👆🏻የዲኔ ጉዳይ ያገባኛል👆🏾


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


በዚህ ቻናል
♦️#ተውሒድና_ሱና በሰለፎች አረዳድ ብቻ ከተለያዩ የሰለፊያ መሻይኾችና ኡስታዞች ትምህርት ይቀርባል።
♦ እንዲሁም ሙስሊሙን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎችን እናጋራለን ተቀላቀሉ
ولقد بعثنا في كل أمة رسولاً عن اعبد الله واجتنبوا الطاغوت
https://t.me/yedine_guday

ሀሳብ እስተያየቶን በ👇ያድርሱን
@Yedinegudaybot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


#ተውሒድ!

ረሱል (ﷺ) ለኢብኑ አባስ እንዲህ ብለውታል፦

 ﴿يا غلامُ احفظ اللهَ يحفظك، احفظ اللهَ تجده تجاهك، إذا سألت فاسألِ اللهَ، وإذا استعنت فاستعن بالله، واعلم أن الأمةَ لو اجتمعت على أن ينفعوك بشيءٍ؛ لم ينفعوك إلا بشيءٍ قد كتبه اللهُ لك، ولو اجتمعوا على أن يضروك بشيءٍ؛ لم يضروك إلا بشيءٍ قد كتبه اللهُ عليك، رفعتِ الأقلامُ، وجفَّت الصحفُ.﴾

“አንተ ልጅ ሆይ! አላህን ጠብቅ ይጠብቅሀል። አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ። ስትጠይቅ እላህን ጠይቅ። ስትታገዝ በአላህ ታገዝ። እወቅ! ህዝቦች
ባጠቃላይ በሆነ ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ አላህ ላንተ በፃፈልህ በሆነ ነገር እንጂ አይጠቅሙህም። ስሆን ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ባንተ ላይ በፃፈው ነገር እንጂ አይጎዱህም። ብእሮቹ ተነስተዋል መዝገቦቹ ደርቀዋል።”

📚 አልሚሽካት: 5302

ጆይን፡‐ https://t.me/BuhariMuslimAmharic


🎊ታላቅ ሙሀደራና ቢሻራ ፕሮግራም🎊
➖➖➖➖➖

【በዕለተ እሁድ ረጀብ 19/1446ھ】

«ታላላቅ ኡስታዞች እና መሻይኾች የሚሳተፉበት»

⏰ከምሽቱ 2:40ጀምሮ የሚተላለፍ ይሆናል !

ተጋባዥ ኡስታዞች እና የክብር እንግዶቻችን
~
🎙ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሒዛም -ከየመን
🎙ኡስታዝ አቡ-ሒዛም - ከሰመራ
🎙ኡስታዝ ኸድር አህመድ _ከከሚሴ
🎙ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሀሰን ኢድሪስ_ከሀርቡ
🎙ኡስታዝ አቡ አብዲረሂም አብዱረህማን ሹመት_ከጃሚዓቱል-ኢስላሚያህ - መዲና
---
☞እንድሁም የአህሉ ተዉሂድ መርከዝ አሚሮችና ወንድሞችም ይሳተፋሉ!

❝በአህሉ-ተውሂድ ኢስላሚክ ሴንተር - ሀርቡ❞ 💡የሚተላለፍበት አድራሻ↓↓↓↓↓↓
https://t.me/sefinetunuh
https://t.me/sefinetunuh


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የዛ ህዝብ ሰቆቃ‼


“With tears and prostrations of gratitude”




This is how Palestinians of #Gaza welcomed the announcement of the ceasefire agreement between Israel and Hamas.


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የጋዛዊያን ደስታ‼

Palestinians in #Gaza chant “Allahu Akbar”, celebrating the announcement of the ceasefire agreement between Israel and Hamas.



የተገደሉትን ህፃናት፣ ሴቶች፣ አዛውንቶችና ሁሉንም አላህ ከሸሂዶች ይመድባቸው።


ነገ ሐሙስ ነው
#አንተስ_አትወድም?
“ሰኞ እና ሐሙስ ስራዎች ወደ አሏህ ይቅቀረባሉ፡ እኔም ፆመኛ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እፈልጋለሁ”
ረሱሉል አሚን صلى الله عليه وسلم


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አምስቱ የወንጀል ሂደቶች

አነስ ባለ ሳይዝ


https://t.me/Muhammedsirage


የአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት ሒጃብ መልበስ የሚከለክለው መመሪያ ላይ ዕገዳ ጥሏል‼
====================

