ኢስላማዊ መልዕክቶች


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


«ኢስላማዊ መልዕክቶች···✍🏻
//طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ//
‘ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ግዴታ
ነው።’
🌷https://t.me/twebte
https://telegram.me/twebte

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


🌹የሱና እህቶች የለውጥ ሚና🌹
♡..አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ! ከመገላለጥ ተጠንቀቂ {{በአላህ ፍቃድ}} ከፈተናዎች ጠባቂሽ የሆነውን ሂጃብሽን አጥብቀሽ ያዢ!❥...
🍃═══ ¤❁✿❁¤ ═══🍃
https://telegram.me/yeswnaehitochmena


Forward from: MuhammedSirage M.Nur.
ብቻ አለህን ፍራ የነብዩን ሱና ተከተል!!
ሠዎች ዘንድ ቦታ የማይሠጥህ፣ ለሽምግልናህንና ለንግግርህ ጆሮ የሚነፈግህ ደካማ ብትሆን አይጭነቅህ — አላህን እስከፈራህና የታላቁን ነብይ ሱና እስከተከተልክ ድረስ! ቤሳቢስቲን የሌለህ ያገር ምስኪን ሆነህ የዱንያ ችግር ቢያንጋላታህም ትካዜ አይግባህ ወንድሜ! ጀነትን በዝተው የሚወርሷት ዳካሞች እና ድሆች ናቸው!!
ብቻ አላህን ፍራ! የነብዩን ሱና ተከተል!


أهمية الصلالة وحكم تاركها نصيحة للنساء بعض العصر في مسجد السنة
የሰላት አገብጋቢነት ሰላትን የተወ ሰውሁክሙሁክሙ
ሰላት በሸሪአችን ምን ያክል ቦታ አላት
አንዳንድ አህሉል ባጢል የሚሰጡዋቸው ፈትዋዎች እዴት ነው
በሚል በሰላት ዙርያ በስፋት የተደረገ ቆጆ ነሲሀ በመስጅደ ሱና


وَأَنَّا لَمَسْنَا ٱلسَّمَآءَ فَوَجَدْنَٰهَا مُلِئَتْ حَرَسًۭا شَدِيدًۭا وَشُهُبًۭا

【አል ጂን】
‹«እኛም ሰማይን 【ለመድረስ】 ፈለግን፡፡ ብርቱ ጠባቂዎችንና ችቦዎችንም ተሞልታ አገኘናት፡፡»

🌺🎧🎶


【የነብያት ውርስ】التوحيد الذي هو حق الله على العبيد.
ﻗُﻞْ ﻫَٰﺬِﻩِ ﺳَﺒِﻴﻠِﻲ ﺃَﺩْﻋُﻮ ﺇِﻟَﻰ اﻟﻠَّﻪِ ۚ ﻋَﻠَﻰٰ ﺑَﺼِﻴﺮَﺓٍ ﺃَﻧَﺎ ﻭَﻣَﻦِ اﺗَّﺒَﻌَﻨِﻲ ۖ ﻭَﺳُﺒْﺤَﺎﻥَ اﻟﻠَّﻪِ ﻭَﻣَﺎ ﺃَﻧَﺎ ﻣِﻦَ اﻟْﻤُﺸْﺮِﻛِﻴﻦَ
سورة يوسف "108"
በወንድማችን ዐብዱረዛቅ【حفظه الله تعالى】
የሱና ደርሶችና ፅሁፍች የሚተላለፍበት!!
https://telegram.me/Abdurezaq12Sunnah


Forward from: Ibnu Muhammedzeyn
ችሁ ኢብኑ ሙሀመድዘይን (ሀምሌ 21/2008)


Forward from: Ibnu Muhammedzeyn
በመንሀጀ ሰለፍ ላይ መፅናት እና ለፅናት የሚያግዙን ነገሮች

በአላህ ስም እጅግ ሩህሩህ እና ፍፁም አዛኝ በሆነው።

(("ፅናት" ማለት በሀቅ ላይ ቀጥ መለት ነው።
"መንሀጅ" ማለት ሙስሊም የሆነ ሰው የሚጓዝበት መንገድ ነው።
እሱም ቀጥተኛው መንገድ ነው።
ﻗﺎﻝ ﺗﺒﺎﺭﻙ ﻭﺗﻌﺎﻟﻰ : { ﻗُﻞْ ﻫَﺬِﻩِ ﺳَﺒِﻴﻠِﻲ ﺃَﺩْﻋُﻮ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻋَﻠَﻰ ﺑَﺼِﻴﺮَﺓٍ ﺃَﻧَﺎ ﻭَﻣَﻦِ ﺍﺗَّﺒَﻌَﻨِﻲ ﻭَﺳُﺒْﺤَﺎﻥَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﻣَﺎ ﺃَﻧَﺎ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻤُﺸْﺮِﻛِﻴﻦَ } ( ﻳﻮﺳﻒ 108: )
አላህ እንዲህ ይላል:-"ይህቺ መንገዴ ናት። ወደአላህ እጣራለሁ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልፅ ማስረጃ ላይ ነን። ጥራት ለአላህ ይገባው። እኔም ከአጋሪዎች አይደለሁም" በል። ዩሱፍ 108))

