Brook News ብሩክ ኒዉስ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


Breaking News from all over the world about our beloved country Ethiopia.

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈትን ተከትሎ ምን ውሳኔ አሳለፈ ?

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ከዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አመራር አካላት ጋር የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሰራት ባለባቸው ስራዎች ዙሪያ ውይይት ማካሄዱን ገልጿል።


በመሆኑም ፦

➡ የዶ/ር አንዱአለም ልጆች ለከፍተኛ ትምህርት ሲደርሱ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በነጻ እንዲማሩ፤

➡ ባለቤቱ ከትምህርት ዝግጅት አንጻር በሲቪል ምህንድስና 2ኛ ዲግሪ ያላት እና ጥሩ አቅም ያላት በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል የምትቀጠርበት ሁኔታ እንዲመቻች፤

➡ ዶ/ር እንዱአለም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመሪያውን ቀዶ ጥገና የሰራው እሱ በመሆኑና ክፍሉን እስከ ህልፈቱ ድረስ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የነበረ በመሆኑ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ዋርድ በስሙ ዶ/ር አንዱአለም ዳኘ ቀዶ ጥገና ዋርድ ተብሎ እንዲሰየም፤

➡ የዶ/ር አንዱአለምን የአገልጋይነት ጥግ እንዲሁም ለሙያው የተሰጠ ተምሳሌታዊነቱን በቋሚነት ለመዘከርና ማስተማሪያ እንዲሆን በጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ሃውልት እንዲቆምለት፤

➡ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ School of Medicine ውስጥ በስሙ BDU Talent Scholarship እንዲቋቋም፤

➡ ለ40ኛ ቀኑ መታሰቢያ የሚደ
ርስ ስለ ዶ:ር አንዱአለም የህይዎት ታሪክ የሚዳስስ መጣጥፍ እንዲዘጋጅ ዩኒቨርሲቲው ወስኗል።

ውሳኔው ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡

#BDU

@tikvahethiopia




የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ መንገደኞች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል እንዲስተናገዱ አሳስቧል፡፡

አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ÷ ዛሬ ከቀኑ 6:30 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ውስጥ ወደ በረራ ይዞ መግባት ከሚከለከሉ ቁሳቁሶች መካከል ከመንገደኞች የሚሰበሰብ የሲጋራ መለኮሻ (ላይተር) ጊዜያዊ የማስቀመጫ ስፍራ ውስጥ ጭስ መከሰቱን አስታውቋል።

በዚህም ምክንያት ለመንገደኞች ደህንነት ሲባል ሕንፃው ለጊዜው አገልግሎት ማቋረጡን አመልክቷል፡፡

በመሆኑም በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎች የሚጓዙ መንገደኞች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራቸው እንዲሳፈሩ አሳስቧል፡፡

ከነገ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለመደው የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት የሚቀጥል መሆኑንም አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው መጉላላትም መንገደኞችን ይቅርታ ጠይቋል፡፡


ዶ/ር አንዷለም ዳኜ ከስራ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲመለስ በጥይት ተደብድቦ በመገደሉ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና መላው የሃገራችን ህዝቦች በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ፍትህን በመጠየቅ ላይ ናቸው።

" ፍትህን እንሻለን ! " በሚል የፍትህ ጥያቄ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።


የታመመች ሀገር የተጎሳቆለች፣
በሽታዋን አዝላ መዳኒት ቀበረች።


🍏Original iPHONE,Samsung አዳዲስ እንዲሁም ያገለገሉ ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ እና ያሎት ስልክ ላይ በመጨመር ከበቂ ዋስትና እና ጥገና ጋር እኛው ጋር ያገኛሉ ።

📢Telegram Channel
https://t.me/+rKw6vNZJp49kOWM0
ቀድመው ይደውሉ 👇
Contact us ☎️
+251911120707
+251904818881
📍ቦሌ መድሃኒአለም


Репост из: Brook News ብሩክ ኒዉስ
አዳዲስ መረጃዎችን ይፈልጋሉ?

