Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
* "በረመዳን የተፈፀመ (ሱና የሆነ) ኸይር ስራ በሌላ ጊዜ እንደተፈፀመ ግዴታ ዒባዳ ነው።
* በረመዳን የተፈፀመ ግዴታ ዒባዳ በሌላ ጊዜ እንደተፈፀመ ሰባ ግዴታ ዒባዳ ነው።"
ይሄ ሐዲሥ ደካማ ነው። ደካማ እንደሆነ ከገለፁ ዐሊሞች ውስጥ የተወሰኑትን ልጥቀስ፦
1- ኢብኑ ሐጀር:- [አተልኺሱል ሐቢር፡ 3/1121]፣
2- አል0ይኒይ:- [ዑምደቱል ቃሪ : 10/383]፣
3- አልባኒይ:- [ተኽሪጁል ሚሽካት ፡ 1906] [ዶዒፉ ተርጊብ፡ 589]፣
4- ኢብኑ ዑሠይሚን:- [ፈታዋ ኑሪን ዐለ ደርብ: 2/ 568]
ማሳሰቢያ:-
~
ይሄ ማለት ከላይ በተጠቀሰው ደካማ ሐዲሥ ላይ ባለው መልኩ ለመደምደም ሶሒሕ ማስረጃ ያስፈልጋል ለማለት እንጂ በተከበሩ ቦታዎች እና ጊዜዎች ውስጥ የሚፈፀሙ ተግባራት ከሌሎች ተግባራት ልዩነት የላቸውም ለማለት አይደለም። በተከበሩ ቦታዎች እና ጊዜያት ውስጥ የሚፈፀሙ ተግባራት ኸይርም ሆኑ ሸር በሌላ ቦታዎች እና ጊዜዎች ከሚፈፀሙት ተግባራት መጠናቸው ከፍ ይላል። ለምሳሌ ሐረም ውስጥ የሚሰገድ ሶላት ከሌላ ቦታ ሶላት መጠኑ በጣም ይለያል። ወንጀልም ላይ እንዲሁ። በዙልሒጃ የመጀመሪያ አስሩ ቀናት የሚፈፀም ዒባዳ በሌላ ጊዜ ከሚፈፀመው በጣም ይበልጣል። ረመዳንም የተከበረ ወር እንደመሆኑ ከሌሎች ጊዜያት ብልጫ አለው። ይሁን እንጂ ከላይ በሰፈረው ዶዒፍ ሐዲሥ ላይ በተጠቀሰው መልኩ መጠኑን ለይቶ ለመናገር ሶሒሕ ማስረጃ ያስፈልጋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor