ቢላል/ኮካ መስጂድና መድረሳ በጎ አድራጎት ማህበር


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified



Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ዒድ ጁምዓ (ዓርብ) ዕለት ሲውል ሰላተል ዒድ እና የጁመዓ ሰላት ሁኔታ

የሳዉዲ ዓረብያ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ በቁጥር 21,160 ባወጣው መግለጫ ተከታዮቹን ሀሳቦች ጠቅሷል።

1) ኢማሙ ሰላተል ጁምዓ እንዲሰገድ የማድረግ ግዴታ አለበት። ጁምዓ ለመስገድ በቂ ሰዉ ካልተገኘ ዙህርን ያሰግዳል።

2) ሰላተል ዒድ የሰገደ ሰው የጁምዓ ሰላትን ባይገኝ ይፈቀድለታል። ዙህርን በወቅቱ ይሰግዳል። ሆኖም ግን ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር ጁምዓን ቢሰግድ የተሻለ ነው።

3) የዒድን ሰላት ያልሰገደ ግን ይህ ፍቃድ አይመለከተዉም። ጁምዓን የመስገድ ግዴታ አለበት።

4) በዚህ እለት ጁምዓ በሚሰገድባቸዉ መስጂዶች ሲቀር የዙህር አዛን አይደረግም።

© ተንቢሀት






ዘካተል ፊጥር እና አፈጻጸሙ

በወንድም ጣሀ አህመድ

ዘካተል ፊጥር ከረመዳን ወር ፆም መጠናቀቅ ጋር በተያያዘ ግዴታ የሚሆን የዘካ አይነት ነው፡፡ ዘካተል ፊጥርን መስጠት እያንዳንዱ ሙስሊም ላይ በነፍስ ወከፍ ግዴታ ሲሆን፤ እያንዳንዱም አባወራ የራሱን ጨምሮ በእርሱ ስር ስላሉ ቤተሰቦቹ ሁሉ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ ኢብኑል ሙንዚር ‘አል-ኢጅማዕ’ በተሰኘው ኪታባቸው ‹‹ዒልምን የተማርንባቸው ዑለማዎች ሁሉ ዘካተል ፊጥር ግዴታ መሆኑን ተስማምተውበታል›› በማለት የጉዳዩን ግዴታነት ከሚያመለክቱት ነብያዊ ሀዲሶች በተጨማሪም የኡለማዎችን አጠቃላይ ስምምነት (ኢጅማዕ) የተገኘበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

√ የተደነገገበት ጥበብ

ድሆች በባዕሉ (ዒድ) እለት ሰዎችን ከመለመን እንዲድኑና የእለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም በፆም ወቅት ተከስተው ላለፉ አንዳንድ ጉድለቶች (ግድፈቶች) ማሟያ እንዲሆን ነው፡፡

ይህን አስመልክቶ ዐብደላህ ኢብን አባስ እንዲህ ይላሉ፤

عن ابن عباس ـ رضي الله عنهما ـ قال: "فرض رسول الله صلى الله عليه وسلم زكاة الفطر طهرة للصائم من اللغو والرفث وطعمة للمساكين، فمن أداها قبل الصلاة فهي زكاة مقبولة، ومن أداها بعد الصلاة فهي صدقة من الصدقات" رواه أبو داود
وابن ماجه
‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥርን ለፆመኛ ለ ‘ለግዉ’ (ጥቅም ለሌላቸው ውድቅ የቀልድ ንግግሮችና ተግባሮች) እና ለ ‘ረፈስ’ (ፆታዊ ስሜትን ቀስቃሽ ለሆኑ ንግግሮች) ማፅጃ፤ ለምስኪኖች (ድሆች) መብል ሲሆን በግዴታ መልኩ ደንግገውታል፡፡ ስለዚህም ከኢድ ሰላት በፊት (ዘካውን በመስጠት ግዴታውን የተወጣ) ተቀባይነት ያለው ዘካን ሰጥቷል፤ ከኢድ ሰላት በኋላ ዘካውን የሰጠ ከሌላ ግዴታ ያልሆነ ሰደቃ አንዱ እንደሆነ ይታሰብለታል፡፡››
(አቡዳውድ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል)


