Buna Tech ቡና ቴክ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Технологии


Welcome to our Buna Technology Telegram channel
It's a channel where you find the amazing and new things about Computer and technology that you don't know in photo and writing, you get a variety of funny surprises and you get knowledge. Thanks 🙏

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Технологии
Статистика
Фильтр публикаций


የአሜሪካ መንግስት Deepseek'ን ከመንግስት ተቋማት መሳሪያዎች እያገደ ነው።

የአለማችንን የቴክኖሎጂ ስቶክ ማርኬት ከፍና ዝቅ ከማድርግ እስከ በረካታ አለማቀፋዊ ተጠቃሚዎችን ማግኘት ድረስ ስኬታማ የሆነው ቻይና ሰራሹ AI deepseek በአሜሪካ የመንግስት ተቋማት መሳሪያዎች ላይ እየታገደ ይገኛል።

ይህም የሆነበት ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው በሀገራዊ ደህንነት ምክነያት ነው ተብሏል።

Deepseek አሁን ላይ ከ20 ሚልዮን በላይ እለታዊ እና ከ30 ሚልዮን ወርሀዊ ተጠቃሚዎችም አሉት።

በተጨማሪም Deep seek'ን ከመረጃ ጥሰት ጋር በተያያዘ እንደ ጣልያን ያሉ ሀገራት መተግበሪያውን አግደውታል።


በሶላር ቻርጅ የሚያደርገው የinfinix ስልክ

አብዛኞቻችን ስልክ ስንገዛ ከምንጠይቃቸው ጥያቄዎች አንዱ የባትሪ ቆይታውን ነው። ይህም የአንድን ስልክ ተቀባይነት መወሰን ይችላል። ታዲያ ሰሞኑን infinixም ከዚህ ጋር ተያይዞ ጨዋታ ቀያሪ የሆነ ስልክ አስተዋውቋል።

ይህ ስልክ የፀሀይ ብርሀንን በመጠቀም ከሌሎቹ ስልኮች በተለየ ቻርጅ ማድረግ ይችላል። ከጀርባው በተገጠሙለት solar panels አማካኝነት ባትሪውን ይሞላል።

ይህ ስልክ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት ለማያገኙ ሰዎች ትልቅ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችልም ተገልጿል።

ነገር ግን ቻርጅ በሚያደርግበት ጊዜ ብዙ ጊዜ መፍጀቱ በበርካቶች ዘንድ ተቀባይነት እንዳያገኝ አድርጎታል።

ይህ ስልክ በሀሳብ ደረጃ ነው ያለው ማለትም ለገበያ አልቀረበም። ከዚህ ቀደምም infinix በርካታ ሀሳቦችን እያመነጨ ለስልክ ተጠቃሚዎች ያስተዋውቅ ነበር።

አስተያየታችሁን comment ላይ አካፍሉን።


#Bug
Account TakeOver Vulnerablity on Better-Auth(made by genius ethiopian dude)

https://castilho.onrender.com/better-auth


Telegram አዳዲስ አፕዴቶችን አስተዋውቋል።

ከነዛ ውስጥ contact list ውስጥ የሌለ አዲስ ሰው inbox ሲያደርግላችሁ ስልክ ቁጥሩ የት ሃገር እንደተከፈተ፣ መቼ እንደተከፈተ፣ share የምታደርጓቸው የጋራ ግሩፖች፣ እንዲሁም verified የተደረገ official account ከሆነ መጀመሪያ ያሳውቃችኋል።

ይህም ማጭበርበርን ለመከላከል ጥሩ ጅማሮ ነው።




አንድ የስልክ አምራች ኩባንያ Safety first ስልክ አምርቶ ለገበያ አቀረበ።

HMD የተሰኘው የቴክኖሎጂ ድርጅት የልጆችን ደህንነት ከግምት ውስጥ ያስገባ Fusion X1 የተሰኘ ስልክ አስተዋወቀ።

ይህ ስልክ በርካታ security Feature ያካተተ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፦

