ኦርቶዶክሳዊ ንድፍ 🌼


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Дизайн


Buy ads: https://telega.io/c/orthodox_graphics1

በኦርቶዶክሳዊ ንድፍ ውስጥ
--> ለአመታዊ በዓላት ፕሮፋይል
--> እለታዊ ጥቅስ
--> ጥያቄ ማግኘት ይችላሉ

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Дизайн
Статистика
Фильтр публикаций


ክፍል ፭



ኢየሱስ ክርስቶስ የት ተወለደ?


የሕይወት እንጀራ ክርስቶስ በእንጀራ ቤት ተወለደ (ሉቃ. ፪፣፬-፲፭)። ቤተልሔም ማለት የእንጀራ ቤት ማለት ነው።  የክርስቶስ መወለድ ድንገት እንደ እንግዳ ደራሽ፣ እንደ ውሃ ፈሳሽ አይደለም። በቅዱሳን ነቢያት የሰውን ሥጋ ተዋሕዶ እንደሚወለድ ትንቢት ሲነገር ነበርና (ኢሳ. ፯፣፲፬)። ከጽድቅ ለተራበው ዓለም መንፈሳዊ ምግብ ይሆን ዘንድ የሕይወት እንጀራ ክርስቶስ በእንጀራ ቤት ተወለደ።

ቤተልሔም በእስራኤል ሀገር ያለች የዳዊት ከተማ የነበረች ቦታ ናት። ነቢያቱ፣ ነገሥታቱ ተወልደውባታል። የነቢያት ሀገር ናት። ከነቢያቱ፣ ከነገሥታቱ ግን የሕይወት እንጀራ ሆኖ የተራበውን ዓለም ማጥገብ የቻለ አልነበረም። ወልደ እግዚአብሔር ግን ከድንግል ማርያም ተወልዶ ዘለዓለማዊ ሕይወትን የሚሰጥ የሕይወት እንጀራ ሆነ።  ምእመናን ንሥሓ ገብተው፣ ሥጋውን በልተው፣ ደሙን ጠጥተው በእርሱ ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ። እርሱም በእነርሱ ይኖራል።


ይቀጥላል


ክፍል ፬


ቃለ እግዚአብሔር



ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ ዋነኛ ትምህርታችን ነው። ቅዱስ አትናቴዎስ በሃይማኖተ አበው እንደተናገረው ሥጋ መክበሩ ቃል ስለተዋሐደው ነው እንጂ መንፈስ ቅዱስ ክብር ሆኖት አይደለም።
ኢየሱስ ክርስቶስ ቃለ እግዚአብሔር ነው። ይህም ማለት ቃለ አብ፣ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ነው ማለታችን ነው። በአንድ ህልውና በአንድ ባሕርይ ለሚኖሩ ሦስቱ አካላት ቃላቸው እርሱ ነው። ይህ ቃል ከሰው፣ ከእንስሳት፣ ከመላእክት ቃል (ድምፅ) የተለየ ነው። እነዚህ ቃላት (ድምፆች) ዝርዋን ናቸው እንጂ አካላውያን አይደሉም። ቃለ እግዚአብሔር አአትሪኮን፣ አተርጋዎን፣ ቦርፎሪኮን ከሚባሉት ቃላት የተለየ ቃል ነው።

ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር የሰሙት ድምፅ እንኳ ዝርው ነው። አካላዊ ቃል የሚባለው ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ነው። ከንባብ (ንግግር) የተለየ አካላዊ ቃል ነው። ይህ ቃል ሥጋ ሆነ። ይህም ማለት ረቂቁ አካለ ቃል ግዙፉን አካለ ሥጋ በተዋሕዶ ገንዘቡ አደረገው ማለታችን ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር እየተመላለሰ ሲያስተምር ለሕዝቡ ጆሮ ይሰማ የነበረው ድምፅ ዝርው ስለሆነ አካላዊ አይደለም። ራሱ ክርስቶስ ግን አካላዊ ቃል ነው። እርሱ የተናገረው ንግግር ግን ከእርሱ ከአካላዊ ቃል የተገኘ ንግግር (ንባብ) ነው እንጂ ራሱ ንግግሩ አካላዊ አልነበረም።

ይቀጥላል


ክፍል ፫




አማኑኤል



አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ (እግዚአብሔር ምስሌነ) ማለት ነው። እግዚአብሔር በአካል ከፍጥረቱ ተለይቶ አያውቅም። እርሱ በአካል የሌለበት ቦታ የለምና። በረድኤትም በብሉይ ኪዳን ከቅዱሳን አበው፣ ከቅዱሳን ነቢያትና፣ ከቅዱሳን ነገሥታት ጋር ነበር። ይህኛው "ምስሌነ" ግን አነጋገሩ ከረድኤት የተለየ "ምስሌነ" ነው። በረድኤት ከእኛ ጋር መኖርን ብቻ የሚገልጽ አይደለም። የእኛን ሥጋ ተዋሕዶ ከእኛ ጋር መኖሩንም የሚገልጽ አነጋገር ነው። አማኑኤል የሚለው ስም ስመ ሥጋዌውን የሚገልጽ ስም ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን እንደእኛ ሰው ሆኖ ክሦ፣ ቤዛ ሆኖ አድኖናል።

