ ምናልባት ትንሽ ልቧ ላይ ያለውን ጥላቻ ማብረድ ከቻልኩ ብዬ አስቤ ስለነበር ነው ንግግሬን ሳልጀምር ማላቀው ስልክ ተደወለልኝ አላነሳሁትም ስልኬን ሳይለንት አድርጌ ኪሴ ከተትኩትና ለፋኖስ ከልጅነቴ ጀምሮ የተፈጠረውን መተረክ ጀመርኩ።
እኔ የተወለድኩት እዚሁ ነው።
እኔ ስወለድ እናቴ መውለድ ሳትፈልግ በድንገት ነው የተረገዝኩት ለማስወረድ ብዙ ብትሞክርም ፈጣሪ ስላልፈቀደው ሳይሳካላት ቀረ አባቴ የልጅ ፍቅሩ በጣም ከፍ ያለ ስለነበር በእናቴ ማርገዝ ደስታው ጣራ ነክቶ ነበር።
እሷ ስትወልድ እንዳትሳቀቅ ብሎ ሰፊ ቤት ተከራየላት እሷ ሌሊት ወጥቶ ማታ እየገባ እሷን አንድም ስራ እንድትሰራ አይፈቅድላትም ሰራተኛ ቀጠረላት ከመሬት እቃ ስታነሳ ሁላ ሚከፋው አባት ነበረኝ።
ይቀጥላል...
🟫ፀሀፊ ✍️ ማኔ
🔻ክፍል 8️⃣ ነገ ማታ2️⃣🟰3️⃣0️⃣ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️