⚫ወላጆች የልጆቻቸውን የስልክ አጠቃቀም መወሰን እና ራሳቸው መመጠን ይችላሉ።
⚫ለልጆቹ ደህንነት ሲባል መጥፎ እና ለልጆች የማይመጥኑ ይዘቶችን መለየትና ብሎክ ማድረግ ይችላል።
⚫ለመደወልና text ለመላክ የወላጆቻቸውን ፈቃድ ማግኘት አለበት።
⚫በትምህርት አሊያም በእንቅልፍ ሰዓት የተመረጡ መተግበርያዎችን ብሎክ ማድረግ ይችላል።
⚫ወላጆች ልጆች ያሉበትን ቦታ መከታተልና እነሱ ከወሰኑላቸው ቦታ ሲረቁ ማሳወቂያ መልዕክት መላክ ካሉት features መካከል ይጠቀሳሉ።

በእንግሊዝ, በአሜሪካ, በጀርመን, በህንድ, በአውስትራሊያና በUAE በሚገኙ 25,000 ልጆችና ላይ HMD ያጠናው ጥናት ከሦስት ልጆች አንዱ private ፕላትፎርሞችን በመጠቀም መልዕክት እንደሚለዋወጥ እንዲሁም 40% የሚሆኑት ልቅ የሆኑ ይዘቶችን እንደሚመለከቱ አሳይቷል።

ጥናቱን በመመርኮዝም ስልኩ ላይ የተካተቱት ሁሉም አፕሊኬሽኖች ለመክፈትና ለመጠቀም የወላጅና የአሳዳጊ ፍቃድን ይጠይቃሉ።

HMD በያዝነው አመት የተለያዩ የደህንነት ፊቸሮችን የያዙ ሁለት የስልክ አይነቶችን ለመልቀቅ እቅድ እንደያዘ ተዘግቧል።

✍እነዚህ ስልኮች ለልጆች ምን ያህል ጠቀሜታ አለው ብላችሁ ታስባላችሁ?


Репост из: የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
ዋና ዋና የሳይበር ጥቃት አይነቶች

መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም በይነመረብ ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊመነትፉ ይችላሉ።
የሳይበር ጥቃት ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ሀገር ድረስ በርካታ ጥፋቶችን የሚያስከትል ነው። እነዚህ የሳይበር ጥቃቶች በተለያዩ የማጥቂያ መንገዶች የሚፈጸሙ ሲሆን በሳይበር ምህዳሩ በስፋት የተለመዱ የሳይበር ጥቃት አይነቶች የሚከተሉት ናቸዉ፥
1. የአገልግሎት መቋረጥ (denial of service - DOS):- ይህ የሳይበር ጥቃት አይነት የሲስተሞችን አቅም ባልተፈለገ ሁኔታ በማጨናነቅ ህጋዊ ተጠቃሚው አገልግሎት እንዳያገኝ በማድረግ የሚፈጸም የጥቃት አይነት ነው፡፡
2. የድረ ገጽ የዲፌስምነት ጥቃት (Defacement attack):- ሆን ተብሎ እና ሳይጠበቅ ጣልቃ በመግባት መደበኛ የኮምፒውተር ተግባርን የሚያውክ የጥቃት አይነት ነው፡፡
3. የማልዌር ጥቃት (Malware attack):- የተጠቂውን ድረ-ገጽ በሀሰተኛ ሰነዶች በመቀየር የሚፈጸም የጥቃት አይነት ነው ፡፡
4. ስፓም (Spam):- ብዛት ያለው እና አጥፊ ተልእኮ ያላቸውን ኢ-ሜይሎችን በመላክ የሚፈጸም የጥቃት አይነት ነው::
5. የፌሺንግ ጥቃቶች (Phishing attack):- የተለያዩ የማታለያ እና የማዘናጊያ ዘዴዎችን በመጠቀም አጭበርባሪዎች ከተጠቃሚዎች ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን ለመመዝበር የሚደረግ የማህበራዊ ምህንድስና ጥቃት ነው።


Open Ai GPT 4.5 የተሰኘ የchatgpt version ለቀቀ።

አሁን ላይ አለማችን ላይ ካሉ የላቀው AI model የተባለው ይህ ሞዴል ከበርካታ features ጋር የቀረበ ሲሆን ከነዚህም መካከል፦

⚫ይህ model ከሌሎቹ ሞዴሎች በተሻለ መልኩ ሰልጥኗል/ተምሯል።
⚫እንደ ትርጉም-የለሽ መልሶች ያሉ አንዳንድ አላስፈላጊ ይዘቶች በከፍተኛ መጠን ተቀርፈውበታል።
⚫የሚሰጣቸው ምላሾች በከፍተኛ ሁኔታ ሰዋዊ እንዲሆኑ ተደርገዋል።

