🔸🔸🔺🔺🔹🔸
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ ማኔ
ክፍል 8️⃣
እቃ ስታነሳ ሁላ ሚከፋው አባት ነበረኝ።
እኔም ተወለድኩ ስራ እረፍት ጠይቆ እንደ እናት አረሳት እሷ ምንም ዘመድ ስላልነበራት ሚጠይቃት ሰው እንኳን የላትም።
ብቻ ምን አደከመሽ እኔ ተወልጄ ሁለት አመት ከሆነኝ ቡሀላ እሱ እንደአራዊት ሌሊት እየወጣ ሌሊት እየገባ አንቀባሮ ሲያኖራት እናቴ ጠገበችና እዛው ግቢ ተከራይቶ ከሚኖር ወንደላጤጋ መማገጥ ጀመረች።
አባቴ ተደጋጋሚ ጊዜ ወሬ ቢደርሰውም ንቆ ያልፈው ነበር።
የሆነ ቀን ግን እጅ ከፍንጅ ያዛት እና ተጣሉ እራሷ አኩርፋ ከቤት ጥላ ወጣች ከወር ቡሀላ ግን እኔ እየተጎዳሁ እንደሆነ ስላሰበ መልሶ እራሱ ለምኖ ታረቃት እሷ ግን ይቅርታ አድርጎላት እንኳን አመሏን አልተወችም አባቴ ደሞ ከምልሽ በላይ ይወዳት ያፈቅራት ነበር ከሷ ሌላ ሴት ምድር ላይ የተፈጠረች አይመስለውም እሷን አጥቶ መኖር መተንፈስ እንደሚችል አያምንም።
ብቻ በጣም ብዙ ጊዜ እየታረቁ እየተጣሉ ቆዩ በመጨረሻም አታስገድደኝ እኔ ከሌላ ሰው ፍቅር ይዞኛል አንተንም ልጄንም አልፈልጋችሁም አለችው።
አባቴ ተስፋ አልቆረጠም ያለማቋረጥ ሽማግሌ እየላከ ሰላም ሲነሳት ወደሌላ ከተማ አድራሻዋን አጥፍታ ጠፋች አባቴ በሷ ናፍቆት ብዙ ተሰቃየ እሷ ልቴድበት ትችላለች ብሎ ያሰበው ቦታ በሙሉ እኔን እየያዘ እየዞረ ይፈልጋት ነበር በሷ ምክንያት ከስራ ተባረረ።
የምንበላው አጣን አባቴ ግን በዛን ሰአት የምንበላው ከማጣታችን በላይ የሷ ካጠገቡ መራቅ አብዝቶ ያሳስበው ነበር እኔንም በጣም ስለሚወደኝ ለደቂቃ ካይኑ ዞር እንድል አይፈልግም።
የሆነ ቀን የድሮ አከራያችን የት እንዳለች ነገረችው እኔን ይዞ ከአክስቴ ብር ተበድሮ ያለችበት ይዞኝ ሄደ እናቴ ከሌላ ሰው አርግዛ ለመውለድ ተቃርባ ነበር ያንን የተመለከተው አባቴ እህቱጋ ሄዶ አደራ ሰቷት እሱ ሄዶ እራሱን አጠፋ ።
በሰአቱ አክስቴ መሀን ስለነበረች እኔን እንደልጇ ተቀበለችኝ እናትም አባትም ሆና አሳደገችኝ።
ግን እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ስለናቴ ምሰማው ነገር ሴትን ልጅ እንድጠላና ፍቅር ሚባለው ነገር በራሱ የሰው ልጅ የመሞቿ ገመድ እንደሆነ እያሰብኩ ነው ያደኩት።መንገድ ላይ ወንድና ሴት ተቃቅፈው ሲሄድ የወንዱ መሞቻ ቀን መች ይሆን እያልኩ ነው የኖርኩት።
