"እንባ የሚያስነባ ገጠመኝ"
"እናቴ! ረመዿንን ደስተኛ ሆነሽ ፁሚ"
بسم الله الرحمن الرحيم
የመናዊው ወንድማችን አንድ ወቅት ሀገሩ ላይ በአይኑ ያየውን አስገራሚና ጥግ የደረሰ ሰብአዊነት የታየበትን ገጠመኝ እንዲህ ሲል ፅፏል፦
🗺️ ["ዐንስ" ከተማ በሚገኘው ገበያ እያለፍኩ ሳለ "አስሷፊያ" የሚባል ሐራጅ ስፍራ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች ልገዛ ቆምኩ። ወዲያውም ሁለት ህፃናት ልጆቿንና አስራ አምስት አመት ገደማ የሚሆናት ሴት ልጇን ከጎኗ አድርጋ የሲሊንደር ጋዝ በአናቷ የተሸከመችን በእድሜዎቿ አጋማሽ ላይ ያለች አንዲትን እናት ተመለከትኩ።
ይህቺ እናት ሲሊንደሩን እሷ የምትጠብቀውን ዋጋ ሳያጓድል ለሚገዛት ሰው ልትሸጥ በማቀድ ነበር ገበያ የወጣችው፤ እናም አንዱ መጥቶ 14 ሺ የየመን ሪያል ይሰጣታል፤ እሷም "እኔ የገዛሁት 19 ሺ ሪያል ነው፤ የምሸጠውም ቤት ላከራየኝ ሰውዬ ለመክፈል ግድ ሆኖብኝ ነው እና ከዚህ አልቀንስም" አለችው።
በድጋሚ ሌላ ሰው መጣና 16 ሺ ሪያል ሲሰጣት፤ ለመሸጥ ፈለገች፤ ነገር ግን እሷ እንዳለችው ግድ ሆኖባት ለገበያ ካቀረበችው ከዚህ እቃ ውጪ የምታነሳው ስለሌላት ለመሸጥ ከበዳት።
⚠️ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች በአቅራቢያቸው ሆኖ በእሷና ሊገዟት በሚባባሏት ሰዎች መካከል የሚደረገውን ቃለምልልስ ሲሰማና ሲከታተል የነበረ አንድ ግለሰብ ወደ ሴትየዋ ቀረብ በማለት ጥግ የደረሰ በሆነ አደብና አክብሮት፣ እንዲሁም ጥግ በደረሰ ሰብአዊነት: "እናቴ! ይህ ሲሊንደር ጋዝ ስንት ነው?" አላት፤ እሷም "20 ሺ ነው" አለችው፤ ቀጠል አደረገችና ጥልቅ የሆነ የሀዘን ስሜት እየታየባት "የቤት ኪራይ መክፈል ተስኖኝ፣ የቤቱ ባለቤትም ወይ የተወሰነ ልከፍለው፤ ካልሆነ ከቤት ሊያስወጣን ለሁለት ቀን ማስጠንቀቂያ ሰጥቶን ለመሸጥ ተገድጄ ነው፤ ከአላህ ውጪ ማንም ከጎኔ ረዳት የሌለኝ፤ የእነኝህ የቲሞች እናት ነኝ" አለችው።
👌 ይህኔ ግለሰቡ: "እናቴ! ይህኮ አስሊ የሆነ እቃ ነው!፤ ዋጋውም አንቺ ከምትጠሪው በላይ ነውና በርካሽ እንዳትጥትይው!" አላት። እሷም "ምን ላድርግ ልጄ!" አለችው።
