🌴ለወጣቶች ምክር🌴


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


🔖ይህ የወንድማችሁ Mohammed ebnu seid ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ውስጥ ብዙ አይነት ትምህርቶችን ለማድረስ እና ለማስተማር እሞክራለሁ ።
ኢንሻአላህ ስህተቴን በቁርአን በሀዲስ ላረመኝ አላህ ይዘንለት እቀበላለሁ @Dear_ibnu_seid አድርሱኝ 🔖
አላህ ዱንያዬም አኼራዬንም እንዲያሳምርልኝ ዱአ አድርጉልኝ ።
@Lewetatoch_mekir 👈👈join ይበሉ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ሰራተኛን በየትኛውም መልኩ አትበድሉ። በምግብ አትቅጡ። አትምቱ። ልጆቻችሁ ሰራተኛ ላይ አይቅበጡ። በነሱ ላይ ከአላህ ጋር የሚያጣላችሁን ክፉ ቃል አትናገሩ። ራሳችሁ ላይ ቢሆን በማትፈልጉት መልኩ እንቅልፍና ረፍት አትንሱ። ከአቅም በላይ የሆነ ስራ አትስጡ። ሐቃቸውን ሳትሸራርፉ ስጡ።

ሶላት እንዲሰግዱ እዘዙ። የነሱ ሐቅ በናንተ ላይ ከሚኖር፣ የናንተ ሐቅ ቢቀር ይሻላል። ደካማ ላይ ጉልበተኛ አትሁኑ። ከውጭም ይሁን ከውስጥ ልክስክስ ወንዶች ወይም ጎረምሳ ልጆች ከነሱ ጋር እንዳይባልጉ ጥንቃቄ አድርጉ። ሰበብ አድርሱ።

በባህሪም ይሁን ሃላፊነትን በመወጣት በኩል ሁኔታቸው የማይጥም ከሆነ በነሱ ሰበብ ወንጀል ላይ ከመውደቅ በሰላም መሸኘት ይሻላል።


--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


ባሮቼ ሆይ! እኔ መበደልን በራሴ ላይ እርም አድርጌያለሁ፣ በመካከላችሁም እርም አድርጌያለሁና አትበዳደሉ

ከኢበኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል:-

ሙስሊም የሙስሊም ወንድም ነው። አይበድለውም፣ አያዋርደውም። ለወንድሙ ጉዳይ የቆመ (የሆነ) ሰው፣ አላህ ለርሱ ጉዳይ ይሆንለታል።

ለአንድ ሙስሊም ከጭንቀቱ መውጫ ያበጀ (ያስተነፈሰ ሰው)፣ አላህ ለርሱ ከቂያማ ቀን ጭንቀቶች መውጫ ያበጅለታል። የሙስሊም ወንድሙን ነውር የሸፈነ ሰው አላህ በእለተ ትንሳዔ (ቂያማ) ቀን ነውሩን ይሸፍንለታል።



በደልን እንጠንቀቅ!! ውጤቱ የከፋ ነው!! የተበዳይ ዱዓም ግርዶሽ የለበትም!!
በዳይ ከመሆን ተበዳይ መሆን ይሻላል ።

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


ወንድሜ ሆይ ብር ወንድም አይሆንም እናትም፣ አባትም፣ እህትም አይሆንም ለቤተሰቦችህና ለተቸገሩት ብር ለማውጣት አትሰስት።! ስጥ አሰጣጥህን አይቶ ይሰጥሃል። አከፋፋዩ ከላይ ነው።!

ሰርቸኮ ነው ያገኘሁት እያልክ አትኮፈስ ለማግኘትህ ሰብበ ማድረስህ ብቻ በቂ አይደለም አላህ ሲፍቅድ ነው የምታገኘው። በጅህ የያስከው ገንዘብ ፈተና መሆኑን አትርሳ። ከጌታህም እንዳያርቅህ ጥንቃቄ አድርግ። ከፈንህም ኪስ እንደሌለው አትርሳ። እንደሞትክ ሞባይልህን፣ ሃብትህን ይቀባበሉታል፣ አንተ ባካበትከው ሃብት እንኳ ለአባቴ፣ ለወንድሜ ሶደቃ የሚሆነው የውሃ ጉድጓድ ላስቆፍር ብሎ የሚያስብ አታገኝም።!

