⚽️ | ታገቢኛለሽ ወይ ?
ነገሩ እንዲህ ነው በባለፈው ሳምንት በአውሮፓዊቷ ሀገር ሮማኒያ የአራተኛ ዲቪዚዮን ኦርዲያ እና ዲዮስጂ በተባሉ ሁለት የእግር ኳስ ክለቦች መካከል ጨዋታ እየተካሄደ ነው።
ጨዋታው ልክ ሊጀመር ሲል የ 22 አመቱ ረዳት ዳኛ ማሪዩስ ማቲካ እንስት ረዳት ዳኛ የሆነችውን የ 20 አመቷን ጂዮርጂ ዱማን ከእግሩ በርከክ ብሎ የታገቢኛለሽ ጥያቄ አቀረበላት። ❤️
ምስጋና ለ ጂዮርጂ በነዛ ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች ፊት አላሳፈረችውም " እሺ አገባሀለሁ " ስትል ምላሿን ሰጠች ፤ ይህንን ያልተጠበቀ ክስትት የሁለት ክለቦች ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች ለጥንዶቹ የወደፊት ህይወት ያማረ እንዲሆን በጭብጨባ አጀቧቸው ።
ጥንዶቹ የመስመር ዳኞች በፍቅር አብረው ሶስት አመታት እንደኖሩ ይነገራል ፤ ጆርጂ ክስተቱን በጭራሽ አልጠበቅኩትም ደንገት ነበር ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች።
✍ |
@Pedri_gonzalezz ☑
@Ke_egerkuas_tarik