ካንቴክ / CANTECH


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Технологии


ውቅታዊ ፣ እውነትኛ የቴክኖልጂ መረጃዎች
🌍ኑ አለም የደረሰበትን እንይ🌍

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Технологии
Статистика
Фильтр публикаций


10 ቢሊየን ፓስዎርዶች በሃከሮች ኦንላይን ተለቀዋል

በአለማችን ሪከርድ ነው የተባለው ይህ ስርቆት ራሱን ኦባማኬር በሚል ድብቅ ስም በሚጠራ ግለሰብ  ከተለያዩ የኦንላይን ዌብሳይቶች እና ዳታቤዞች አስር ቢልየን የሚደርሱ  ፓስዎርዶችን ኦንላይን ላይ አውጥቷል።

rockyou2024.Txt የተባለው ይህ ፋይል ከዚህ በፊት ከተለቀቀው rockyou2021.Txt በ1.5 ቢሊዮን የሚበልጡ ፓስውርዶችን ይዟል። እነዚህን ፓስዎርድን በመጠቀም ሀከሮች የማንነት ስርቆት የባንክ ገንዘብ ስርቆት እና የመርጃ ስርቆትን ሊያደርሱብን ይችላሉ።


ይህ እንዳይከሰት የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማድረግ አአስፈላጊ ነው

1    የምንጠቀምባቸውን የኦንላይን ፓስወርዶች ረጅም, ካራክተር እና ቁጥር የያዙ ለመገመት ከባድ አድርጎ መቀየር

2  two Factor Authentication የተባለውን ፊቸር መጠቀም

3 ፓስዎርድ ማኔጀር ሶፍትዌሮችን በበመጠቀም ጠናካራ ፓስዎርዶችን ጄኔሬት አድርጎ መጠቀም

@bgr

#technews
#Passwordleak
#cyber_crime


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ጂን ሲኩኤንሲንግ የህጻናት ካንሰርን ለማከም

በአለማችን በየአመቱ 400 ሺህ የሚሆኑ እድሜያቸው ከ1 እስከ 19 አመት የሆናቸው ህጻናት በካንሰር ህመም ይጠቃሉ።

በእንግሊዝ የሚገኘው የብሄራዊ ጤና አገልግሎት ድርጅት የሕጻናትን ካንሰር ለማከም የጂን ዲኮዲንግን በመጠቀም አመርቂ ውጤቶችን እንዳገኙ አስታውቀዋል።

የህክምና ባለሙያዎቹ 281 ሕጻናት ላይ ይህን ህክምና አድርገዋል ከእነዚህ ህጻናት ለአንድ ሶስተኛው ስለበሽታቸው በደምብ ለማወቅ እና የሚያስፈልጋቸውን የህክምና አይነት ለማውቅ ተችሏል።

ከህክምናው ተጠቃሚዎች መካከል ኤዲ አንዱ ስሆን እድሜው 6 አመት እያለ ነው በሉኪሚያ ካንሰር የተጠቃው። ዶክተሮቹ ጂን ሰኩኤንሲንግን በመጠቀም ኬሞቴራፒ ህክምና ቤኤዲ ላይ ምን ያክል እንደሚሰራ በማርጋገጥ ተገቢውን ህክምና እንዲያደርግ እና እንዲድን ረድተውታል።

ጂን ሲኩኤንሲንግ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ የጂን ስሪቶች መለየት ነው። ይህም ለየት ያሉ የጂን ለውጦችን(gene Mutation) ለመለየት፣ ለታካሚዎች ለየራሳቸው የሚሆን ህክምና ለመስጠት፣ የበሽታውን የእድገት ደረጃ ለመረዳት እና በሽታውን ሳይስፋፋ ለመከላከል እና ለማከም ይጠቅመናል።

@skynews

#techinfo
#Gene_sequencing
#Cantech


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ሀሪኬንን የሚከታተሉ የውቅያኖስ ድሮኖች

ሀሪኬኖች በውቅያኖሶች መሞቅ ምክንያት የሚከሰቱ ከባድ ዝናብ፣ አውሎንፋስ፣ ነጎድጓድ እና መብረቅን የቀላቀሉ እጅግ አደገኛ የተፈጥሮ ክስተቶች ናቸው። በክብደታቸው ከደርጃ 1 እስከ 5 የሚመደቡት ሀሪኬኖች ከ119 እስከ 252 ኪሎሜትር በሰዕት እየተጓዙ መሰረተ ልማቶችን እና የሰው ህይወትን ያጠፋሉ።

በአለማችን የተከሰተው ከፍተኛው ሀሪኬን ብሆላ ሳይክሎን ይባላል የተከሰተውም በ1970 በሀገረ ባንግላዲሽ ሲሆን በሰዐት 185 ኪሎሜትር እየትጓዘ ከ300,000 እስከ 500,000 ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል።