ከዱንያ ስካር ንቃ! ትሞታለህ ለማንም ዘላለም መኖርን አልተሰጠውም።!መሞቴ አይቀርም ስሞት ከኔጋር ምንድን ነው ወደቀብሬ አብሮኝ የሚሄደው እያልን ራሳችንን እንጠይቅ።

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


يَوْمَ تُقَلَّبُ وُجُوهُهُمْ فِى ٱلنَّارِ يَقُولُونَ يَٰلَيْتَنَآ أَطَعْنَا ٱللَّهَ وَأَطَعْنَا ٱلرَّسُولَا۠

ፊቶቻቸው በእሳት ውሰጥ በሚገለባበጡ ቀን «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ»

وَقَالُوا۟ رَبَّنَآ إِنَّآ أَطَعْنَا سَادَتَنَا وَكُبَرَآءَنَا فَأَضَلُّونَا ٱلسَّبِيلَا۠
ይላሉም «ጌታችን ሆይ! እኛ ጌቶቻችንንና ታላላቆቻችንን ታዘዝን፡፡ መንገዱንም አሳሳቱን፡፡

رَبَّنَآ ءَاتِهِمْ ضِعْفَيْنِ مِنَ ٱلْعَذَابِ وَٱلْعَنْهُمْ لَعْنًا كَبِيرًا

ጌታችን ሆይ! ከቅጣቱ እጥፍን ስጣቸው፡፡ ታላቅን እርግማንም እርገማቸው፡፡»

(አህዛብ)

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


«ወጣትነት ሳይበግርሽ የጌታሽን ትዛዝ ለምትፈፅሚዋ እህት ሆይ! ክብር ላንቺ ይሁን አላህ እስከመጨረሻው ያፅናሽ ።
   
--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


💬🌸የዕለቱ መልዕክቴ...
يَٰوَيْلَتَىٰ لَيْتَنِى لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًۭا
«ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፡፡"

🌸➲የምንልበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከማን ጋር እንደምንውል እናስብ!

➽አብረሻቸው የምትውያቸው ጓደኞችሽ ያንተን ማንነት ይወስናሉና ጥሩ አኼራሽን የምያስታውስሽ ጓደኛ ምረጪ!!


--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


አላህን ከፈራነው
የወደድነውን ሁሉ ይሰጠናል።!


ነገር ግን እሱን አስከፍተን የወደድነውን ነገር ብናገኝው እንኳ በረካ አይኖረውም።! ውሳኜያችን በጥንቃቄ የተሞላ ይሁን አላህን መቸም መሸወድ አንችልም።

አይ ብለን አግበስብሰን እናልፋለን ብለን ካሰብን አላህ አይረሳም የሆነ ሰአት ይይዘናል።! በልጃች ወይም በሃብታችን ወይም በጤናችን ወይም በቤተሰባችን።  አላያችሁም በሃብታቸው መጥፋት፣ መቃጠል፣መሰረቅ በልጃቸው መታገት እንዲሁም ታመውባቸው ካገር አገር ሲንከራተቱ... ይሄ ሁሉ የወንጀላችን ውጤትኮ ነው።! ሰለዚህ የበላይነትን ከፈለግን ሁሌም አላህን የፈራን እንሁን! በተውበትም ከጌታችን ጋር እንታረቅ። ተውበታችንንም አጥብቀን እንያዝ። ወንጀል ሲሰራም እያየን ዝም አንበል ይመለከተኛል ብለን ከዱአ ጋር ሰበቡን እናድርስ።

አንዳንዶቻችን ደግሞ በችግር ላይ በበሽታ ላይና በተለያዩ ጭንቀት ውስጥ ገብተን ነገር ግን ወንጀልን የማንርቅ አለን ምን እያሰብን ነው? ከአላህ የምንፈልግው ነገር የለም እንዴ ካለንበት መከራና ጭንቀት መውጣት አንፈልግም? ታዲያ ከአላህ ጋር ተጣልተን እንዴት ነው የምንፈልግውን ምናገኘው ብናገኘውስ እንዴት እርካትና ደስታን እናገኛለን? እንመለስ ወደ አላህ

ወደ አላህ አይመለሱምና ምሕረትን አይለምኑትምን? አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡   (አል ቁርዓን)

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


ወጣቱ ወዳጄ ሆይ…ለእህቴም!

