የክልሉን ሰላም በዘላቂነት ለመፍታት በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ የቋሚ ኮሚቴ አባላት አሳሰቡ።
አማራ ፖሊስ: ጥር 27/2017 ዓ.ም
የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕ እና አሥተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተላቸውን ተቋማት የሥራ አፈጻጸም እየገመገመ ነው።
ቋሚ ኮሚቴው የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ እና የተጠሪ ተቋማቱን የሥራ አፈጻጸም ገምግሟል።
የቋሚ ኮሚቴ አባላትም የጸጥታ ተቋሙ የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ እየከፈለው ያለው መስዋዕትነት ክብር የሚያሰጠው መኾኑን ገልጸዋል። በራስ አቅም የአካባቢን ሰላም ለማረጋገጥ እየተሠራ ያለው ሥራም የሚበረታታ ነው ብለዋል።
መስዋዕትነት እየከፈለ በሠራው ሥራ በክልሉ አንጻራዊ ሰላም እንዲመጣ አድርጓል ነው ያሉት። የጸጥታ ኀይሉ ለሕዝብ ሰላም እና ደኅንነት በጀግንነት እየታገለ ነው፣ ለዚህ ክብር ልንሰጠው ይገባል ብለዋል።
የጸጥታ ችግሩን ሕግ በማስከበር ብቻ ሳይኾን በእርቅ እና በይቅርታ ለመፍታት እየተሄደ ያለው ርቀትም የሚበረታታ ነው ብለዋል።
የጸጥታ ተቋሙ የክልሉን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመመለስ መስዋዕትነት ከመክፈል ባሻገር ውይይትን እንደ አማራጭ መጠቀም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ነው ያሉት።
ከሕዝብ ጋር ጥብቅ ቁርኝት መፍጠር እንደሚጠበቅበትም አንስተዋል። የክልሉን ግጭት በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ በመቋጨት ሕዝቡን ከተራዘመ ጦርነት መውጣት ይጠበቃል ነው ያሉት።
የሰላም እና የጸጥታ ተቋማት የሕዝብን መታገት፣ መገደል እና መጎዳት ማስተካከል እንደሚገባቸውም ገልጸዋል። የጸጥታ ኀይሉን መፈተሽ እና ታማኝነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።
ለሕዝብ የሚሠሩ እንዳሉ ሁሉ መረጃ የሚያወጡ ከመንግሥት በተቃራኒ የሚሠሩ የጸጥታ ኀይሎች አሉ ነው ያሉት።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/share/p/19qZHk8Zts/