ይህን አደጋ ለማስቆም የውቅያኖሱን የሙቀት መጠን እና ወደ ከባቢው የሚለቀውን የሙቀት መጠን መለካት ሀሪኬኑ ከመከሰቱ በፊት ጥንቃቄ ለማረግ ያስችላል ነገር ግን ይህን ሙቀት በሰው ልጅ ለመለካት ለህይወት አስጊ ያደርገዋል።

ይህን ችግር ለመፍታት በሀገረ አሜሪካ ሳሊድሮን የተባለ ድርጅት በውሃ ላይ የሚንቀሳቀሱ ድሮኖችን ሰርቷል። እነዚህን ድሮኖች በኮምፒውተር ከርቀት በመቆጣጠር የውቅያኖስን ሙቀት በመለካት እና የተለያዩ የከባቢ መረጃዎችን በመሰብሰብ ሀሪኬኖች እንዴት ሊከሰቱ እንደሚችሉ እና የመከሰቻ ጊዜያቸውን ቀድሞ ለመገመት ጠቃሚ ናቸው ተብሏል።
@BBC

#technews
#hurricane_drones
#cantech


ሰውሰራሽ አስተውዕሎት የባንኩን ሴክተር እየቀየረ ይገኛል

ሰውሰራሽ አስተውዕሎት በግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ጤና፣ ማርኬቲንግ በመሳሰሉ ትላልቅ ዘርፎች ላይ ተጸዕኖውን እያሳረፈ ይገኛል።

አሁን በርካታ ባንኮች ሰውሰራሽ አስተወዕሎትን በመጠቀም የደምበኛን የአካውንት መረጃ ለመስጠት ፣ የፋይናንሻል ምክር አገልግሎት፣ የቨርቿል አሲስታንስ በአጠቃልይ ደምበኞች በየቀኑ ለሚያከናውኗቸው የባንክ አገልግሎቶች እርዳታ ለመስጠት እየተጠቀሙበት ይገኛል።

በቅርቡ ደግሞ በሲውዘርላንድ የሚገኘው በአለም የባንኮች ደረጃ 28ኛ ደርጃን የያዘው ዩቢኤስ ባንክ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች ብድር በሚጠይቁበት ጊዜ ያለምንም የባንክ ሰራተኛ ንክኪ በፍጥነት ብድር የሚያገኙበትን መንገድ ሰውሰራሽ አስተውዕሎትን በመጠቀም ማመቻቸቱን አስታውቋል።
@reuters

#technews
#Fintech
#cantech


ኢንተርናሽናል ስፔስ ስቴሽን ሊወገድ ነው

ኢንተርናሽናል ስፔስ ስቴሽን ከ26 አመት በፊት በ1998 አስራ አምስት ሀገራትን በወከሉ በአምስት የስፔስ ተቋምት በ100 ቢሊዮን ዶላር ወጪ በአለማችን ከተከናውኑ እጅግ ውስብስ የኢንጂነሪንግ ስራዎች የመጀምርያው በመሆን ተጀምሯል። ሰርቶ ለማጠናቀቅም 40 የህዋ ጉዞዎች እና 13 አመት ፈጅቷል።

በአሜሪካ፣ ራሺያ፣ ጃፓን፣ አውሮፓ እና ካናዳ አስተዳደር ስር ከ3300 በላይ ሳይንሳዊ ምርምሮች ተከናውነውበታል። የእነዚህ ሀገራት ስምምነት በ2030 ያበቃል በዚህ ምክንያት ስቴሽኑ ከኦርቢት መወገድ አለበት።

ይህንን ስራ ለማከናወን ናሳ የኤለን መስኩ ድርጅት ስፔስኤክስ ስቴሽኑን በ2030 አውድሞ ወደውቅያኖስ እንዲጥለው ፍቃድ ሰጥቶታል።

ስፔስኤክስ ይህን ስፋቱ አንድ ስታዲየም የሚያክል ስፔስ ስቴሽን ለማውደም ተሽከርካሪን በመጠቀም ስፔስ ስቴሽኑን ጎትቶ ወደውቅያኖስ ይጥለዋል። ድርጅቱ ይህን ስራ ለማሳካት  843 ሚልዮን ዶላር  ተቀብሏል።

ስፔስ ስቴሽኑ ከወደመ በኃላ በቦታው እንደ ስፔስ ኤክስ፣ አግዚኦም፣ ብሉ ኦሪጅን ያሉ የግል ድርጅቶች የራቸውም ስፔስ ስቴሽን ያመጥቁበታል ተብሎ ይጠበቃል።