በፕሮፌሺናል ጋዜጠኞች ተከፍቶ መረጃዎችን ተከታትሎ በሚዛናዊነት የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ ፡፡

ተማመኑበት ታተርፉበታላችሁ ተቀላቀሉት
👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0


‎[#ውርስ_ትርጉም]

‎“ምክር ለትግራይ ህዝብ በተለይም ለትግራይ ምሁራን ❗️”

‎በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደገለጽኩት የትግራይ መሬት እና ህዝብ የስልጣኔ መነሻ፣ ጋሻና የኢትዮጵያ መንግስት ጉልህ አስተዋጽኦ አድርጓል። የትግራይ መሬትም የመንግስት አስተዳደር፣ የአስተዳደር ስርዓት እና የሀገር እሴቶች መፍለቂያ ነው። የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን በመፍጠርና በመንከባከብ ውስጥ ያለው ሚና ጥልቅ መሆኑ እሙን ነው። የትግራይ ህዝብ በማይፋቅ ቀለም የተፃፈ ብሩህ ታሪክ ያለው ህዝብ ብቻ አይደለም፤ ከምንም በላይ ደግሞ የአገሩ ወዳጅ፣ የሰላምና የብልጽግና ወዳጅና ሥራ ወዳጅ ነው።

‎ትግራይ ብዙ ምሁራንን፣ የሀይማኖት አባቶችን፣ ፖለቲከኞችን እና ህዝባቸውንና አገራቸውን የሚጠቅሙ ታላላቅ የሀገር ሽማግሌዎችን አፍርታለች። የትግራይ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ የመንግስትን ምንነት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን ክልል መስርቷል። ይህ ብቻ ሳይሆን ክልሉ አደጋ ላይ በወደቀበት ወቅትም ቢሆን ግዛቱን በጥልቅ ዋጋ ያስጠበቀ ህዝብ ነበር። ለዚህም ነው ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመሆን ለሀገሩና ሉዓላዊነቱ ክብር ሲል ከደርቡሽ፣ ከግብፅ እና ከጣሊያን፣ በኋላም ከምዕራብ ወይም ከምስራቅ እንዲሁም ከሰሜን ወራሪ ሃይሎች ጋር ተዋግቶ መስዋእትነት የከፈለው። በተጨማሪም የዴሞክራሲ፣ የሰላምና የልማት ዋጋ ከሌሎች ወንድማማች ብሔሮች ጋር በመጋራት በኢትዮጵያ ልማት ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

‎ሌላው የትግራይ ህዝብ ባህሪ የሀገር ፍቅር ነው። የትግራይ መሬት የኢትዮጵያ መሰረት እና ማዕከል ሆኖ እንዳገለገለ ሁሉ የትግራይ ህዝብም ልብ በአገር ፍቅር ስሜት ተሞልቷል። የትግራይ ህዝብ በብልጽግናውም ሆነ በችግር ጊዜ ኪዳኑን ሳይክድ የአባቶቹን አደራ ጠብቋል። ማእከላዊ መንግስት በተለያዩ ዘመናት እንቅፋት ሲገጥመው ሀገሪቱን በማዳን እና ክፍተቶችን በመሙላት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ከአክሱማዊ መንግሥት ውድቀት በኋላ የተፈጠረውን ክፍተት በመዝጋት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

