የተውሒድ ዳዕዋ በወሎ–ወረኢሉና አውራጃዋ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


የተውሒድ ዳዕዋ በወረኢሉ
وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ zariyat :56

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


በወረኢሉ ወረዳ ሰኞ ገበያ
የተደረገውን ዳዕዋ ለማግኘት
በሚከተለው ሊንክ ይግቡ

እሁድ ህዳር 15/2017

📔 ርዕስ  አል እስቲቃማ በድን ላይ ቀጥ ማለት
🎙 በወንድም አቡ ፋኪሃ ኡመር አሳልፍ  ሃፊዘሁላህ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/tewuhidWereilu/5647
📔 ተውሒድ እና ሽርክ
🎙 በሸህ እንድሪስ ከታሪ ሃፊዘሁላህ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/tewuhidWereilu/5648
📔 ሱናን መከተል እና ውጤቱ እንድሁም ስለ ተቅዋ ሰፋ ተደርጎ ተዳሷል
🎙በኡስታዝ ተውፊቅ ሙሀመድ ሃፊዘሁላህ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/tewuhidWereilu/5646

ፕሮግራሙን በመምራት እኔ ወንድማችሁ ጀማል እንድሮ አቡ መርየም

ማሳሰቢያ
ታስረው የነበሩትም ወንድሞቻችን በሰላም ተለቀዋል አልሃምዱሊላህ !


አስተያየትና ጥቆማ ካለችሁ
ህዳር 19/2017

@JemalEndroAbuMeryem


አድስ ዳዕዋ

ህዳር 13/2017
✅ ከመጝሪብ እስከ ኢንሻ የተደረገ
📔 ርዕስ  ተውሒድ የነብያት ተልዕኮ

🎙 በኡስታዝ ተውፊቅ ሙሃመድ ሃፊዘሁላህ

🕌 በወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ

https://t.me/tewuhidWereilu/5650




አድስ ሙሐደራ

ህዳር 15/2017

📔 ርዕስ  ተውሒድ እና ሽርክ


🎙 በሸህ እንድሪስ ከታሪ ሃፊዘሁላህ

🕌 በወረኢሉ ወረዳ ሰኞ ገበያ ሸህ ዑመር መስጅድ

https://t.me/tewuhidWereilu/5648


አድስ ሙሐደራ

ህዳር 15/2017

📔 ርዕስ  አል እስቲቃማ በድን ላይ ቀጥ ማለት

🎙 በወንድም አቡ ፋኪሃ ኡመር አሳልፍ  ሃፊዘሁላህ

🕌 በወረኢሉ ወረዳ ሰኞ ገበያ ሸህ ዑመር  መስጅድ

https://t.me/tewuhidWereilu/5647


አድስ ሙሐደራ

ህዳር 15/2017

📔 ርዕስ  ስለ ሱናን መከተል እና ውጤቱ እንድሁም ስለ ተቅዋ ሰፋ ተደርጎ ተዳሷል

ስለ ሁሉም መደምደሚያው ነው አዳምጡት !

🎙 በኡስታዝ ተውፊቅ ሙሀመድ ሃፊዘሁላህ

🕌 በወረኢሉ ወረዳ ሰኞ ገበያ ሸህ ዑመር  መስጅድ

https://t.me/tewuhidWereilu/5646


ህዳር 13/2017
✅ ከየጁመዓ ኹጥባ
📔 ርዕስ  ኢስላማዊ ወንድማማችነት

🇪🇹የኹጥባው አማረኛው  ከ14:00 ደቂቃ በሗላ ነው !
🎙 በኡስታዝ ተውፊቅ ሙሃመድ ሃፊዘሁላህ

🕌 በወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ

https://t.me/tewuhidWereilu/5643


ቆይ ግን ጀመዓው እኔ ወንድማችሁማ ሳላውቀው የምኖረው እሌላ ሃገር ሳይሆን አይቀርም !

ዞሮ የሆነ ሰው አንተ እኮ የምትኖረው ወረኢሉ አይደለህም ወረኢሉ መስሎህ ነውጅ አይነት ወሬ ሰማሁኝ !?

እስኪ ያለሁበትን ቦታ ሹክ በሉኝ !


@JemalEndroAbuMeryem

"እራስህን አታምነውም እንዴ ያልከኝ ልጅ "
ለእርግጠኝነቱ ነው !

በእርግጥ ንግግሬ ያልገባችሁ ወንድሞች እና እህቶች ትኖራላችሁ እናንተ እለፉት !