እንግዲህ ምንንም፣ ማንንም አንፈራም። የሚያስፈራን ፍጡር የለም። ምክንያቱም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው። በእምቢታችን ጸንተን፣ በራሳችን ፈቃድ ከእግዚአብሔር ጋር መኖር አንፈልግም ብለን ከሰይጣን ጋር ካልተባበርን በስተቀር እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለሆነ በእርሱ ሁሉን አሸንፈን እንኖራለን።

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆኖ ነጻነትን መለሰልን፣ ፍጹም መንፈሳዊ ደስታን ሰጠን። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ሁሉ አለን። ኵሉ ብነ እንዘ አልብነ ኵሉ እንዳለ።

ይቀጥላል


ክፍል ፪




ክርስቶስ





ክርስቶስ በዕብራይስጥ ማስያስ፣ በዐረብ መሢሕ፣ በግሪክ ክርስቶስ፣ በግእዝ ቅቡዕ ማለት ነው። ቅቡዕ ማለትም የተቀባ ማለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነ አምላክ፣ አምላክ የሆነ ሰው ነው። ወልደ እግዚአብሔር ከድንግል ማርያም የነሣውን ሥጋ ሲዋሐድ በአምላክነት አከበረው። ሥጋም ቃልን ስለተዋሐደ ከብረ። ስለዚህም ቅቡዕ ተባለ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መባሉ በሰውነቱ እንደሆነ ሁሉ ቅቡዕ መባሉም በሰውነቱ ነው። በአምላክነቱ ክብርን (ቅብዕን) የሚሻ አይደለምና። ክርስቶስ ለተዋሐደው ሥጋ ክብር የሆነውም ራሱ ቃል ነው። እንጂ የቅባት እምነት አራማጆች እንደሚሉት መንፈስቅዱስ ቅብዕ (ክብር) አልሆነውም። በሥላሴ ዘንድ ቅብዕ፣ ተቀባዒ፣ ቅቡዕ የሚል አካላዊ ግብር የለምና። በማክበር፣ በክብር አንድ ስለሆኑ አብ አከበረው፣ ወልድ አከበረው፣ መንፈስ ቅዱስ አከበረው ቢል አንድ ነው። ለሥጋ ክብር የሆነው በተለየ አካሉ ቃል ነው። ምክንያቱም ሥጋ ቃልን ሆነ እንጂ ልብን ወይም እስትንፋስን አልሆነምና ነው። ሥጋ ከበረ መባሉ እንኳ ቃልን ሆነ ማለት ነውና።

ክፍል ፫ ይቀጥላል።


እንደምን አረፈዳቹ


ክፍል ፩



_ኢየሱስ_



ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ነው። ዓለም በአዳም በደል ምክንያት ታሞ ይኖር ነበር። ዓለምን መፈወስ የቻለ ሰው ደግሞ እስከ ክርስቶስ ልደት ድረስ አልተገኘም ነበር። ስለዚህ ዓለምን ለማዳን ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ተዋሐደ። ዓለምን የማዳን ሥራውም ከማኅፀን በተዋሕዶ ጀመረ። በዓለም ላይ ብዙ መድኃኒቶች ቢኖሩም መድኃኒትነታቸው የጸጋ ማዳን ነው። በባሕርይው አዳኝ የሆነ እግዚአብሔር ነው። እርሱ እግዚአብሔር ሥጋን ተዋሕዶ አድኖናልና ኢየሱስ ተብሏል። ሰውን ያዳነው፣ ወደቀደመ ቦታውም የመለሰው ኢየሱስ ነው። ሌሎች ፍጡራን ቢያድኑ ግን ማዳንን ከክርስቶስ በጸጋ ተቀብለው ነው። ኢየሱስ የሚለው ስም በአማርኛ መድኃኒት፣ መድኃኒ ዓለመ፣ መድኃኔ ዓለም ተብሎ ሊገለጽ ይችላል።

የኢየሱስ ስሙ፣ አካሉ፣ ሁለንተናው አዳኝ ነው። ስለሆነም በየጊዜው በየሰዓቱ ከሰይጣን ተንኮል ያድነን ዘንድ ስሙን እንጠራለን። ስለሆነም እንደ ደራሲው ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ሠረፀ እምቤተ ሌዊ፣ ኮሬባዊ መለኮታዊ፣ ቃል ሰማያዊ እምድንግል ተወልደ እንለዋለን።


