የባህር ዳር ሙስሊሞች መማማሪያ መድረክ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


የቻናሉ ትኩረት!
✔ ተዉሒድ እና ሽርክን በማብራራት የነብያትን ተልዕኮ ማስገንዘብ
✔ ትክክለኛ የአህለሱናን መንሀጅ ግንዛቤ ማስጨበጥ
✔ ከትክክልኛው የኢስላም አስተምህሮ ያፈነገጡ አንጃዎችን በመረጃ ማጋለጥ እና ጥናታዊ ምላሾችን ማሰራጨት!
✔ ኢስላማዊ ወንድማማችነትን ማጠናከር

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: ባህር ዳር – ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር °|° IBNU MAS'OUD ISLAMIC CENTER BAHIR DAR BRANCH
ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም

🎙በሸይኽ ሙሀመድ አወል ሰዒድ


⌚️እሁድ ህዳር 15/2017 ከዓስር ሶላት      በኋላ

   👉   ቦታ : – ቀበሌ 16 በተውፊቀል ኸይራት መስጅድ

መልዕክቱን ለሌሎችም በማስተላፍ የአጅር ተካፋይ ይሁኑ !


አዘጋጅ:–ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ባህር ዳር ቅርንጫፍ


Forward from: ባህርዳር — ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት
ወገን ለወገን // 13ኛ ዙር የደም ልገሳ

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ባህርዳር ቅርንጫፍ ከደም ባንክ ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ፕሮግራም አዘጋጅቷል ።

እሁድ ህዳር 15 ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ቀጠሮዎ ከኛ ጋር ይሁን !!

አድራሻ : -  ቀበሌ 16 ተውፊቀል ኸይራት መስጅድ






Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
እዩኝ፣ እዩኝ ማለት ደብቁኝ፣ ደብቁኝ ማለት ያመጣል
~
ባህሩ እኛ ተመቅኝተን ትኬት እንዳይሸጥላቸው እንዳደረግን አድርጎ እየከሰሰ ነው። በመጀመሪያ "በቁጭታችሁ ሙቱ!"፣ "ጩኸት በህመም ልክ ነው" እያላችሁ በፎከራችሁ ማግስት አሰናከላችሁብን ብላችሁ ማልቀስ ጥሩ አይደለም። ቢያንስ ሰንበትበት በሉ እንጂ። ይልቅ ካልተሳካ ማላከኪያ ሰበብ ከመፈለግ እውነተኛ ምክንያቱን ከራሳችሁ ዘንድ ፈልጉት። እንደኔ ጥቂት ነጥቦችን ብታስተውሉ መልካም ነው።
1ኛ፦ ለአንድ ቀን ደዕዋ 1000 ብር መጠየቅ ልክ ነው ወይ? በታዳሚው ቦታ ሆናችሁ ራሳችሁን ጠይቁ።
2ኛ፦ ሚሊኒየም አዳራሽ ምን አንጠለጠላችሁ? በልካችሁ አትሞክሩም? ቢሳካስ ለአንድ ቀን አዳራሽ 810ሺ ብር፣ እንደገና ለሻይ ቡና 3.1 ሚሊዮን ብር ሌሎች ወጭዎችን ሳይጨምር ይሄ ብቻ አራት ሚሊዮን አካባቢ ብር ከማውጣት በተመሳሳይ መጠን ብዙ ስራ መስራት ይቻላል። ብዙ ሰው ያላቸው አካላት ጋር ትከሻ እየተለካኩ ሲንገዳገዱ ከማዘን በአቅም ልክ ማሰብ ይሻላል።
3ኛ፦ የራሳችሁ ጩኸት ሸውዷችኋል። ሶሻል ሚዲያ ላይ የሚረብሸው ድምፃችሁ ስለ ራሳችሁ ቁጥር የተጋነነ ምስል እንድትይዙ አድርጓችኋል። ግርግር አይሸውዳችሁ። በሐጅማችሁ ሁኑ።
4ኛ፦ ኢኽላሳችሁን ፈትሹ። የቀስድ መበላሸት ብዙ ነገር ያበላሻል። እዩኝ፣ እዩኝ ማለት ደብቁኝ፣ ደብቁኝ ማለት ያመጣል። እነዚህን ነጥቦች በደንብ ብታጤኗቸው ለሌላ ጊዜ ይጠቅሟችኋል።
የአሁኗ ለቅሶ አላማ ከመንጋው ዘንድ ቁጭት ፈጥሮ መቀስቀስ ከሆነም ኒያችሁን አጥሩ። ያለ ኢኽላስ እንዲሁ ለእልህ የወጣ ገንዘብ ከአላህ ፊት ያስጠይቃል። ከዚህ በፊት እንዳደረጋችሁት ከሩቅ በእልህ ተጠራርታችሁ ዛሬን ብታሳኩ እንኳ የኋላ ኋላ ውርደት ያስከትላል። እልህና ኢኽላስ የተለያዩ ናቸው።
አንድ ነገር ግን አስረግጬ ልንገራችሁ! ቁጥራችሁ አሁን ካለውም የበለጠ እያነሰ ነው የሚሄደው። በተቃርኖ የተሞላ አካሄዳችሁን የታዘበ ሰው ይህንን ለመረዳት አይከብደውም። በሆይሆይታ ያሰለፋችኋቸው መንጋዎች ወደ ቀልባቸው ሲመለሱ ጊዜ እናንተ ከምትሾፍሩት የስሜት ባቡር እየተንጠባጠቡ ይወርዳሉ።
ማስታወሻ፡
{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّمَا بَغۡیُكُمۡ عَلَىٰۤ أَنفُسِكُمۖ }
"እናንተ ሰዎች ሆይ! ወሰን ማለፋችሁ (ጥፋቱ) በነፍሶቻችሁ ላይ ብቻ ነው።" [ዩኑስ፡ 23]
{ وَلَا یَحِیقُ ٱلۡمَكۡرُ ٱلسَّیِّئُ إِلَّا بِأَهۡلِه }
"ክፉ ተንኮልም በባለቤቱ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይሰፍርም።" [ፋጢር፡ 43]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor




Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram




Forward from: ባህር ዳር – ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር °|° IBNU MAS'OUD ISLAMIC CENTER BAHIR DAR BRANCH
ልዩ የዳዕዋ እና የምርቃት ፕሮግራም

🎤 በሸይኽ ሙሳ ሙሀመድ
🎤 በኡስታዝ አህመድ አብዴ (ዶ/ር)
🎤 በኡስታዝ አህመድ ሙሀመድ

⌚️ እሁድ መስከረም 19/2017
ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ

አድራሻ :-ነሲሐ መርከዝ አየር ጤና ቀበሌ 11 ከዳሩ ሰላም መስጅዱ ከፍ ብሎ

https://t.me/merkezunabdr




Forward from: ባህርዳር — ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት
ወገን ለወገን // 12ኛ ዙር የደም ልገሳ

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ባህርዳር ቅርንጫፍ ከደም ባንክ ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ፕሮግራም ቀበሌ 16 በቶውፊቀል ኸይራት መስጅድ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል ።


Forward from: ባህርዳር — ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት
ወገን ለወገን // 12ኛ ዙር የደም ልገሳ

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ባህርዳር ቅርንጫፍ ከደም ባንክ ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ፕሮግራም አዘጋጅቷል ።

እሁድ መስከረም 12 ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ቀጠሮዎ ከኛ ጋር ይሁን !!

አድራሻ : - ቀበሌ 16 ተውፊቀል ኸይራት መስጅድ


Forward from: 🗞 የ አቡጁነይድ መልዕክቶች Abujunaid posts
በካፊሮች በዓል እንኳን አደረሳችሁ ማለት ይፈቀዳልን?

በበአላት ሰሞን በተደጋጋሚ እገሌና እገሌ ላይክ አድርገውታል ከሚለን ፖስቶች መካከል ከፊሎቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶች ናቸው። ለጌታ መወለድ፣ ለጌታ መሰቀል፣ ለጌታ ሞቶ መነሳት (ትንሳኤና) መሰል ክስተቶች እንኳን አደረሳችሁ ሲባል ሼር ወይም ላይክ የሚያደርጉ ብዙ እህትና ወንድሞችን አስተውያለው። አንዳንዴ በስህተት ሌላ ግዜም ነገሩን እንደቀላል በመውሰድ የሚፈፀም ሊሆን ይችላል። ሆኖም እጅግ ከባድና በአኼራ ዋጋ የሚያስከፍል መዘናጋት ነው!!

በካፊሮች በአል፤ እንኳን አደረሳችሁ... እንኳን ደስ አላችሁ... እንኳን አብሮ አደረሰን ማለት እነሱን ለማስደሰትም ይሁን ለመመሳሰል ከአላህ ዲን መንሸራተት እና የካፊሮችን ኩፍር የመናገር ስነልቦና መካብ ስለሆነ
ክልክል ነው። መከባበር እና አብሮነትን ለማሳየት ከእምነታችን መንሸራተት አይጠበቅብንም። ዲን ከምንም በላይ ነውና ሸሪዓን መተላለፍ ፍፁም ጥፋት ነው!!

ፈጣሪ ወለደ ተወለደ የሚለው አስተምህሮ የጥፋትነቱ ክብደት ሰማያትንና ምድርን ሊሰነጥቅ እንደሚቀርብ ቁርአን ይነግረናል። አላህን የሚያስቆጣ ተግባር በመፈፀማቸው እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት ከሙስሊም አይጠበቅም!!

(وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحۡمَـٰنُ وَلَدࣰا * لَّقَدۡ جِئۡتُمۡ شَیۡـًٔا إِدࣰّا * تَكَادُ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تُ یَتَفَطَّرۡنَ مِنۡهُ وَتَنشَقُّ ٱلۡأَرۡضُ وَتَخِرُّ ٱلۡجِبَالُ هَدًّا * أَن دَعَوۡا۟ لِلرَّحۡمَـٰنِ وَلَدࣰا * وَمَا یَنۢبَغِی لِلرَّحۡمَـٰنِ أَن یَتَّخِذَ وَلَدًا * إِن كُلُّ مَن فِی ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِ إِلَّاۤ ءَاتِی ٱلرَّحۡمَـٰنِ عَبۡدࣰا * لَّقَدۡ أَحۡصَىٰهُمۡ وَعَدَّهُمۡ عَدࣰّا * وَكُلُّهُمۡ ءَاتِیهِ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ فَرۡدًا)

አልረሕማንም ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡ ከባድ መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ፡፡ በእርሱ (በንግግራቸው ምክንያት) ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ፡፡ ለአልረሕማን ልጅ አለው ስለአሉ፡፡ ለአልረሕማን ልጅን መያዝ አይገባውም!! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ (በትንሣኤ ቀን) ለአልራሕማን ባሪያ ኾነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም]
Surah Maryam 88 - 95

ለመሆኑ አንድን ካፊር ለሀይማኖታዊ በአል እንኳን አደረሰህ ስትለው፤ ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ አይደለምን?

እንኳን አደረሰህ...
ጌታ ተወልዶ ተሰቅሎ ሞቷል ብለህ ለማወጅ፣ ለመስቀል ለመስገድና የፈጣሪን ክብር የሚነኩ ንግግሮችን ለመናገር እንኳን በቃህ!

እንኳን አደረሰህ...
ማርያም ፈጣሪዋን ወለደችው፤ በመጠቅለያም ጠቀለለችው እያልክ ለመዘመር እንኳን በቃህ!

የኩፍር ተግባርን ለመከወን ከሆነ የደረሰው ለምንስ እንኳን አብሮ አደረሰን እንላለን?

እውቁ አሊም ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላህ ይህ ተግባር የተከለከለ ስለመሆኑ የኡለማዎች የጋራ አቋም መሆኑን በመጠቆም እንዲህ ብለዋል፤ «ኩፍርን ብቻ በሚያንፀባርቁ የሀይማኖታቸው መገለጫዎች እንኳን አደረሳችሁ...እንኳን ደስ ያለችሁ ማለት ሀራም መሆኑ የሁሉም ሊቃውንት ስምምነት ያለበት ነው።
ለምሳሌ አንድ ሙስሊም በነሱ በዓላትና ፆም ጊዜ፤ «በአሉን የተባረከ ያድርግልህ» ወይም «መልካም የደስታ በአል ያድርግልህ» እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ቢያስተላልፍ፤ ተናጋሪው ከኩፍር ቢድን እንኳ ከባድ ወንጀል ነው የፈፀመው። ይህም፤ ልክ «እንኳን ለመስቀል ሰገድክ» ብሎ ደስታን እንደመግለፅ ነው!

ይህ እንደውም፤ አንድ ሰው ነብስ በማጥፋቱ፣ አልኮል በመጠጣቱ፣ ዝሙት በመፈፀሙና በመሰል ተግባራት እንኳን ደስ ያለህ ከማለት በወንጀልነት የከበደ እና አስቀያሚ ነው። ለኢስላማዊ ድንጋጌዎች ተገቢዉን ክብር የማይሰጡ ብዙ ሰዎች ይህንን ይፈፅማሉ። ምን ያክል የሚያስጠላ የግባር እንደፈፀሙም አያስተውሉም። ቢድአ፣ ኩፍር እና ወንጀሎች በመፈፀማቸው እንኳን አደረሰህ፣ እንኳን ደስ ያለህ እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ያስተላለፈ፤ እራሱን ለአላህ ቁጣና ጥላቻ የተገባ እንዲሆን የሚያደርግ ምክኒያት ፈፅሟል» አህካም አህሉዚማህ

የዘመናችን ፈቂህ ሸይኽ ኡሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ አሉ «ካፊሮችን እንኳን አደረሳችሁ ማለት ኢብኑል ቀይም እንዳለው የዚህን ያክል ከባድ የሆነበት ምክኒያት እነርሱ የሚፈፅሟቸውን የኩፍር መገለጫዎች ማፅደቅ ስለሆነ ነው። ምንም እንኳን ለራሱ ይህንን ኩፍር መፈፀምን ባይወድም እነሱ መፈፀማቸውን ወዷልና። ሙስሊም ደግሞ የኩፍር መገለጫዎችን መውደድም ይሁን ሌሎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት አይፈቀድለትም።»
መጅሙዑ ፈታዋ ወረሳኢል አሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን 3/44