√ የዘካተል ፊጥር መጠን

ኢብኑ ኡመር ሀዲስ ላይ እንዲህ የሚል መልዕክት ስለተላለፈ ነው፤
‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ከተምር ወይም ከገብስ አንድ ‹‹ሷዕ›› በእያንዳንዱ ሙስሊም፤ ባሪያ፣ ጨዋ (ባሪያ ያልሆነ)፣ሴት፣ ህፃን፣ አዋቂ ላይ ግዴታ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም ሰዎች ወደ (ዒድ) ሰላት ከመውጣታቸው በፊት ለሚገባቸው ሰዎች እንዲደርስ አዘዋል፡፡›› (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

ሷዕ የመስፈሪያ አይነት ሲሆን በድሮ ጊዜ የነበረ የእህል መስፈሪያ ነው። በዘመናዊ መለኪያ አንድ ‹‹ሷዕ›› 2.04-2.5 ኪ.ግ ይመዝናል፡፡ 1 ሷዕ = 4 የሁለት ዕጅ እፍኞች ነው።

√ ዘካተል ፊጥር በማን ላይ ግዴታ ይሆናል?

ዘካተል ፊጥር ግዴታ የሚሆነው ሁለት መስፈርቶችን ባሟላ ሰው ላይ ብቻ ነው፤ እነርሱም 1. ሙስሊም በሆነ 2. ዘካተል ፊጥር ማውጣት ግዴታ በሚሆንበት ቀን እና ሌሊት፤ ለራሱ እና ለቤተሰቦቹ የሚበቃ መብል ኖሮት የተረፈው እና ተጨማሪ ነገር ያለው፡፡

√ ዘካተል ፊጥር የሚሰጠው መቼ ነው?

ዘካተል ፊጥርን ከ(ዒድ) ሰላት በኋላ ማዘግየት የተከለከለ ሲሆን፤ ማውጣቱ ግዴታ የሚሆንበት ወቅት የሚጀምረው ከረመዳን የመጨረሻው እለት ፀሀይ ከጠለቀችበት ወይም ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዓት አንስቶ ነው፡፡ ነገር ግን ኢብኑ ዑመርን ጨምሮ ሌሎቹም ሰሀቦች ያደርጉት እንነበረው ከዒድ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀድሞ ዘካተል ፊጥርን ማውጣት ይፈቅዳል፡፡

√ ለዘካተል ፊጥር የሚሰጡ የእህል አይነቶች

ዘካተል ፊጥር ሙስሊሞች ከሚመገቡዋቸው እንደ እሩዝ፤ በቆሎ፤ ጤፍ…. ባሉ የምግብ እህል አይነቶች ነው። መልእተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) በሀዲስ የጠቀሷቸው የምግብ እህሎች (እንደ ገብስ፤ ተምር፤ ዘቢብ) የመሳሰሉት ሲሆኑ፤ ነገር ግን የምግብ አይነቶቹ በነዚህ ላይ ብቻ እንደማይገደቡ የሻፊዒያ እና የማሊኪያ መዝሀብ ዑለማዎች ሲስማሙበት ሸይኹል ኢስላምም የመረጡት አቋም ነው፡፡

የአላህ መልአክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ከተምር ወይም ከገብስ አንድ ‹‹ሷዕ›› እንዲወጣ ማዘዛቸውን በተመለከተም እነዚህ ዑለማዎች የሚሰጡት ምላሽ ‹‹መልእክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) እነዚህን የምግብ አይነቶች የጠቀሱት የመዲና ሰዎች በምግብነት ይጠቀሟቸው የነበሩ ከመሆናቸው አንፃር ነው፡፡ ስለሆነም የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) አነሱ የሚያገኙትንና የሚመገቡትን የምግብ አይነት ነው እንዲያወጡ ያዘዟቸው›› የሚል ነው፡፡

በዚህም መሰረት በማንኛውም አካባቢ የሚኖር ሙስሊም ማህበረሰቡ አዘውትሮ ከሚመገባቸው የምግብ እህሎች ዘካተል ፊጥሩን መልዕክተኛው ሲጠቀሙበት በነበረው መስፈርያ መጠን ማውጣት ይችላል፡፡

√ ዘካተል ፊጥር መሰጠት የሚገባው ለማን ነው?

በዚህ ጉዳይ ላይ ዑለማዎች ሁለት አይነት አመለካከት ያለቸው ሲሆን ሚዛን የሚደፋው ሀሳብ ለምስኪኖች እና ለድሆች ብቻ ይሰጣል የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱም በኢብኑ አባስ ሀዲስ ላይ መልዕክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ‹‹ለምስኪኖች መብል …›› በማለት ዘካተል ፊጥር የተደነገገበትን አላማ ከመግለፃቸው ጋር የተያያዘ ነው፡፡

√ ዘካተል ፊጥርን በገንዘብ ተምኖ መክፈል

ዘካተል ፊጥርን በዋጋ ተምኖ መክፈል አይፈቀድም።
ምክንያቱም፤ በኢብኑ አባስ ሀዲስ ላይ መልዕክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥር የተደነገገበትን አላማ ሲገልፁ ‹‹ለምስኪኖች መብል …›› በማለታቸው ጋር የተያያዘ ነው፡፡

አቢ ሰዒድ አልኹድሪይ እንዲህ ብለዋል፤
“የአላህ መልዕክተኛ በነበሩበት ዘመን ዘካተል ፊጥር የምናወጣው ከምግብ አንድ ሷዕ ነበር” ብለዋል።

ዘካተል ፊጥርን ከተገደበለት ጊዜ ማስቀደም ወይም ማቆየት እንደማይቻል ሁሉ የአወጣጡን አይነትም መቀየር አይቻልም። ዒባዳ ሁልጊዜ በአላህ የሚደነገግ እንጂ በአስተያየት ምንፈፅመው አይደለም። ማንኛዉም ሙስሊም ዒባዳው እንዳይበላሽበት ሊጠነቀቅ ይገባዋል። በገንዘብ መተመን በቀደምት ሰለፎች አልተፈፀመም። ከጥቂቶች በቀር አብዛኞቹ የኢስላም ሊቃዉንት በገንዘብ ማዉጣትን ይቃወማሉ። አል-ኢማም ማሊክ፣ አል-ኢማም አሻፊዒይ እና አል-ኢማም አህመድ ይህ መዝሀባቸው ነው። ስለዚህም በተባለው መልኩ በእህል ያወጣ ሰው በሁሉም ስምምነት ትክክለኛ ዒባዳ ሰርቷል።

√ ዘካተል ፊጥርን ወደ ሌላ ቦታ መላክ፤

እያንዳንዱ ሙስሊም በጾመበት ቦታ ዘካተል ፊጥርን ማዉጣቱ ቢሆንም የሚያስፈልገው ነገር ግን ምግብ የሚቀበል ሚስኪን ሰው የሌለበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በቤተሰቦቻቸዉ ወይም ጓደኞቻቸው አማካኝነት ችግረኞች ወዳሉበት ቦታ መላክ ይችላሉ።

በጥቅሉ ማንኛዉም ሰው ኢባዳውን በኢልም ላይ የተመሰረተ በማድረግ ኢስላምን በሚገባ ለመተግበር መሞከር ይገባዋል።

تقبل الله الصّيام والقيام وجميع الطّاعات
--
"አላህ መልካም የሻለትን (ሰው) ዲኑን ያስገነዝበዋል" ቡኻሪና ሙስሊም


Forward from: Abduljelil soresa


Forward from: Abduljelil soresa


Forward from: Taha Ahmed
ለይለተል‐ቀድርን መጠባበቅ

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– « ለይለተል‐ቀድርን ከረመዳን ከመጨረሻውቹ አስርት ለሊቶች "ዊትር" ጎደሎ በሆኑት ተጠባበቋት።»
ቡኻሪና ሙስሊም  ዘግበውታል።

እንደሚታወቀው ለይለተል‐ቀድር እንደ ስሟ እጅግ የገዘፈች ለሊት ናት። ከአንድ ሺህ ወራት በላይ ዋጋ ያላት ለሊት። ታዲያ እንዲህ አይነቷን አንድ ለሊት በሚገባ አላህን በማመለክ ላይ ሆኖ ማሰለፍ ለአንድ ሙእሚን እጅግ በጣም የሚያጓጓ መሆኑ ግልፅ ነው። መልእክተኛውም ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ይህችን ለሊት መቼ የበለጠ በርትቶ መጠባበቅ እንደለብን ጠቁመውናል። በዚሁ ማስታወስ የሚያስፈልገው ለይለተል‐ቀድርን መጠባበቅ ሲባል በዱዓእ፣ በዚክር፣ ቁርአን በመቅራት፣ በሰላት እና በመሳሰሉት ነብዩ እና ሰሀቦቻቸው በሰሩት መልካም ስራዎች ማለት እንጂ ጫት በመቃም፣ በ"ኢስላማዊ ነሺዳ" ስም የተዘጋጁ ሙዚቃዎችን በማደመጥ፣ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ ወደ ሰማይ በማንጋጠጥ ወይም ሌላ ያልታዘዘ  አልያም የተከለከለ ነገር በመፈፀም አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል።
በዚህ ሀዲስ ውስጥ  "ዊትር" ጎደሎ በሆኑት ለሊቶች የሚለው ቃል የተፈለገው ሙሉ ቁጥር ያልሆኑትን 21፣23፣25፣27፣29 ለማለት ነው።