የኢንተርኔት ዘመን ፈተናው ብዙ ነው። ሳትፈልግ የማትፈልገውን ሆነህ ራስህን ታገኛለህ። በዚህ አማላይ የሶሻል ሚዲያ ዘመን ሊተዋወቅህ የሚፈልግህ ሰው ሁሉ ንፁህ ልብ ይዞ የሚቀርብ እንዳይመስልህ፡፡
እርግጥ ነው ካንተ ሊያተርፍ የሚቀርብህ እንዳለ ሁሉ፤ እንደ እባብ ባንተ ላይ ተጠምጥሞ ሊጥልህ የሚቀርብህም አለ፡፡

አንዳንዱ ሰው የሚቀርብህ ዋናው ሸይጧን፤ አሊያም ደግሞ የሰው ሸይጧንም ልኮት ይሆናል፡፡ ያንን ሰው መጣል አልቻልኩም ጣልልኝ ብሎት፡፡

እና አንዳንዴ ሳታውቅ የዚህ ዓይነት ተልዕኮ ባለው ሰው እጅ ላይ ልትወድቅ ትችላለህ፡፡  ሳይፈልግህ የፈለገህ፤ ሳይወድህ የወደደህ የሚመስል ሰላይ ይመጣብሃል፡፡ በጊዜ ሂደት ሆነብሎ አታች እንድትሆን ያደርግሃል፡፡ ከዚያ ዉስጥህ መሸርሸሩን ሲያውቅ ድንገት ከአጠገብህ ዘወር ይላል፡፡  ወደማትፈልገው መንገድ በስንት ውትወታ ከመራህ በኋላ መሀል መንገድ ላይ ትቶህ ይሄዳል፡፡ ከዚያ እህእ ስትለው መልሶ እንደማያውቅህ ሰው እህእ ምን ላርግልህ ይላል፡፡

እንዲህ የወደቁ ብዙ ናቸው።ነቃ በል ነግሬሃለሁ፡፡ ሱንና የለበሰ ሁሉ ዲነኛ መስሎህ እንዳትበላ፡፡ ከሚያምሩ ኒቃቦችና ፂሞች ጀርባ ስንት ጉድ አለ መሰለህ፡፡ ከሱናና ዋጂቡ መገለጫ ባሻገር አሻግረህ ተመልከት፡፡ አቀራረብህን ቆጥብ፣ አታችመንትህን ቀንስ፡፡
ብዙ የዋህነት ይጎዳሃል፡፡ ጥቂት የዋህነትን ያዝና ብዙ ጥንቃቄን ምረጥ፡፡ ሰው ሁሉ የከተማ ሰው በሆነበት ዘመን የገጠር ልጅ አትሁን፡፡ በፍየል ዘመን በግ ከመሆን ተጠንቀቅ፡፡  ከወደቅክ በኋላ ሰው ስላንተ ምንም ጉዳይ የለውም ስልህ፡፡ አንተ ትልቁ ሰውዬ ብትወድቅ የዛሬ ሰው ምንም ዑዝር አይሰጥህም፡፡ በመጨረሻም ሊል የሚችለው ግዙፉ ዋርካ ወደቀ! ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ! ነው፡፡

ወዳጄ … የአንዳንድ ሰው ሴራው ከሸይጧንም በላይ ሆኗል፡፡ በገዛ እጁ ገዝግዞ ጥሎህ አያዝንልህም፡፡ ትንሽ ፈቅ ብሎ ቆሞ ይስቅብሃል፡፡ ጉድ ሠራሁት ይላል፡፡ ደግሞ የሴት ተንኮል መብዛቱ፡፡ የወንዱም እንደዚያው፡፡

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


Репост из: 🌴ለወጣቶች ምክር🌴
. 人 ★* 。 • ˚* ˚
. (__ _)*ኢድ ሙባረክ*★
. ┃口┃ *ተቀበለሏሁ ሚና*
. ┃口┃★ *ወሚንኩም *˛•
. ┃口┃★ 。* •★ 。•˛˚˛*
. ┃口┃ •˛˚˛* 人 •˛˚ *
. ┃口┃ .-:'''"''''"''.-.
. ┃口┃ (_(_(_()_)_)_)


🛍አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ 🛍
ውድ የተከበራችሁ #ለወጣቶች ምክር የቻናላችን ተከታዮች በሙሉ እንኳን #ለኢድ አል-አደሃ #በሰላም አደረሳችሁ 🛍🛍

🎁እንደዚሁም #ለአብሮነት ኢስላሚክ ግሩፕ ተከታታይ በሙሉ እንኳን #ለኢድ አል-አደሃ በሰላም #አደረሳችሁ 🎁

🎈እንደዚሁም በጣም የምወዳችሁ #ለሀገሬ ልጆች ወሎ #ባቲ ለምትኖሩ እና እንደዚሁም በመላው አለም ለይ ለምትኖሩ ሙስሊም እህት እና ወንድሞች #በሙሉ እንኳን #ለኢድ አል-ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ 🎈