በሀቅ ላይ እስከለተ ሞታችን ድረስ መፅናት በጣም አሳሳቢ ነው የመጨረሻችን ነገር ሊያሳስበን ሊያስጨንቀን ይገባል ለዚህም ሶላት በሰገድን ቁጥር "ቀጥተኛውን መንገድ ምራን" በማለት በቀጥተኛው መንገድላይ ፅናት እንዲሰጠን መማፀን ተደንግጎልናል
ﻗﺎﻝ ﺍﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﺔ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ : “ ﻭﻟﻬﺬﺍ ﻛﺎﻥ ﺃﻧﻔﻊ ﺍﻟﺪﻋﺎﺀ، ﻭﺃﻋﻈﻤﻪ ﻭﺃﺣﻜﻤﻪ ﺩﻋﺎﺀ ﺍﻟﻔﺎﺗﺤﺔ : { ﺍﻫﺪِﻧَﺎ ﺍﻟﺼِّﺮَﺍﻁَ ﺍﻟﻤُﺴﺘَﻘِﻴﻢَ ﺻِﺮَﺍﻁَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺃَﻧﻌَﻤﺖَ ﻋَﻠَﻴﻬِﻢْ ﻏَﻴﺮِ ﺍﻟﻤَﻐﻀُﻮﺏِ ﻋَﻠَﻴﻬِﻢْ ﻭَﻻَ ﺍﻟﻀَّﺎﻟِّﻴﻦَ
} [ ﺍﻟﻔﺎﺗﺤﺔ 6: ، 7 ] ، ﻓﺈﻧﻪ ﺇﺫﺍ ﻫﺪﺍﻩ ﻫﺬﺍ ﺍﻟﺼﺮﺍﻁ ﺃﻋﺎﻧﻪ ﻋﻠﻰ ﻃﺎﻋﺘﻪ ﻭﺗﺮﻙ ﻣﻌﺼﻴﺘﻪ، ﻓﻠﻢ ﻳﺼﺒﻪ ﺷﺮ، ﻻ ﻓﻲ ﺍﻟﺪﻧﻴﺎ ﻭﻻ ﻓﻲ ﺍﻵﺧﺮﺓ
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያ አላህ ይዘንለዎት እና እንዲህ ይላአሉ"ለዚህም ሲባል ጠቃሚ እና ጥቅል እንዲሁም ትልቅ ዱአ የፋቲሀ ዱአ ነው 'ቀጥተኛውን መንገድ ምራን የእነዚያን በነሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ' (ምራን በሉ)። (ፋቲሀ 6-7)
እሱ (አላህ ባሪያን) እሄን መንገድ ከመራው እሱን በመታዘዝ እና እሱን ማመፅን በመተው ላይ አገዘው በዱኒያም ይሁን በአኼራ ሸር(ተንኮል) አያገኘውም" መጅሙኡል ፈታዋ 14/320—321

በዲን ላይ መፅናት የነብዮች ኑዛዜ ነው።
ﻗﺎﻝ ﺗﻌﺎﻟﻰ : { ﻭَﻭَﺻَّﻰ ﺑِﻬَﺎ ﺇِﺑْﺮَﺍﻫِﻴﻢُ ﺑَﻨِﻴﻪِ ﻭَﻳَﻌْﻘُﻮﺏُ ﻳَﺎ ﺑَﻨِﻲَّ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﺍﺻْﻄَﻔَﻰ ﻟَﻜُﻢُ ﺍﻟﺪِّﻳﻦَ ﻓَﻼ ﺗَﻤُﻮﺗُﻦَّ ﺇِﻟَّﺎ ﻭَﺃَﻧْﺘُﻢْ ﻣُﺴْﻠِﻤُﻮﻥَ } ( ﺍﻟﺒﻘﺮﺓ 132: )
"በርሷ (በህግጋቲቱ) እብራሂም ልጆቹን አዘዘ የእቁብም (እንደዚሁ ልጆቹን አዘዘ) ልጆቸ ሆይ! አላህ ለናንተ ሀይማኖትመረጠ ስለዚህ እናንተ ሙስሊሞች ሁናችሁ እንጅ አትሙቱ" አላቸው

በሀቅ ላይ ለመፅናት የሚረዱን ነገሮች
1)ኢማንን ማረጋገጥ
2)መልካም ስራ
3)በእውነት ላይ አደራ መባባል
4)በትእግስት ላይ አደራ መባባል