#Techinfo
#international-space-station
#Cantech


ሺኢን/SHEIIN

ሺኢን ከ16 አመት በፊት ክሪስ ዡ በተባለ ቻይናዊ የሰርች ኢንጅን ኦፕቲማይዜሽን ስፔሻሊስት የተመሰርተ ኢንተርኔትን በመጠቀም የተለያዩ የልብስ ምርቶችን የሚሸጥ ድርጅት ነው።  ሺኢን  እንደአማዞን ሁሉ ከ6000 በላይ ቻይና ውስጥ የሚሰሩ የልብስ አምራች ድርጅቶችን ምርት ቀጥታ አለም ላይ ላሉ የልብስ ተጠቃሚዎች ያቀርባል።

ድርጅቱ አሁን ላይ በ220 ሀገራት አልባሳቱን ይሸጣሉ በ2022 ብቻ 100 ቢልየን ዶላር የሚገመት ሽያጭ እና ከ10 እስከ 16 ቢልዮን ዶላር የሚገመት ትርፍ አግኝቷል።

ሺኢን የሚሸጣቸው አልባሳት ከሌሎች ብራንዶች ጋር ሲነጻጸሩ ርካሽ መሆናቸው በብዙ እንዲሸጡ አንዱ ምክንያት ሲሆን  ከብዙ የሶሻል ሚድያ ኢንፍሉዌንሰሮች እና ታዋቂ ሰዎች ጋር መስራቱ ፣ ጊዜውን የጠበቁ ፋሽኖችን እና ትሬንዶችን በብዛት ማምረቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ አስተዋጾ አድርጓል።

ይህ ድርጅት ምንም እንኳን ስኬታማ ቢሆንም በሚሰራበት ቦታ ላይ ያሉት ሰራትኞችን የጉልነት አጠቃቀም እና የማይመች የመስርያ ቦታ፣ የሚያደርሰው የከባቢ ብክለት እና አልባሳቱ ላይ የሚጠቀማቸው መርዛማ ኬሚካሎች ለወቀሳ ይዳርጉታል።
@times MEGAZINE

SHEIN WEBSITE: https://m.shein.com/?lang=en

#techinfo
#Shein
#cantech


እጅግ ፈጣኑ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ

የተለያዩ ድርጅቶች የኤሌክትሪክ መኪናዎችን በፈጣን ቻርጅ ማድረግያ በመጠቀም ቻርጅ የማድረግያ ሰዓታቸውን ለመቀነስ እየሰሩ ይገኛሉ።

ከነዚህ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው ኒዮቦልት በአስገራሚ ሁኔታ አንድን የኤሌክትሪክ መኪና  በ4 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ ውስጥ ከ10% ወደ 80% ቻርጅ አድርጓል።

ኒዮቦልት ይህን ሊያሳካ የቻለው የራሱን የስፖርት ኤሌክትሪክ መኪና እና ከሊትየም-አየን የተሰራ አዲስ የባትሪ ምርትን በመጠቀም ነው። ሊትየም-አየኑ እሳት ሳይፈጠር እና ቻርጀሩን ቶሎ በማይጨርስበት ሁኔታ ሆነ በዚህ ፍጥነት ቻርጅ እኒዲያደረግ አስችሎታል።

በመኪናው ሙከራ ጊዜ አንዳንድ እክሎች አጋጥመው ነበር ለምሳሌ የመኪና ማቀዝቀዣ ሲስተሙ መስራት  አቁሞ ነበር ይሁን እንጂ ይህ ስታርታፕ ያሳካው ነገር ለኤሌክትሪክ መኪና ተጠቃሚዎች ገላግሌ ነው ተብሏል።
@Tnw

#cantech
#Electric-cars
#technews


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የሰው ስጋ ያላቸው ሮቦቶች

የጃፓን ሳይንቲስቶች ለሮቦቶች የሰውን ቆዳ ሴሎች በመጠቀም ሕይወት ያለው የሚመስል ሰውሰራሽ ቆዳን ማምረት ችለዋል።

በቶክዮ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙት የፈጠራ ባለቤቶች ረቡዕ እለት ባወጡት ሳይናሳዊ ጆርናል  የሰውን ልጅ ጅማቶች አፈጣጠር በማየት "perforation Type Anchor" በተባለ ሰውሰራሽ ቆዳ የመስራት ሂደት እንዴት ቆዳውን መስራት እንደቻሉ አስነብበዋል።

እነዚህ ሳይንቲስቶች ግባቸው ልክ እንደባዮሎጂካል ቆዳ  ራሱን ማከም የሚችል ሰው ሰራሽ ቆዳ ማምረት እንደሆነ ተናግረዋል።

የቆዳ አሰራሩን በተመለከተ ዝርዝር ሂደቱን ከፈለጋችሁ ይህን ሊንክ ተጠቅማችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።

https://www.cell.com/cell-reports-physical-science/fulltext/S2666-3864(24)00335-7
@gizmodo

