🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ቻናሉ ሕጎችንና የፍ/ቤት ዉሳኔዎችን ያጋራል። አጫጭር የሕግ ማብራሪያዎችንና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ጠበቃ ካሊድ ከበደ እና ጠበቃ አማረ እሸቱ
በማንኛዉም የፌዴራል እና የክልል ፍ/ቤት ጠባቃና የሕግ አማካሪ
ስልክ- 0935439820
ኢሜይል- khalidbinkebe@gmail.com

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


235739 (3).pdf
644.0Кб
አከራካሪዉ የገጠር መሬት ይዞታ ተጠሪ እና የአመልካች ልጅ የስር ተከሳሽ ጋብቻቸዉን ሲፈጽሙ አመልካች በጎጆ መዉጫነት በምስክሮች ፊት እንደሰጧቸዉ በሕግ ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን የተሰጣቸዉ የወረዳ ፍርድ ቤት እና ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያረጋገጡት
ፍሬ ነገር ነዉ፡፡የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔ የሰጠዉም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በማስረጃ ያረጋገጠዉን ይህንኑ ፍሬ ነገር መሰረት በማድረግ ነዉ፡፡የስጦታ ዉል በተለይም በልማድ የዳበረዉ
በየአካባቢዉ ማሕብረሰብ ለጎጆ መዉጫነትነት ተብሎ የሚሰጥ የገጠር እርሻ መሬት የተለየ ፎርም እንዲኖረዉ የሚያስገድድ ድንጋጌ በወቅቱ ተግባራዊ ሲሆን በነበረዉ በኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 ላይ አልተመለከተም፡፡በዚህ መልኩ በሕጉ ጥብቅ ፎርማሊቲ ያልተደነገገበት ምክንያት ይህ እሴት ያለዉን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጠቀሜታ ከግምት በማስገባት ጥብቅ ስርዓት መከተል አስፈላጊ እንዳልሆነ በማሰብ ነዉ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ለጎጆ መዉጫ ተብሎ የሚደረግ የገጠር መሬት ስጦታ የተለየ የዉል ፎርም እንዲኖረዉ ሕጉ የግድ የሚለዉ አለመሆኑን በሰ/መ/ቁጥር 107840፣ 197998፣206535 እና ሌሎች መሰል መዛግብት ላይ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ከዚህም የምንገዘበዉ ከገጠር መሬት
ይዞታ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በተለይም የባለይዞታዉ ልጅ ወይም ሌላ የባለይዞታዉ የቤተሰብ አባል ትዳር
ሲይዝ ለመተዳደሪያ የሚሆን በተለምዶ ለጎጆ መዉጫ ተብሎ የሚደረግ የመሬት ስጦታ ጥብቅ የሆነ የአጻጻፍ ስርዓት ወይም የስጦታ ዉል ፎርም ባያሟላም በየማህበረሰቡ የዳበረዉን ልማድ እና ጠቃሚ እሴት ከግምት በማስገባት ሕጋዊ ዉጤት እንዲኖረዉ ማድረግ ተገቢነት ያለዉ ስለመሆኑ ነዉ::


Репост из: ስለ ህግ
#Interesting Decision !!
አባትነትን የመካድ ክስ ቀርቦ ወይም ልጅ አይደለም የተባለ ሠው ጋር በፍ/ቤት በሚደረግ ክርክር የዘረ መል ሳይንሳዊ ምርመራ/DNA/ እንደማስረጃ ከቀረበ የዘረመል ምርመራው ከሶስተኛ ወገን ጋር ወይም ከወንድምና ከእህት ጋር የተደረገ ከሆነ ከ3ኛ ወገን ጋር በተደረገ የዲ.ኤን.ኤ መሠረት አይመሣሰልም የሚል ውጤትን ተመስርቶ ልጅ አይደለም በሚል የሚሠጥ ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ነው ሲል የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሠሚ ችሎት በመ/ቁ:- 245455 ግንቦት 28 ቀን 2016ዓ.ም በተሠጠ ውሳኔ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ተሰጥቷል።
የሠበር ችሎቱ ልጅ አይደለም ለማለት አባት አይደለህም ከተባለው ሰው ላይ ወይም ጋር የተደረገ ቀጥተኛ የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ ነው አግባብነትም ተገቢነትም ያለው ማስረጃ በሚል ደምድሟል።