በሌላ በኩል ሌሎችን መረጃዎች መሰረት በማድረግ ሙሉ የሆኑ ማለትም እንደ 22፣24 እና 26 ያሉ ለሊቶችንም ችላ ማለት እንደማይስፈልግ እና በነሱ ውስጥ ለይለተል‐ቀድር ሊሆን የሚችል መሆኑን የጠቆሙ ዑለማዎች መኖራቸውን ማስታወስ ያሰፈልጋል።
እንደአንዳንድ ዑለማዎች አባባል ከሆነ ደግሞ ከዊትር ለሊቶች አንደኛው የጁመዓ ለሊት ከሆነ ይህ ለሊት የበለጠ ተስፋ የሚጣልበት ይሆናል።
ስለሆነም በቀሪዎቹ ጊዚያት ተጠቃሚ ለመሆን እንዘጋጅ።

አላህ ያግራልን!

✍️ ጣሀ አህመድ

🌐
https: rel='nofollow'>//t.me/tahaahmed9


Forward from: Taha Ahmed
ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት

እናታችን ዓኢሻ (ረዲየላዑ ዓንሀ)  እንዲህ ብለዋል፡‐ ‹‹ የአላህ መልዕክተኛ ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ሲገባ ለሊቱን በዒባዳ ላይ በማሳለፍ ህያው ያደርጉ፣ ቤተሰባቸውን ያነቃቁ ፣ ቀበቷቸውን በማጥበቅ (በዒባዳ ላይ) ይተጉ ነበር፡፡›› ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
በሐዲሱ ውሰጥ "ቀበቷቸውን ያጠብቁ ነበር" በሚል የተጠቀሰውን ቃል በተመለከተ ብዙ የሐዲስ ተንታኞች ይህ ‘‘አሽሙራዊ አገላለፅ ሲሆን ለማለት የተፈለገውም በከፍተኛ ሁኔታ በዒባዳ ከመጠመዳቸው በመነሳት ከሴቶቻቸው ይርቁ ነበር ለማለት ነው።’’ ብለዋል።

✍ ጣሀ አህመድ

🌐
https://t.me/tahaahmed9


Forward from: Taha Ahmed
ለይለተል-ቀድር መሆኑን ባውቅ ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ?

እናታችን ዓኢሻ ረዲየ ‐አላሁ ዓንሀ እንዲህ ብለዋል፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለይለተል-ቀድር የትኛዋ ለሊት መሆኖን ባውቅ ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ? ብዬ ጠየቅኳቸው። እሳቸውም:- "አላሁመ ኢነከ ዓፉዉን ቱሂቡ አል-ዓፍው  ፈዕፉ ዓኒ " በይ አሉኝ:: ትርጉሙም "አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ" ማለት ነው።
  ቲርሚዚይ፣ኢብኑ ማጃህ፣ ኢማሙ አህመድ እና ሃኪም ዘግበውታል:: ሸይኽ አልባኒም  ሀዲሱን ሰሂህ ከማለታቸውም ባሻገር በአንዳንድ የቲርሚዚይ ኪታብ ህትመቶች ላይ የሚታየው "ከሪሙን" የሚለው ቃል ጭማሪ ከአንዳንድ ፀሀፊዎች ወይም አታሚዎች ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል::

✍ ጣሀ አህመድ

🌐
https: rel='nofollow'>//t.me/tahaahmed9




🔴 የሴት ልጅ ኢዕቲካፍ በተመለከተ

በመሰረቱ ሴት ልጅ ልክ እንደ ወንዶች ኢዕቲካፍ ማድረግ ትችላለች። በነቢዩ ዘመንና ከእሳቸው ህለፈትም በኃላ ሚስቶቻቸው ኢዕቲካፍ እድርገዋልና።

የተወሰኑ ሊቃውንት በመሰረቱ ሴት ልጅ ተገዳ ካልሆነ በስተቀር ከቤት መውጣቱ የተወገዘ ስለሆነ ኢዕቲካፍ ማድረጓም የተጠላ ይሆናል ሲሉ ሌሎች ደግሞ በእድሜ ከፍ ላሉ ሴቶች እንጂ ለወጣትና ታዳጊ ልጃገረዶች ኢዕቲካፍ አይቻልም የሚል አቋም አላቸው:: ከባሏ ጋር ከሆነ ትችላለች ካልሆነ አትችልም ያሉም አሉ።