ለነዚህ ሁሉ መረጃው የአላህ ቃል ነው።
{ ﻭَﺍﻟْﻌَﺼْﺮِ . ﺇِﻥَّ ﺍﻟْﺄِﻧْﺴَﺎﻥَ ﻟَﻔِﻲ ﺧُﺴْﺮٍ . ﺇِﻟَّﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻭَﻋَﻤِﻠُﻮﺍ ﺍﻟﺼَّﺎﻟِﺤَﺎﺕِ ﻭَﺗَﻮَﺍﺻَﻮْﺍ ﺑِﺎﻟْﺤَﻖِّ ﻭَﺗَﻮَﺍﺻَﻮْﺍ ﺑِﺎﻟﺼَّﺒْﺮِ}
"በግዚያት እምላለሁ። ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው። እነዚያ ያመኑት እና መልካሞችን የሰሩት፣በመታገስም አደራ የተባባሉት ሲቀሩ።"
አሁንም በዚህ ላይ የአላህ ቃል መረጃ ነው።
"አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል ከሀዴዎችንም አላህ ያሳስታቸዋል አላህም የሚሻውን ይሰራል።" [ኢብራሂም(26)]
አሁንም በዚህላይ የአላህ ቃል መረጃ ይሆናል
: { ﻭَﺍﺳْﺘَﻌِﻴﻨُﻮﺍ ﺑِﺎﻟﺼَّﺒْﺮِ ﻭَﺍﻟﺼَّﻼﺓِ ﻭَﺇِﻧَّﻬَﺎ ﻟَﻜَﺒِﻴﺮَﺓٌ ﺇِﻟَّﺎ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﺨَﺎﺷِﻌِﻴﻦَ } ( ﺍﻟﺒﻘﺮﺓ 45
"በመታገስ እና በሶላት ተረዱ እሩሷም (ሶላት) በፈሪይዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት።"

እውነተኛ በሆነ መንሀጅ ላይ መፅናት የአህሉሱናዎች ባህሪ ነው።

በዲን ላይ መገለባበጥ እና ሀቅ በሆነ መንሀጅ ላይ አለመፅናት የአህሉል ቢደእ ባህሪ ነው

ﻗﺎﻝ ﺍﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﺔ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ : “ ﺇﻧﻚ ﺗﺠﺪ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﻜﻼﻡ ﺃﻛﺜﺮ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺍﻧﺘﻘﺎﻻً ﻣﻦ ﻗﻮﻝ ﺇﻟﻰ ﻗﻮﻝ، ﻭﺟﺰﻣًﺎ ﺑﺎﻟﻘﻮﻝ ﻓﻲ ﻣﻮﺿﻊ، ﻭﺟﺰﻣًﺎ ﺑﻨﻘﻴﻀﻪ، ﻭﺗﻜﻔﻴﺮ ﻗﺎﺋﻠﻪ ﻓﻲ ﻣﻮﺿﻊ ﺁﺧﺮ، ﻭﻫﺬﺍ ﺩﻟﻴﻞ ﻋﺪﻡ ﺍﻟﻴﻘﻴﻦ،
ለዚህም ሲባል ሸይኹል ኢስላም እንዲህ ይላሉ:- "አንተ የፍልስፍና ባልተቤቶችን ከአንድ ንግግር ወደ አንድ ንግግር ባንድ ቦታ በንግግር መቁረጥን በሌላቦታ ደግሞ ያን ንግግራቸውን በማፍረስ እንዲሁም (ይባስ ብለው) የዚያን የንግግር ባልተቤት በሌላ ቦታ በማክፈር ታገኛቸዋለህ ይህ ደግሞ (በያዙት አቋም ላይ) እርግጠኝነት እንደሌላቸው መረጃ ነው" መጅሙኡል ፈታዋ 4/ 50

ሸይኽ ሙሀመድ ሰኢድ ረስላን እንዲህ ይላአሉ:- "ከቢዳአ ሰዎች አንዱ በአንድ መንገድ ላይ ያነጋል በሌላ መንገድ ላይ ያመሻል ከልቦና እና ከአስተያየት ጋር ከመገለበበጥ አይወገድም በአንድ ነገር ላይ አይፀናም ምክኒያቱም እሱ ዘንድ (የሚፀናበት) እርግጠኛ የሆነ ነገር የለም
አህሉሱናዎች ጋር (የሚፀኑበት) ቁራአን እና ሀዲስ አለ እነሱም መልእክተኛው ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም የመጡባቸው እውነታዎች ናቸው" [ምንጭ ደዓኢሙ ሚንሀጅ ኑቡዋ (65)]
ሁዘይፋ ረዲየላሁ አንሁ እንዲህ ይላል:-
"እውነተኛ ጥመት ብሎ ማለት መጥፎ የምትለውን ነገር ጥሩ አድርገህ ልትመለከት ነው ወይንም ጥሩ የምትለውን መጥፎ አድርገህ ልትመለከት ነው በዲን ላይ መገለባበጥን አደራህን የአላህ ዲን አንድ ነው" [አብረዛቅ ፊል ሙሰነፍ (11/249) አላለካእይ (120)]