‎በዘመነመሳፍንት ጊዜ ክፍሎቹን በማስተካከል ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። አገራዊ አንድነትን በማረጋገጥ ረገድም ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የትግራይ ህዝብ ታታሪ ነው። የትግራይ ህዝብ ኮረብታ ላይ ወጥቶ ያርሳል፣ ድንጋይ ይቆርጣል፣ ፈልፍሎ ቤተመንግስት ይሰራል። ይህንን ግልጽ እና የታወቀ እውነታ ለማሳየት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገኝም። የትግራይ ህዝብ ትንሽ ሰላም በነበረበት ወቅት በንግድ፣ በግብርና፣ በህንፃ፣ በኪነጥበብ፣ በቴክኖሎጂ መስክ ያከናወኗቸው ተግባራት መንገደኞች የሚገነዘቡት ሃቅ ነው። ከዚህም በላይ በፈተና የማይናወጥ በመንፈስ የጠነከረ ሕዝብ ነው። እንደ አለመታደል ሆኖ ግን በተለይ ባለፉት መቶ ዓመታት በተለያዩ አጋጣሚዎችና ምክንያቶች በተለይም ከማዕከላዊ መንግሥት(ለአብነት ደርግ) ጋር ባለው ጠላትነት የትግራይ መሬት የጦር አውድማ ሆኗል፤ የትግራይ ሕዝብም የጦርነት ኢላማ ሆኗል። ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን መነሳት ያለበት ጥያቄ የትግራይ ህዝብ ባለፉት መቶ አመታት ከጦርነት ምን አይነት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ጥፋቶች አተረፈ? ብለህ ጠይቀህ። በዚህ ጊዜ አንድ አስተዋይ የትግራይ ምሁር ትግራይ እና ህዝቦቿ ከጦርነቱ የበለጠ ጥቅም አግኝተዋል ወይስ ጠፍተዋል ብሎ መጠየቅና መልስ ማግኘት አለበት። ሌላው ሊነሳ የሚገባው ጥያቄ ጦርነቶች ሁሉ ብቸኛው አማራጭ ነበር ወይ? ሌላ መፍትሄ አልነበረውም? የሚለው ጥያቄ መልስ ነው። እና ከአሁን በኋላ ጦርነትን ለመከላከል ምን የተሻለ ዘዴ ነው? ጥያቄውን መጠየቅ እና መልሱን ማግኘት አስፈላጊ ነው. አሳዛኙ ነገር የትግራይ ህዝብ የትላንት ቁስሉን ሳያገግም አሁንም በጦርነት ወሬ በፍርሃት እየኖረ ነው። እንዲህ ዓይነቱን አደጋ እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ተረጋግቶ መወያየት ያለበት ጉዳይ መሆኑ ከጠቢባን የተሰወረ አይደለም።

‎ስለዚህ የትግራይ ተወላጆች በፖለቲካ፣ በቢዝነስ፣ በደህንነት፣ በአካዳሚክ እና በሚዲያ እና በሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ ምሁራን እስካሁን የተከፈለው ዋጋ በቂ ነው፣ ከጦርነት ምንም ትርፍ የለም መንገዱን መጨረስ ያስፈልጋል። በተጨማሪም ከፌዴራል መንግስትና ከሌሎች ሃይሎች ጋር ያላችሁን አለመግባባት በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት እና በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ እንድትሆኑ አሳስባለሁ።

‎በፌዴራል መንግሥት በኩል በሁሉም ጉዳዮች ላይ በመወያየት፣ የሃሳብ ልዩነቶችን እንደ የአመለካከት ልዩነት ወስደን ስናበቃ በተግባባንባቸው አገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንድንሠራ የሚያደርግ ሁኔታ እንዳለ በመገንዘብ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ​​እንዲመለስ ተነጋግረናል። እንደገና አብረን እንድንሰራ በአጽንኦት አሳስባለሁ።

‎“የትግራይ ህዝብ ከትላንት ቁስሉ ሳያገግም ዛሬም በጦርነት ወሬ በፍርሃትና በሰቀቀን እንዲኖር በፍጹም ሊፈረድበት አይገባም።

‎ጥር 26፣ 2017 ዓ.ም




ገረሰሱት!

አርሰናል 5-1 ማን ሲቲ 🇬🇧
            #ኦዴጋርድ 2'  #ሃላንድ 55'
            #ፓርቴ 56'
            #ስኬሊ 62'
            #ሀቨርት 76'
            #ንዋኔሪ 90+3'


🛑 25% ብቻ በመክፈል ለውጥ ፈጣሪ ኮርሶችን እንደ Graphics design, video Editing, Digital Marketing, Upwork የምትወስዱበት የዘውድ ቴክ 4ተኛ ዙር ምዝገባ በብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሰረት ለጥቂት ጊዜ ተራዝሟል።

✅100% የስራ እድል
✅ጥራት ያለው ስልጠና በ professional አስተማሪዎች
✅አንዴ ከፍለው 4 ስልጠናዎችን የሚወስዱበት
✅ certificate ያለው