ነገ ጠዋት እንጀምራለን 🙏❤️

ነገረ ክርስቶስን በቀላል እና በተብራራ መንገድ 🙏

ጠዋት አንድ ክፍል ማታ አንድ ክፍል እንለቅላቹሀለን 🙏

አደራችሁን በዋላ አነበዋለሁ ብላችሁ እንዳትተው እንደተለቀቀ አንብቡ


ታተርፋላችሁ ጥያቄዎቻችሁ ሁሉ ይመለሳሉ 🙏❤️


እግዚአብሔር በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስፈፅመን 🙏❤️


ተከታታይ ትምህርቶች በየቀኑ ይለቀቁ?
Опрос
  •   አዎ
  •   አይ
27 голосов


ማንኛውም ማኅሌት ሲጀምር ፈጣሪ ጸሎታችንን ሰምቶ እንዲቀበል በመማጸን ነው ። ቃሉም እንዲህ ይላል ።

ስምዐኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዐርየ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ

አቤቱ ጸሎቴን ስማኝ ፤ ጩኸቴም ከፊትህ ይድረስ ፤ፊትህንም ከእኔ አትመልስ ፤ በችግሬ ቀንም ጆሮህን ወደእኔ አዘንብል፤  በምጠራሁህ ዕለትም ፈጥነህ ስማኝ ።


አቤቱ ጸሎታችንን ስማን ።


#ወዳጄ

ችግርህን

ለሚወድህ ሰው አትንገረው
- ያሳስበዋልና!

ለሚጠላህ ሰውም አትንገረው
- ይደሰታልና!

ለፈጣሪህ ግን ንገረው
- ይረዳሃልና!!

አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ


ሁልጊዜ ሥስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ፡፡
እነርሱም፡-
           ✞ ክፉ ከመናገር መከልከልን
           ✞ ማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና
           ✞ እንደልምድ አደርጋችሁ ከያዛቸሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)


“የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያደርግ ርጉም ይሁን።”
  — ኤርምያስ 48፥10


“ከእናንተ አንዳንዶች ሥራ ፈቶች እንደ ሆኑ ሰምተናል፤ እነርሱም ያለ ሥራ እየዞሩ በሰው ጕዳይ ጣልቃ የሚገቡ ናቸው።”
  2 ተሰሎንቄ   3 : 11


ለስንፍናህ ሁሉ ምክንያት አትስጥ መልካሙን ነገርም ዛሬ ሥራው፤ ክፉውን ነገርም ዛሬ ተናዘዘው፡፡ እያንዳንዱ የጊዜ ሽርፍራፊ የገነትና የሲዖል ሰው ለመሆን ዋጋ እንዳለው እወቅ፡፡


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በችግራችን ብቻ ስንጠራው ያልታዘበንን አምላክ አመስግኑ!

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን


“... በጊዜው እናጭዳለንና
መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት።”
  — ገላትያ 6፥9


"
እያንዳንዱ ሰው የፈራው የመሬቱን መንቀጥቀጥ ሲኾን እኔ የፈራኹትን ግን የመሬት መንቀጥቀጡን ምክንያት ነው።"


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


Репост из: Smart ፕሮፋይል Pictures🌼™
LuCy gems የሰራቹትን በየሳምንቱ Withdraw ማረግ ትችላላችሁ ትኩረት ሰታቹ ከሰራቹት እስከ 200$ ድረስ በቀላሉ ትሰራላቹ በዚ ሰዐት ትክክለኛ ቶሎ  ከፋይ airdrop  ነው። ቴሌግራም ላይ ገንዘብ አጊቶ ማያቅ በሙሉ መስራት በቀላሉ መስራት ይችላል አዲስ ባሻሻሉት ህግ 1$ ብሰሩም ማውጣት ትችላላችሁ።

ለመጀመር

👇👇👇
https://t.me/lucky_gems_official_bot/app?startapp=2CmLcR2xntyguj8wqTvkGjUPbvNQfJQTe97pZsMYtEqRE3D
https://t.me/lucky_gems_official_bot/app?startapp=2CmLcR2xntyguj8wqTvkGjUPbvNQfJQTe97pZsMYtEqRE3D


#እህቴ_ሆይ፦

ደፋርና ለእውነት የምትቆም
  👉እንደ አስቴር

ታማኝ
👉 እንደ ሩት

ስስት የማታውቅ
👉 እንደ ሊዲያ

በጸሎቷ ትጉህ
👉 እንደ ሃና

ትሁትና ታዛዥ
-እንደ ማርያም

6- በመክሊቷ የምትጠቀም
👉 እንደ ዶርቃስ

እንድትሆኝ እግዚአብሔር ይርዳሽ!🙏


Репост из: ኦርቶዶክሳዊ ፎቶዎች💠🖼️
ወርኃ ጽጌ
ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን ዘመነ ጽጌን ታከብራለች ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ

በዚህ በወርኃ ጽጌ በዘመነ ጽጌ የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ.7፡47) እንዲል

የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸው የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡

Показано 20 последних публикаций.