በተመሳሳይ መልኩ፤ ክሪስማስም ሆነ ሌሎች በአላት ላይ ስጦታ ወይም ፓስት ካርዶችን መለዋወጥ፤ እንዲሁም ማንኛውም ደስታን መግለጫ የሆኑ ነገሮችን መፈፀም በአሉን መካፈል ስለሆነ የተከለከለ ነው!!

በዚህ ፅሁፍ መጠቆም የፈለኩት ምንም አይነት ማህበራዊ ግንኙነት ሀራም ነው የሚል መልእክት አይደለም። በተለይም ከክርስቲያን እና አይሁዶች ጋር ባለን ማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ የተፈቀዱ ብዙ በመልካም የመኗኗር እሴቶች አሉን። ሆኖም ሀይማኖታዊ ወሰኖች የሉም ማለት አይደለም። የተፈቀደውን ስንተገብር እንደ ያልተፈቀደ ጋብቻ፣ በአላት ላይ መሳተፍ፣ ለሞቱት የአላህን ማርታ መለመንና ባጠቃላይ በዲን መመሳሰልን ግን በፍፁም አንፈፅምም። ይህንን የእምነትና የሀይማኖት ወሰን መናድ አይቻልም። ማንነታችንን ማክበር፣ ግንኙነታችንን በዲናዊ ገደቦች ማጠር ብሎም አለመሟሟት ለሌሎች ሞራል ዲንና ማንነት ከመጨነቅ ይቀድማል። ዲን ከምንም በላይ ነውና ከመሸማቀቅ እንውጣ። ይህ የዲናችን መገለጫ እንጂ እንደ ማክረርና ፅንፈኝነት የሚታይ አይደለም። በነገራችን ላይ የአንድ እምነት ተከታይ ከሌሎች ለመቀራረብ ብሎ ከራሱ እምነት ጋር የሚጣላበት ሁኔታ ድሮ ቀርቷል። ሌሎቹም ቢሆኑ ይህ በኛ ሀይማኖት አልፈቀድም እና ይቅርታ ይሉሀል።
(فَلَا تُطِعِ ٱلۡمُكَذِّبِینَ * وَدُّوا۟ لَوۡ تُدۡهِنُ فَیُدۡهِنُونَ * وَلَا تُطِعۡ كُلَّ حَلَّافࣲ مَّهِینٍ)

አስተባባዮችንም አትታዝዙ፡፡ ብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡
[Surah Al-Qalam 8 - 10]

ወላሁ አዕለም

አላህ ከጥፋት ሁሉ ይጠብቀን!

____
አቡጁነይድ ረጀብ 24/1437 ዓ.ሒ / ሜይ 1/ 2016 ከጥቂት ማሻሻያዎች ጋር

https://t.me/abujunaidposts/141


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Forward from: ባህርዳር — ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት
አንድ እሽግ ደብተር ለአንድ ተማሪ

ለየቲሞች እና መግዛት ለማይችሉ ተማሪዎች ድጋፍ ያድርጉ

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ባህርዳር  ቅርንጫፍ

ንግድ ባንክ
1000441566666

ሂጅራ ባንክ
1001318180001

አዋሽ ባንክ
014251151025300


ለበለጠ መረጃ : -
📱
0904947575
📱
0913881760
📱0918711081

http://t.me/nesihacharitybdr




Forward from: ባህርዳር — ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት
ወገን ለወገን // 11ኛ ዙር የደም ልገሳ

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ባህርዳር ቅርንጫፍ ከደም ባንክ ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ፕሮግራም ቀበሌ 16 በቶውፊቀል ኸይራት መስጅድ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል ።


ልዩ የዳዕዋ እና የደም ልገሳ መርሀግብር

🎙 በሸይኽ ሙሀመድ አወል ሰዒድ


   እሁድ ሀምሌ 28/2016

👉 ዳዕዋው ከአሱር በሗላ

👉 11ኛው የደም ልገሳ መርሀግብር
ከ4:00 ጀምሮ ይካሄዳል

   👉   ቦታ : – ቀበሌ 16 በቶውፊቀል ኸይራት መስጅድ

መልዕክቱን ለሌሎችም በማስተላፍ የአጅር ተካፋይ ይሁኑ !


አዘጋጅ:– ነሲሓ በጎአድራጎት እና
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ባህር ዳር ቅርንጫፍ

20 last posts shown.