(በሒጃብ ምክንያት ተማሪዎችን ያገዱ ትምህርት ቤቶች ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ አዟል!)

||



✍ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት በአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሒጃብ ለብሰው እንዳይማሩ አስተዳደራዊ እግድ ባደረጉ 5 ትምህርት ቤቶች ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል።

ጉዳዩ በዛሬው ዕለት የአክሱም ከተማ ወረዳ ፍርድቤት ላይ ቀርቦ ውሳኔ ተስጥቶበታል። ፍርድ ቤቱ አስተዳደራዊ እግድ ባደረጉ ትምህርት ቤቶች ላይ እግድ ጥሏል።

ጉዳዩ በተማሪዎቹ ላይ የማይቀለበስ የሰብአዊ መብት ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ተማሪዎቹ ሒጃባቸውን ለብሰው ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የሚል ውሳኔ አስተላልፏል።

በሒጃብ ምክንያት ተማሪዎችን ያገዱ ትምህርትቤቶቹ ለጥር 16/2017 ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ ትእዛዝ ተሰጥቷል።

በተያያዘ ዜና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማሳሰቢያ ፥ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ዛሬ ጥር 6/2017 ዓ.ል ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።

የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል አገር አገር አቀፍ ፈተና ለማሳተፍ የሚያስችላቸው ፎርም ሳይሞሉ የተሰጠው የምዝገበ ቀነ ገደብ ዛሬ አልቋል።

© ሀሩን ሚዲያ


አላህ ወንጀሌን ይቅር ይለኝ ይሁን!?

የ ማዒዝ ኢብኑ ማሊክ ደንቅ ታሪክ!

🎙ወንድም አቡ ሱፍያን
=t.me/Sle_qelbachn1


አያሙል ቢድ ፆም ነገ ሰኞ ይጀመራል የቻለ ይፁም ያልቻለ ሌሎችን ያስታውስ!
===========>

↪️የረጀብ ወር የአያመል'ቢድ ቀናቶች ነገ ሰኞ ይጀምራሉ። በወር ውስጥ 3 ቀናቶችን መፆም ተወዳጅ ነው። አያመል'ቢድ የሚባሉትን 13፣ 14 እና 15 ቀኖችን መፆምም ለብቻው ሐዲስ መጥቶበታልና ከቻሉ ይፁሙ።

• አቡ ሑረይረህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ብለዋል: የቅርብ ጓደኛዬ (መልእክተኛው ﷺ) እስክሞት ድረሥ ሶሥት ነገራቶችን እንድሰራቸው ምክር ለግሰውኛል አለ፦ "በየወሩ ሶሥት ቀናቶችን እንድፆም፣የ'ዱሃ ሶላት እንድሰግድ፣ ዊትር ከሰገድኩ በኃላ እንድተኛ።"
[ቡኻሪ: 1178፣ሙስሊም:721)]

• አቡ ዘር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ሲል አስተላልፏል "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ  ወሰለም እንዲህ አሉኝ:– "ከወሩ ውስጥ የተወሰኑ ቀናት ከፆምክ 13ኛ፣ 14ኛ አና 15ኛውን ቀን ፁም"
(ቲርሚዚ 761,ነሳኢ 2424)

||- አያሙል ቢድ --> ሰኞ       13
||- አያሙል ቢድ --> ማክሰኞ 14
||- አያሙል ቢድ --> እሮብ     15

©wrumsu




በ19ኛው ክ/ዘመን አስተሳሰብ የሚገኙት የ21ኜው ክ/ዘመን አክሱማዊያን

ችግሩ
በምስራቅ አፍሪካ ብቻ፣ በኢትዮጵያ ብቻ፣ በትግራይ ብቻ፣ በጭቆና ማሳያዋ እርኩሲት #አክሱም ብቻ ያልለ፣ በሕዝብና መንግስት የሚተዳደርን ትምህርት ቤት እምነትን መሰረት አድርጎ በindirect discrimination (በአሏህ ፈቃድ በሰፊው እመለስበታለሁ በሌላ ጽሁፍ) ከትምህርት ገበታ ውጪ እንዲሆኑ ተደርገዋል።

እኝህ በ21ኛው ክ/ዘመን ላይ እየኖሩ የአያታቸውን ዮሐንስ IV የ19ኛው ክፍለዘመን ርዕዮት ያነገቡ ቆሞቀሮች ናቸው።

እንደ አፄው ሁሉ መጨረሻችሁ አያምርም ውርደት ይከተላችኋልና!