#TECHNEWS
#ROBOTICAS
#CANTECH


በስዊድን የካሽ ገንዘብ መቅረት ህዝቡን ለዘረፋ እያጋለጠው ነው
ስዊድን ካሽ አልባ ማህበረሰብን ለመፍጠር በምታደርገው ጥረት ለብዙ የዲጂታል ወንጀሎች እየተጋለጠች እንደሆነ ተዘግቧል። ዘራፊዎቹ እንደ ባንክ አይዲ ያሉ መረጃዎችን በመጠቀም የባንክ ደምበኞችን ይዘርፋሉ፣ ለምሳሌ ኤለን የምትባል ሲውዲናዊ ወጣት ልብስ ለመሸጥ አካውንቷን በምታስገባበት ሰአት  በሳይበር ወንጀለኞች አንድ ሺህ ዶላር መሰረቋን ዘግባለጭ።

በስዊድን እየትባባሰ በመጣው የዲጂታል ገንዘብ ስርቆት በ2023 ብቻ 1.2 ቢሊዮን ክሮነር የኦንላይን ዘረፋ ተፈጽሟል ይህም በ2021 ከተፈጸመው ጥቃት በእጥፍ የጨመረ ነው። ይህ የወንጀል ኢኮኖሚ የስዊድንን 2.5% ይሸፍናል።

ካሽ የማይጠቀም ማህበረሰብ መገንባት ጥሩ ጎኖች ቢኖሩትም በዲጅታሉ አለም የሚሰራው የወንጀል አይነት እየተራቀቀ እና ከጊዜ ወደጊዜ ዘመናዊ እየሆነ ስለመጣ ምንም እንኳን የባንኮችን ሳይበር ሰኩሪቲ ለመጨመር ቢሞከርም በዲጂታል የባንክ ስርሃት ላይ እየተጋረጠ የመጣው አደጋ እየጨመረ መጥቷል።
 
በነዚህ ወንጀለኞች የሚፈጸሙ የማታለል አይነቶችን በሌላ ጊዜ በሰፊው ምንመጣበት ሲሆን ለአሁን ግን በእንደዚህ አይነት ዘራፊዎች እንዳንታለል ማድረግ ያለብንን ጥንቃቄዎች እንይ፡

1 ጠንካራ ፓስዎርድ መጠቀም እና ፓስዎርዳችንን አለማጋራት
2 የምንጠቀማቸውን የባንክ እና የተለያዩ የዲጅታል ገንዘብ መተግበርያዎች በየጊዜው አፕዴት ማድረግ
3  ከባንኮች እና ከተለያዩ የመርጃ ምንጮች የሚሰሙ የሳይበር መረጃዎችን መከታተል
4 እንደ ቪፒኤን ያሉ ኔቶርካችንን ሰኪውር የሚያደርጉ መተግበርያዎች መጠቀም
5 በስልክ ከሚመጡ ከምንጠቀመው ባንክ ጋር የሚመሳሰሉ መልዕክቶች እና ፖፕአፖች ስሚኖሩ እነሱን  በተጠንቀቅ መፈተሽ

እነዚህን ጥንቃቄዎች በማድረግ ከሳይበር ወንጀለኞች ራሳችንን ማዳን እንችላለን።


የሚበላ ሮቦት

የህክምና ባለሙያዎች የሰወነታችንን ውስጣዊ አካል ለመመርመር ከካሜራ ጀምሮ ብዙ አይነት መሳርያዎች ይጠቀማሉ። እነዚህ መሳርያዎች በተለይ ሰውነታችን ውስጥ የሚቆዩ ከሆነ የተለያዩ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ያስከትላሉ።

ይህን ችግር ለመፍታት ሮቦፉድ የተባለ ፕሮጀክት ሙሉ ለሙሉ የሚበላ ሮቦት አስተዋውቋል። እነዚህ ሮቦቶች በውስጣቸው የሚበላ ባትሪን ጭምር የያዙ ሲሆን ባትሪው ሮቦቱ ሰውነታችን ውስጥ ከገባ በኋላ መረጃ እንዲሰጥ እና እስኒንቀሳቀስ የሚረዳው ነው። ሮቦቱ ለመብላት ጣፋጭ እና ማኘክ ሳይጠበቅብን እንድንበላው ተደርጎ የተሰራ ነው።

ተመራማሪዎችን ሁለት አይነት የሚበሉ ሮቦቶችን የሰሩ ሲሆን አንደኛው ባትሪውን በመጠቀም የሚንቀሳቀስ ሲሆን አንደኛው ደግሞ አይንቀሳቀስም። እነዚህ ሮቦቶች የታካሚውን ምቾት በመጠበቅ እና የጎንዮሽ ጉዳትን በማስቀረት ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል።
@bgr