ይህን ያሉት ወጣትና ታዳጊ ሴቶች በእድሜ ከገፉት ይልቅ ለፈተና ስለሚጋለጡ ወይም ወንዶችን ለፈተና ስለሚያጋልጡ ነው፤ በተለይ ኢዕቲካፍ ከቤት ውጪ ውሎ ማደርን ስለሚያስከትል።

ከዚህም አንጻር ሴት ልጅ ኢዕቲካፍ በማድረጓና ለኢዕቲካፍ ብላ ከቤት በመውጣቷ ምክንያት ከወንድ ጋር የምትቀላቀል ወይም ከወንድ ጋር ተገልላ የምትቀመጥ ከሆነ፣ እራሷ ፈተና ላይ የምትወድቅ፣ ወይም ሌሎችን ፈተና ላይ የምትጥል ከሆነ፣ ወይም ደግሞ ደህንነቷ በአስተማማኝ ሁኔታ የማይጠበቅ ከሆነ ከኢዕቲካፍ ትከለከላለች።

የባል ፈቃድ
ሴት ልጅ ባሏ ወይም ኃላፊዋ ከፈቀደላትና ሌሎች መስፈርቶች ከተሟሉ በኃላ ለደህንነቷ የማያሰጋ የትኛውም መስጂድ ላይ ኢዕቲካፍ ማድረግ ትችላለች። በባሏ ፈቃድ ኢዕቲካፍ የገባች ሴት ባሏ ኢእቲካፍ እንድታቋርጥ ከፈለገ ይችላል። ያለርሱ ፈቃዱ የምታደርገው ኢዕቲካፍም ትክክለኛ አይሆንም። ወንጀለኛ ከመሆን ጋር ኢዕቲካፉ ትክክል ይሆናል የሚል አቋም ያላቸው ሊቃውንት አሉ። ለሱንናህ ብሎ ግዴታ የሆነን የባል ሐቅን መጠበቅ መተውም አግባብ አይደለም፣ ለተጨማረ ዒባዳህ ብሎ ወንጀለኛ መሆን ብልህነት አይደለምና ሴት ልጅ ያለ ባሏ ፈቃድ ኢዕቲካፍ ልታደርግ አይገባም። ባለትዳር ያልሆነች | ሴትም ብትሆን በስሩ ያለችን አባቷንም (ወላጆቿን) ወይም ወንድሟን ሰታሳውቅና ሳታስፈቅድ ኢዕቲካፍ ልታደርግ አይገባም። ባልና ወላጆችም | በቂ ምክንያት ወይም ስጋት እስከሌላቸው ድረስ፣ የኢዕቲካፉ ቦታ ደህንነቱ አስተማማኝ እስከሆነ ድረስና ቦታው ላይ እምነት ወይም ስነ-ምግባራቸው እንዲበላሽ የሚያደርግ ነገር መኖሩን እስካላረጋገጡ ድረስ ከመልካም ነገር ሊከለክሉ አይገባም። ባል ፈቅዶ ሚስት ሱንናህ የሆነን ኢዕቲካፍ ከጀመረች ኋላ ሀሳቡን ቀይሮ እንድትወጣ ቢያዛት እሺ የማለት ግዴታ አለባት። | “በነዝር” (በስለት) ምክንያት ግዴታ የሆነ ኢዕቲካፍን ግን አስፈቅዳው ከጀመረች በኋላ | ሳትጨርስ ባሏ ማስቋረጥ አይችልም።

|ምንጭ፦ አል መጅሙዕ ሊን-ነወዊይ 8/4፣ አል-ኢትሓፍ 29

( ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚይያህ የሚከተለውን ብለዋል፤ "ሐይድ ላይ | ያለች ሴት ልድ አስገዳጅ ለሆኑ ነገሮች መስጂድ መግባት ትችላለች፤ ነገር ግን | ለመስገድና ለኢዕቲካፍ ብላ መግባት አትችልም፤የ “ነዝር” የስለት ኢዕቲካፍ እንኳ | ቢሆን፡፡ ኢዕቲካፍ ላይ ያለች ሴት ሐይዷ ከመጣ ከመስጂድ ወጥታ ግቢው ላይ ድንኳን ተጥሎላት እዛ ላይ ትቆያለች፤ … ሐይድ | ኢዕቲካፏን | አያበላሽም፤ ምክንያቱም እሷ ፈልጋ የምታደርገው ነገር ስላልሆነ፤ | ከመስጂድ ትውጣ የተባለው ለመስጂዱ ክብር ሲባል ነው ... ከመስጂዱ እንጂ ከኢዕቲካፉ አይደለም ምትከለከለው.. :: ይሁንና ከኣወዛጋቢ ነገሮች ለመራቅ ሲባል ሴቶች ሐይድ ላይ ሆነው ኢዕቲካፍ ባያደርጉ ይመረጣል።

