የወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ እስልምና ጉዳዮች (መጅሊስ) ቴሌግራም ፔጅ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ይሄ የወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ እስልምና ጉዳዮች (መጅሊሱን) በተመለከተ የሚለቀቅበት የቴሌግራም ቻናል ነው አላህ መልካም መገጠሙን ይወፍቀን ስህተት ስታዩ በውስጥ መጥታችሁ አስተያየት ስጡን እናንተንም አላህ በአዱኒያም በአኼራም መልካሙን ይወፍቃችሁና !

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus
🎉
እንኳን ለ1446ኛው የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ

የረመዿን ጨረቃ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ስለታየች ነገ ቅዳሜ የካቲት 22, 2017 E.C. (March 1, 2025 G.C.) የረመዷን የመጀመሪያ ቀን ይሆናል ።
ረመዿን 1/1446


አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን!
ረመዷን ሙባረክ! 🌙✨


ወንድማችሁ ጀማል እንድሮ አቡ መርየም
ከወሎ–ወረኢሉ


https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15530


በጫት የተተረተረው የጫሌ ጉንጭ?


በፊትና ወቅት አቋማችን ምን መሆን አለበት !?

ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሃፊዘሁላህ
መቼም ከማይረሱ ከወርቃማ ምክሮቹ ውስጥ ጥያቄ ተጠይቆ ከመለሳቸው መልሶቹ ውስጥ ተጋበዙ

~ አላህ የፊትና በር መዝጊያ የኸይር ነገር መክፈቻ እንድያደርገን ዱዓ እናድርግ !

@Ibnumunewor

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15517


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አንዳንድ እህቶች ኒካሕ ሲቃረብ አባቶቻቸው ሺርክ ላይ እንደሆኑ በመጥቀስ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ይጠይቃሉ።
1- በመጀመሪያ የእውነት ሺርክ መኖሩን በተጨባጭ ማረጋገጥ ይገባል። ኹራፋት፣ ቢድዐዎች፣ ተወሱላት ብቻቸውን ሺርክ ላይ ላይደርሱ ይችላሉ። ችግሩ እዚያ የሚደርስ መሆን አለመሆኑን በትክክል መለየት ይገባል።
2- በተጨባጭ አባት ሺርክ ላይ መሆኑ ከተረጋገጠ ተስፋ ሳይቆርጡ የሚችሉትን ሁሉ ጥረት በማድረግ ለመመለስ መጣር ይገባል። ይሄ የኒካሕ ሰሞን ሳይሆን ቀድሞ ነው ሊሰራበት የሚገባው። ከኒካሑ የበለጠ የሚያሳስበው ይሄ ነው። "ክፉ ደግ አይቶ፣ ለፍቶ ያሳደገኝ አባቴ ኒካሕ አታስርም ሲባል በጣም አዘንኩኝ፣ ከፋኝ፣ ..." የሚል የዓጢፋ (ስሜት) ንግግር ዋጋ የለውም። ሺርክ ከኢስላም የሚያስወጣ፣ ዘላለማዊ ክስረትን የሚያስከትል፣ እስከወዲያኛው ከሚወዱት የሚለያይ ከባድ ጥፋት ነው። ከኒካሑ በፊት ሺርክ ውስጥ ሲኖሩ ያልተሰማን ስሜት "ወሊይ አይሆኑም" ሲባሉ ከተሰማን ችግሩ ከራሳችን ነው። ገና ያልጠራ ነገር አለ ማለት ነው። እናጥራ።
3- በተረፈ ከኢስላም የሚያስወጣው ትልቁ ሺርክ መኖሩ በተጨባጭ ተረጋግጦ፣ ተመክረው ተዘክረው ከተቀበሉ ወሊይ ሆነው ኒካሑን ያስራሉ። ከኢስላም የሚያስወጣው ትልቁ ሺርክ መኖሩ በተጨባጭ ተረጋግጦ፣ ተመክረው ተዘክረው ለመቀበል አሻፈረኝ ካሉ ግን ወሊይ ሆነው ኒካሕ ሊያስሩ አይፈቀድም። ከዚህ ዝቅ ባለ ጉዳይ ሶላት የማይሰግዱ ሆነው እንዲሰግዱ ቢመከሩም ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ለኒካሕ አይሆኑም። የሶላት ጉዳይ በንፅፅር ከተውሒድ ያነሰ ከመሆኑ ጋር ማለት ነው።
4- እንዲህ አይነት ሁኔታ ከገጠመ ወሊይነቱ ወደሌላ ቅርብ ቤተሰብ ይሻገራል። ኒካሑ በነሱ በኩል ይታሰራል። ለኒካሕ የሚሆን ቤተሰብ ከሌለ በቃዲ ይታሰራል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከታሪክ አምባ
(ክፍል አራት)
~
ኢብኑ ጀሪር አጦ፞በሪይ ረሒመሁላ፞ህ እንዲህ ይላሉ:—