Репост из: Dereje Tariku Law Office
138497.pdf
1.1Мб
182136.pdf
1.7Мб
፨ ሰ.መ.ቁ. 182136 [ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም]

፨ በተከራካሪው የተወከለው ጠበቃ ሌላ ችሎት ስለተደረበበት ክርክሩ በሚሰማበት ቀን መቅረብ ባለመቻሉ መዝገቡ ከተዘጋ እንደነገሩ ሁኔታ በቂ ምክንያት በመሆኑ የተዘጋው መዝገብ ሊከፈት ይገባል።

በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.74 [2] ደንጋጌ መሰረት “በቂ ሆኖ የሚገመት እክል” ምን እንደሆነ የተመለከተ ባይሆንም አመልካች ቀጠሮ ለመቅረት የቻለዉ በምን ምክንያት እንደሆነ አጠቃላይ ሁኔታዉን መመርመር የሚያስፈልግ ሆኖ፣ አመልካች በራሱ ጉድለት ወይም ቸልተኛነት ቀጠሮዉን ሳይከታተል ቀርቶ ካልሆነ በስተቀር፣ ፍትሕ የማግኘትና የመከራከር መብት ከግምት በማስገባት አመልካችን የገጠመዉ እክል እንደበቂ ምክንያት በመውሰድ ለተጠሪ [መዝገቡ የተዘጋው በክልል ሰበር ችሎት በነበረው ክርክር ነው] ተገቢ ኪሳራና ወጪ በማስከፈል፣ የተዘጋዉ መዝገብ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲሰማ መድረጉ አግባብ ነዉ። በመሆኑም አመልካች ክርክሩን በጠበቃ ለማካሄድ ወስኖ በሕጉ አግባብ ተገቢዉን ዉክልና ሰጥቶ እያለ ጠበቃዉ ችሎት በሚሰጠዉ ቀነ ቀጠሮ ተገኝቶ አመልካችን ወክሎ ተገቢዉን ክርክር የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል። ነገር ግን ጠበቃ የተለያዩ ደንበኞች ሊኖሩት ስለሚችል ፍ/ቤት በሚሰጠዉ ቀነ ቀጠሮ በተቻለ መጠን ለደንበኞቹ ተገቢዉን የጥብቅና አገልግሎት መስጠት በሚያስችለዉ አግባብ አጀንዳዉን አስማምቶ ቀጠሮ እንዲያዝለት ለፍ/ቤቱ ማመልከት ይጠበቅበታል። ይህም ሆኖ ቀጠሮ ተደራርቦበት በአንድ ጊዜ በተለያዩ ችሎቶች የሚቀርበበትን እድል በማዛባቱ ምክንያት የባለጉዳዩ መዝገብ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ የህጉ ድንጋጌ መሰረት ተዘግቶ እንደሆነ፣ አጠቃላይ የነገሩን ሁኔታ በመመርመር፣ የአመልካች የመከራከርና ፍትሕ የማግኘት መብት ታሳቢ በማድረግ መዝገቡ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲሰማ ማድረጉ ተገቢ ነዉ።


Репост из: አለሕግAleHig ️
#የውርስ_ንብረት በሆነ ጊዜ ክርክር መኖሩን ቢያውቁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ አንቀጽ #358 መሰረት የማቅረብ መብት ያላቸው ስለመሆኑ የተሰጠ የሕግ ትርጉም


230493 (2).pdf
881.9Кб
የተከራየ መኪና ተከራይ እጅ እያለ በሌላ ሰዉ ንብረት ላይ ጉዳት ካዳረሰ ለደረሰዉ ጉዳት ተጠያቂዉ ተከራይ ብቻ ነዉ። ስ/መ/ቁ 230493 ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም


ሽልማት ያለው ጥያቄ
***
👉የተከሳሽ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያ በስር ወረዳ ፍርድ ቤት ተቀባይነት አግኝቶ የከሳሽ ክስ በይርጋ ቀሪ ቢደረግ እንዲሁም

👉ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤት ክሱ በይርጋ ቀሪ ሊሆን አይገባም በሚል መዝገቡን ወደ ስር ፍ/ቤት በነጥብ ቢመልሰው፤

👉"ተከሳሽ በዝህ የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ወደ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረብ ያለበት ጊዜ መቸ ነው?"

ሀ/ ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ውሳኔ በሰጠ (እንደጉዳዩ አይነት) በ2 ወይም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ?

ለ/ የስር ወረዳ ፍ/ቤት (በነጥብ በተመለሰለት አግባብ) በመዝገቡ የፍሬ ነገር ጉዳይ ላይ ውሳኔ እስኪሰጥ ጠብቆ (እንደጉዳዩ አይነት) በ2 ወይም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ?

🔥ቀድሞ ከነማብራሪያው (ሰበር የሰጠውን የህግ ትርጉም ጨምሮ) ለመለሰ የ15 ብር ካርድ እንሸልማለን🔥
https://t.me/khalidkebede


የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ውድቅ የተደረገበት ተከሳሽ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ? (ጠበቃ ካሊድ ከበደ)
***
ፍ/ቤቱ ከሳሽ ያቀረበውን ክስ እና ተከሳሽ ያቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት በአንድ ላይ ሲያከራክር:-

👉ተከሳሽ ያቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ከሳሽ ባቀርበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያ መሰረት ውድቅ አድርጎ ከሳሽ ወዳቀረበው ክስ ፍሬ ነገር ጉዳይ በማለፍ ግራ ቀኙን ለአንድ ዓመት ያክል ካከራከረ እና መዝገቡን ከመረመረ በኋላ ውሳኔ ሰጠ ብንል፤

"👉ተከሳሽ ፍ/ቤቱ ከአንድ ዓመት በፊት በሰጠው ብይን ውድቅ ባደረገበት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ (ጉዳይ) ላይ ለበላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረብ የነበረበት/ያለበት ጊዜ መቸ ነው?"

ሀ/ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ውድቅ በማድረግ ብይን በተሰጠ እንደ ጉዳዩ ዓይነት በ2 ወር ወይም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ?

ለ/ ፍ/ቤቱ ከሳሽ ባቀረበው የፍሬ ነገር ጉዳይ ላይ ውሳኔ በሰጠ እንደ ጉዳዩ ዓይነት በ2 ወር ወይም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ?

መልሱ:- "ለ" ነው። (የፌ/ጠ/ፍ/ሰ/ሰ/ ችሎት  በመ/ቁ. 231324 በቀን 26/03/2015 ዓ.ም የሠጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ይመልከቱ)


Репост из: Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ
ገንዘብ እንዲከፍል የተወሰነበት የፍርድ ባለእዳ አፈጻጸም መዝገብ ሳይከፈት ገንዘቡን በፍርድ ባለመብት የባንክ አካውንት ቢያስገባ እና አፈጻጸሙ ሲጀመር የፍርድ ባለእዳ የተከፈለኝ ገንዘብ የለም ብሎ ቢከራከር አፈጻጸሙን የያዘው ፍርድ ቤት ገንዘቡ ከፍርድ ቤት ውጭ ተከፍሏል አልተከፈለም የሚለውን ማጣራት አለበት ከታች ያለው ውሳኔ