⚫ከፍተኛ ችግርን የመፍታት/problem solving ክህሎት ያለው gpt 4.5 በረቀቁ የmachin learning ዘዴዎች የሰለጠነ ሲሆን ይህም ከተፎካካሪ Ai chat bots ጋር ብልጫ እንዲኖረው ሊያድርግ ይችላል የሚሉ አስተያየቶች እየሰነዘሩ ይገኛሉ።

ይህንን ሞዴል chatgpt pro ተጠቃሚዎች መሞከር እንደሚችሉም ተገልጿል።

ምን አዲስ ነገር እንዳለው ሙሉ ፊቸሩን white paper ላይ ማንበብ ትችላላችሁ።
https://cdn.openai.com/gpt-4-5-system-card-2272025.pdf


ጥንት በአባቶቻችን ዘመን ታሪክ ለመጻፍና ምርጥ ግዜ ነበር ከጥንት ቀጥሎ ግን
ምርጡ ግዜ አሁን እና አሁን ነው ፡፡
እኛም የተረክብነውን ታሪክ ዘመኑ በሚጠይቀው ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለትውልድ እናስተላልፍ
አደራችንን እንወጣ ፡፡

በመጨረሻም አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ በማድረግ እናሳካው ዘንድ ከጎናችን እንዲቆሙ እንጠይቃለን ፡፡
ጌዴኦን ይጎብኙ (Visit Gedeo)


የኮምፒውተራችሁ Browser ላይ በዚህ መልኩ password save ታደርጋላችሁ?

ኮምፒውተራችሁን የሚጠቀም ማንኛውም ሰው በቀላሉ ፓስወርዳችሁን ሊያውቀው እንደሚቻል ታውቃላችሁ? በጣም በቀላሉ!!


አሁን ከሁለት ደቂቃ በፊት የማዘር ጀበና ተሰበረ።

ተፈጸመ..

' ' ሄደ ሄደ ወደ አባቱ' ' 😬


ጥንት በአባቶቻችን ዘመን ታሪክ ለመጻፍና ምርጥ ግዜ ነበር ከጥንት ቀጥሎ ግን
ምርጡ ግዜ አሁን እና አሁን ነው ፡፡
እኛም የተረክበውን ታሪክ ዘመኑ በሚጠይቀው ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለትውልድ እናስተላልፍ
አደራችንን እንወጣ ፡፡
በመጨረሻም
አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ በማድረግ እናካው ዘንድ ከጎናችን እንዲቆሙ እንጠይቃለን ፡፡
ጌዴኦን ይጎብኙ (Visit Gedeo)


Dear Cyber Warriors🔥,

እንኳን ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና ነጻነት ተምሳሌት ለሆነው የ129ኛ የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ቀን በሰላም አደረሳችሁ !

Ethiopia Needs to be Safe on the CyberSpace too, That is Our Responsibility


"ጣልያን በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ ሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ። አምላክ ሀያላን ረድቶኝ ፈጀሁት። ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ!"

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ለፈረንሳዊዉ ሙሴ ሞንዶን ከፃፉለት የምስራች ደብዳቤ የተገኘ ቃል ነዉ።

አንኳን ለሰው ልጅ መኩሪያ ለሆነው የአድዋ ድል በሰላም አደረሳችሁ።

🔥🔥የካቲት 23, 1888 ዓ.ም

#Share_x5
#Join
@bunatech
@bunatechdiscussion


Microsoft Skype የተሰኘውን ፕላትፎርም ሊዘጋ ነው።

ከAugust 29, 2003 ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ የበረው Skype ከ21 አመት በኋላ ማለትም በmay 5, 2025 ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱ ሊቋረጥ ነው።

Microsoft ይህንን ፕላትፎርም በ2011 $8.5 billion አውጥቶ ቢገዛውም አሁን አሁን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተበለጠ መጥቷል።

የተጠቃሚዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱና Teams የተሰኘው የmicrosoft ፕላትፎርም ይበልጥ ውጤታማ መሆኑ ለskype መዘጋት እንደምክነያት ይጠቀሳሉ።

የskype ተጠቃሚዎችም skype ላይ ያላቸውን chat historyና መረጃዎች ወደ Microsoft Teams ማዘዋወር ይችላሉ ተብሏል።