"በሐጅ ወቅት መካ ውስጥ ነበርኩ። አንድ ከኹራሳን የሆነ ሰው ‘እናንተ ሑጃጆች ሆይ! እናንተ የመካ ሰዎች ሆይ! ነዋሪዎች! መጤዎች! አንድ ሺህ ዲናር የያዘ ከረጢት ጠፍቶብኛል። የመለሰልኝ ሰው አላህ ምንዳውን ይክፈለው። ከእሳትም ነፃ ያድርገው። በምርመራው ቀንም ምንዳና ሽልማት ይኖረዋል’ ሲል ሰማሁት።

በዚህን ጊዜ ከመካ ነዋሪዎች ውስጥ አንድ ትልቅ አዛውንት ተነሳና ‘አንተ ኹራሳኒዩ ሆይ! ሃገራችን ሁኔታዋ የከፋ ነው። የሐጅ ቀናት ጥቂት ናቸው። ክብረ በአላቱም ውስን ናቸው። የስራ በሮች ተዘግተዋል። ምናልባትም ይሄ ገንዘብ ከድሃ አማኝ፣ ከትልቅ አዛውንት እጅ ወድቆ ወሮታውን እንድትሰጠው ቃል እንድትገባለት ሊከጅል ይችላልና ገንዘቡን ቢመልስ ትንሽ ሐላል ገንዘብ ትቸረዋለህ ወይ?’ አለ።

ኹራሳኒዩ:— ስንት ነው ወሮታው? ስንት ይፈልጋል?
አዛውንቱ:— አንድ አስረኛ ይፈልጋል። መቶ ዲናር። የአንድ ሺው 10%።
ኹራሳኒዩ:— አልተስማማም። ‘አላደርገውም። ይልቅ የዚህን ሰውዬ ጉዳይ ወደ አላህ አስጠጋለሁ። በምናገኘውም (የቂያማ) ቀን ወደሱው እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን፣ ያማረ የሆነ መመኪያ’ አለ።"

ኢብኑ ጀሪር አጦ፞በሪይ ቀጥለው እንዲህ ይላሉ:— "ድሃ ሰው የተባለው ይሄ ሽማግሌ መሰለኝ። ምናልባትም የዲናሮቹን ከረጢት አግኝቶት ከሱ ትንሽ ፈልጎ ነው። ተከተልኩት። ወደቤቱ ተመለሰ። እንደጠረጠርኩት ነበር።