🌙በመጨረሻ ለመላው #ኢስላምና ተከታይ እህት ወንድሞቼ እንኳን #ለኢድ አል-አደሃ በሰላም #አደረሳችሁ ማለት እፈልጋለሁ 🌙

🖊ወንድማችሁ mohammed ebnu seid ነኝ 🌹ከወሎ ባቲ🌹


በስልክህ ጉዳይ የውመል ቂያማ አላህ ፊት ትጠየቃለህ ።

እያንዳንዱ ስለፃፍከው ፅሁፍ
በስልክ ስለምትመለከተው ነገር
ሼር፣ ላይክ፣ ኮመንት ስላደረገው
ስለምትደዋወለውና ስላወራኸው
ስለእያንዳንዱ ትጠየቃለህ።

መልካም ስትሰራበት ከነበረ በጥሩ ትመነዳለህ። ክፋ ከነበረ ደግሞ የእጅህን ታገኛለህ።

የዛኔ ቁጭት በማይጠቅምበት ቀን ዋ! ጥፋቴ ምናለ ስልክ ባልነበረኝ ምናለ ሚዲያ የሚባል ባላወቅኩኝ ብለህ ከምትመኝና ከምትፀፀት ዛሬውኑ የስልክና የሚዲያ አጠቃቀምህ አስተካክል።

በስልክህ ሰበብ ጀነት ልትገባ አልያም የጀሀነም እሳት ልትወርድ መሆኑን አስበህ ምርጫህን አስተካክል።

‏سيسألك الله عن هذا الجهاز الذي بين يديك!


--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


የአደም ልጅ አብዘሃኛውን ስህተት የሚፈፅመው በምላሱ ነው !!

ከዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል አለ:-

የአደም ልጅ አብዘሃኛው ስህተቱ ያለው ምላሱ ላይ ነው። [ሶሂሁ'ል ጃሚዕ 1201 አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

ምላሳችንን አጥብቀን እንጠብቃት!!   
በምላስህ በአላህ ላይ አታሻርክባት!  
በምላስህ በሀይማኖትህ አዲስፈጠራ (ቢድዓ) አትናገርባት!   
በምላስህ የሰዎችን ስጋ አታላምጥባት!    በምላስህ ወሬ አታመላልስባት!
በምላስህ ውሸት አትናገርባት፣
በውሸትም አትመስክርባት፣ 
በምላስህ ሰውን ከሰው አታባላባት!!
በምላስህ ሰዎችን ወደ ሀራም ነገር አታነሳሳባት!!       በምላስህ…?!

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


ወዳጆቸ የጀሃነምን እሳትን አስበነው እናውቃለን !!

ፊት ለፊታችንኮ እሳት አለ! ወላሂ አደጋ ላይ ነው ያለንው! እድሚያችንም እየሮጠ ነው ሞትም እየመጣ ነው! የጀሃነም እሳት የበረታች ናት በሰውነታችን ሁሉ የምትመላለስ ናት ያውም የሰውነታችን ቆዳ እየተቀያየረ! ያ አላህ  አላህ ሆይ ከጀሃነም እሳት ጠብቀን!

ወዳጆቸ ከአላህ በራቅን ቁጥር ሀሳብ፣ ጭንቀትና መከራ ይወረናል! ነገር ግን ወደ አላህ በአንድ ስንዝርም ቢሆን በተመለስን ቁጥር ደስተኛ እንሆናለን! አላህ ደግሞ ያመፀውን ባሪያውን አይረሳውም! ታዲያ እንዴት እሱን የታዘዙትን ይረሳል ጥራት ይገባውና!
እስከመቸ ነው ወንጀል ላይ መዘውተራችን የአላህን ፍቅር አልነፈቀችም ልባችን? እ? አልናፈክም አንናፈቅሽም?

   እንመለስ ወደ አላህ ባረከላሁ ፊኩም

አላህ ሆይ ስለአንተ መልካም የሆነ አመለካከት አለን! አላህ ሆይ ከኛ መካከል የተጨነቀ ሰው ካለ ጭንቀቱን አስወግድለት!!

ከኛ መካከልም የታመመ ካለ ፈውሰው! ከክልከላዎችህ ለመራቅ የሚታገሉትንም አግዛቸው።

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


.    人  ★* 。 • ˚* ˚
. (__ _)*ኢድ   ሙባረክ*★
. ┃口┃ *ተቀበለሏሁ ሚና*
. ┃口┃★ *ወሚንኩም *˛•
. ┃口┃★ 。* •★ 。•˛˚˛*
. ┃口┃ •˛˚˛*   人  •˛˚  *       
. ┃口┃      .-:'''"''''"''.-.     
. ┃口┃  (_(_(_()_)_)_)


🛍አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ  ወበረካትሁ 🛍
ውድ የተከበራችሁ ለወጣቶች ምክር የቻናላችን ተከታዮች በሙሉ እንኳን #ለኢድ አል-ፊጥር   በሰላም አደረሳችሁ 🛍🛍