በርካቶቻችን ለመጀመሪያ ጊዜ video call ከማውራት ጀምሮ በርካታ ትዝታዎች በዚህ ፕላትፎርም ላይ አሉን።

በዚህ መረጃ የተሰማችሁን አሳውቁን።

©bighabesha_softwares


ስልካችሁ SAMSUNG ከሆነ ያለበትን እያንዳንዱን ችግር ቼክ የምታደርጉበት app
Samsung members

Play store ላይ ስለማታገኙት በዚህ ሊንክ ማውረድ ትችላላችሁ።
https://t.me/big_habesha/287

ስለ አጠቃቀሙ ከደቂቃዎች በኋላ TikTok ላይ video post አደርጋለሁ።


Репост из: የዲላ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ፣

ካራት የካቲት 19/207 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማና በቀሪ ግማሽ  ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮው ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አቶ ተካልኝ አክለውም ቢሮው በክልሉ ያሉ ዞኖች በዘርፉ ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖራቸው የተጠናከረ የድጋፍና ክትትል ተግባራትን ማከናወኑን የገለፁ ሲሆን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በአንዳንድ ዞኖች  በጥንካሬ እየተመራ መሆኑን እና በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በሚገባ እየተመራ ባለመሆኑ ኢኒሼቲቩን ለማሳካት በጉዳዩ ዙሪያ መምከር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እመቤት ወንድሙ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ወቅቱን የጠበቀና በቴክኖሎጂ የዳበረ ሀገርን ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።

ቢሮው በክልሉ ዞኖች የዲጂታል ቴክኖሎጂን ለማስፋፋትና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ  በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን እንደ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በመስክ ምልከታ ማረጋገጣቸውን ወ/ሮ እመቤት ተናግረዋል።


Репост из: Biruk Afework
Welcome to My Channel!

Join me as I share insights from my work and personal life, including:

Work Projects

Personal Experiences

Milestones  Achievements

Inspirations  Motives

Book Reviews

Challenges  Failures

Lessons Learned Along the Way

Expect valuable recommendations on resources, engaging QA sessions, and exciting guest features. Let’s build a supportive community together as we explore our journeys.

Contact Me :@Biruk_Buraa

Join me: here
https://t.me/BirukAfework


Adobe Photoshop በSamsung Galaxy ስልኮች ላይ መስራት ሊጀምር ነው

ዝነኛው የፎቶ ማቀናበሪያ ሶፍትዌር Adobe Photoshopን ከአንዳንድ ገደቦች ጋር በስልክ መጠቀም ሊቻል ነው።ይህም ለጊዜው የታቀደው በgalaxy ስልኮች ላይ ነው።

ይህ መተግበሪያ በርካቶች ከሚውቁት የተለየ ሲሆን ለተጠቃሚዎችም ከዴስክቶፕ version አንፃር ቀላል እና ለአጠቃቀም ምቹ ነው።

የዴስክቶፕ versionኡን ሙሉ በሙሉ ባይተካም መሰረታዊ የሆኑ edits ለማድረግ ያስችላል።

አሁን ላይ ካሉት የስልክ editing softwares በእጅጉ የተለየ ነው የተባለው ይህ መተግበሪያ ብዙ በAI የተደገፉ features እንደሚያካትትም ተገልጿል።

በዚህ ሀሳብ ዙሪያ አስተያየታችሁን አካፍሉን።


Meta ይቅርታ ጠይቋል።

ከትናት ጀምሮ የሚረብሹ የተለያዩ ቪዲዮዎች  reels ላይ በመምጣታቸው ምክንያት ብዙዎች X ላይ በመውጣት ሲነጋገሩበት ነበር። ይህንንም ችግር አሁን እንዳስተካከለው Meta አስታውቋል። በይፋም ይቅርታ ጠይቀዋል።

እኔ እራሴ check እንዳደረኩት Instagram reels ላይ ቪዲዮዎች ቢስተካከሉም የተለያዩ ችግሮች (bugs) ግን አሁንም አሉ።
ለምሳሌ
⚫ሁለት ወይም 3 ጊዜ scroll ካደረጋችሁ በኋላ scroll ማድረግ አትችሉም stack ያደርጋል።
⚫አንዳንድ ቪዲዮዎች ድምፃቸውን መዝጋት አትችሉም። አፕሊኬሽኑን ብትዘጉት እራሱ ድምፁ አይጠፋም። ስልካችሁን restart ወይም ዳታ እያበራችሁ ማጥፋት ይኖርባችኋል።

እናንተ ምን አስተዋላችሁ?

Показано 20 последних публикаций.