እሱም: "እናቴ! እኔ በትክክለኛ ዋጋው እገዛሻለሁ" አለና፤ በዙሪያው ከበው የሚመለከቱ ሰዎችን አስደማሚ በሆነ ትንግርት 100 ሺ ሪያል ከኪሱ አውጥቶ ሰጣት።
🥀 የየቲሞቹ እናት ገጠመኙ አንጀቷን በልቷት አለቀሰች፤ ሰውየውም "እናቴ! ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሽው? ይህኮ የእቃሽ ዋጋ ብቻ ነው" በማለት እያፅናናት እንባዎቿን በሶፍት አበሰላት።
🤲 እሷም "ጭንቄን እንደገላገልከኝ፤ አላህ ያንተንም ጭንቅ ይገላግልህ" በማለት ዱዓ ስታደርግለት፤ ሰውየው "ላ ላ! (አይደለም! አይደለም!) ይህ የእቃው ዋጋ ብቻ ነው፤ ይልቁም እኔ ከአንቺ አንድ ነገር እፈልጋለሁ" ሲል አናገራት።
እሷም "ምንድን ነው የፈለግከው ልጄ?" አለችው።
እሱም "ነገ ሩቅ ወደ ሆነ ሀገር ልሄድ ነውና ይህ እቃ ከጉዞ እስክመለስ ድረስ አንቺ ዘንድ በአማና እንዲቀመጥልኝ እፈልጋለሁ።" አላት።
እሷም "ልጄ! አታውቀኝ አላውቅህ ስትመለስ እንዴት ልታገኘው ትችላለህ?" አለችው።
እሱም "የባለቤቱን ስልክ ቁጥር ስጭኝና ስመለስ እደውልለታለሁ ከዚያ በእሱ አማካኝነት ትሰጪኛለሽ" አላት።
📱ከዚያ የአከራዯ ቁጥር የተፃፈበትን ወረቀት አውጥታ ሰጠችው፤ ቁጥሩን እንደተቀበላትም ወዲያው ወደሱ በመደወል "የአክስቴን የቤት ኪራይ ልሐውልልህ ስለሆነ ሙሉ ስምህን ላክልኝ" በማለት ያወራዋል። አከራዩም "ሴትየዋ የሁለት ወር 50 ሺ ሪያል አለባት" እያለ ይመልስለታል። ሰውየውም "አሁን የስድስት ወር አስተላልፍልህና ደረሰኙን ለአክስቴ እሰጣታለሁ" አለው።
የየቲሞቹ እናት በሁኔታው ተደሰተች፤ አለቀሰችም! ጎዳናው ላይ ተብረከረከች፤ ሰዎችም ተሰባሰቡ፤ እኔም ተመስጬ ሁኔታውን መከታተሌን ቀጠልኩ።
🚘 ከዚያ ይህ ኢስላማዊ መልካም ስብእናን የተላበሰው ድንቅ ግለሰብ እናቱን፣ ሚስቱንና ልጆቹን የጫነች መኪናው ከገበያው ማዶ የሚገኝ ጎዳና ላይ ቆማ ስለነበር ይህቺን ሚስኪን እናት ወደዚያ ወሰዳት።
ያ አላህ! ምን አይነት ግለሰብ ነው!? ምን አይነት ልብ እና ችሮታ የታደለ ሰው ነው!?