#technews
#robotics
#cantech


የማላዊ ገበሬዎችን እያገዘ ያለው ሰውሰራሽ አስተውዕሎት

ከማላዊ ዋና ከተማ ሊሎንግዌ 40 ኪሎሜትር ርቃ በምትገኝ ንዶዶ በተባለች መንደር የሚገኙ ገበሬዎች “ኡላንግዚ” ወይም በትርጉሙ “ምክር” የተባለ ሰውሰራሽ አስተውዕሎት በተግባር ላይ በማዋል ስራቸውን እያቀለለ እና እያገዛቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

ኦፖርቹኒቲ ኢንተርናሽናል በተባለ ድርጅት የበለጸገው ሰውሰርሽ አስተውዕሎት ቻትጂፒቲን እና በአካባቢው የተዘጋጁ የግብርና ማኑዋሎችን በመጠቀም ለግበሬዎች ጥያቄ መልስ ይመልሳል በተጨማሪም የሰብል እና እንስሳ በሽታዎችን ይመረምራል።

ኡላንግዚ የተጀመረው ሳይክሎን ፍሬዲ የተባለ ከባድ የተፈጥሮ አደጋ ማላዊን አጥቅቶ የገበሬዎችን አብዛኛውን ሰብል ካወደመባቸው በኋላ ነው። ገበሬዎቹ ይህ አደጋ በተፈጠረበት ጊዜ መተግበርያው ቢኖር መከላከል እንችል ነበር ይላሉ። በመጋቢት ወር የአሳማ በሽታ ተከስቶባቸው መተግበርያውን በመጠቀም የበሽታው አይነት ምን እንደሆነ እና ምን አይነት መድሃኒት መጠቀም እንዳለባቸው ነግሯቸዋል።መጻፍም ሆነ ማንበብ የማይችሉት ገበሬዎች ረዳት ተቀጥሮላቸው በረዳታቸው አማካኝነት ጥያቄያቸውን ይጠይቃሉ።

ባደጉት ሀገራት ሰውሰራሽ አስተውዕሎት በግብርናው ዘርፍ ሰፊ ጥቅም ላይ ይውላል። ከስሀራ በታች የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ግን ሰውሰርሽ አስተውዕሎትን በንደዝህ አይነት መልክ መጠቀም የሚበረታታና ወደሌሎች ሀገራት ቢስፋፍ ብዙ ጥቅሞችን ይሰጣል።
@japantimes

#technews
#AI
#cantech


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አዲሱ የቡጋቲ ምርት ቱርቢላን (በ250 ሚሊዮን ብር ብቻ😊)

በአለማችን ድንቅ እና ቅንጡ እንድሁም የሃብት መለክያ ጣርያ ከምንልቸው የመኪና ብራንዶች ቡጋቲ ከመጀመርያቹ ተርታ ይመደባል። ይህ የመኪና አምራች ድርጅት ከስምንት አመታት በኋላ ቱርቢላን የተሰኘ አስገራሚ መኪና አምርቶ አስተዋውቋል።

ቱርቢላን V16 drivetrain የተባለ ባላ16 ሲሊንደር ኢንጅን ተገጥሞለታል፣ ሁለት ከፊት አንድ ከኋላ በአጠቃላይ ሶስት ሞተሮችም ተካተውለታል ይህም 1800 የፈረስ ጉልበት እንዲኖረው አድርጎታል፣ በሙሉ ቻርጅ በሰዐት 402 ኪሎሜትር መጓዝ ይችላል ይህ ማለት ከዚህ ባህርዳር በአንድ ሰዐት ተኩል ያደርሰናል።

በተጨማሪም ለሚቀጥሉት ሰላሳ አመታት ታስቦ እጅግ በተዋበ የመኪና ውስጥ ዲዛይን ተሰርቷል፣ ምንም እንኳን የዘመኑ መኪናዎች በስማርት ስክሪኖች የተሸፈኑ ቢሆኑም ድርጅቱ ለሚቀጥሉት ሰላሳ አመታት የመኪና ውስጥ ዲዛይን ስማርት ስክሪን ያካትታል ብሎ ስለማያስብ በውስጡ አንድም ስክሪን አልተካተተበትም።

ታድያ ይህ መኪና የማይቀመስ ዋጋ ነው ያለው ይህም 4 ሚልዮን ዶላር ወይም 250 ሚልዮን ብር ነው። ድርጅቱ 250 መኪኖች ብቻ እንደሚመርቱ ያስታወቀ ሲሆን ከወዲሁ ሁሉም ተሽጠው አልቀዋል።
@slash_gear

