🔸🔸🔺🔺🔹🔸
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ ማኔ
ክፍል 2️⃣1️⃣
ይውሰዱት አልኳት።
ሁለቱም ተናደዱብኝ ልእልት ተስፋ በመቁረጥ አይን ተመለከተችኝ፡፡
ተነስቼ ልወጣ ስል እዮብ አስቆመኝና እንግዳኮ ነኝ ለቤቱ ትተኸኝ ልትወጣ ነው እንዴ ብሎ አስቆመኝ፡፡
ተመልሼ ቁጭ አልቁ ስለቤቱ እርእስ ማንሳት አልፈለኩም እነሱም ሁኔታዬ ስለገባቸው ዝምታን መረጡ፡፡
ቀኑ እየመሸ ሲሄድ ልእልት ቤት ደርሼ ሸውጄ እወጣለሁ ካልሆነ እናቴ ትገለኛለች ብላ ተነስታ ወጣች፡፡
ትንሽ ቆይቶ በር ተንኳኳ ተመልሳ እንደመጣች አስበን እዮብ በር ከፈተ ግን እሷ አልነበረችም ከሱቅ ሳጥን ቢራ የያዘ ሰው በር ላይ ቆማል እኔ ደረጃው ላይ ቆሜ ስለነበር እዮብ ግራ ገብቶት ማነው ያዘዘው ማእዶት ናት የላከችው እያለ ነው አለኝ።ግራ ገብቶኝ እኔጃ ማናት ማእዶት አልኩት ሰውዬው ቀበል አድርጎ እዚህ ጎረቤታችሁ ናታ ቆንጅዬዋ ድምፕል ያላት ፀጉረ ረጅሟ ልጅ አለ፡፡
ስለማን እያወራ እንደሆነ ስለገባን ተቀብለነው ወደውስጥ አስገባነው ልእልት እስክትመጣ እዮብ እኔ አልጋ ላይ የነበረውን ፍራሽ ሳሎን አነጣጠፈና ና ዱቅ እንበል አለኝ፡፡ ለአይን ያዝ ያዝ ሲያደረግ ልእልት በድጋሜ በር አንኳኳች ከፍተን አስገባናት እዮቤ ገና ከበር አንቺ ማእዶት ነው እንዴ ስምሽ አላት። አዎ እኔኮ ብዙ ስም ነው ያለኝ ይሄኔ በስሜ ልክ ብር ቢኖረኝ እኔ ነበርኩ ሀብታም ብላ እየቀላለደች ፍራሹ ላይ ቁጭ አለች።
እስክመጣ እንድትጠጡኮ ነው ቀድሜ መጠጡን የላኩላችሁ አጠጡም እንዴ አለችን።
እዮብ አብራን ከጠጣች ብለን እየጠበቅናት እንደሆነ ነገራት፡፡
ታውቁ የለ እንደማልጠጣ እናንተ ጠጡ አለችን ተጀመረ ሞቅታው ሲጀምርን እርስ በርስ መተራረብና ከጣራ በላይ መሳቁን ተያያዝነው፡፡ ልእልት ሁኔታችን ግራ ገብቷት ድምፅ እንድንቀንስ አጥብቃ እየጠየቀችን እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡
ልክ መጠጡ ድንዝዝ ማድረጉን ሲቀጥል ልእልት እንድናቆም ነገረችን እኔ አሻፈረኝ አልኩኝ የእናቴን ፎቶ እያየሁ ድፍት ብዬ እዬዬ ማለት ጀመርኩ ልእልትና እዮብ እንደምንም አስነስተው አስገብተው አስተኙኝ።
ጠዋት አረፋፍጄ ተነሳሁ እዮብ ብቻውን ነው ያለው ፡፡ቁርስ ላቅርብ ተነስና ታጠብ አለኝ።
ተጣጥቤ ቁርስ እየበላን እዮብ አንድ ሀሳብ አቀረበልኝ አሁን አንተ ለዚህ ቤት በብርቱ አላማ የመታገል ሀሳብ ከሌለለህ ለምን ቤቱን በልእልት ስም አታረገውም ቢያንስ ዘመድ ጎረቤት ፊቱን ሲያዞርብህ አንድ ያልተወችህ ሰው እሷ ናት ።
እናትህም ለሷ ነው አደራ የሰጠችህ።