ህዳር 15/2017

ለማንኛውም የዛሬው የሰኞ ገበያው ዳዕዋ ይለቀቅላችሇል ኢንሻ አላህ ጠብቁ !......


ህዳር 6/2017
✅ የጁመዓ ኹጥባ
📔 ርዕስ  የቂያማ ቀን ምልክቶች

የኹጥባው አማረኛው ከ13:00 ደቂቃ በሗላ ነው !
🎙 በኡስታዝ ተውፊቅ ሙሃመድ ሃፊዘሁላህ

🕌 በወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ

https://t.me/tewuhidWereilu/5643


አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ ወበረካቱሁ

ታላቅ የደዕዋ ፕሮግራምበሰኞገበያ ትንሿዱባይ    በሰኞ እናበዙሪያዋ  ላላችሁ  ሙስሊም  ወንድሞች እና  እህቶች  ፕሮግራም ስለ ተዘጋጀ መረጃውን በፍጥነት እየተለዋወጣቹህ    ህዳር 15/ 3/ 2017    እለተ   
እሁድ ከጧቱ 2:30 በተጠቀሰው ቦታ  እንድትገኙ ስንል በታላቅ ደስታ
ነው።


በቦታው ተገኝታችሁ   ፕሮግራሙን   ለመከታተል  የምትፈልጉ  በሙሉ

የፕሮግራሙን አስተባባሪወች   በማናገር ፕሮግራሙን ትካፈሉን ዘድ በታላቅ ደስታ  ጠርተነወታል ፡፡

የፕሮግራሙአስተባባሪወች  ስም  አድራሻ  👇👇👇👇

 
0912367200 ሙነወር
0914320445 አብዱሮህማን
0912954681 ሼይኽ ኡመር

2:30 ጀምሮ


በፕሮግራሙ  ላይ ከሚሳተፉ መሻይኾች እና  ኡስታዞች

① ሼይኽ ኢድሪስ ከከታሪ

⓶ ሼይኽ ሙሀመድ ሱልጣን ዙላል

⓷ ኡስታዝ ተውፊቅ ሙሀመድ ከወረኢሉ
④ ወንድም ኡመር አሳልፍ ከወረኢሉ
እና ሌሎችም ወንድሞች ይኖራሉ ኢንሻ አላህ

የፕሮግራሙ  ርእስ በእለቱ የሚገለፅ ይሆናል   ሌሎችም ጣፋጭ የሆኑ ፕሮግራሞች ስላሉ እንዳያመልጠወት


ከወረኢሉ መሄድ የምትፈልጉና ቦታውን የማታውቁት
አቡ መርየም ጀማል እንድሮ 0933519871
አቡ ፋኪሃ ኡመር አሳልፍ
0938369567 ይደውሉ
መልክቱን ሸር በማድረግ ላልደረሳቸው እንድደርስ እናድርግ ባረከአላሁ ፊኩም፡፡

ህዳር  15
/3 /2017  እለተ እሁድ   ከጧቱ 2:30 ስአት ጀምሮ

https://t.me/segnogebaya1

https://t.me/tewuhidWereilu/5642


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከጭፍን ተከታይነት መጠንቀቅ
~
ከሱና ሰዎች አበይት መገለጫዎች ውስጥ አንዱ የፈለገ ቢገንኑ ለዑለማዎች ጭፍን ወገንተኛ አለመሆን ነው፡፡ የፈለገ ብንወደው ማንም ቢሆን የተናገረው ሁሉ ልክ አይሆንም፡፡ ስለሆነም ለማንም ጭፍን ወገንተኛ ልንሆን አይገባም፡፡ ዑለማዎቻችንን ስለወደድናቸው ብቻ ንግግራቸውን ሁሌ እንደወረደ አንወስድም፡፡ ይህንን በተግባር ያስተማሩን ራሳቸው ዑለማዎቹ ናቸው፡፡ ለአብነት ያክል የአራቱን መዝገቦች ኢማሞች ንግግሮች ላስፍር፡-