"(ሰለፎች) በዲን ላይ መገለባበጥን ይጠሉ ነበር" [አል-ኢባነቱል ኩብራ(574)]
ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላአሉ:-
"መድሀኒት የለለው በሽታ በዲን ላይ መከረባበት ነው" [አልኢባነቱል ኩብራ (576)]

አሁንም በሀቅላይ ለመፅናት ከሚያግዙን ነገሮች ክርክርን እና በዲን ላይ ጭቅጭቅን መተው
ﻭﻟﻬﺬﺍ يقول – ﻋﻤﺮ ﺑﻦ ﻋﺒﺪ ﺍﻟﻌﺰﻳﺰ:- ﻣﻦ ﺟﻌﻞ ﺩﻳﻨﻪ ﻏﺮﺿًﺎ ﻟﻠﺨﺼﻮﻣﺎﺕ ﺃﻛﺜﺮ ﺍﻟﺘﻨﻘﻞ
ለዚህም ሲል ኡመር ኢብኑ አብዱልአዚዝ እንዲህ ይላል "ዲኑን ክርክር ያደረገ መገለባበጥ ያበዛል" መጅሙኡል ፈታዋ

ሌላው ለሰባት ከሚረዳ ነገር ቂራአት መቅራት ቂራአት የቀራ ሰው እና ጃሂል መቸም ቢሆን ሊነፃፀር አይችልም በተለይ በዚህ ሹበሀ በበዛበት ዘመን ከምን በላይ ቂራአት አስፈላጊ ነው እውቀት ከሌለን ጯሂን ሁሉ እነከተላለን ሰዎች ሂዱ ሲሉን እነሄዳለን ተቀመጡ ሲሉንም እንቀመጣለን እንደው ባጭሩ ኢልም ከሌለን የጯሂ ሁሉ ተከታይ ነው የምንሆነው በቃ ድምፁን ከፍ አድርጎ የጮህ ሁሉ ሀቅ ላይ ያለ ነው የሚመስለን

በመቀጠል አላህ በሀቅ ላይ እንዲያፀናን ዘውትር ዱአ ማድረግ አለብን

ኡሙ ሰለማ እንዳስተላለፈችው የነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ብዙዱአ "አንተ ልቦችን የምታገለባብጥ (ጌታ ሆይ) ልቤን በአንተ ሀይ ማኖት ላይ አፅናልኝ" ነበር ትላለች (ትርሚዝይ ዘግበውታል)

እኛም እነዚህን እና መሰል ዱአዎች ሰባት እንዲሰጠን ማብዛት አለብን

አላህ በመንሀጀ ሰለፍ ላይ ፀንተው መጨረሻቸው አምሮላቸው ከሚሞቱት ያድርገን
https://telegram.me/IbnuMuhammedzeyn
ወንድማ


Forward from: Nurye Musa
"ተውሒድ"

የሁለት ሀገር ስኬት
መክፈቻ ቁልፍ የጀነት
እሳት ውስጥ የማያዘወትር
ጥቃቅን ወንጀሎችን የሚያስምር
የነብያት ሁሉ ጥሪ
የሽርክ ተፃራሪ
የአንድነት መሰረት
መሆኑን እያወቁ
ለምንድን መደበቁ?
ለምን አይጣራም ጧት ማታ?
ወደ ተውሂድ ገበታ
በድብቅም በይፋ
ይጠራ ወደ ተውሒድ…
ሽርክ ከምድረ ገፅ እስኪጠፋ
ከወንድም አማችነት በፊት
ስለ አኽላቅም ከማተት
ወደ አንድነት ከመወትወት
ቅድሚ ወደ ተውሒድ ይጠራ
ተውሂድ ከተስተካከለ እነዚህን…
እሱ ራሱ ስለሚጠራ
አውነት ለህዝበ ሙስሊሙ…
ያሰበ ቅድሚ ወደ ተውሒድ ይጣራ፡፡

(ኑርየ ሙሳ)

https://www.facebook.com/nurye.musa.