#techreview
#Bugatti
#cantech


ሀከሮች በ2024ቱ በአውሮፓ ዋንጫ የፖላንድ ጨዋታ ላይ ጥቃት አድርሰዋል

ከአንድ ሳምንት በፊት የ2024ቱ የአውሮፓ ዋንጭ ተጀምሯል። በዚህ ውድድር ላይ የምትስተፍው ፖላንድ በሁለት ግጥሚያዎቿ ላይ ጨዋታው በፖላንድ በቀጥታ እንዳይተላለፍ በህገሪቱ የሚገኝው TVP ቴሌቭዥን ላይ ሀከሮች ጥቃት እንደደረሰባት ተዘግቧል።

የመጀመርያው ጥቃት የደረሰው ፖላንድ ከኦስትሪያ ጋር በምታደርገው ጨዋታ ላይ ሲሆን distributed denial of service (DDoS) የተባለ የጥቃት አይነት ብዙ ትራፊክ ኔትዎርኩን እንዲያጨናንቅ እና ደጋፊዎች ጨዋታውን እንዳያዩ አድርጓል።

ሁለተኛው ጥቃት ደግሞ ፖላንድ ከኔዘርላንድስ ጋር የምታደርገውን ጨዋታ ላይ የደረሰ ሲሆን tvp በቴክኒካል ጉዳዮች ምክንያት ጨዋታውን ማስተላለፍ እንዳልቻለ በማስረዳት ተመልካቾች ሌላ ጨዋታውን የሚመለከቱበት ድህረገጽ ለቋል። የጥቃቱ አድራሾች አይፒ አድራሻም የዛው የፖላንድ ሀገር እንደሆነ አሳውቋል።

#technews
#EURO 2024
#cantech


ኢንተርኔት በምንጠቀምበት ጊዜ ማንነታችንን እንዴት መደበቅ እንችላለን (የመጨረሻ ክፍል)

ታድያ እነዚህ መረጃዎች እንዳይያዙብን ከፈለግን የሚቀጥሉትን ሶስት መንገዶች ተጠቅመን ማንነታችችንን እና መረጃዎቻችንን መደበቅ እንችላለን

ፕሮክሲ ሰርቨር
፡ ፕሮክሲ ሰርቨር አይፒ አድሬሳችን በዌብ ሰርቨሮች እንዳይታይ የሚያደርግልን ሰርቪስ ነው። በተለይም ኦንላይን ዌብ ሰርቨሮችን በመጠቀም የምንፈልገውን ዌብሳይት ቀጥታ ሰርች ማድረግያው ላይ በመጻፍ አይፒ አድራሻችንን መደበቅ እንችላለን። የዚህ አገልሎት መጥፎ ጎን የኢንተርኔት ፍጥረቱን ዝግ ማድረጉ ነው። ከኦንላይን ዌብ ፕሮክሲዎች መካከል https://www.proxysite.com/ ይጠቀሳል

ፌክ ኢሜል አካውንት፡ ዌብሳይቶችን ስንጠቀም ኢሜይላችንን ተጠቅመን ሎግኢን እንድናደርግ ይጠይቃሉ ለዚህ አግልጎሎት ትክክለኛ ኢሜይላችንን ከመጠቀም አንድ ፌክ እና ብዙ መረጃዎቻችንን ያልያዘ ኢሜል አካውንት ፈጥረን በሱ መጠቀም ከመረጃ መንታፊዎች ያድነናል።
የብሮውሰር ሂስትርያችንን እና ኩኪያችንን ማጥፋት፡ የምንጠቀምበትን ብሮውሰር አይነት በመለየት የብሮውሰር ሂስትሪያችንን ማጥፋት። ሌላው ደግም ብሮውሰራችን ላይ third party cookieን ማጥፋት አሪፍ መፍትሄ ነው።
ምሳሌ፡ ክሮም ላይ third party cookieን ለማጥፋት እነዚህን መመርያዎች መከተል እንችላለን
1) ከላይ በቀኝ በኩል ሶስት ነጥብ መጫን
2) settingን መጫን ከዛ privacy and security መጫን
3) third party cookie የሚለውን በመጫን
4) Block third-party cookies የሚለውን በመጫን ዌኤባስይቶች ኩኪ እንዳዪዙ ማድረግ እንችላለን።

#techhelp
#online_privacy
#Cantech


ኢንተርኔት በምንጠቀምበት ጊዜ ማንነታችንን እንዴት መደበቅ እንችላለን (ክፍል 1)