[ሀ] የአቡ ሐኒፋ ንግግሮች፡-

1. “አንድ ሐዲሥ ትክክለኛ ከሆነ መዝሀቤ እሱ ነው፡፡”
2. “ከየት እንደወሰድነው ካላወቀ ለማንም አቋማችንን ሊወስድ አይፈቀድለትም፡፡”
3. “ማስረጃዬን ያላወቀ ሰው በኔ ንግግር ፈትዋ ሊሰጥ ሐራም ነው፡፡”
4. “እኛ ሰዎች ነን፡፡ አንድ ንግግር ዛሬ እንናገርና ነገ ከሱ እንመለሳለን፡፡”
5. “የላቀውን አላህ መፅሐፍና የመልእክተኛውን ﷺ ንግግር የሚፃረር ንግግር ከተናገርኩኝ የኔን ንግግር ተውት፡፡”

[ለ] የማሊክ ንግግሮች፡-

1. “እኔ ሰው ነኝ፡፡ እስታለሁ፣ አገኛለሁ፡፡ ስለዚህ እይታየን ተመልከቱ፡፡ ቁርኣንና ሱና ጋር የገጠመውን በሙሉ ያዙት፡፡ ቁርኣንና ሱና ጋር ያልገጠመውን ተውት፡፡”
2. “ከነብዩ ﷺ በስተቀር ንግግሩ የሚያዝለት ወይም የሚመለስበት ያልሆነ አንድም የለም፡፡”
3. “ከነብዩ ﷺ በኋላ ከንግግሩ የሚያዝና የሚተው ያልሆነ አንድም የለም፡፡ ነብዩ ﷺ ሲቀሩ፡፡"

[ሐ] የሻፊዒይ ንግግሮች፡-

1. “አንድ የነብዩ ﷺ ሱና የተገለፀለት ሰው ለማንም ንግግር ሲል እሷን (ሱናዋን) መተው እንደማይፈቀድለት ሙስሊሞች በሙሉ ኢጅማዕ አድርገዋል፡፡”
2. “በኪታቤ ውስጥ ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ሱና የሚፃረር ነገር ካገኛችሁ የአላህ መልእክተኛን ﷺ ሱና ተከተሉ፡፡ የኔን ንግግር ተውት፡፡”
3. “ሐዲሥ ትክክለኛ (ሶሒሕ) ከሆነ መዝሀቤ እሱ ነው፡፡”
4. “እኔ ከተናገርኩት በተቃራኒ በዘርፉ ምሁራን ዘንድ ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ትክክለኛ ዘገባ የመጣበት ርእስ ሁሉ እኔ በህይወት ሳለሁም ሆነ ሞቼ ከሱ ተመልሻለሁ፡፡”

[መ] የአሕመድ ንግግሮች፡-

1. “የአውዛዒይ ግላዊ አስተያየት (ረእይ)፣ የማሊክም ግላዊ አስተያየት፣ የአቡ ሐኒፋም ግላዊ አስተያየት ሁሉም አስተያየት ነው፣ እኔ ዘንድ፡፡ መረጃ ያለው ከነብዩ ﷺ እና ከሶሐቦቹ ቅሪት ዘንድ ነው፡፡”
2. “ማሊክንም፣ ሻፊዒይንም፣ አውዛዒይን፣ ሠውሪይን በጭፍን አትከተል፡፡ እነሱ ከያዙበት ያዝ፡፡”