🎈እንደዚሁም በጣም የምወዳችሁ ለሀገሬ ልጆች   ወሎ ባቲ ለምትኖሩ እና እንደዚሁም በመላው አለም ለይ ለምትኖሩ ሙስሊም እህት እና ወንድሞች  በሙሉ እንኳን #ለኢድ አል-ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ 🎈

🌙በመጨረሻ ለመላው ኢስላምና ተከታይ እህት ወንድሞቼ እንኳን #ለኢድ አል-ፊጥር  በሰላም አደረሳችሁ ማለት እፈልጋለሁ 🌙

🖊ወንድማችሁ mohammed ebnu seid ነኝ 🗞 @Dear_mahammi    🌹ከወሎ ባቲ🌹

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


🌙 ረመዳን ሙባረክ ❤️ Ramadan Mubarak 🕌

ሙስሊም እህት ወንድሞቼ እንኳን የኸይር፣ የዒባዳ፣ የቁርዓን፣ የራህመት፣ የበረካ፣ የሰላት፣ የሰደቃ፣ የኡምራ፣ የመተዛዘን፣ የመረዳዳት፣ የመዋደድ፣ የይቅርታ ወር የሆነው ታላቁ የረመዳን ወር አደረሳችሁ አደረሰን።

ረመዷን ከመግባቱ በፊት ፣ ለበደሉኝ ፣ እኔን ለካዱ ፣ ለኔ ጥሩ ነገር ለማያስብ ሁሉ ፣ አላህ ይቅር ይበላቸው ፣ ምናልባት በዚህ ይቅርታ ጀነትን ብገባ!

ፆመው ከሚጠቀሙት አላህ ያድርገን !!

Obboloota Koo Amantaa Musliimaa hordoftan baga ji'a Kayirii ji'a Ibaadaa, Ji'a Qur'aanaa, Ji'a Rahmataa, Ji'a Barakaa, Ji'a Salaataa, Ji'a Sadaqaa, Ji'a Umraa, Ji'a Jaalalaa Ji'a Dhiifamaa Ji'a Kabajamaa Ramadaanaa Baga geessan Baga geenye! Warra Somee fayyadamu Rabbi nuhaagodhu!

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


Репост из: 🌴ለወጣቶች ምክር🌴
#ፊዳካ_አቢ_ወኡሚ_ያረሱላላህ
--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


መጥፎ በሆኑ በማይፈቀዱ ቪድዮዎች ፎቶዎች እና የወሲብ ፊልሞችን በመመልከት ለተፈተነ ትልቅ ምክር ‼️

             بــســم الــلــه الــرحــمــن الــرحــيمــ
                         الحمد الله رب العالمين

ሀይ እና ቀዩም የሆንከው ጌታዬ አላህ ሆይ!ሰማያትና  ምድርን አስገኚ የሆንከው አላህ ሆይ!የአለማቱ ጌታ  ሆይ!ልባችንን ከዚህ ፈተና አድንልን! አላሁመ አሚን

በመጀመሪያ ለኔና ለወንድሞቼ የምመክረው ነገር አይን ከአላህ የተቸረች ፀጋ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ነው።

ከአላህ ትላልቅ ፀጋዎች ውስጥ ነው። ከፀጋም በያሰከንዱ  የሚደጋገም ፀጋ ነው። ስለሆነም አላህን በመታዘዝ ላይ  መዋል ይኖርብናል። አላህን በማመፅ ላይ ልናውለው  አይገባም። የአላህን ፀጋዎች አላህን በማመፅ ያዋለ  ምንም እንኳን ፀጋዋ ብትኖርም ሊያጣት ደርሶዋል።

#ሁለተኛ! ረሳችንን ማስታወስ ያለብን ስለዚህች አይን አላህ ፊት  የምንጠየቅ መሆኑን ነው። በክፍልህ ውስጥ ተቀምጠህ  ማንም በሌለበት ማንንም ሰው አያይህም ከዛም ይህን  ልታይ ስታስብ አላህ ፊት የምትቆም መሆንክን  አስታውስ ስለዚህች አይን እንደምትተየቅ አስተውል።
ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል'ከናንተ ውስጥ በእሱና በጌታው መካከል  አስተረጓሚ ሳይኖር ጌታው የሚያናግረው ቢሆን እንጂ የለም። ወደ ቀኝ ይመለከታል የሰራውን ስራ እንጂ ሌላን አይመለከትም ወደ ግራም ይመለከታል የሰራውን ስራ እንጂ ሌላን አይመለከትም ወደፊትለፊቱ ሲመለከት ⇝እሳትን እንጂ ሌላን አይመለከትም'ብለዋል። ይህ እንደሚጠብቀው ያስታውስ።