ኢንተርኔት በምንጠቀምበት ጊዜ ድህረገጾች ማንነታችንን ይዘው ለመረጃ መንታፊዎች እንዳይሸጡብን፣ መንግስትም ሆነ ሌሎች ድርጅቶች የምንጠቀመውን ኢንተርኔት እንዳያገኙ፣ መረጃችን ለማስትወቅያ እንዳይውል እና በመሳሰሉት ምክንያቶች በኢንተርኔት ላይ የምናደርጋቸው ተግባራት እና መረጃዎቻችን እንዳይታዩ ልንፍልግ እንችላለን።

ኢንተርኔት ላይ የግል መረጃችን በሁለት አይነት መንገድ ይያዛል

አይፒ አድረስ፡ አይፒ አድረስ ኮምፒውተራችን የሚገኝበት አድራሻ ሲሆን መርጃ ከዌብ ሰርቨር ወደ ኮምፒውተራችን የሚመጣው ይህን አድራሻ በመጠቀም ነው። ይህ አድራሻ በኢንተርኒት ሰርቪስ አቅራቢዎች ማለትም በኛ ሀገር ኢትዮ ቴሌኮም አማካኝነት ከግል መረጃዎቻችን ጋር ለምሳሌ ስልክ ቁጥር፣ ኢሜይል ጋር ይያያዛል።

ኩኪስ፡ አነስ ያሉ የቴክስት ፋይሎች ሲሆኑ ዌብሳይቶችን በምንጠቀምበት ጊዜ በዌብ ብሮውሰራችን ሴቭ ይደረጋሉ። አገልግሎታቸውም የኢንተርኔት ግልጋሎታችንን እኛ እንደምኖደው አይነት እንዲሆን ለማድረግ ነው። ይህ ፋይል የሎግኢን መረጃዎቻችንን ጭምር ሊይዙ ይችላሉ።


ካስፐርስኪ በአሜርካ ታግዷል

በአለማችን ብዙ ተጠቃሚዎች ያሉት ካስፐርስኪ የአንቲ ቫይረስ ሶፍትዌር የሀገር ደህንነትን አደጋ ላይ ይጥላል በሚል ምክንያት በአሜሪካ ሀገር መታገዱ ተሰምቷል። እግዱ ተግባር ላይ ከዋለ በኋላ መተግበርያውን መሸጥ፣ መጠቀም፣ ላይሰንስ ማደስ ክልክል ይሆናል።

ካስፐርስኪ በራሽያ ዜጎች ተመስርቶ በዛው ሀገር ላይ ዋና መስርያቤቱን አድርጎ የሚሰራ ድርጅት ነው። አሜሪካም ይህን መተግበርያ ለማገድ እንደዋና ምክንያት ያነሳችው የራሽያ መንግስት ካስፐርስኪን ለራሱ አላማ የማዋል አቅም እንዳለው በማመኗ እና ልታደርሰው የምትችለውን የሳይበር ጥቃት ፍራቻ መሆኑን ገልጻለች። እንድሁም መተግበርያው ማሊሽየስ የሆኑ ሶፍትዌሮችን የመጫን አቅም እንዳለው ተገልጿል።
@slashgear

#technews
#Kaspersky
#Cantech


የአለም ሰውሰራሽ አስተወዕሎት ኤክስፖ በቻይና

ቻይና የ2024ቱን የአለም ሰውሰራሽ አስተውዕሎት ኤክስፖ ታዘጋጃለች። ይህ ኤክስፕ ከ4500 በላይ በሰውሰራሽ አስተውዕሎት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶችን የሚያሳትፈው ዝግጅቱ በአርቴፍሻል ኢንተለጀንስ፣ በሰውሰራሽ ሰልአስተውዕሎት የተሳሰሩ መኪናዎች፣ ሮቦቲክስ እና ኢንተለጀንስ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ይህ ኤክስፖ ከሰኔ 23 እስከ 26 የሚከናወን ሲሆን በአለማቀፍ ደረጃ በሰውሰርሽ አስተውዕሎት ላይ ተባብሮ መስራትን እና የውድድር መድርኮች ማመቻቸትን አላማ አድርጎ ይከናወናል።

የቻይና ሰውሰራሽ አስተውዕሎት ኢንዱስትሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በ2024 80 ቢሊየን ዶላር ደርሷል።
@cgtn

#technews
#AI_expo
#Cantech


ባይናንስ በተለያዩ ሀገራት እግድ እና ቅጣት እየተጣለበት ይገኛል

ባይናንስ በአለማችን ከሚገኙ ትላልቅ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ መተግበርያዎች ዋንኛው ነው። ከመቶ በላይ ሀገራት ላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ይህ መተግበርያ ክሪፕቶከረንሲዎችን እና ገንዘቦችን ለመገበያየት፣ ለፊውቸር ትራዲንግ እና ማርጂን ትራዲንግ ለመስራት ይጠቅመናል።