እዚህ ጋር የሚነሳው በሰበር መዝገብ ቁጥር 98263 ቅጽ 17 ላይ በፍርድ የተወሰነን ነገር በእርቅ ጨርሰናል ብሎ ፍርዱን ለማስለወጥ እርቁ ፍርድ ቤት ቀርቦ መመዝገብ እንዳለበት;ይህም መደረግ ያለበት በፍርድ የተገኘን መብት ፈጽሚያለው አልፈጸምኩም በሚል መቋጫ የሌለው ክርክር ስለሚከፍት ነው ከሚለው የሰበር አቋም ጋር እንዴት ይታያል


Репост из: Mizan Law / ሚዛን ሎዉ⚖️
የፌደራል_ጠቅላይ_ፍርድ_ቤት_የሰበር_ሥነ_ሥርዓት_መመሪያ_ቁጥር_17_2015_.pdf
610.3Кб
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የሰበር ሥነ-ሥርዓት መመሪያ ቁጥር
17/2015


Репост из: ስለ ህግ
ሰ/መ/ቁ. 237198
ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም
በፍታብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ 358 መሠረት በሚቀርብ የመቃወም አቤቱታ ላይ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ (የመቃወም አቤቱታ ባቀረበው ላይ) ሊስተናገድ አይችልም።




Репост из: ነገረ ፈጅ Negere Fej
ሰ/መ/ቁጥር 221828 ሕዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም
አስተዳደራዊ መፍትሔ ለማግኘት የተደረገ ጥረት ይርጋን አያቋርጥም። አስተዳደራዊ መፍትሔ በመሻት ለጉምሩክ ቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት አቤቱታ በመቅረቡ የጠፋው ጊዜ ይርጋን ለማቋረጥ በቂ ምክንያት ኣለመሆኑን፣ ይርጋ ሊቋረጥ የሚችለው ስልጣን ለሌለው ፍርድ ቤት እንጂ ስልጣን ለሌለው አስተዳደራዊ ቅሬታ ሰሚ ተቋም አቤቱታ ሲቀርብ አይደለም።


የትራንስፖርት አበል እና የመጓጓዣ ወጪ ከግብር ነፃ የሚደረግበት ሁኔታ

ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አፈፃጸም መመሪያ ቁጥር 1/2011 መሠረት

👉በስራ ባህሪው ምክኒያት ስራውን ከቦታ ወደቦታ በመዘዋወር የሚያከናውን
ተቀጣሪ በአንድ ወር ጉዞ የሚከፈለው የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ
የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደመወዙ ከአንድ አራተኛ(1/4) ባልበለጠ መጠን ብቻ
ነው፡፡ ይሁንና የተቀጣሪው ጠቅላላ የወር ደመወዝ አንድ አራተኛ ከብር2200
የሚበልጥ ሲሆን ከግብር ነፃ የሚደረገው የትራንስፖርት አበል በማንኛውም ሁኔታ
ከብር 2200 ሊበልጥ አይችልም፡፡

👉 አንድ ተቀጣሪ በስራ ባህሪው ምክኒያት በመዘዋወር ለሚሰራው ስራ ለነዳጅ
ወጪ የሚከፈለው ጥሬ ገንዘብ ለትራንስፖርት አበል እንደተከፈለ ተቆጥሮ ከገቢ
ግብር ነፃ የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደመወዙ ከአንድ አራተኛ(1/4) ባልበለጠ
መጠን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና የተቀጣሪው ጠቅላላ የወር ደመወዝ አንድ አራተኛ
ከብር 2200 የሚበልጥ ሲሆን ከግብር ነፃ የሚደረገው የነዳጅ ወጪ በማንኛውም
ሁኔታ ከብር 2200 ሊበልጥ አይችልም፡፡

👉አንድ ተቀጣሪ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ስራው ቦታ እንዲሁም ከስራው ቦታ ወደ
መኖሪያ ቤቱ የሚጓጓዝበት የመስርያ ቤቱ የትራንስፖርት ሰርቪስ ቢቀርብም
ባይቀርብም ለዚህ ዓይነቱ የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር
600 ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

👉አንድ ተቀጣሪ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ስራው ቦታው እንዲሁም ከስራው ቦታ ወደ
መኖሪያ ቤቱ ለመሄድ ለነዳጅ ወጪ በጥሬ ገንዘብ የሚፈለው የትራንስፖርት
አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 600 ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