️ያሉት ቦታዎች ውስን ስለሆኑ አሁኑኑ ከታች ባለው የዘውድ ቴክ ቻናል ሊንክ ተቀላቅለው orientation ይመልከቱ በመቀጠልም እዛ ላይ ባሉት ስልክ ቁጥሮች መልዕክት መላክ ወይንም መደወል ይችላሉ።

📩ቻናል ሊንክ👇

https://t.me/zewdtech/43


ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ተገደሉ

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊት ሃኪም፣ ተመራማሪ እና መምህር እንዲሁም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ጠብቀው በተወለዱ በ37 አመታቸው በደረሰባቸው ድንገተኛ ሞት የተሰማንን መሪር ሃዘን እየገለፅን ለሟች ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን እንመኛለን።

ዶ/ር አንዷለም በዩኒቨርሲቲያችን፣ ብሎም በአገራችን አሉን ከምንላቸው በቁጥር ትንሽ የዘርፉ ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞቻችን ውስጥ አንዱ የነበሩ ሲሆን ከስራ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ በአጋጠማቸው ግድያ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሐኪማችን ላይ ያጋጠመውን ግድያ እና በተደጋጋሚ በዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ያልተገባ መሰል ድርጊት ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በጥብቅ ያወግዛል። በየትኛውም አካል ሊሰነዘር የሚችል ይሄን አይነት መሰል ድርጊትም ለአገርም ሆነ ለወገን አጉዳይ እንጅ አንዳች የሚጨምር ነገር እንደሌለ ሁሉም ሊገነዘበው የሚገባ ጉዳይ ነው።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ


በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጂቡቲ ድንበር አቅራቢያ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በደረሰ የድሮን ጥቃት ሰዎች ተገደሉ

ሐሙስ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እና ጂቡቲ ድንበር አቅራቢያ በደረሰ የድሮን ጥቃት ሰዎች መሞታቸውን እና መቁሰላቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ 

ጥቃቱ መጀመሪያ በሁለት አርብቶ አደሮች ላይ የተፈፀመ ሲሆን አንዱ ሲሞት አንዱ መትረፉ ታውቋል። በተጨማሪም 2 ሴቶች እና 5 ወንዶች በሌላ ጥቃት መገደላቸውን የመረጃ ምንጫችን ገልጸዋል፡፡

በኤሌዳአር ወረዳ ሂሉ እና ቲኪቦ ቀበሌ ሲያሪ ጣቢያ ሟቾችን ወደ ቤተሰብ ይዘው ሲመጡ በድጋሜ ህዝብ በተሰበሰበበት ጥቃት ተፈጽሟል ተብሏል።

"ባለን መረጃ መሰረት ጥቃት የፈጸመው የጅቡቲ መንግስት እንደሆነ እናምናለን" ብለው ለመሠረት ሚድያ የተናገሩት የመረጃ ምንጫችን ከዚህ ቀደም በጣቢያው ያሉ አርብቶ አደሮችን ከቦታው ለማስለቀቅ የጅቡቲ ወታደሮች ነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ተኩስ ይከፍቱ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡
ጥቃቱን ተከትሎ በአሜሪካ የሚኖሩ የአፋር ዲያስፖራ ማሕበር አባላት ባወጡት መግለጫ ድርጊቱን "ጨካኝ" በማለት አውግዘውታል።

የዲያስፖራ ማህበሩ ጥቃቱ የተፈጸመው በጂቡቲ መከላከያ ሀይል ድሮን መሆኑን ገልጾ በጥቃቱ ሲያሮ እና ኤሊዳር በተባሉ ቦታዎች 2 ወንድማማቾችን ጨምሮ አምስት ሰዎች መገደላቸውንና 3 ሰዎች ደግሞ በከፋ ሁኔታ በጽኑ መቁሰላቸውን በመግለጽ ድርጊቱን አውግዞ የሰላማዊ ዜጎች ግድያ እንዲቆም በመጠየቅ አለም አቀፍ ማህበረሰብ ማህበረሰብ፣ የሰብአዊ መብት ተሟቾችና መገናኛ ብዙሃን ትኩረት እንዲሰጡት ጠይቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ በኢትጵያም ሆነ በጂቡቲ መንግስት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡
MeseretMedia


ከአሜሪካ እና ከቻይና ፖሊሶች ጋር ውድድሩን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ስዋት ቡድን ልምምዱን በዱባይ ጀመረ

የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች ባዘጋጀቺው የዓለም አቀፍ የ2025 SWAT Challenge ላይ ለመወዳደር ወደ ዱባይ ያቀናው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ SWAT ቡድን ልምምድ እያደረገ ነው

የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች ባዘጋጀቺው የዓለም አቀፍ የ2025 SWAT Challenge ላይ ለመወዳደር ወደ ዱባይ ያቀናው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ SWAT ቡድን በአልሩዋይ ከተማ በሚገኘው የSWAT Challenge ማሰልጠኛ ማዕከል ልምምድ እያደረገ ይገኛል።

ውድድሩ እ.ኤ.አ የካቲት 1-5 እንደሚካሄድ ታውቋል።


ቀሲስ በላይ መኮንን በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ተቀጡ

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ የቀረቡ የግራ ቀኝ ማስረጃዎችን መርምሮ በዛሬው የችሎት ቀጠሮ በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወሰነ።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ቀሲስ በላይ መኮንን፣ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ፣ በኮሚሽን ስራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ እና አለምገና ሳሙኤል እንዲሁም የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ በተባሉ ተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ ቁጥር 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና የሙስና ወንጀሎች ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 2 እና ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ እና በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ ቁጥር 382 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፋቸውን ጠቅሶ ዝርዝር ክስ አቅርቦባቸው ነበር።

በዚህም ተከሳሾቹ ከአፍሪካ ህብረት ምንም አይነት የክፍያ ትዕዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ ላይ ተከሳሾች በተለያየ መጠን ክፍያ እንዲፈጸምላቸው የሚል አጠቃላይ የ6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሀሰተኛ የክፍያ ሰነድ በአንደኛ ተከሳሽ አማካኝነት ለባንኩ መቅረቡ ተጠቅሶ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።

በዚህ መልኩ የቀረበውን ዝርዝር ክስ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተከሳሾች ብቻ ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በአድራሻቸው ባለመገኘታቸውና በተደጋጋሚ ቀጠሮ ባለመቅረባቸው ለጊዜው ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል።

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ክሱ እንዲሻሻልላቸው ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ ክስ መቃወሚያ ነጥቦችን ፍርድ ቤቱ መርምሮ ወደፊት በማስረጃ የሚጣራ መሆኑን ገልጾ መቃወሚያቸውን አልተቀበለውም።

ከዚህም በኋላ ተከሳሾቹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው የዕምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ አጠቃላይ ሶስት ምስክሮችን አቅርቦ ምስክርነታቸውን አሰምቶ ነበር።

ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል መርምሮ በክሱ ዝርዝር የተጠቀሰው የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን በዐቃቤ ሕግ በማስረጃ ማረጋገጡን ጠቅሶ በአንደኛው ክስ ብቻ እንዲከላከሉ በሙሉ ድምጽ ብይን ሰጥቶ ነበር።

ሁለተኛውን ክስ በሚመለከት በሐሰተኛ ሰነድ የተፈጸመ ድርጊት መሆኑ በአንደኛውን ክስ ላይ መገለጹን ተከትሎ በሰበር ሰሚ ችሎት ትርጉም የተሰጠባቸው በተደራራቢነት የቀረቡና ተጠቃልለው ሊያስቀጡ የሚችሉ ድንጋጌዎች መኖራቸውን ፍርድ ቤቱ አብራርቶ ሁለተኛውን ክስ ውድቅ በማድረግ በአንደኛው ክስ ብቻ በከባድ አታላይነት ሙስና ወንጀል እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።

ሆኖም ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ በሰጠው ብይን የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው ማስተባበል አለመቻላቸው ተጠቅሷል።

በዚህም 1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን በሙሉ ድምጽ የጥፋተኝነት ፍርድ የተሰጠባቸው ሲሆን፤ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በአንድ ዳኛ የሀሳብ ልዩነት በአብላጫ ድምጽ ጥፋተኛ ተብለዋል።