በቦታው ላይ የነበርን ሰዎች በሰውየው ባህሪና አድራጎት ተደመምን! ከመጓጓታችን የተነሳም ገጠመኙን እስከ ፍፃሜው ለመከታተል ወደ ጎዳናው ተከተልናቸው። እዚያ እንደደረሱ ለሴትየዋ ሁለት ተጨማሪ የሲሊንደር ጋዝ ገዛላትና "ይህ ላንቺ የምናበረክተው የእኔ፣ የእናቴና የባለቤቴ ስጦታ ነው" አላት።
💸 ከዚያም ቅድም ቃል ከገባው በተጨማሪ 100 ሺ የየመን ሪያልና አንድ ስማርት ስልክ ሰጣት፤ እንዲህም አላት: "እናቴ! አሁን እንግዲህ (አንገትሽን ሳትደፊ) ራስሽን ከፍ አድርገሽ ወደ ቤትሽ ተመለሺ፤ የ6 ወር የቤት ኪራዩን አሁን አስተላልፍለታለሁ፤ ረመዿንን በራሓ ተረጋግተሽ ፁሚ፤ እኔ እደውልልሻለሁ የምትፈልጊው ነገር ካለ አደራ አሳውቂኝ! ከዛሬ ጀምሮ የአንቺም የልጆችሽም ሀላፊነት በኔ ላይ ነው።"
🖥️ ሴትየዋ ሳትለየው ቶሎ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሐዋላ ቤት ሂዶ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ለአከራዯ 200 ሺ ሪያል ያስተላለፈበትን ደረሰኝ ይዞ ተመለሰና እንዲህ አላት "ያለፈውን የሁለት ወር ኪራይ 50 ሺ ሪያልና ተጨማሪ የስድስት ወር 150 ሺ ሪያል አስገብቸለታለሁ።" በማለት ደረሰኙን ሰጣት።
🌹ወዲያውም ከሰውየው መኪና ውስጥ አንዲት እናት ወረደችና የገንዘቡ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ባላውቅም በድህነት ልቧ ተሰብሮ ለነበረው እናት ሰጠቻት፤ ግንባሯንም ሳም አደረገቻት። የየቲሞቹን እናት ግንባር ለመሳም ከመኪና የወረደችው ሴትዮ የዚያ ቅን ግለሰብ ወላጅ እንደሆነች አወቅን፤ ግለሰቡ ሚስኪኖችን እንዲወድና እንዲንከባከብ ኮትኩታ ያሳደገችው እሷው ትሆናለች ብለንም ገመትን።
🤲 የአላህ መልእክተኛ ዐለይሰላቱወሰላም "ጌታዬ ሆይ! ሚስኪኖችን መውደድን እለምንሃለሁ" በማለት ዱዓ ያደርጉ ነበር። ድሆችንና ደካማዎችን መውደድና መንከባከብ ኢስላማዊና ሰብአዊ በጎ ተግባር የሆነውም ለዚሁ ነው።
👌መውቂፉ አካላት የሚኮማተሩበት መውቂፍ ነው፤ ትክክለኛ ኢማናዊ መውቂፍና ቀናነት የተንፀባረቀበት፤ ትክክለኛ ሂውማኒቲና እውነተኛ ወንድነት የታየበት ድንቅ ገጠመኝ ነው!!
እዚህ ላይ በአይኔ ያየሁትን ይህን ገጠመኝ የምተርከው፦ እንድንጠቀምበት፣ ሰጭነትንና ቸርነትን እንድማርበት፣ እንዲሁም መልእክቱ ለሀብት ባለቤቶችና በሀብታቸው ኣኺራን መግዛት ለሚሹ ሰዎች እንዲደርስ በማለም ነው!!
እያንዳንዱ ነጋዴ የዚህን ግለሰብ አይነት በጎ ተግባር ቢሰራ የበርካታ ድሆች ፍላጎትና ችግር በተቀረፈ ነበር!!
👌 ቢላሂ ዐለይኩም! ገጠመኙ ውስጣችሁ ላይ ተፅእኖ አልፈጠረባችሁም!?
አዎ! በፅሁፍ ተፅፎ የምታነቡት ገጠመኝ ተፅእኖ እንደሚያሳድርባችሁ እገምታለሁ። በአይናችሁ ብትመለከቱትስ እንዴት ትሆኑ ነበር!?...
በመጨረሻም፦ ሰዎችን ማስደሰት ለአድራጊው እንጂ ከእሱ ውጪ ለማንም ሰው ሊሰማውና ሊያጣጥመው የማይቻለውን የውስጥ ደስታና እርካታን የሚያስገኝ መሆኑን እየገለፅኩ ፅሁፉን እቋጫለሁ፤ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ይበልጥ አዋቂ ነው።]
N.B. የየመን 100 ሺ ሪያል በኢትዮጲያ 10 ሺ ገደማ ይሆናል (ተቅሪበን)።
☝️ይህ ከዐረበኛ ፅሁፍ የተወሰደ ነው።
6/8/1446
https://t.me/AlFawaedAssalaffiyya