በህጋዊ ጉዳዮች፣ በብር ዕጥበት(money laundering)፣ ፍቃድ ሳያገኙ በመስራት በመሰሳሰሉት ምክንያቶች በአመሪካ፣ ቻይና ፣ ጀርመን እና ሌሎች 9 ሀገሮች እንዳይሰራ እግድ ተጥሎበታል። ከሰሞኑን ደግሞ በብር እጥበት ወንጀል ምክንያት በህንድ 2.5 ሚልዮን ዶላር በካናዳ ደግሞ 4.38 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ተጥሎበታል እንዲሁም። ከዚህ በፊት የቀድሞ የድርጅቱ ባለቤት ቻንግፔግ ከዚሁ ወንጀል ጋር በተያያዘ 4 ወር ታስረው እንደነበር ይታወቃል።

ይህ ገንዘብ የመገበያያ መተግበርያ በሀገራችን ብዙ ተጠቃሚዎችን እያፈራ ሲሆን ተጠቃሚዎች ገንዘብን በጥቁር ገበያ ወደ ዶላር ለመቀየር እና የተለያዩ ክሪፕቶ ከረንሲዎችን ለመገበያየት ይጠቀሙበታል። በሀገራችን መንግስት የትኛውንም የክሪፕቶ ከረንሲ መያዝም ሆነ መገበያየት መታገዱ ይታወሳል።
@reuters

#technews
#Binance
#Cantech


ሊንክዲን ስራ እንድናገኝ የሚረዳን ሰውሰራሽ አስተውዕሎት አስተዋውቋል

ስራ እና አሰሪን ለማገናኘት ጠቃሚ የሆነው ማህበራዊ ድህረገጽ ሊንክዲን ስራ ፈላጊዎች ሪዙሜ ለመስራት እና ስራ ለመፈለግ የሚረዳቸውን አርቴፍሻል ኢንተለጀንስ አስተዋውቋል።

ከነዚህ ሰውሰራሽ አስተውዕሎቶች መካከል የመጀመርያው በሊንክዲን ትምህርቶች ላይ መረጃ የሚስጥ እና በስራ ዘርፋችን ላይ የኤክስፐርት ምክር የሚሰጥ ኤአይ ነው። በተጨማሪ የሊንክዲን ሰርች ማድረግያም በኤአይ የበለጸገ ሲሆን ከተጠቃሚዎች ጋር የሚመሳሰሉ ስራዎችን ለመጠቆም ይጠቅማል። ድህረገጹን የሚጠቀሙ ስራ ፈላጊዎች ለተለያዩ የስራ አይነቶች ብቁ መሆናቸውን ያረጋግጣል።

ሊንክዲን በተለይ በክፍያ ለሚጠቀሙ ሰዎች ቻትቦት በመጠቀም የሚፈልጉትን ጥያቄ እንዲጠይቁ ለምሳሌ “ደሞዜን እንዴት መደራደር እችላለው” የመሰሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስችላቸዋል። የኤአይ ቻትቦቱ በስራ አያያዝ ዙርያ ስልጠና በሚሰጡ አስተማሪዎች የሰለጠነ ነው።
@cnet

#technews
#linkdin
#Cantech


ስታርሊንክ የኢንተርኔት አገልግሎት

ስታርሊንክ ሳተላይቶችን በመጠቀም የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት ኤለን መስክ በባለቤትነት በሚመራው ድርጅት ስፔስኤክስ የተቋቋመ ድርጅት ነው። የድርጅቱ ዋና አላማ የኢንተርኔት ፍጥነትን በመጨመር፣ ላተንሲን(መረጃ ከአንድ ኮምፒውተር ወደ ሌላኛው ለመድረስ የሚፈጀው ሰዐት) በመቀነስ በአለማቀፍ ደረጃ ተደራሽነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት ነው።

እስከአሁን ድረስ 6000 ሳተላይትችን ያመጠቀው ድርጅቱ በተለያዩ ሀገራት አገልግሎቱን መስጠት ጀምሯል። የስታርሊንክ ኢንተርኔት ሳተላይት በሚሰራባቸው አካባቢዎች ከሳተላይቱ ጋር ለመገናኘት የምንጠቀምበትን እቃ በመግዛት እና መተግበርያውን በማውረድ በቀላሉ ማገናኘት እንችላለን።

ስታርሊንክ አሁን ደሞ የኢንተርኔት አገልግሎቱን በስፋት ተደራሽ ለማድረግና ወጪውን ለመቆጠብ አዲስ በቤት ውስጥ የሚቀመጥ ትንሽዬ ዲሽ አስተዋውቋል። ይህን ዲሽ በመጠቀም የድርጅቱ ደምበኞች በ 5 ደቂቃ ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ።

#technews
#Cantech

Показано 20 последних публикаций.

7

подписчиков
Статистика канала