#ሶስተኛ አላህ አብሮት እንደሆነ ያስታውስ አላህ የይሃል አላህ  እንደሚሰማውና አላህ እንደሚያውቅበት ያስታወስ አላህ  በመስማቱ በማየቱና በእውቀቱ ከሱጋር መሆኑን  ያስታውስ። ብቻህን ስትሆንና ይህን መጥፎ ቆሻሻ ፊልም  ስትመለከት አላህ አሁን እያዬ መሆኑን አስታውስ"(በዚህ ሁኔታ ላይ ቢይዝህስ?)"አላህ  በሁኔታህ አዋቂ ነው።'ብቻዬ ነኝ አትበል አላህ እያየህ  መሆኑን ለነፍስህ አስገንዝባት። በመቀጠልም ወንድሜ ሆይ!አላህን በመታዘዝም አላህን በማመፅም ግዜ   ያልፋል ግዜ አላህን ለሚታዘዙትም ለሚያምፁትም ቆሞ   አያቅም። ይህችን ትንሽዬ ደቂቃ በመታገስ ካሳለፍካት   ግዜህን ወንጀል ሳይፈፀምባት እንደምታልፍ ነፍስህን  አስታውሳት። ግን ይህን ወንጀል ከፈፀምክባት ግዜዋ   በወንጀል ታልፋለች። በልቦነህ ውስጥም መበላሸትን  አውርሳህ ታልፋለች ህይወትህንም ጭንቅ ታደርግብሃለች  የመጥፊያ ምክንያትም ልትሆንብህ ትችላለች። ልትሰጥ  የነበረውንም ፀጋ ልትከለክልህ ትችላለች። ነፍስህን በዚህ  አስታውሳት።

#በመቀጠልም...አይንህ ባንተ ላይ እንደሚመሰክርብህ አስታውስ  ባየሃቸው ነገሮች አይንህ አላህ ፊት ትመሰክርብሃለች። ስለሆነም አላህን ፍራ የሱን(የአላህን)ጉዳይም አክብር  ይህን ካደረክ በአላህ ሀይልና ፍቃድ ሸይጧንን ታሸንፋለህ። 

#በመጨረሻም ዱዓ በማብዛትም አደራ እላለሁ በወንጀል የተፈተነ ሰው የለሊቱን መጨረሻ ላይ(ዘጠኝ ሰአት አከባቢ)አላህ ፊት  ይቁምና ጌታዬ ሆይ!ማረኝ

ጌታዬ ሆይ!አንተ ሁኔታዬን ታውቃለህ ጌታዬ ሆይ!በዚህ  በሽታ ተፈትኛለሁ እንድጠላው አድርገኝ ። አላህ ሆይ !ምስራቅና ምዕራብን እንዳራራከው ሁሉ በእኔ እና በሱ(በወንጀሉ)መካከል ሰፊ መረራቅን አድርግ እያለ  መማፀን ይኖርበታል የምር ወደ አላህ መመለስ  የሰውዬው ሁኔታ ከሚስተካከልባቸው መንገዶች ዋነኛው መንገድ ነው........።

ባረከላሁ ፊኩም በዱዓችሁ አትርሱኝ

ሼር ማድረግ አንርሳ የአንድ ሰው የመመለስ ሰበብ መሆን ትልቅ ነገር ነው ብዙ እህትና ወንድሞች ከዚህ ስቃይ ለመውጣት ተቸግረዋል የችግሩን መፍትሄም በግልፅ ለመጠየቅ ስለምንፈራ ለብዙ ግዜ ተጎጂ እየሆን ነው።