|ምንጭ፦ አል-ሙሐላ 5/322፣ ተስሂሉል- ፊቅህ 1/594። 3 መጅሙዕ አል-ፈታዋ 26/210፣ አል-መጅሙዕ ሊን-ነወዊይ 8/44።

http://t.me/sultan_54




Forward from: NESIHA TV ነሲሓ ቲቪ
ሲሳያችን ከሀላል ወይስ ከሀራም

የጁሙዓ ኹጥባ ሸይኽ ኢልያስ አህመድ|| NesihaTv

https://youtu.be/xnd8Nk53HuA

ነሲሓ ቲቪ...
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!

Telegram: @nesihatv
Facebook: https://www.facebook.com/nesihatv/
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCX2E30J71sKpnLQuGr7kt6w


Forward from: NESIHA TV ነሲሓ ቲቪ
ውድ የነሲሓ ቤተሰቦች...
አሰላሙዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

ነሲሓ ቲቪን ለማስቀጠል ገንዘባችሁን ለለገሳችሁ እና በማስተባበር ርብርብ ለምታደርጉ ሁሉ ከፍተኛ ምስጋናችን ይድረሳችሁ። አላህ አጅሩን ይፃፍላችሁ

በአላህ ፈቃድ ስርጭቱ በቅርብ ቀን የሚጀመር ይሆናል። ስርጭቱን ከማስቀጠል ባከፈ በዘመቻው  ለ 1 አመት የሚሆን መጠባበቂያ አቅም የማግኘትን አላማ ያነገብን ሲሆን በናንተ ትብብር በቀጣይ ቀናት ከግብ እንደሚደርስ ተስፋ እናደርጋለን። ጀዛኩሙላሁ ኸይረን!

በ CBE ንግድ ባንክ ለመርዳት በቃል የሚያዝ አጭር የአካውንት ቁጥራችን 444 ነው። የሌሎች ባንኮች አካውንቶችን ኮሜንት ላይ እናሰፍራለን።

ቋሚ ደጋፊ አባል ለመሆን እና በአይነት ለመለገስ እንዲሁም ለማንኛውም መረጃ በ 0972757575    ይደውሉ

ነሲሓ ቲቪ... ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!
t.me/nesihatv


Forward from: Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
ሪከርዱ በአንድ ወንድማችን የመቶ ሺህ (100, 000) ብር ሶደቃ ተሰብሯል። አላሁ አክበር! ማሻ አላህ‼


አላህ ከመጥፎ ነገሮች ጠብቆ የመልካሙን በር ይክፈትለት። ሶደቃ ከገንዘብ ምንም እንደማያጎድል በቁርኣንና በሐዲሥ ተነግሮናልና አላህ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይተካው። ሌሎቻችሁንም አላህ በሰፊው ይስጣችሁ። ዱንያ አኺራችሁን ያሳምርላችሁ።


የሚገርመው ግን ይሄም የመቶ ሺህ ብር ሪከርድ ቅድም አንድ ወንድም በላከልኝ ሶደቃ ተሰብሯል። እርሱን ኢንሻ አላህ በሰላም እንደርና ነገ እነግራችኋለሁ።

እስከዛው ሁላችሁም ወደዚህ ኸይር ሥራ ተሽቀዳደሙ! ሪከርዱን የሚያሻሽልም ካለ ይሽቀዳደም። አላህ ኢኽላሱንም ይወፍቃችሁና ወጥሩ'ማስ!