መፍትሄ

በተረፈ መጅሊስና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሴቶችና ሰብአዊ መብት ተቋማት ባላቸው legal standing እነዚህን ቆሞ ቀሮች በወንጀል ተጠያቂ በማድረግ በትንሹም ቢሆን ፍትሐዊነትም ያስፍኑ።

በተረፈ የትግራይ መጅሊስ ላሳየው ቁርጠኝነት እና በቦታው አናሳ ቁጥር እንደመኖሩ ከነዚህ ቆሞቀሮች ጋር እየተጋፈጠ ያለበት ሁኔታ እጅግ የሚደንቅ ነው አሏህ ይገዛቸው።
Amnesty International Africa
UNICEF Ethiopia
UN Human Rights Council
African Union
Merahit
United Nations OCHA Ethiopia
Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር
Ministry of Education Ethiopia
Getachew K Reda
Debretsion Gebremichael
BBC News Amharic
Al Jazeera English
https://t.me/yedine_guday


የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በተዋረድ ባሉ የክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ጽ/ቤቶችና ትምህርት ቤቶችን በበላይ የሚመራ እንደመሆኑ በግልጽ የፈቀደው መመሪያ (ሒጃብ) አንድ ተራ በወረዳ/ዞን ያለ ትምህርት ቢሮ ተፃራሪ ኢ-ሕገመንግስታዊ፣ ኢ-ሞራላዊ፣ ኢ-ህጋዊ የሆነ እና ከምቀኝነት እና ጥላቻ በመጣን ትዕዛዝ መሰረት ከብሔራዊ ፈተና systematically exclude እየተደረጉ ያሉ ከ150 በላይ ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን መሰረታዊ የሰብአዊ እና ሃይማኖታዊ መብታቸውን እንዲያስከብር፣ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ከመመዝገቢያ deadline በኋላም ቢሆን አካትቶ፣ ይህን ታሪካዊ አሳፋሪ ትዕዛዝ በሰጡ የትምህርት ቤቶቹ አመራሮች ላይ በተጀመረው የህግ እንቅስቃሴ የበኩሉን በማድረግ በሌላ ቦታ እንዲህ ያለ ፀብአጫሪ ኩነት በድጋሚ እንዳይከሰት በማድረግ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ስንል እንጠይቃለን።
Cc: Ministry of Education Ethiopia
https://t.me/yedine_guday


ይህ የሆነው በእኛ ዘመን ነው!

ከአፄዎቸ የግፍ አገዛዝ በኋላ እንዲህ ያለ ሕገወጥ ጭቆና አፍጥጦ መጥቷል። በአክሱም ጽንፈኞች ላይ ከህጋዊ አካሄዱ ባሻገር የተደራጀ ማዕቀብ መጣል ያስፈልጋል።

ይህ ከትራንስፖርት አቅራቢዎች እስከገበሬው፣ ከደላላው እስከነጋዴው፣ ከአስመጪው እስከቸርቻሪው አቀናጅቶ ተጽእኖ ማሳደር ያሻል። ይህ የሚሆነው ከህጋዊ መፍትሄው ጎን ለጎን ነው።

ይህንን ሀላፊነት መጅሊስ ወስዶ በንግዱም ሆነ በግብርናው ለአክሱማዊያን የሚቀርቡ አቅርቦቶች እና ከነርሱ የሚሸመቱ ምርቶች ላይ በተደራጀ መልኩ መቅጣት ያስፈልጋል።

በእኛ ዘመን የአፄ ዩውሃንስ ዘመን ተመልሶ መጥቷል። አንዲት ሙስሊም ከሃይማኖቷ ወይም ከትምህርቷ አንዱን እንትመርጥ አስገዳጅ ምርጫ እየቀረበላት ነው። ሙስሊም ሁና እንድትማር አልተፈቀደላትም። አክሱም እየሆነ ያለው ይህ ነው። እስልምናዋ (ሒጃቧ) ነው የሚሰጠውን የፈተና ፎርም እንዳትሞላ ያስከለከላት።

ሙስሊም በመሆኗ መማር አልቻለችም፤ መፈተን አልቻለችም። ዩኒቨርስቲ የመግባቷ ነገር አይታሰብም። ይህ በእኔና አንተ (በእኛ) ዘመን ነው። በእኛ ዘመን አፄው ዳግም ተወልዷል። ተመልሶ መጥቷል።
ታድያ ምን ትጠብቃለህ?!