https://t.me/nuryemusa


🇮ዲን መመካከር ነው-الدين النصيحة🇮
ቁርአንና ሀዲስን በሰለፎች ግንዛቤ ለመረዳት የሚያስችሉ ተከታታይ ሙሀደራዎች አጠር አጠር ያሉ የነብዩ ﷺሀዲሶችን እና የሰለፎችን ንግግሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው። በተለየመልኩ የኡስታዝ አብዱልዋሲእን ደርሶች ሚያገኙበት ቻናል ነው።
(("الدين النصيحة"، قلنا: لمن يا رسول الله؟ قال:" لله ولكتابه ولرسوله ولأئمة المسلمين وعامتهم")).ሙስሊም ፥ 55
https://telegram.me/ibnyahya7


Forward from: ABU MUSLIM A-DUROOS
📚 المحاضرة 29

📚 ሙሓደራ ክፍል / 29

📌 أخي المريض / أختي المريضة

📌 ታማሚው ወንዱሜ እና ታማሚዋ እህቴ

📍ووصايا هامة للمريض

📍 አንገብጋቢ ምክር ለታማሚ

📚 قال الله تعالى :
{وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ} [الشعراء : 80]

🔗 የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ Mp3

https://goo.gl/RJpYJK

🔗 የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ Amr

https://goo.gl/PRG3xP

🎙 أبو مسلم عمر بن حسن العروسي

🎙 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ዑመር ሀሰን አልአሩሲ ሀፊዘሁሏህ

🌐 t.me/AbumuslimAlarsi




Forward from: 🌹ሀያዕ የኢማን መመዘኛ🌹
🌷ጥቅል ምክሮች ~ለሙስሊም ቤተሰብ🌷

#بسم الله الرحمن الرحيم

الحمد لله رب العالمين والعاقبة للمتقين ولا عدوان على الظالمين وصلي اللهم وسلم وبارك على نبينا محمد وعلى آله وصحبه ومن تبعهم بإحسان إلى يوم الدين
أما بعد:
①,ልጅን በተርቢያ ማሳደግ ኢስላማዊ ግዴታ እንጂ ሱና ወይም ሲፈለግ ብቻ ሚደረግ አይደለም::
,
②,ተርቢያ የሁለቱም ወላጆች ግዴታ እንጂ አንዱ ላይ ብቻ የሚጣል አይደለም::

③,ተርቢያ ስኬታማ የሚሆነው እያንዳንዱ ወላጅ የስራ ድርሻውን ሲያውቅና አንዱ በሌላው ስራ ጣልቃ ካልገባ ነው::

④, ለተርቢያ ሀብታም መሆን ወይም ድሃ መሆን መስፈርት አይደለም::

⑤,ተርቢያ ልክ እንደሌሎች ኢባዳዎች ኢኽላስ ይፈልጋል::

⑥,ተርቢያ በፍቅርና በመተሳሰብ የሚሆን እንጂ አምባ ገነንነትና ግትርነትን አይቀበልም::
,
⑦,ልጆችን በተሳካ መልኩ ተርቢያ ለማድረግ ከያንዳንዱ የእድሜ ደረጃቸው ጋር የሚመጥነውን አያያዝ ማወቅ ያስፈልጋል::
,
⑧,በልጆች መካከል ማፎካከር ወይም አንዱን ከሌላው ማስበለጥ እርስ በርሳቸው ምቀኝነት መበቃቀልና ጥላቻን ስለሚፈጥር ከባድ ጥንቃቄ ይሻል::
,
⑨, የወላጆች አለመከባበር ወይም በልጆች ፊት መወቃቀስ ልጆች ላይ አሉታዊ ተጽኖ ይፈጥራል::
,
⑩,ልጆችን መጥፎ ስድብ መስደብ ብልግና ከመሆኑም በተጨማሪ ወላጅን እንዳይታዘዙና እንዲጠሉም ያደርጋል::
,
⑪, ቁጣና ቅጣት እንዲሁም ተደጋጋሚ ምክር ልጆችን ያሰልች እንጂ አያቀናም:: ስለዚህ ከወላጅ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን እንዲያዩ ማድረግ አልፎ አልፎ ሳይበዛ መምከር አንዳንዴም ጥፋታቸውን እንዳላዩ ሆኖ ማለፍ አስፈላጊ ነው::
,
⑫,ልጆች ላይ መጮህ አሉታዊ ተፅኖ ያሳድራል::

⑬, ልጆች ልጅ እንደመሆናቸው እንዲጫወቱና እንዲዝናኑ ማድረግ ግድ ነው:: በመሆኑም እንዳይረብሹ ወይም ልብሳቸው እንዳይቆሽሽ በማለት ከጫወታ ማገድ ከባድ በደል ነው::
,
⑭, ልጆች በትምህርትም ሆነ በማንኛውም ስልጠና አቅማቸው ሊታወቅና ከሚችሉት በላይ እንዳይሸከሙ መቆጣጠር ያስፈልጋል::