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


«እህቴ ሆይ! አንቺ ምናልባትም አሁን በሕይወት እያለሽ የተሟላውን ሒጃብ ለመልበስና በአግባቡ ለመሸፋፈን ላትፈልጊ ትችያለሽ፡፡ ያው በግልጽ እንደምናየው ፀጉርሽን ከፍተሽ፣ ሽቶ ተቀባብተሸ ከናፍርሽን ሊፒስቲክ አጥግበሽ፣ ጡትሽን እሹለሽ፣ ደረትሽ ከፍተሽ፣ ዓይኖችሽን ተኳኩለሽ፣ እጆችሽንና እግሮችሽን ገላልጠሸ፣ የውስጥ ሱሪሽን እያሳየሽ ወሲብ ቀስቃሽ ጨርቆችን ለብሰሽ የትም እየታየሽ ነው፡፡ ከሩቁ ድብን ብላሽ የሰው ዓይን ውስጥም እየገባሽ ነው፡፡ በእውነቱ ቀበጦቹ ሒጃቢስቶች ዓይነ-ግቡ ለመባል ከፍተኛ ጥረትን እያደረጉ ነው፡፡ ነገር ግን አስታውሺ!  አንድ ቀን ከራስ ፀጉርሽ እስከ እግር ጥፍርሽ ድረስ በተገቢው ሁኔታ ትለብሻለሁ፡፡
ግና የዛኔ ወደመቃብር ነው የምትወርጂው፡፡ ስለዚህ ያንን ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሟላ ሒጃብን የምትለብሽበት ዕለት አታድርጊው፡፡ እባክሽን አሁኑኑ ልበሺው "ዞሮ ዞሮ ከቤት ኖሮ ኖሮ ከመሬት" ሲባል አልሰማሽም? ገላ ፈራሽ ነው፤ ውበትም ጠፊ ነው፡፡ አዎ! ምንም ያህል ብታምሪ፣ የቱንም ያህል ድብን ብለሽ የወንዶች ዓይን ውስጥ ብትገቢ አንድ ቀን ሟች ነሽ፡፡ እናም ከወዲሁ የኣኼራ ሕይወትሽን ገንቢ። በዱንያ ሳለሽ ለቀበርሽ ስንቅ ያዥ፡፡

ሙስሊሟ እህቴ ሆይ! ልክ እንደ ሉል ሁኚ፡፡ እንደሚታወቀው ሉል ውድ እና ብርቅ ነው፡፡ ለዚህም የበቃው የተቀመጠበት ቦታ ነው፡፡ ሉል ለፈላጊዎች እሩቅ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ውድ ሆኗል። አንቺም እንደዚያ መሆን አለብሽ፡፡ በሌላ በኩል እንደዘመኑ ቀበጥ ሒጃቢስቶች እዚያም እዚህ አትታይ፡፡ የትም የሚገኘው እኮ ድንጋይ ነው፡፡ እንደ አበባም እትሁኚ፤ ተጠቅመውብሽ ይወረውሩሻልና፡፡ እናም እንቺ ትክከለኛ ሒጃቢስት ሴት ሁኚ፡ በዚያን ጊዜ ሒጃብሽ መከበሪያሸ ይሆናል፡፡ ምንዳሽም ጀንት ይሆናል።

አረዓያዎችሽ ሰሃብያት እንጂ
የፊልም አክተሮች በፍፁም አይሁኑ!

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


የአደም ልጅ አብዘሃኛውን ስህተት የሚፈፅመው በምላሱ ነው !!

ከዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል አለ:-

የአደም ልጅ አብዘሃኛው ስህተቱ ያለው ምላሱ ላይ ነው። [ሶሂሁ'ል ጃሚዕ 1201 አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

ምላሳችንን አጥብቀን እንጠብቃት!!   
በምላስህ በአላህ ላይ አታሻርክባት!  
በምላስህ በሀይማኖትህ አዲስፈጠራ (ቢድዓ) አትናገርባት!   
በምላስህ የሰዎችን ስጋ አታላምጥባት!    በምላስህ ወሬ አታመላልስባት!
በምላስህ ውሸት አትናገርባት፣
በውሸትም አትመስክርባት፣ 
በምላስህ ሰውን ከሰው አታባላባት!!
በምላስህ ሰዎችን ወደ ሀራም ነገር አታነሳሳባት!!       በምላስህ…?!

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


ለወጣቶች ይህ ትምህርት ይድረስልኝ ...‼️

#መዓዘላህ አንድ ደሀ ወጣት ነበር ፦ በመንገዶች ላይ  እየተዘዋወረ ይሸጣል አንዲት ባዶ የሆነች ሴት ነበረች  ሀራምን ከ መስራት አትቆጠብም የሸይጧን ተላላኪ ነበረች አንድ ቀን በቤቷ አጠገብ አለፈ  በበሩ በኩል ብቅ ብላ ስለሸቀጦቹ ጠየቀችውና ነገራት እቃወቹን እንድታየ እቤት እንዲገባ ጠየቀችው ቤት ሲገባ በሩን ቆለፈችበትና ወደ ሀራም ጋበዘችው   መዓዘላህ! ብሎ ጮኸ። ጊዚያዊ ጣፉጭ ነገሩ ጠፍቶ ፀፀቱ በሚቀርበት ጊዜ የሚኖረውን ሁኔታ አስታወሰ  ዚና የሰራባቸው አካላቶች የተራመደባቸው  እግሮቹ የዳበሰባቸው እጆቹ የተናገረበት ምላሱ በእሱ ላይ የሚመሰክሩበትን ቀን አስታወሰ የእሳትን አቃጣይነትና የአላህን ቅጣት አስታወሰ