ከትግራይ ሙስሊም ሚዲያ ትንሽ የታከለበት
https://t.me/yedine_guday




⚠️ የካንሰር በሽታ ⚠️

💎 مرض ﺍﻟﺴّﺮﻃﺎﻥ :
ﺗﺒﻴّﻦ ﻟﻨﺎ ﺃﻥ ﻣﻦ ﺃﺳﺒﺎﺏ ﻭﻗﻮﻋﻪ ﺍﻟﺴِّﺤﺮ، ﺇﺫﺍ ﻓﻚّ ﺍﻟﺴّﺤﺮ ﺯﺍﻝ ﺍﻟﻤﺮﺽ . .

الشيخ سليمان الرحيلي

🪴 ሼይኽ ሱሌይማን አርሩሄይሊ አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ብለዋል:

🔷 የካንሰር በሽታ ከሚከሰትባቸው ምክኒያቶች ውስጥ አንዱ ሲህር /ድግምት/ መሆኑ ግልፅ ሆኖልናል, ስለሆነም ሲህሩ ከተፈታ በሽታው ይወገዳል።

🔷 ስለዚህ እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ! በዚህ ምቀኝነትና ድግምት በበዛበት ዘመን ጠንካራ ምሽጋችን እና ከባዱ መሳሪያችን የሆኑትን ነቢያዊ አዝኮሮችን በማዘውተር ራሳችሁን ከምቀኞች ሴራ ለመጠበቅ ሰበብ አድርሱ።

➡️ እንዲሁም ለታመሙ ወንድም እህቶቻችሁ ሩቃ አድርጉላቸው፣ ኢንሻ አላህ በርግጠኝነት የቁርአን መድኃኒትነትን አምነን ከተጠቀምንበት ከብዙ አይነት በሽታ ለመፈወስ ሰበብ ይሆንልናል።

✔️አላህ በካንሰር በሽታ ታመው እየተሰቃዩ ያሉ ወንድም እህቶቻችን በቃችሁ ይበላቸው!!

🔶 በተጨማሪ እባካችሁን! ባለንበት ወቅት ሲህር በዝቷልና ራሳችሁን ጠብቁ፣ በተለይም እህቶች ራሳችሁን በደምብ ጠብቁ፣ ብዙ ግዜ ከምቀኞች,ከሴረኞችና ከጠላት በኩል የሚወረወሩ ቀስቶች እናንተን እላማ ያደረጉ ናቸው።

https://t.me/Hawassayesunajemea


ስልጤን እንደ ሞዴል
~
የስልጤ ወገኖቻችን ለቀሪው የኢትዮጵያ ሙስሊም ጌጥ ናቸው፣ ድምቀት። ከዚህም አልፎ መቀዛቀዝ አልፎም ማንቀላፋት ለሚታይበት የብዙ አካባቢ ሙስሊም ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው። ከዞኑ አልፎ በአዲስ አበባ የሚኖሩት፣ ከዚህም አልፎ በውጭ የሚኖሩት ጭምር ለዲናቸው ትጉ ናቸው። ይሄው ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ለመገንባት ተግተው እየታገሉ ነው። ቀላል የማይባል ርቀትም ተጉዘዋል። በዞኑ ዐረብኛ ትምህርት እንዲሰጥም ዝግጅታቸውን እየጨረሱ ነው። ሀይረንዚ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በዚህ ት/ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ወደ ዩኒቨርሲቲ ማሳለፍ ባቃታቸው ጊዜ ሙሉ ተማሪዎቹን እያሳለፈ ያለ ድንቅ ተቋም ነው። ዞኑ ውስጥ ካለው ባሻገር አዲስ አበባ ያሉ ዱዓቶች ወደተለያዩ የስልጤ ዞን ወረዳዎች እየተጓዙ ደዕዋ የሚሰጡበት አሰራር አላቸው። ይሄ በዱዓት ብቻ የሚቻል አይደለም። ስለመጠኑ ባላውቅም የነጋዴው ሚና ወሳኝ ነው። ባጠቃላይ በዞኑም ከዞኑም ውጭ ከሌላው ማህበረሰብ በተሻለ መልኩ active ናቸው። አላህ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጣቸው። ከሆነ ጊዜ ወዲህ ስልጤን የሚያጠለሹ ድምፆች ከፍ እያሉ የመጡት ያለ ምክንያት አይደለም።

መልእክቴ ምንድነው?