⑮, ልጆችን ተርቢያ ማድረግ ብዙ ትግል የሚጠይቅና ውጤቱ ቶሎ ላይታይ ስለሚችል ሰብር አድርጎ መቀጠል እንጂ ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም::
Be_Ustaz_Selsebil zumekan [Hafizehullah]

https://t.me/ye_Sunnyi_Setochi_Medrek


🔊 "ሀኒፍ" ማለት ምን ማለት ነው?
🎤 ሸይኽ ኢልያስ አህመድ

وَأَنْ أَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ
📖 [ፊትህንም (ወደ ቀጥታ) ያዘነበልክ ስትሆን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ] ዩኑስ 105








Forward from: أختي المسلمة كوني مفتاح للخير و كوني مغلاق للشر!!!
#ክረምቱን___እንጠቀምበት!

ክረምቱን ነፃ የሆናችሁ ተማሪዎችና መምህራን በምትችሉት አቅም ጊዜያችሁን ስለዲናችሁ በመማር አሳልፉት፡፡
#የሚያስተምራችሁ ካጣችሁ በድምፅ የተለቀቁ ትምህርቶችን በማዳመጥ፣ ቁርኣን በመሐፈዝ፣ መፃህፍትን በማንበብ እራሳችንን እንለውጥ፡፡

#ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “አላህ መልካም የሻለትን ሰው ዲኑን ያሳውቀዋል፡፡” ባይሆን የወላጆችን ሐቅ በማይጋፋ መልኩ መሆኑ እየተስተዋለ፡፡

#ማስተማር የምትችሉ ደግሞ ያላችሁን በማካፈል ላይ ተጠመዱ፡፡

ቁርኣን በደንብ የያዘ እሱን ያስተምር፡፡ ዛሬ ዛሬ ነብዩ ﷺ “ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው” ማለታቸውን ብዙዎቻችን ትኩረት ነፍገነዋል፡፡

#አጫጭር የተውሒድ ኪታቦችን የቀራ ሰው ያንኑ ያካፍል፡፡
ደዕዋ ማድረግ የሚችል በተለይም በገጠር አካባቢ አቅሙ በሚችለው ሰዎችን ያስተምር፡፡

#ወላጆች ልጆቻችሁ ክረምቱን ባግባቡ እንዲጠቀሙ አግዙ፡፡ የክረምት ትምህርት የሚሰጡ መድረሳዎች ካሉ ልጆቻችሁ፣ ታናናሽ ወንድምና እህቶቻችሁ እዚያ እንዲከታተሉ አድርጓቸው፡፡

#አስተማሪዎች አመቱን ሙሉ እንደ ልብ የማታገኙት ሙስሊም እንዳለ አስባችሁ የተሻለ ጥረት ለማድረግ ተንቀሳቀሱ፡፡
#ነብዩ ﷺ “ወደ መልካም የሚያመላክት እንደሚተገብረው ሰው ነው” ማለታቸው ይታወስ፡፡ አላህ ሁላችንንም ያግዘን፡፡

ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (ሀፊዘሁአሏህ)

https://www.facebook.com/selewa.kibebu

https://t.me/joinchat/AAAAAERyyRMpclyde0IEZw


Forward from: أختي المسلمة كوني مفتاح للخير و كوني مغلاق للشر!!!
#ከሰውነታችን__ላይ__ማስወገድ__የሚፈቀደውና የሚከለከለው ፀጉር የቱ ነው?

#ሰውነት ላይ የሚወጣ ፀጉርን በተመለከተ ዐሊሞች ለ 3 ይከፍሉታል።

① #ይወገዱ ዘንድ ሸሪዐዊ ትእዛዝ የመጣባቸው የፀጉር አይነቶች።
ለምሳሌ:–
– የብብት ፀጉር፣
– የብልት አካባቢ ፀጉር፣
– የቀድሞ ቀመስ ፀጉር (ማሳጠር)፣
– በሐጅ/ በዑምራ የእራስን ፀጉር መላጨት ወይም ማሳጠር

② #መወገዳቸው የተከለከሉ የፀጉር አይነቶች። ለምሳሌ:–
– የቅንድብን ፀጉር ማስወገድ (ከከባባድ ወንጀሎች ነው)፣
– ፂምን መላጨት (በኢጅማዕ የተወገዘ ነው)

③ #ክልከላም ይሁን ትእዛዝ ያልመጣባቸው የፀጉር አይነቶች። ለምሳሌ:–
– የክንድ ላይ ፀጉር፣
– የእግር / የጭን ላይ ፀጉር፣
– የደረት ፀጉር፣
– የአፍንጫ ፀጉር፣ ወዘተ
በነዚህ ላይ ዐሊሞች ተወዛግበዋል።