እንደምታያት ጎበዝና ጠንካራ ልጅ ናት በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ አትተውህም ስለዚህ አሁኑኑ ፕሮሰሱን እንጀምርና በሷ ስም አድርግላት አለኝ።
እሺ ማለትም መቃወምም አልፈለኩም።
ዝም አልኩት፡፡እዮብ ቁጭ አድርጎ ብዙ ነገሮችን ነገረኝ መከረኝ ። ያው በሰአቱ ለምንም ነገር ፍላጎት ስላልነበረኝ ዝም ብዬ እሺ እሺ አልኩት።
እስከ ምሳ ሰአት አንዴ ስንጠጣ አንዴ ስናጨስ ከቤት ግቢ ውስጥ ከግቢ እቤት ስንመላለስ ምሳ ሰአት ደረሰ። ልእልት መጣች ትምህርት ቤት እንደሚሄድ ሰው ለባብሳ
ነበር፡፡እዮብ እንዳያት ሄዶ ጥምጥም አለባት።
እኔ ዝም ብዬ ቁጭ አልኩ።
አጠገቤ መጥታ ቁጭ አለችና ዛሬ እቴቴ መቃብርጋ አትሄድም አደል ይኸው ቤቱም ምኑም የሷ ፎቶ ስለሆነ እዚህ እሷን ማየት ትችላለህ ።
ስትወጣ ስትገባ እያዩህ እንዳይረብሹህ ብዬ ነው አለችኝ፡፡ በሀሳቧ ተስማማሁ እዮብ ገና ከመቀመጧ ቤቱን ባንቺ ስም ሊያደርግልሽ ነው አላት።
ደነገጠች አረ አይሆንም በስማም እኔ አልፈልግም ይሄ ቤትኮ እቴቴ ነፍሷን ያጣችበት ቤት ነው ለሱ ደሞ ምን ማለት እንደሆነ ያቀዋል አለች።
እኔ ሀሳብ አልሰጥም ወሳኝም ፈራጅም ሁለቱ ሆነው ቁጭ አሉ።እዮብ ከነምክንያቱ እትትት እያለ ያስረዳት ጀመር።
በመሀል እዮብ ለልእልት በዛውምኮ ይሄ ቤት በስምሽ ከሆነ መቼም ቢሆን ተለያይታችሁ አትለያዩም አናቱን ባሰ ቁጥር ቤቱን ያስባል ቤቱን ባሰበ ቁጥር ደሞ አንቺን ያስብሻል አላት። ትንሽ አንገራገረችና እሺ አለች።
የዛን ቀን ልእልትና እዮብ ባንድ ነጠላ ካላስቀደስን እያሉ አብረው ቤት ሲያፀዱ አብረው ምግብ ሲሰሩ ቀኑ አለፈ። በነጋታው ልእልት ከቤቷ እስክትመጣ ጠብቀን አብረን ወደሚመለከተው አካል ሄድን ።
የሚያስፈልገውን ሁሉንም ፕሮሰስ ጠየቅን ነገሩን ያን ያህል ከባድ አልነበረም ፕሮሰሱን ጀመርን ሙሉ ያለኝ ነገር የቀረኝ አንድ ሀብት ቤታችንን በልእልት ስም አደረግነው አክስቶቼ ቤቱን ሊጠይቁ ሲመጡ በሷ ስም እንደሆነ ሲያውቁ የሚሰማቸውን ስሜት እያሰብኩ ደስታ ተሰምቶኝ ነበር።
ብቻ በዛን ሰአት ልክ ቤቱን በስሟ አድርገን ስንመለስ ፏ ብዬ ለብሼ ፀጉሬን ተስተካክዬ ነበር ምክንያቱም እዛ ቦታ ላይ ከንግግር በላይ የለበስነው ልብስ ዋጋ አለው፡፡
መንገድ ላይ ልእልትና እዮብ ተያይዘው እየሄዱ እኔ ከኋላቸው ብቻዬን እጄን ኪሴ ከትቼ እየተራመድኩ እነሱን እየተመለከትኩ ነበር ሁሉም ሰው አይኑ እነሱ ላይ ነው ሲመስለኝ እዮብና እሶ ፍቅረኛሞች መስለዋቸው ሳይሆን
አይቀርም። ቤት ገባን አሪፍ ጊዜ እንዲያሳልፉ ነግሪያቸው መኝታ ቤቴ ገብቼ ቆለፍኩና ጋደም አልኩ።
ጭንቅላቴ እረፍት አጣ ልእልት የምር ምትታመን ሰው ናት ከፋኖስ ቡሀላ መመማር መቻል ነበረብኝ እንዴት በድጋሜ......