#እኔም_ለነሲሓ





✔️ የአካውንት ስም፦ ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
✔️ የአካውንት ቁጥሮች፦

√ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000145615929 ፣

√ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል: 1445091300001፣


√ አቢሲኒያ ባንክ (BOA):  73169062 ፣

√ ንብ ኢንተርናሽናል: 7000025634638፣

√ ዘምዘም ባንክ: 7122፣

√ ሂጅራህ ባንክ: 1000030030001፣

√ አዋሽ ባንክ: 01410844116300 !
*
ከላካችሁ በኋላ ደረሰኙን በውስጥ መስመር ወይም በቴሌግራም t.me/Murad_Tadesse ላይ ላኩት።


ተሽቀዳዳሚዎች ተሽቀዳደሙ


የተከበራችሁ የነሲሓ ቲቪ ቤተሰቦች

የነሲሓ ቲቪ ስርጭት ይመለስ ዘንድ መላው የነሲሓ ቤተሰቦች ጠንካራ ርብርቦሽ በማድረግ ላይ ናቸው። ኢን ሻ አላህ በናንተ ትብብር በቅርቡ ይመለሳል።

ነሲሓ ቲቪ ለኢስላማዊ እውቀትና ዳዕዋ ወሳኝ መድረክ ነውና በዚህ ጣቢያውን በዘላቂነት  በምናስቀጥልበት ዘመቻ ኃላፊነትዎን ይወጡ። ሁላችሁም የተቻላችሁን ድጋፍ እንደምታደርጉ ተስፋ እናደርጋለን።

ጣቢያውን በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚደረገውን ዘመቻ በማገዝ ከጎናችን ለቆማችሁ ሁሉ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።

የሚከተሉትን አካውንቶች በመጠቀም የበኩልዎን ድጋፍ ያድርጉ።
ባረከላሁ ፊኩም!

– ንግድ ባንክ 444 ወይም 1000145615929

– ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል 1445091300001

– አቢሲኒያ ባንክ 73169062

– ንብ ኢንተርናሽናል 7000025634638

– ዘምዘም ባንክ 7122

– አዋሽ ባንክ 01410844116300

https://t.me/nesihatv


የተከበራችሁ የነሲሓ ቲቪ ቤተሰቦች

የነሲሓ ቲቪ ስርጭት ይመለስ ዘንድ መላው የነሲሓ ቤተሰቦች ጠንካራ ርብርቦሽ በማድረግ ላይ ናቸው። ኢን ሻ አላህ በናንተ ትብብር በቅርቡ ይመለሳል።

ነሲሓ ቲቪ ለኢስላማዊ እውቀትና ዳዕዋ ወሳኝ መድረክ ነውና በዚህ ጣቢያውን በዘላቂነት  በምናስቀጥልበት ዘመቻ ኃላፊነትዎን ይወጡ። ሁላችሁም የተቻላችሁን ድጋፍ እንደምታደርጉ ተስፋ እናደርጋለን።

ጣቢያውን በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚደረገውን ዘመቻ በማገዝ ከጎናችን ለቆማችሁ ሁሉ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።

የሚከተሉትን አካውንቶች በመጠቀም የበኩልዎን ድጋፍ ያድርጉ።
ባረከላሁ ፊኩም!

