"ሰውነት ምንድን ነው?"
በነገራችን ላይ
አንዳንድ ሰው አለ፣
ሰውነት ምንድን ነው፣ብለህ ብጠይቀው
ሰውነት እንድህ ነው፣ብሎ ለመናገር በጣም የሚጨቀው።
እውነት ነው ይጨቃል
የሰውነት ልኩ፣በምን ይታወቃል?
እስቲ እንጠያየቅ፣ሰወውነት ምንድን ነው?
ብለን ብንጠይቅ፣
ለብዙዎቻችን መልሱ ጥያቄ ነው።
ምክንታቱም
በዚች በኛ ሀገር፣ከሰው ልጆች ይልቅ ግዑዝ ይከበራል
በጠራራ ፀሀይ፣የሰውልጅ እደጉድ ለጉድ ይወገራል።
እናም በኛ ሀገር፣በህዝባችን መሃል
ሰውነት ምንድን ነው?
ብለህ ብትጠይቅ፣እመነኝ ያማሃል።
የሰውነት ትርጉም ምኑም አልገባንም
ቢሆንም
ሰውነት ምንድነው?
Nurye Musa
https://t.me/nuryemusa