እንዴት በድጋሜ ሰው አምናለሁ እያል መብሰልሰል ጀመርኩ ትንሽ ቆይታ ልእልት መጥታ በር አንኳኳች እራት እንብላና ወደቤቴ ልሂድ አለች፡፡
እናንተ ብሉና ሂጂ እኔ አልመጣም አልኳት፡፡
በር ላይ ቆማ ለረጅም ሰአት ከለመነችኝ ቡሀላ እሺ ደና ደር ብላኝ ሄደች።
ምሽቱን ሙሉ ብቻዬን ስነሳ ስቀመጥ ዝም ብዬ ክፍሉ ውስጥ ስንጎራደድ አራት ሰአት አካባቢ ሆነ የዛኔ መተኛትም ማሰብም አልቻልኩም የማስበው ግራ ገባኝ ጭንቅላቴ ውስጥ ጭጭጭጭ የሚል ድምፅ ብቻ ይሰማኝ ጀመር።
ተነስቼ ከክፍሌ ወጣሁና ወደ እዮብጋ ሄድኩ ቤት ውስጥ የለም ዞር ዞር ብዬ አየሁትና ወደ ውጭ ወጣሁ ቀጥጥጥ ብሎ ቆሞ ሰማይ ሰማይ እያየ ፈገግ ይላል እግሩ ስር ቢያንስ አራት አምስት የተጨሰ ሲጋራ ተጥሏል።
አየሁትና አጠገቡ ሄጄ ምን እንደሆነ ጠየኩት።
ዝም ብሎ ፈገግ ብሎ እያየኝ ምንም አልሆንኩም አንተ ለምን መጣህ አለኝ። ቤት ስለጨነቀኝ ወክ እንድናደርግ ጠየኩት እሺ አለኝ ቤቱን እንኳን ሳንዘጋው የውጭውን በር ብቻ ቆልፈን ወጣን።
ሰፈሩ ጭር ብሏል እኛ ዝም ብለን መራመዳችንን ቀጥለናል ሁለታችንም ዝም ብለን እስከ አስፋልት ደረስን ወዴት እንሂድ ወደቀኝ ወንስ ወደግራ ተባብለን ወደቀኝ ጉዞ ጀመርን በመሀል እኔ ቅድም ለምን ነበር ብቻህን ፈገግ ስትል የነበረው አልኩት።
ልእልትን እያሰብኩ ነበር አለኝ።
በጥያቄ አይን እያየሁት ከምርህን ነው እሷን አስበ በጥያቄ አይን እያየሁት ከምርህን ነው እሷን አስበህ ፈገግ አልክ አልኩት፡፡ አዎ ፈጣሪ እንደማይወደኝ የገባኝ እሷን ከረፈደ ቡሀላ ባንተ በኩል አድርጎ ወደኔ ሲያመጣት ነው አለኝ፡፡ እንዴት????
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️