– ንግድ ባንክ 444 ወይም 1000145615929

– ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል 1445091300001

– አቢሲኒያ ባንክ 73169062

– ንብ ኢንተርናሽናል 7000025634638

– ዘምዘም ባንክ 7122

– አዋሽ ባንክ 01410844116300

https://t.me/nesihatv


Forward from: የአቡ ሱለይማን ዳውድ ያሲን የመማማሪያ መድረክ
👉 ዶክተር አቡበክር

ዛሬ አንድ የፈትዋ ፕሮግራም ተብሎ የአህባሽ ተከታይ ለሆነው ለዶክተር አቡበክር የተጠየቀ ጥያቄን በጣም በሚያሳፍር ሁኔታ ድብን ያለ ውሸት እየዋሸ መልስ ብሎ ሲያወራ ሰማሁኝ
ዶክተሩ የተጠየቀው አል ኡሱሉ ሰላሳ የተባለውን ኪታብ ኡለማዎች እንዳይቀራ አስጠንቅቀዋል ይባላል ምክንያቱ ምንድነው? የሚል ነበር
አዎ በርካታ አሊሞች ኪታቡ እንዳይቀራ አስጠንቅቀዋል አለ ግን አንድ አሊም አልጠቀሰም
የተከለከለበት ምክንያት ደግሞ ሲያብራራ
🔹አንደኛ ተውሂድ በሶስት ይከፈላል ብሎ ያስተምራል አለ ይህ ሌላኛው ውሸቱ ነው እስቲ በዚህ ኪታብ የት ጋር ስንተኛው ገፅ ላይ ነው ተውሂድ በሶስት ይከፈላል ያለው? አብዛኛው ወጣት አል ኡሱሉ ሰላሳ ተምሯል ይህ ማለት ያንተን ውሸትም አውቋል ማለት ነው
🔹ሁለተኛ የአሁኖቹ ሙሽሪኮች ከቀደምቶቹ ሙሽሪኮች የባሱ ናቸው ብሎ ይናገራል በዚህም የተነሳ ላኢላሃ ኢለሏህ ያለን ግለሰብ ያከፍራል እያለ ቅጥፈቱን ይቀጥላል ይህ ግለሰብ ዶክተር የተባለው በውሸቱና በማጭበርበሩ ሳይሆን አይቀርም ። አል ኡሱሉ ሰላሳ ላይ ስለዚህ ርእስ የሚያወራ የለም
በጣም የሚያሳዝነው ያ በደዊ ያ አብሬት ብሎ መጣራት አይቻልም ሽርክ ነው ብሎ ያስተምራል ስለዚህ እኛን ሙስሊሞችን ነው ከቀደምት ሙሽሪኮች የባሱ ናቸው ብሎ የሚናገረው ይላል። ሙስሊሞች ያ አላህ ብለው ወደ ፈጣሪያቸው ይጣራሉ እንጂ ወደ ሌላ አካል ፈፅሞ አይጣሩም።
👉 ማስገንዘቢያ
1ኛ~ ተውሂድ ለሶስት እንደሚከፈል በርካታ መረጃዎች ያሉ ሲሆን ይህን ለመረዳት ሱረቱል ፋቲሀን በጥሞና ማንበብ ተገቢ ነው
2ኛ~ የዘመናችን ሙሽሪኮች ከቀደምት ሙሽሪኮች የባሱ ለመሆናቸው ይህን አንቀፅ አስተውለህ አንብብ

”فَإِذَا رَكِبُوا فِي الْفُلْكِ دَعَوُا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ فَلَمَّا نَجَّاهُمْ إِلَى الْبَرِّ إِذَا هُمْ يُشْرِكُونَ“

«በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ኾነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡» አል አንከቡት 65
3ኛ~ ሙታንን ድረሱልኝ ብሎ መጣራት ከእስልምና የሚያስወጣ ትልቁ ሽርክ ነው ። አላሁ ተአላ እሱን ብቻ እንድንለምነውና ከእሱ ውጪ ማንንም እንዳንጣራ ከልክሎናል ።

”وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ“

«ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡ »ጋፊር 60

”وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُو مِن دُونِ اللَّهِ مَن لَّا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَن دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ“

«እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለትን (ጣዖት) ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡» አህቃፍ 5
ከእንዲህ አይነት ጠሞ አጥማሚ አላህ ይጠብቀን ። ቤተሰቦቻችን በተለይ እናት አባቶቻችን በዚህ ሰውዪ እንዳይሸወዱ ቻናሉን ሙሉ በሙሉ አስወግዱላቸው ።
T.me/dawudyassin


Forward from: ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር 🌴 የዳሩል ሐዲሥ የሴቶች ክፍል ኦፊሺያል ግሩፕ
"በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ"(አል-ማኢዳ 2)

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
የዳረ'ል ሐዲሥ ኢስላማዊ ኮሌጅ

አስ'ሰላም ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ

  ላለፉት 14 አመታት ኢስላማዊ ዕውቀትን በተለያዩ ደረጃዎች ላሉ ተማሪዎች በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ሲሰጥ የቆየው የዳረል ሐዲሥ ኢኒስቲትዩት ሲያስተምረበት የቆየውን ህንፃ ግንባታውን በማስፋፋት ወደ ተሻለ እርከን ከፍ ለማድረግ ስራዎችን በትጋት  እየሰራ ይገኛል።

በጥንስሱ ላይም ይህንን መርከዝ እውን ለማድረግ የሴቶች የጎላ ተሳትፎና ሚና ከፍተኛ እንደነበር አይዘነጋም።

እነሆ!  በማስፋፋቱ ሂደቱ የመጨረሻ እርከን ላይም የተለመደውን አሻራችሁን ታሳርፉ ዘንድ በተዘጋጀው የሴቶች ዳእዋና የጉብኝት ፕሮግራም እርስዎም እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

እሁድ ህዳር 4፣2015 ከጠዋቱ 3:00
   
አድራሻ :-18 አደባባይ አካባቢ የቀድሞ አል-አፊያ ት/ቤት በሚገኘው የኢብኑ መስኡድ መርከዝ

https://t.me/Maahad_DarulHdith

20 last posts shown.

289

subscribers
Channel statistics