ገባሽ ሴትን ልጅ አደለም ለፍቅር ለጓደኞነት እራሱ ለመቅረብ አስቤ ሞክሬ አላቅም ሁሉም ሴቶች እንደናቴ ይመስሉኛል ልክ እናቴ አባቴን ለሞት እንደዳረገችው እኔም ባፈቀርኳት ሴት የምጠፋ ይመስለኛል ።
ለዛ ነው እራሴን ከሴት ልጅና ከፍቅር ማርቀው።
ደሞ የዛን ቀን እህትሽ ከነዩኒፎርሟ መጥታ እወድሀለሁ ተረዳኝ ስትለኝ ገና ህፃን እይደሆነችና አርፋ ትምህርቷን እንድትማር ስነግራት እሷ ግን ግግም ብላ ስልክህን ስጠኝ ስትለኝ ገና በዛ እድሜዋ ለዛውም ከነዪኒፎርሟ እንደዛ መሆኗ አናዶኝ ነው በጥፊ የመታኋት እንጂ እኔ እንድትሞት አደለም ከልቤ ፀፅቶኛል አስተዳደጌ ነው እንደዚህ ያደረገኝ አልኳት።
አደል አትርሳ አሳዳጊህምኮ ሴት ናት ለሴት ልጅ ጥላቻ ካለህ እሷን እንዴት በዚህ ልክ ልትወዳት ቻልክ አለችኝ።
ንግግሯ አናደደኝ እማዬንማ የምወዳት ከልቧ ሴት ስለሆነች ነው ገባሽ ለኔ ላልወለደችው ልጇ ህይወቷን ለመስጠት ስለማታመነታ ነው።
ጠያቂ ዘመድ ባጣሁ ሰአት እሷ ብቻዋን ዘመድ አዝማድ ሆና ስላሳደገችኝ ነው።
አንድም ቀን የናትና አባቴን አለመኖር እንዳስታውለው እድል ስላልሰጠችኝ ነው
በኔ ምክንያት ስትሰደብ ስትገፋ የሰውን አይን ሲገርፋት አንገቷን ደፍታ ስላሳለፈች ነው።
ኮንፊደንስ ያለው ጠንካራ ወይድ አድርጋ ስላሳደገችኝ ነው ገባሽ እማዬን መጥላት ማለት እራሴን መጥላት ነው ።
ደሞ ይቅርታ አድርጊልኝና እህትሽንኮ እኔ አፍቅሪኝ አላልኳትም እኔ እንደሌሎች ወንዶች አፈቅርሻለሁ እወድሻለሁ ብዬ አልሸወድኳትም በህይወቷ በሴትነቷ አልተጫወትኩም እኔን እንደጠላት ማየትሽ እራሱ ተገቢ አደለም።በእርግጥ ሴት ልጅ ላይ እጅ ማንሳት ወንድነት አደለም አጥፍቻለሁ እኔም ካለፈ ቡሀላ ፀፅቶኝ ነበር ግን እኔ እንደሞተች እንደዚህ አይነት አደጋ የደረሰባት ሴት እሷ እንደሆነች አላወኩም አንድ ተማሪ ተገጭታ ሞተች የሚል ወሬ ብቻ ነው የሰማሁት አልኳት።
ዝም አለች በእጇ ሂድ የሚል ምልክት ሰጠችኝ ከዛ በላይ እዛ ቦታ መቆየቴ አስፈላጊነቱ አልታየኝም ስትረጋጋ ባወራት እንደሚሻል አስቤ ተነስቼ ሄድኩኝ ጓደኞቿ ሁላ ገላመጡኝ።
ልክ ከዛ ቤት ለቅቄ እንደወጣሁ ስልኬን ከኪሴ አወጣሁት መጀመሪያ የተደወለልኝ ስልክ 15 ሚስኮል ተደርጓል።
እማዬም ከአስር ጊዜ በላይ ደውላለች ልቤ መምታት ጀመረ እየተንቀጠቀጥኩ መልሼ ደወልኩ አይነሳም የማላቀው ስልክ ላይም ደጋግሜ ደወልኩ አይነሳም እንዴት ብዬ መኪና ውስጥ እንደገባሁ አላቅም ግን ወደሰፈር መሄድ ጀመርኩ መኪና ውስጥ ከገባሁባት ሰአት አንስቶ ያለማቋረጥ እየደወልኩ ነበር ከየትኛውም ስልክ ግን ምላሽ አላገኘሁም መኪና ውስጥ የተቀመጥኩበት ወንበር በረዶ ሰራብኝ።