#ከፊሎቹ ተፈጥሮን ከመቀየር ጋር በማያያዝ ሲከለክሉ፣ ሌሎች ግን ሸሪዐው ዝም ስላለው መሰረቱ ፍቁድነት ነው ብለዋል። ይህም በፍቃድም ይሁን በክለከላ መልክ ሸሪዐው ያልገለፀው ነገር ባለበት የመተውም ይሁን የማስወገድ ምርጫ አለው ማለት ነው። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–

★ "#ሐላል ማለት አላህ በመፅሐፉ የፈቀደው ነው።

★ #ሐራም ማለት አላህ በመፅሐፉ የከለከለው ነው።
★ #ከሱ ዝም ያለው የተተወ (ያልተከለከለ) ነው።" [ሶሒሕ አትቲርሚዚ]

ስለዚህ በማስወገድም ይሁን በመተው ቁርኣንና ሐዲሥ ላይ ያልተገለፁት አይነቶች ከሶስተኛ ምድብ ላይ ያርፋሉ ማለት ነው።

እናም ባለበት የመተውም ይሁን የማስወገዱ ምርጫ ለባለቤቱ የተተወ ነው።

ይህንን አቋም በርካታ ዐሊሞች መርጠውታል። ለምሳሌ ያክል የሳዑዲ ዑለማዎች ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ (ለጅነተ አድዳኢማህ) "

#ለሴት የሰውነቷን ፀጉር ማስወገድ ብይኑ ምንድን ነው?" ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ ብለው መልሰዋል:–

" #ከቅንድብና ከእራስ ፀጉር ውጭ ያለውን ማስወገድ ይፈቀድላታል። እነዚህን ግን ልታስወግዳቸው አይፈቀድላትም። …
" [ፈታዋ ለጅነት አድዳኢማህ: 5/194]

#በተለይ ደግሞ ፀጉሩ ባልተለመደ መልኩ የወጣ ከሆነ!
#ለምሳሌ የሴት ፂም ወይም ቀድሞ ቀመስ ገፅታዋን ስለሚያበላሽ ማስወገድ ትችላለች።

ከተለያዩ ምንጮች የተሰበሰበ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 02/2010)

https://www.facebook.com/selewa.kibebu

https://t.me/joinchat/AAAAAERyyRMpclyde0IEZw


Forward from: ኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር(አቡ ዓማር)
ውድ አንባቢያን እንደሚታወቀው አላህ (ሱብሀነሁ ወተዐላህ) በእዝነቱ የሰው ዘር ሁሉ የበላይ የነብያት ሁሉ አለቃና መደምደሚያ ፍጡራንን ከፈጣራ የሚያስተዋውቁ ለአለም እዝነት የተላኩ የሰው ልጅን ከሽርክ ጨለማ ወደ ተውሂድ ብርሃን የሚያወጡ አላህን እንዴት ማምለክ እንዳለብን በታላቅ ትህትና የሚያስተምሯቸውን መልክተኛ ልኳል፡፡እሳቸውም ለዑማው ምንንም ሳያስቀሩ ግልፅ ባለ መልኩ አስተምረዋል ስለዚህ እኛም የአላህ ውዴታ አግኝተን ጀነት ለመግባት የምንፈልግ ከሆነ የሳቸውን ፈለግ ስንዝር በስንዝር እርምጃ በእርምጃ መከተል ይኖርብናል ፡፡
ታዲያ ይህንን ለማረጋገጥ (ለማግኘት ) ደፋ ቀና ስንል ከሸሪዓ ጋር በስድስት ነጥቦች መከተላችን መግጠም እና መጣጣም አለበት እነሱም፡-


👉1.ምክኒያት (السبب) ፡- የምንተገብረው ተግባር በምክንያቱ ላይ ሸሪዓን የገጠመ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ፡- አንድ ሰው ቤት በገባ ቁጥር ሁለት ሪአዓ ቢስዓድና ሰላቱንም ሱና ብሎ ቢይዝ ይህ ተግባሩ በሸሪዓ እይታ መሰረት ቢስና ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ ምክኒያቱም ሰላቱ ዒባዳ ሲሆን ቤት መግባቱ ግን ሁለት ረከዓ ለመስገድ በሸሪዓ ምክንያት አልተደረገም፡፡


👉2. አይነት(الجنس)፡- የምንተገብረው ተግባር በአይነቱ ላይ ከሸሪዓን ጋር የገጠመ መሆን አለበት ለምሳሌ አንድ ሰው ዶሮን ለኡዱሂያ ቢያርድና ተግባሩንም ሱና አድርጎ ቢወስድ ይህ ተግባሩ ከሸሪዓ ሚዛን አንፃር መሰረተ ቢስ እና ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ ምክኒያቱም ኡዱሂያ ዒባዳ ቢሆንም ለእርድ ያቀረበውን አይነት ግን ሸሪዓ ካስቀመጣቸው ጋር የገጠመ አይደለም፡፡ ለኡድሂያን መቅረብ ያለባቸው ከቤት እንስሳት ውስጥ ግመል፣ከብትና ፍየል ናቸው፡፡