1ኛ፦ ለስልጤ ህዝብ ከዚህም በላይ አቅም አላችሁና ትጋታችሁን ይበልጥ አጠናክሩ እላለሁ። ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ጭምር እያሰባችሁ ተንቀሳቀሱ። እንቅስቃሴያችሁ በጥናት የታገዘ ይሁን። ዙሪያችሁ ያሉ ስጋቶችን የምትቋቋሙበት ሁለ ገብ አቅም መገንባት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ከዞኑም ውጭ አጎራባች አካባቢዎች ላይ ጭምር ስሩ። ዳር ካልተከበረ መሀል ዳር ይሆናል።

2ኛ፦ ለሌሎች አካባቢዎች ተወላጆች ደግሞ ከሰመመናችሁ ውጡ፣ ተንቀሳቀሱ፣ ተደራጁ እላለሁ። ቢቻል በዞን ደረጃ። ካልተመቸ ቢያንስ በወረዳ ደረጃ መንቀሳቀስ ይገባል። በተለይ አዲስ አበባ ውስጥ የምትኖሩ መነሳሳቱን ብትወስዱ መልካም ነው።
* አንዳንዱ አካባቢ ብዙ ህዝብ እየከ -ፈ ^ ረ ያለበት ነው። ይሄ እንቅልፍ የሚነሳ ጉዳይ ነው። ጉራጌ ዞን እና ኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ይሄ አደጋ በተጨባጭ አለ።

* አንዳንዱ አካባቢ ህዝቡ እጅግ ዘግናኝ በሆነ መልኩ ከዲን የራቀ በመሆኑ የተነሳ ብዙ አይነት ሺርክ፣ የካ - fiሮችን በዓል ማክበር፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት፣ ሶላት አለመስገድ፣ ጥንቆላና ድግምት፣ እርስ በርስ መገ ^ዳደ ል በሰፊው አለ። እነዚህ አደጋዎች ሁሉም ወይም ከሌሎቹ በየክልሉ ይታያሉ። ይሄው ሰሞኑን ትግራይ ውስጥ ጥምጣማቸውን የለበሱ ወገኖች የገና በዓል በጭፈራ ሲያከብሩ አይተናል። አማራ ክልልም ጥምቀትን የሚያከብረው ብዙ ነው። ኦሮሚያም አንዳንድ አካባቢዎች አለ። ሙስሊም በዝ በሆኑ ክልሎች ላይ ያለው ብሄር ወለድ ግጭትም ሰፊ ነው። ሺርኩ አይወራም። ከቤኒሻንጉል እስከ ሶማሌ፣ ከትግራይ እስከ ሞያሌ የተንሰራፋ ነው። ዐፋር ለራሱ ቀርቶ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ባጠቃላይ የክፉ ጊዜ መከታ ነው። ከዚህም በላይ ደጀን መሆን የሚያስችለው አቅም ነበረው። የንቃቱ የመደራጀቱ ጉዳይ ግን ገና ነው። የሶማሌም ሙስሊም ለኢትዮጵያ ሙስሊም አለኝታ የሚሆንበትን አቅም አላዳበረም። በተውሒድ ረገድ ሁሉም ብዙ ስራ ይፈልጋል። በአካደሚው ዘርፍ በጣም ወደኋላ የቀረን ነን።
ሌላው ሁሉ ቢቀር አዲስ አበባ የሚኖረው የነዚህ ክልሎች ተወላጅ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ቢሰራ የሚያቅተው አልነበረም። ነጋዴዎች ባለ ሃብቶች ጉዳዩን ለዱዓት አትተውት። ዛሬ ህዝብን ለማንቃት ቀርቶ ለደዕዋ እንኳ ያለ ገንዘብ ምንም ማድረግ አይቻልም። ስለዚህ አደራጁ ተረባረቡ። የምትችሉ አካላት የማነሳሳቱን ጉዳይ ኃላፊነት ወስዳችሁ ስሩበት። አላህ ያግዘን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


በዳዒ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም የተጻፈው "አልገደሉትም አልሰቀሉትም" የሚለው መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ።