እነዚህንና መሰል ወርቃማ ንግግሮችን ከሸይኹል አልባኒይ “ሲፈቱ ሶላቲ ነቢይ” ኪታብ መግቢያ ላይ እናገኛለን፡፡

ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! እኛ ከዚህ ምን እንማራለን? ለየትኛውም ዓሊም ጭፍን ተከታይ አንሁን። ከላይ ያለፉትን ንግግሮች በአንክሮ እናስተውል፡፡ የህይወታችን ቋሚ መመሪያም እናድርጋቸው፡፡ “ማሊክንም፣ ሻፊዒይንም፣ አውዛዒይንም፣ ሠውሪይንም በጭፍን አትከተል” የሚለውን የኢማሙ አሕመድ ንግግር እናስተውል። እነዚህን የኡማው ከዋክብት በጭፍን መከተል ካልተፈቀደ ከነሱ በእጅጉ የሚያንሱትንስ በጭፍን መከተል ይፈቀዳልን? ጤነኛ ለሆነ ሰው መልሱ አይጠፋውም፡፡ እናም ተመሳሳይ ነገር ልበል፡፡
- ኢብኑ ተይሚያንም፣ ኢብኑል ቀይምንም፣ ዘሀቢይንም፣ ኢብኑ ከሢርንም፣ … በጭፍን አትከተል፡፡
- ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወህሃብንም፣ ዐብዱረሕማን ብኑ ሐሰንም፣ ዐብዱለጢፍ ኣሊ ሸይኽንም፣ ሰዕዲይንም፣ ሙሐመድ ብኑ ኢብራሂንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- ኢብኑ ባዝንም፣ አልባኒይንም፣ ኢብኑ ዑሠይሚንንም፣ ሙቅቢልንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- ፈውዛንንም፣ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድንም፣ ሙሐመድ አማን አልጃሚይንም፣ ረቢዕ አልመድኸሊይንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- በሰፈርህ፣ በአካባቢህ፣ በሃገርህ ያሉ መሻይኾችንም፣ ተማሪዎችንም የፈለገ ብትወዳቸው በጭፍን አትከተል፡፡ የተወሰኑትን ከሌሎች ለይተህ የሐቅ መለኪያ ሚዛን አታድርጋቸው፡፡ ማንም ይሁን ማን፡፡
እዚህ ላይ ይህ ፅሑፍ ዑለማን ከማክበርና ትንታኔያቸውን ከመጠቀም ጋር የሚፃረር የሚመስለው ካለ የፅሑፉን መልእክት ፈፅሞ አልተረዳም፡፡ የዚህ ፅሑፍ አላማ ግለሰቦችን የሐቅ መለኪያ በማድረግ ሊከሰት ከሚችል ፈተና መጠንቀቅ እንደሚገባ ማሳሰብ ብቻ ነው፡፡ እንጂ የቁርኣንና የሐዲሥን ማብራሪያ የምንወስደው ከዑለማዎች እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን የአንዱ ዐሊም ትንታኔ ከሌላው የሚፃረርበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም በጭፍን ልንከተል እንደማይገባ የሚያሳይ ነው፡፡ ዛሬ ግን ታላላቅ መሻይኾችን ቀርቶ በአካባቢያቸው የሚገኙ ዝቅ ያሉ አስተማሪዎችን ጭምር በጭፍን በመከተል የወደዱትን የሚወዱ፣ የጠሉትን የሚጠሉ፣ የነኩትን የሚነኩ፣ የፈቀዱትን የሚፈቅዱ፣ የከለከሉትን የሚከለክሉ፣ ያስጠነቀቁትን የሚያስጠነቅቁ ብዙ ናቸው፡፡ የሚከተሏቸው ሰዎች በሆነ ምክንያት አቋም ሲቀይሩም ያለምንም ማገናዘብ ሰልፋቸውን በመቀየር ዥዋዥዌ ይጫወታሉ፡፡ ይሄ ፈፅሞ ሊሆን አይገባም፡፡ አላህ ማስተዋሉን ያድለን፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 07/2010)
=
* የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

* የዋትሳፕ ቻናል፦
https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M

* ፌስቡክ
https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL




Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የደጋጎችን ቅሪት ማሳደድ
~
ለብዙዎች ሺርክ ላይ መውደቅ ሰበብ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ የደጋጎችን ቅሪት ማሳደድ ነው። በኢስላም የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት የቀብር ዚያራ የተከለከለ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ አዲስ ሰለምታዎች የቆየ ልማድ እንዳይጎትታቸው ነው። ኢማናቸው ሲጠነክር ክልከላው ተነስቷል። ዚያራው የራሱ ፋይዳ አለው፣ አኺራን ማስታወስ። ለዚህ ደግሞ ባቅራቢያ ያለን ቀብር እንጂ ለዚያራ አገር ማቋረጥ አያስፈልግም። አገር አቋርጦ ቀብር ዚያራ መጓዝን የሚደግፍ አንድም ቁርኣናዊ አንቀፅና ትክክለኛ የሱና ማስረጃ የለም። ሸሪዐው የሚደግፈው ቢሆን ኖሮ ከትልቅ እስከ ደቂቅ ያሉ ነገሮች ሲተላለፉልን አብሮ ይተላለፍ ነበር። መልካም ቢሆን ኖሮ ከማንም በላይ ለኸይር ጉጉት የነበራቸው ሶሐቦች ይቀድሙን ነበር። ለቀብር ዚያራ ብለው ካገር አገር ቢኳትኑ ኖሮ ሌሎች ነገሮቻቸው እንደተላለፉልን ይህም ይተላለፍልን ነበር።
ዛሬ ሰለጠነ በሚባለው አውሮፓ እንኳን በያመቱ ሚሊዮኖች የሚጎበኟቸው መቃብሮች አሉ። በሙስሊሙም አለም ተመሳሳይ ጥፋቶች በስፋት ይፈፀማሉ። በርግጥ እምነታችን መስፈርት ያስቀምጣል እንጂ የቀብር ዚያራን ድፍን አድርጎ አይከለክልም።