‘ሉባባ ሆይ!’ ብሎ ሚስቱን ሲጣራ ሰማሁት።
‘አቤት የጊያሥ አባት!’ አለች።
‘የገንዘቡን ባለቤት እያፈላለገ ሲጣራ አገኘሁትኮ። ላገኘለት ሰው ምንም ሊሰጥ አይፈልግም። ከሱ ላይ መቶ ዲናር ስጠን ብየው ነበር። እምቢ ብሎ ጉዳዩን ወደ አላህ አስጠጋ። ምን ባደርግ ይሻላል ሉባባ? የግድ መመለስ አለብኝ። እኔ ጌታዬን እፈራለሁ። ወንጀሌ እንዳይደራረብ እሰጋለሁ’ አለ።
በዚህን ጊዜ ሚስቱ እንዲህ አለች:— ‘ሰውየ! እኛኮ ካንተ ጋር ከአምሳ አመት ጀምሮ በድህነት እየማቀቅን ነው። አራት ሴት ልጆች፣ ሁለት እህቶች፣ እኔ፣ እናቴ አለን። አንተ ዘጠነኛችን ነህ። ፍየል የለን፣ የግጦሽ ቦታ የለን። ገንዘቡን ሁሉንም ውሰድ። ተርበናል አጥግበን። ያለንበትን ታውቃለህ አልብሰን። ምናልባትም አላህ — ዐዘ ወጀለ— ከዚያ በኋላ ያብቃቃህ ይሆናል። ያኔ ቤተሰብህን ካበላህ በኋላ ገንዘቡን ትሰጠዋለህ። ወይ ደግሞ በትንሳኤ ቀን እዳህን አላህ ይከፍልልሃል’ አለች።

ሰውየው:— ሉባባ ሆይ! እድሜዬ 86 አመት ከደረሰ በኋላ ሐራም ልበላ ነው? ድህነቴን ይህን ያክል ከታገስኩ በኋላ አካሌን በእሳት ላቃጥል? ለቀብሬ ከቀረብኩ በኋላ የኃያሉን ቁጣ በራሴ ላይ ላስወስን? በፍፁም አላደርገውም ወላ፞ህ!’ አለ።"

ኢብኑ ጀሪር እዚህ ላይ እንዲህ ይላሉ:— "የዚህ ሰውዬና የሚስቱ ነገር እያስደነቀኝ ተመለስኩኝ። በነጋታው ያ የዲናሮቹ ባለቤት ልክ እንደ ትላንቱ ሲጣራ ሰማሁት። ያ አዛውንት ተነሳና
‘አንተ ኹራሳኒዩ! ትላንት ያልኩትን ብዬህ መክሬህ ነበር። ሃገራችን ወላ፞ሂ አዝመራውና እላቢው የቀለለ ነው። ገንዘቡን ያገኘው ሰው ሸሪዐን እንዳይፃረር ትንሽ ገንዘብ ብትሰጠው፤ ላገኘው ሰው መቶ ዲናሮችን ስጠው ብልህ እምቢ ብለሃል። ገንዘብህ አላህን — ዐዘ ወጀለ— ከሚፈራ ሰው እጅ ላይ ቢወድቅ በመቶው ፋንታ አስር ዲናሮችን ብቻ ብትሰጠው ምናለበት? እነሱንም ይሰትራቸዋል፣ ይሸፍናቸዋል፣ ቀለብም ይሆናቸዋል’ አለ።

ኹራሳኒዩ:— ‘አላደርገውም። ገንዘቤን ከጌታዬ ዘንድ እተሳሰበዋለሁ። በትንሳኤ ቀንም ወደሱ እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን ምን ያማረ የሆነ መመኪያ ነው’ አለ።"

"በቀጣዩም ቀን የዲናሮቹ ባለቤት እንደቀደሙት ቀናት ጥሪውን አስተጋባ። አሁንም ያ ሽማግሌ ተነሳና እንዲህ አለ:—
‘አንተ ኹራሳኒዩ! የመጀመሪያ ቀን ላይ ገንዘቡን ላገኘው ሰው መቶ ዲናር ስጠው ብዬህ እምቢ ብለሃል። ከዚያ አስር አልኩህ እምቢ አልክ። እሺ አንድ ዲናር ብትሰጠውና በግማሿ የሚፈልጋትን ነገር ቢሸምት፣ በግማሿ ደግሞ የሚያልባት ፍየል ቢገዛና ሰዎችን እያጠጣ ገቢ ቢያገኝ፣ ልጆቹን እያጠጣም ምንዳውን ቢያስብ ምናለበት?’
ኹራሳኒዩ:— ‘አላደርገውም። ለአላህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። በቂያማ ቀንም ከጌታዬ ዘንድ እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን ምን ያማረ የሆነ መመኪያ ነው።’
ሽማግሌው:— ሰውየውን ልብሱን ጎተተውና ‘ና ተከተለኝ። ዲናሮችህን ውሰድና ሌሊቱን እንድተኛ ተወኝ። ይህንን ገንዘብ ካገኘሁበት እለት ጀምሮ ሰላም አላገኘሁም’ አለ።