ድሮ ድሮ ክርስቲያኖች "ክርስቶስ አልተገደለም አልተሰቀለም" የሚል ከቁርኣን በፊት ምንም የታሪክ ማስረጃ እና መረጃ የለም" የሚል ሙግት ነበራቸው፥ ዛሬ ላይ እኛ በተራችን "ክርስቶስ አልተገደለም አልተሰቀለም" የሚል ወንጌል እና አማኞች ከቁርኣን መወረድ በፊት በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የታሪክ ማስረጃ እና መረጃ ስናቀርብ ወንጌሉን "ኑፋቄ" አማኞቹን "መናፍቅ" በማለት ያነውራሉ። ለመሆኑ አሥራ ሁለቱ የክርስቶስ ሐዋርያት በዚህ ነጥብ ላይ ያላቸው አቋም ምንድን ነው? በመጽሐፉ ተዳሷል።

መጽሐፉን የምትፈልጉ አገር ውስጥ ያላችሁ ሆነ ከአገር ውጪ ያላችሁ በ +251928444408 ዐብዱ መርካቶ ብላችሁ በቀጥታ አሊያም በዋትሳፕ ታገኙታላችሁ፥ እንዲሁ በቴሌ ግራም ይህንን ዩዘር ኔም በመጠቀም http://t.me/merkatozon ማግኘት ትችላላችሁ።

ለብዙዎች ሠበቡል ሂዳያህ ለመሆን ሁሉም ቦታ ሼር አርጉት!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

©: ወሒድ አቃቤ ኢስላም


Репост из: Ethiopian Muslim Lawyers Association (EMLA)⚖
የኢትዮጵያ ሙስሊም የህግ ባለሙያዎች ማኀበር ምንድነው?አላማውና ግቡስ?እነ ማንን ያካትታል?
***

የኢትዮጵያ ሙስሊም የህግ ባለሙያዎች ማህበር በሙስሊም የሕግ ባለሙያዎች በመመስረት ላይ ያለ ማህበር ሲሆን በሀገሪቷ ላይ ያሉ መላው ሙስሊም የህግ ባለሙያዎችን እንዲሁም የህግ ተማሪዎችን በማቀናጀት በመሀከላችን አንድነትን በማጎልበት ብሎም የሙስሊሙን ማህበረሰብ ውክልና በመውሰድ ኡማውን የሚመለከቱ ማናቸውም አይነት ህግ ነክ ጉዳዮችን በህግ አግባብ ለመፍታትና ለማገልገል ያለመ ማህበር ነው።

የማህበሩ ቁልፍ ተግባራት ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ እና የሙስሊሙን ማህበረሰብ መብት የሚያስከብሩ ባለሙያዎችን መፍጠር ከዚህም ባሻገር እንደ አስፈላጊነቱ ከተለያዩ በስራ ላይ ካሉ ማህበራት ጋር ትስስር በመፍጠር የህግ ምክር አገልግሎት መስጠት፣ የህግ ሴሚናሮችን ማደራጀትና ለማህበረሰቡ ሁሉን አቀፍ የህግ ተደራሽነት ላይ በሰፊው መስራትን ያካትታል።

በተጨማሪም ለሰብአዊ መብቶች፣ ለእኩልነት እና የፍትህ ተደራሽነት ጉዳዮች ላይ ተሟጋች ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን የኢስላማዊ ስነ-ምግባር እና እሴቶች መርሆዎችን ባከበረ ሁኔታ ለሙስሊም ጠበቆች፣ የህግ ተማሪዎች እንዲሁም ለሁሉም ሙስሊም የህግ ባለሙያዎች በሙሉ ክፍት በመሆኑ ማህበሩ በህግ ጉዳዮች ለሰፊው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ትርጉም ያለው ተፅእኖ ለመፍጠር እንዲያስችለው ዓላማውን እና ግቡን ተረድታችሁ በሀገሪቱ ለሚገኙ ሙስሊም ጠበቆች፣ ተማሪዎች እና የህግ ባለሙያዎች በሙሉ እንዲቀላቀሉን ቻናሉን በማጋራት የበኩላችሁን እንድትወጡ በአላህ ስም እንጠይቃለን።

#EMLA

https://t.me/MLS2742017




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አጠር ያለ መልእክት

የቢድዓ ሰዎችን መራቅና አንዳንድ የነሲሐ ዱዓቶች

وَلَا تَرْكَنُوا إِلَى الَّذِينَ ظَلَمُوا فَتَمَسَّكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ

ወደእነዚያም ወደ በደሉት አትጠጉ፡፡ እሳት ትነካችኋለችና፡፡ ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም፡፡ ከዚያም አትረድዱም፡፡

🎙ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙ/ኑር

ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/Muhammedsirage

Показано 20 последних публикаций.