የሀሳብ ልዩነት ያቀረቡት አንደኛው ዳኛ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት የባንክ ሂሳባቸው በመገለጹ ብቻ የወንጀል ተግባሩ በስምምነት ተፈጽሟል ለማለት አያስችልም የሚል የሀሳብ ልዩነት እንዳላቸው ጠቅሰው ልዩነታቸውን አሳይተዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት መርምሮ ዐቃቤ ሕግ ወንጀሉ የተፈጸመው በትብብር መሆኑን ጠቅሶ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ ይዟል።

በዚህም1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን ያቀረቡትን አራት የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕርከን 21 መሰረት በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት ደግሞ እያንዳንዳቸው አራት፣ አራት የቅጣት ማቅለያ አስተያየት በመያዝ በዕርከን 17 መሰረት በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

በፍርድ ቤቱ በተከሳሾች ላይ የተወሰነውን የጽኑ እስራት ውሳኔን የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እጃቸው ከተያዘ ጀምሮ ታሳቢ በማድረግ እንዲያስፈጽም ታዟል።

ዘገባው የፋና ሚዲያ ነው


የጥንቃቄ መልዕክት!
******************

• ስለ ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ምን ያህል ያውቃሉ ?

ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ስልካችን ላይ ከማህበራዊ ትስስር ድረ-ገፆች በምንጭናቸው መተግበሪያዎች አማካኝነት ወደ ስልካችን ሰርጎ የሚገባ ሲሆን እንደ ቴሌግራም፣ዋትስአፕ፣የመሳሰሉ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በስፋት እየተሰራጨ ጥቃትን የሚሰነዝር መተግበሪያ ነው፡፡
• ጉዳቱ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመረጃ ሥርዓት ደህንነት ክፍል ሰሞኑን ፋርማ ፕላስ (Pharma+) የተሰኘውን መተግበሪያ ጉዳት አምጪነቱን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ እንደገለጸው ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ከማህበራዊ ትስስር ገጾች አውርደን በምንጭናቸው ሌሎች መተግበሪያዎች ጋር በመለጠፍ ወደ ስልካችን ሰርጎ በመግባት የስልካችንን ስክሪን ማየት፤ አጭር የጽሑፍ መልዕክቶችን ማንበብ፣ ሀሰተኛ የመግቢያ ገጾቸን በማዘጋጀት የይለፍ ቃሎችን መመንተፍ እና የመሳሰሉ የግል መረጃዎችን የሚሰርቅ መተግበሪያ ነው፡፡

የፋይናንሻል ግብይቶችን ከተጠቂው እውቅና ውጪመፈፅሙ እና ስልካችን ላይ ተጭነው ካሉት መተግበሪያዎች ውስጥ መደበቁ ማየት ስለማንችል ለመከላከል በጣም አዳጋች መሆኑ ነው።

• እንዴት ራሳችንን ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ይጠብቃሉ

• ካልታመኑ ምጮቾች ማንኛውንም መተግበሪያ ስልኮት ላይ አይጫኑ፤
• በማህበራው ገጽ አማካኝነት የሚላክሎትን ማንኛውንም ማስፈንጠሪያ ወይም መተግበሪያ ምንነቱን ሳያረጋግጡ አይክፈቱ፤
• ብቅ ባይ (Pop up) ማስታወቂያዎችን ወይም አጠራጣሪ ገጾችን በፍጹም አይክፈቱ፤
• እንደ ጎግል ፕሌይ፣ አማዞን፣ አፕስቶር ወይም ሳምሰንግጋላክሲ ስቶር ጥብቅ የደህንነት ፍተሻዎችን የሚያደርጉ ይፋዊ የመተግበሪያ ማከማቻዎችን ብቻ ይጠቀሙ።
ትክክለኛ የስልክ መተግበሪያዎችን በመጠቀም እራስዎትን ይጠብቁ!


የፕሪሜርሊጉ ዳኛ ሜይክል ኦሊቨር የአርሰናልን ጫወታ ካሁን በኃላ እንዳይዳኝ ፊርማ እየተሰበሰበ ይገኛል።

መፈረም የምትፈልጉ 👇

https://www.change.org/p/prohibit-michael-oliver-from-refereeing-any-arsenal-matches


Репост из: Brook News ብሩክ ኒዉስ
ይሄን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ።



Показано 19 последних публикаций.