ዝሙተኞች በ እሳት ውስጥ እንዲንጠለጠሉ ተደርገው ከብረት በሆነ አለንጋ ይገረፋሉ ከዝሙተኞች አንደኛው ከቅጣቱ እንዲያድኑት ጮኾ ሲጠይቅ °መላኢኮች° አላህን ሳትፈራና ይቆጣጠረኛል ሳትል(ሀራም በመስራት) ስትስቅ ስትደሰት ስትፈነድቅ ይሄ አሁን ያሰማሀው ድምፅ የት ነበር? ይሉታል

ወጣቱ ረሱል (ሰለላሁ አለይኺ ወሰለም) እንዲህ ብለው የተናገሩትን ሐዲስ አስታወሰ።

🍃የሙሀመድ ህዝቦች ሆይ ወላሂ እኔ እማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ትንሽን ስቃችሁ ብዙ ባለቀሳችሁ ነበር።🍃

ነፍስያውም:–ስራና ትቶብታለህ አለችው። እሱም አዑዙቢላህ የጌታዪን ግርዶ እንዴት እዳፈራለሁ? የተከበረውና የተላቀው አላህ ከበላያችን ሆኖ እየተመለከተን የማትፈቀድልኝን ሴት እንዴት እመለከታለሁ እንዴት ከ ፍጡራን እየተደበቅን ፈጣሪ ፊት እናምፃለን? አለ። ወደ በሩ እየተመለከተና እንዴት መውጣት  እንደሚችል እያሰበ ዝም አለ አመፀኛዋ ሴትም: –ወላሂ የምፈልገውን ካልፈፀምክ ጮኼ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አደርግና ይህ ወጣት ዘሎ ቤቴ ገባብኝ እላለሁ የዚህ ጊዜ ሞት ወይም እስር እንጂ ሌላ አይጠብቅህም አለችው። ጥብቁ ወጣት ይንቀጠቀጥ ጀመር በ አላህ አስፈራራት ምንም አልመሰላት ይህን ሁኔታ ያየ ጊዜ ከሷ የሚገላገልበትን ዘዴ ማሰብ ጀመረ ከዚያም ሻወርና ሽንት ቤት እፈልጋለሁ አላት ። እሷም ወደ ሽንት ቤት አመለከተችው

መፀዳጃ ቤት ሲገባ ወደ መስኮቱ ተመለከተ ነገር ግን በመስኮቱ ማምለጥ አይችልም ከእሷ የሚላቀቅበትን መንገድ አሰላሰለ  ሠገራ ወደ ሚጠራቀምበት ሄደና ከሰገራው እያነሳ ልብሱን እጁንና ሰውነቱን መቀባት ያዘ ከዚያም እሷ ጋር ወጣያየችው ጊዜ ጮኸች እቃውን ፊቱ ላይ ወርውራለት ከቤቷ አባረረችው ቤቱ እስኪደርስ ድረስ ህፃናት ከኋላው ሆነው እብድ እያሉ ይጮሁበት ነበር።
ቤት ሲደርስ ነጃሳውን አስወገደና ገላውን ታጠበ  ከዚያም ቡኋላ ወጣቱ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ሰውነቱ የሚስክ ሽታ የሚስክ ሽታ ይሸት ነበር።

(ታሪኩን ኢብኑ ጀውዚ ጠቅሰውታል።)

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


ከስራዎች ሁሉ በላጩ አላህን በየትኛውም ቦታ ከልብ መፍራት ነው!!
———
ኢብን ረጀብ አል-ሀንበሊ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“ከስራዎች ሁሉ በላጩ በድብቅም በግልፅም አላህን መፍራት ነው። አላህን በድብቅ መፍራት ከኢማን ጥንካሬና ከነፍሲያና ከስሜት በመታገል የሚገኝ ነው። ስሜት በብቸኛነት ጊዜ ወደ ወንጀል ይጠራል፣ ለዚህም ነው ከከባባድ ነገሮች አንዱ አላህን በድብቅ መፍራት ነው ተብሏል።” [ፈትሁል ባሪይ 6/50]

በዚህን ጊዜ አላህን በግልፅ ማመፅ በዝቷል! ይህ የሆነውም አላህን በድብቅ መፍራት አላህ ያዘነላቸው ባሮቹ ሲቀሩ ብዙሃን ዘንድ መጥፋቱ ነው። አላህን በድብቅ መፍራት እየጠፋ ሲሄድ ወንጀል በግልፅ መሰራት ይጀምራል፣ ምክንያቱም አላህ ይጠብቀንና በድብቅ ወንጀል መስራት ከተጀመረ ቆይቷልና ነው።

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir

Показано 20 последних публикаций.