ሸሪዐዊ የቀብር ዚያራ፡-
=
አኺራን ለማስታወስ ወይም ለሟቾቹ ዱዓእ ለማድረግ ታስቦ የሚደረግ ሲሆን ሸሪዐው የሚያበረታታውና ነብዩ ﷺ የፈፀሙት ነው። ሸሪዐዊ የቀብር ዚያራ ሶስት መስፈርቶችን ያሟላ ነው።
1. አገር አቋርጦ አለመጓዝ፡- ምክንያቱም ነብዩ ﷺ {ወደ ሶስት መስጂዶች ካልሆነ በስተቀር ለጉዞ (የግመል) መጫኛዎች አይጠበቁም። (አገር አቋርጦ መጓዝ አይቻልም።) (እነሱም) ይሄ መስጂዴ (መዲና የሚገኘው የሳቸው መስጂድ)፣ መስጂደል ሐራም እና መስጂደል አቅሷ ናቸው} ብለዋልና። [ቡኻሪ፡ 1189] [ሙስሊም፡ 1397]
2. መጥፎ ነገር አለመናገር፡- ነብዩ ﷺ {ቀብሮችን እንዳትጎበኙ ከልክያችሁ ነበር። ከዚህ በኋላ ግን ጎብኙ። ምክንያቱም አኺራን ታስታውሳችኋለችና። መጎብኘቱም መልካምን ይጨምራችኋል። እናም መጎብኘት የፈለገ ይጎብኝ። መጥፎ ነገር ግን እንዳትናገሩ} ብለዋል። [አሕካሙል ጀናኢዝ፡ 227] ሟቹን መለመን፣ ሙሾ ማወረድና መሰል አላህን የሚያስቆጡ ንግግሮችን መራቅ ይገባል።
3. ገደብ አለማስቀመጥ፡- የቀብር ጉብኝት ዒባዳ ወይም አምልኮት ነው። አምልኮት ውስጥ ደግሞ ሸሪዐው ያላስቀመጠውን ገደብ ማስቀመጥ አይፈቀድም። የሆነን ቀብር ለይቶ በቋሚነት መመላለም አይገባም። ነብዩ ﷺ {ቀብሬን መመላለሻ አድጋችሁ አትያዙት} ማለታቸው ይህን የሚገልፅ መልእክት አለው። [አሕካሙል ጀናኢዝ፡ 280]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


የኢማን ወንድማማችነት

🎙 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔗 t.me/Achachir_mkroch


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
* የራስን ብሄር በተለየ ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ የሌሎችን ብሄር የሚያንቋሽሹ፣ ሰዎች በብሄራቸው ተለይተው ጥቃት ሲደርስባቸው ለአጥፊዎቹ የሚከላከሉ ፖስቶችን ወይም ኮሜንቶችን ሼር፣ ላይክ የምታደርጉ፣
* ዘር ላይ ያነጣጠሩ ዘረኛ ቀልዶችን በሳቅ የምታጅቡ፣
* በየትኛውም መልኩ ለዘር ተኮር ጥላቻ ድጋፍ የምታደርጉ አካላት የወንጀሉ ተካፋይ ናችሁ።
* የራሳችሁ ዘር ላይ ቢፈፀም የማትወዱትን ሌላው ላይ ሲሆን የምታደርጉት ከሆነ የዘረኝነት በሽታ ላይ ወድቃችኋል። "ተዋት! እሷ ጥንብ ነች!"
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


በሹብሃ የወደቁ ወንድሞች የጠየቁት ጥያቄ እና መልሶች

በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ(አቡ ሓቲም)
https://t.me/UstazKedirAhmed/8218
https://t.me/UstazKedirAhmed/8218


Forward from: Ustaz Kedir Ahmed Al—Kemisse (Abu Juweyriya)
በ ጀምዕያ እና በ ዑዝር ቢል ጀህል በተሰኘው አርእስት ላይ ሹብሃ ላይ የወደቁ ተማሪዎች ኡስታዝ ኸድር ዘንድ መተው የጠየቁትን ጥያቄ እና መልስ የምንልክ ይሆናል