መኪናው እየተነዳ ያለ አልመስልህ አለኝ ሹፌሩን ተቀብዬ ባበረኩት ብዬ ተመኘሁ።
ሰፈር እንደረስኩ እየተሯሯጥኩ ነው ወደውስጥ የገባሁት ልክ ከሩቅ ቤታችን ሳይ ግርግር የሚሉ ሰዎችን ስመለከት አንዳች የተስፋ መቁረጥ ስሜት ተሰማኝ በደመነፍስ ደረስኩ ግቢው በለቅሶ እየተደበላለቀ ነው በር ላይ የቆሙት ሰዎች አልታይ አሉኝ።
እንዴት አልፊያቸው እንደገባሁ አላቅም ብቻ ስደርስ እናቴ ሞታ ነበር።
ለመሳቅና እናቴንም ቀልዱን ትታ እንድትስቅልኝ አውቃ እንደሆነ እያተናገርኩ ለመቀስቀስ ሞከርኩ እናቴ የምሯን ነው የሞተችው።
ያቺ ውጭ ምግብ ከበላሁ የተጎዳሁ ሚመስላት እናቴ
ያቺ ማታ ትንሽ ሲመሽብኝ ከግቢ ውጭ እየተጎራደደች ተጨንቃ መንገድ መንገዱን እያየች ምትጠብቀኝ ደርባባዋ ሴት ያቺ ዘመድ ያልወለድሽውን ልጅ ለማሳደግ ምን አሰቃየሽ አንቺስ እንደናቱ አትጥይውም ብለው ሲናገሯት እኔን የጎዱባት መስሏት ከሙሉ ዘመዶቿ የተቆራረጠችው እናቴ ያቺ ሳትበላ ሳትለብስ ሙሉ ህይወቷን ክርትት ስትል የኖረችልኝ እናቴ ሞታለች።
በሰአቱ የሰው ልጅ በህይወት ኖሮ እንደሚሞት ተረድቻለሁ እኔ ቆሚያለሁም ሞቻለሁም ።
የእናቴን አስክሬን ለማስለቀቅ ሲሞክሩ አቅፊያት ከሷጋ መሆን እንደምፈልግና ከአጠገቤ እንዳይወስዷት ከሁሉምጋ መጣላት ጀመርኩ።
የእናቴን ፊት ገልጬ ተመለከትኩት አሳዘነችኝ ፊቷ እንደከፋው ነው
እንባዬ ደረቀ ከፊት ለፊቴ ልእልት ቆማ ስትንሰቀሰቅ አየኋት እንደእብድ እየጎተትኩ መኝታ ቤት አስገባኋትና እናቴ ምን እንደሆነች ጠየኳት።
ለማውራት እየተናነቃት እቴቴ ከታመመች ቆይታለች በየተኛውም ሰአት እንዳትጨነቂ ንዴትና ጭንቀት የሞትሽን ቀን ያፋጥኑታል ተብላ በሀኪም ተነግሯት ነበር ቀን ከተፈጠረው ነገር ቡሀላ እቴቴ ደና አልነበረችም የሆነ ሰአት በጣም ሲብስባት ለመረጋጋት ያንተን ድምፅ መስማት ፈልጋ ደጋግሜ ስደውል አታነሳም እሷም እየደወለችልህ አታነሳም በዛ ሰአት ልጄ በንዴት የሆነ ነገር ሆኖብኝ ነው ብላ እንደ እብድ አደረጋት ተነስታ ከቤት ለመውጣ ስትሞክር ወደቀች ግን ደግማ አልተነሳችም አለችኝ።
በቃ የዚህ ሁሉ መንስኤ ፋኖስ ናት እሷ ናት የናቴ ገዳይ እያወራሁ ተቻኩዬ ኪችን ገባሁ ስለት ያለውን ቢላ አንስቼ ከጀርባዬ ሱሪየ ውስጥ ከተትኩት የኔ እናት ሞታ እሷ በህይወት አትኖርም እገላታለሁ ....
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️