👉 አንድ ተቀጣሪ ሥራው ለማከናወን መደበኛ የሥራ ቦታው ከሚገኝበት ከተማ
ውጪ ሲንቀሳቀስ ለመጓጓዣ ወጪ የሚሰጠው ክፍያ ከግብር ነፃ ሊሆን
የሚችለው በስራ ላይ ባለው የትራንስፖርት ታሪፍ ወይም በሚያቀርበው ማስረጃ
ላይ የተመሰረተ ሆኖ ከከፈለው የአየር፣ የውሃ እና የየብስ ትራንስፖርት
የአገልግሎት ዋጋ ሊበልጥ አይችልም፡፡

👉አንድ የውጭ አገር ዜጋ ሥራን ለማከናወን ወደ የኢትዮጵያ ሲመጣ እና የውል
ዘመኑን ጨርሶ ከሀገር ሲወጣ የሚከፈለው የትራንስፖርት ወጪ ከግብር ነፃ ሊሆን
የሚችለው በተፈጸመው የቅጥር ውል መሰረት እና የአየር፣ የውሃ እና የየብስ
ትራንስፖርት የአገልግሎት ዋጋ ታሪፍ መሰረት ሆኖ ከግብር ነፃ የሚሆነው ለግል
መገልገያ ዕቃዎቹ የሚከፈለው የጭነት ሂሳብ ከ300 ኪሎ ግራም ሊበልጥ
አይችልም፡፡

👉አንድ ግብር ከፋይ ከመደበኛ መኖሪያ ቦታቸው ርቀው ሥራቸውን የሚያከናወኑ
ሠራተኞች ቤተሰባቸውን ለመጠየቅ የሚያደርጉትን ጉዞ ውጪ የሚሸፍን
በሚሆንበት ጊዜ የዚህ ዓይነት ወጪ ከግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው በተፈፀመው
የቅጥር ውል ውስጥ ቀጣሪው ይህ ግዴታ ያለበት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ሆኖም ለዚህ
ዓይነቱ ጉዞ የሚከፈለው ወጪ ከግብር ነፃ የሚደረገው በአንድ የግብር ዓመት
ከሁለት የደርሶ መልስ ጉዞ ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

Source:- Ministry of Revenue


Репост из: የኢትዮጵያ ሕጎች / Ethiopian Laws 🇪🇹
254672 .pdf
892.3Кб
"...አንድ ዳኛ በየደረጃዉ ባሉት ሁለት ፍርድ ቤቶች ተሰይመዉ በጉዳዩ ላይ ዉሳኔ የሰጡበት አግባብ ከላይ በተጠቀሱት በነባሩ ሕግም ሆነ አሁን ተፈጻሚ እየሆነ ባለዉ የክልሉ ፍርድ ቤቶች አዋጅ ላይ ስለችሎት አሰያየም እና ዳኛ ከችሎት ስለሚነሳበት አግባብ በአስገዳጅነት የተዘረጉትን ደንቦች የጣሰ ሥነ ሥርዓታዊ ጉድለት ብቻ ሳይሆን የተከራካሪ ወገኖች ሥነ ሥርዓታዊ መብት፣ በሕገ መንግሥቱ እና በሌሎች ሕግጋት ጥበቃ የተደረገላቸዉ መሠረታዊ መብቶች እንዲጣስ፣ የሕግ የበላይነት እንዲሸረሸርና ሕዝቡ በዳኝነት አካሉ ላይ እምነት እንዲያጣ የሚያደርግ ዉጤት የሚያስከትል በመሆኑ እንደመሠረታዊ የሕግ ስህተት ተቆጥሮ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት አለመታረሙ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2(4/ሀ እና ሸ) እና 10(1/ሐ) መሠረት ሊታረም የሚገባዉ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ ብለናል፡፡"

Показано 14 последних публикаций.