በቅርቡ…
https://t.me/UstazKedirAhmed/8217


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሰከን፣ ጎጆ እንዳይበተን
~
ፍቺ ላይ መጠንቀቅ ይገባል። ሚስት በትንሽ በትልቁ ፍቺ ልትጠይቅ አይገባም። ባልም ፍቺን ማስፈራሪያ ሊያደርግ አይገባም። ህይወት የጋራ ነው። ፍቺ በድንገተኛ ብስጭት ሳይሆን አስቦና አሰላስሎ ነው መወሰን ያለበት። እለታዊ ግጭትን መነሻ በማድረግ ለፍቺ መቻኮል ኋላ ፀፀት ላይ ይጥላል። ትዳር ተቋም ነው። ጤነኛ ሰው ተቋምን በቅፅበታዊ ግጭት አይበትንም። ይልቁንም ከማፍረሱ በፊት ጊዜ ወስዶ ደግሞ ደጋግሞ ያስብበታል።

መታወቅ ያለበት በኢስላም ፍቺ ገደብ የለሽ አይደለም። ልቅ በሆነ መልኩ እንደፈለጉ እየፈቱ መመለስ፣ እየፈቱ መመለስ የሚባል የለም። ዳግም መመላለስ የሚቻልበት ፍቺ ቁጥሩ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው። ሶስተኛ የፈታ ሰው በቀላሉ መመለስ አይችልም። በረባ ባልረባው ፍቺ እየፈፀሙ ኋላ ሲጨንቃቸው መፍትሄ ፍለጋ የሚባዝኑ ብዙዎች ናቸው። እንደዋዛ የቀለዱበት ትዳር እንደዋዛ አይጠገንም። ኋላ ለከባድ ፀፀት ከመጋለጥ በፊት በጊዜ መጠንቀቅ ነው የሚበጀው። በተለይ ደግሞ ልጅ ሲኖር ጉዳቱ ጥልቅ ስለሚሆን ይበልጥ መጠንቀቅ ይገባል።

በነገራችን ላይ ሚስት የወር አበባ ላይ እያለች ፍቺ መፈፀም አይቻልም። እንደዚሁም ከወር አበባ ከጠራች በኋላ ግንኙነት ተፈፅሞ ከሆነም ፍቺ አይፈፀምም። ይህንን ሱና መጠበቅ በድንገተኛ ስሜት ፍቺ እንዳይፈፀም ይረዳል። አብዛኞቹ ትዳሮች የሚፈርሱት ጥንዶቹ የጦዘ ብስጭት ላይ በሚሆኑ ጊዜ ነው። ብስጭታቸው እስከሚበርድ ውሳኔያቸውን ቢያቆዩት ብዙ ኒካሕ ከመፍረስ ይድናል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor


Forward from: ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus
"ከማንም ጋር በገባበት ልንገባ፣ በወጣበት ልንወጣ የህይወት ዘመን ውል የለንም። መንሃጅ ያገናኘናል። መንሃጅ ይለያየናል። መንሃጅ ከለያየን ከትላንት ቀርቶ ከዛሬ ወዳጅም ጋር እንለያያለን። መንሃጅ ካገናኘን ዛሬ ከምንርቃቸው አካላት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን እንጓዛለን። መለኪያችን የሰለፊያ መንሃጅ ብቻ ነው። ትላንት አንድ የነበርን የተለየናቸው አሉ። ትላንት ተወጋግዘን ዛሬ ከልብ የምንወዳቸው ብዙ ናቸው። አላህ በሰለፊያ ላይ ያፅናን።"
ኡስታዝ
@IbnuMunewor

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15186


Forward from: የኒቃብ እና ጅልባብ ባንክ channel
የዳዕዋና የኒያ ፕሮግራም

የፊታችን ጁመዓ በሱና ኡስታዞቻችን ደማቅ የዳዕዋና የኒያ ፕሮግራም አዘጋጅተን አየጠበቅናችሁ እንገኛለን።  ስለሆነም ሁላችሁ የዚህ ፕሮግራም ተካፋይ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

     ተጋባዥ ኡስታዞች

1 ሳዲቅ ኢብኑ ኸይሩ
2 ኡስታዝ አብዱሰመድ ሙሐመድ ኑር
3 ወንድም ኑረዲን አል-ዐረቢ


ሰአት ⏰  ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ

አድራሻ ➡️ t.me/nikab_jilbab_group

🔄Share

20 last posts shown.