👉3 .ልክ ወይምመጠን (القدر)፡- የምንተገብረው ተግባር በልኩ (መጠን) ላይ ሸሪዓን የገጠመ መሆን አለበት ለምሳሌ አንድ ሰው እያንዳንዱ አካሉን ውዱእ በሚያደርግ ጊዜ አራት አራት ጊዜ ቢያደርግ ይህ ተግባሩ በሸሪዓ እይታ መሰረት ቢስ እና ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ ምክኒያቱም የውዱእ ተግባሩ ዒባዳ ቢሆንም ከሶስት በላይ ጨምሮ ማድረግን የሚከለክል የአላህ መልክተኛ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ሀዲስ ስላለ ሰውየው ሸሪዓ ካስቀመጠው መጠን (ልክ)ሳይገጥም ድንበር ተላልፋል፡፡


👉4.ሁኔታ ወይም ገፅታ(الكيفية)፡- የምንተገብረው ተግባር ሁኔታው ገፅታው ላይ ሸሪዓን የገጠመ መሆን አለበት፡፡ለምሳሌ አንድ ሰው ሰላት እየሰገደ ሩኩዕ ሳያደርግ ሱጁድ ቢወርድ ይህ ተግባሩ በሸሪዓ እይታ መሰረተ ቢስና ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ምክንያቱም ሰላት መስገዱ ዒባዳ ሆኖ የተከተለው ያሰጋገድ ሁኔታ (ቅደምተከተል)ግን ሸሪዓን ያልገጠመ ነው፡፡


👉5.ጊዜ ወይም ወቅት (الزمان)፡- የምንተገብረው ተግባር ከጊዜ አንፃር ሸሪዓን የገጠመ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ሰላትን ያለ ወቅቱ ወይም ኡድህያን ከኢድ ሰላት በፊት ቢያርድ ሁለቱም ተግባሮች ከሸሪዓ እይታ ተቀባይነት የሌላቸው ተግባሮች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ሰላትም ይሁን ኡዱህያ ዒባዳ ቢሆንም ሰውየው የፈፀማቸው ሸሪዓ ባስቀመጠው ጊዜና ወቅት አይደለም ፡፡


👉6. ቦታ( المكان)፡-የምንተገብረው ተግባር ከቦታ አንፃር ሸሪዓን የተከተለ መሆን አለበት ለምሳሌ አንድ ሰው ቤቱ ወይም መድረሳ ኢዕቲካፍ ቢያደርግ ኢዕቲካፍ ከሸሪዓ ሚዛን አንፃር ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ ምክንያቱም ኢዕቲካፍ ኢባዳ ቢሆንም ከቦታ አንፃር ግን ሸሪዓን የገጠመ አይደለም ፡፡ኢዕቲካፍ ቦታ መስጂድ ነውና፡፡
ውድ አንባቢያን በአሁኑ ሰአት የተለያዩ ሰዎች ቢድዐን ይሰሩና ለምን ይህ ተግባር ትሰራላችሁ ተብለው ሲጠየቁ ምናለበት የፈፀምነው ኢባዳ ነው ሲሉ መስማት የዘውትር ጉዳይ ሆኗል ፡፡ ነገር ግን ኢባዳ መስራታችንን ብቻ ሳይሆን መመልከት ያለብን ተግባሬ ሸሪአን ገጥሟል ወይ የሚለው ጭምር ነውና እንጠንቀቅ !!! ፡፡በቢድዐ ተግባር ላይ ደክመን እና ባዝነን ተጠያቂነት ከማትረፍ በሱና ላይ ተገድቦ መፅናቱ ትልቅ እድል ነው፡፡ደግሞስ ወደ ቢድዐ የምንሄደው ምን ያክሉን የነብዩን ሱናዎች በህይወታችን ውስጥ ተግብረን ነው ?፡፡ አላህ ሆይ ቅናቻውን መንገድ ምራን ፡፡አሚን !!!
🌲ቢድዓ በቁርኣን እና በሐዲስ ብርሀን🌲ከተሰኘው መፅሐፍ የተወሰደ፡፡


✍ አቡ ኢብራሂም(ሸምሱ ነስሮ)
ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮት ወይንም ዐቂዳ ማለት፣ በቁርኣንና ሀዲስ በ(ሠለፎች) ቀደምቶች ግንዛቤ ላይ በተመሰረተ መልኩ ከሆነ ብቻ ነው።
https://telegram.me/shemsuNesro

20 last posts shown.

965

subscribers
Channel statistics