አዲሱ የአፕል አይ ኦ ኤስ (iOS) 18.3 ሶፍትዌር
አይፎን ተጠቃሚዎቹ ያለ ኢንተርኔት ዳታ ወይም ያለ ዋይፋይ የጹሁፍ መልዕክት ለመላላክ የሚችሉበትን አይ ኦ ኤስ (iOS) 18 ነጥብ 3 የተባለ ሶፍትዌር አስተዋውቋል።
ይህ አዲሱ ሶፍትዌር በአይፎን 14 እና ከሰሱ በኋላ በተሰሩ በሁሉም የአይፎን ሞዴሎች ይሰራል ተብሏልለ።
ተጠቃሚዎች የኢንተርኔት ዳታ እና ዋይፋይ በማይሰራባቸው ቦታዎች ሆነው ሳተላይት ብቻ በመጠቀም የጽሑፍ መልእክት፣ ኢሞጂዎችን ለመቀበል እና ለመላክ ያስችላቸዋል ተብሏል።
አፕል በቅርብ የአይ ኦ ኤስ (iOS) 18 ነጥብ 3 ማሻሻያን የስታርሊንክ ሳተላይት ቴክኖሎጂን ወደ አይፎን በማካተት የሞባይል ግንኙነቱን ቀይሯል።
ይህ ስራ በስፔስ ኤክስ እና ቲ-ሞባይል መካከል በተደረገው ትብብር አማካኝነት የተሰራ ሲሆን ወደ ፊትም ፎቶዎችን፣ ሙዚቃዎችን እና ቪዲዮዎችን መላላክ የሚችሉበትን መንገድ ለማካተት ታቅዷል።
አዲሱ ስምምነት አፕል በግሎባልስታር ላይ ካለው የረዥም ጊዜ ጥገኝነት ሲወጣ የመጀመሪያው ሲሆን ወደፊት ለሚደረጉ የሞባይል ግንኙነት የበለጠ እንዲሚያጠናከር ፍንጭ የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል።
የመልዕክት ሳተላይቱ በአሜሪካ እና ካናዳ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን የአይፎን 14 እና ከሱ በኋላ ባሉ በሁሉም ሞዴሎች ላይ ይሰራል ተብሏል። ሶፍትዌሩ ስልክ ላይ ከተጫነ በኋላ ደንበኞች ለሁለት ዓመት ያህል በነፃ መጠቀም እንደሚችሉም ከአፕል ድረገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አዲሱ አሰራር ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ የግሎባልስታር አክሲዮኖች በ11 በመቶ እንዲቀንስ ማድረጉን ተዘግቧል።
@Ethionews433 @Ethionews433