ኢብኑ ጀሪር ቀጥለው እንዲህ ይላሉ:— "ባለ ዲናሩ ሰውየ ከሽማግሌው ጋር ሄደ። ተከተልኳቸው። ሽማግሌው ከቤቱ ገባ። መሬት ቆፍሮ ዲናሮቹን አወጣና ‘ገንዘብህን ውሰድ። አላህን ይቅር እንዲለኝና ከትሩፋቱ እንዲለግሰኝ እለምነዋለሁ’ አለ።”
ኹራሳኒዩ:— ተቀበለና መውጣት አሰበ። በሩ ጋር ሲደርስ እንዲህ አለ:— ‘አንተ አዛውንት ሆይ! እኔ አባቴ ሶስት ሺህ ዲናር ትቶ ሞቷል፣ አላህ ይዘንለትና። እና ‘ሲሶውን አንተ ይበልጥ ይገባዋል ለምትለው ስጥ’ ብሎኝ ነበር። በዚህ ከረጢት ውስጥ ያስቀመጥኩት ለሚገባው ለመስጠት ነው። በአላህ ይሁንብኝ! ከኹራሳን ከወጣሁ ጀምሮ እዚህ እስከምደርስ ድረስ ካንተ የበለጠ የሚገባው ሰው አላየሁም። ስለዚህ ውሰደው አላህ ይባርክልህና። አማናህን ስለተወጣህ፣ በድህነትህ ላይ ስለታገስክ አላህ በመልካም ይመንዳህ’ አለና ገንዘቡን ትቶ ሄደ። ሽማግሌው ተነስቶ አላህን እየተማፀነ ማልቀስ ያዘ። እንዲህም አለ:— ‘የዚህን ገንዘብ ባለቤት (ሟቹን) በቀብሩ ውስጥ አላህ ይዘንለት። በልጁም ይባርክለት።’

ምንጭ:— [ጀምሀረቱል አጅዛኢል ሐዲሢያ፞ህ: 251]

ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል:—
{ذَلِكُمْ يُوعَظُ بِهِ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَمَنْ يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَلْ لَهُ مَخْرَجًا (٢) وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ وَمَنْ يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ إِنَّ اللَّهَ بَالِغُ أَمْرِهِ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لِكُلِّ شَيْءٍ قَدْرًا}
"ይህ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰፅበታል። አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል። ከማያስበውም በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል። በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው። አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው። አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል።" [አጦ፞ላቅ: 2–3]
=
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ዳዒያው ሆይ! አስመሳይ እንዳትሆን ተጠንቀቅ!
~
ታላቁ ኢትዮጵያዊ ዓሊም ሙሐመድ አማን አልጃሚ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
“ከሁሉም ሰው ዘንድ ተወዳጅ መሆን የሚፈልግ፤ በተለያዩ ደረጃዎች፣ ዝንባሌዎችና ቡድኖች ላይ ሆነው ሳለ ሁሉም የሚወዱት ዳዒያህ አስመሳይ ነው!! ሁሉንም ሰው ሊያስደስት፣ ማንም እንዳይቆጣበት የሚጥር፣ ሁሉም “እከሌ ሚዛናዊ ነው፣ ረባሽ አይደለም” የሚለው ዳዒያህ፣ ሁሉም ቡድኖች፣ ሁሉም አንጃዎች፣ ሁሉም ጭፍራዎች፣ የተለያየ የአስተሳሰብ አቅጣጫዎች ላይ ያሉ ሁሉም ሰዎች የሚወዱለት ሰው ይህ አስመሳይ ሙ^ና^ፊ^ቅ ነው፡፡ በዚህ ላይ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ምክንያቱም ይሄ የማይሆን ነውና፡፡ ሻፊዒይ ረሒመሁላህ እንዳሉት 'ሁሉን ሰው ማስደሰት የማይደረስበት ግብ ነው።'

ስለዚህ ሁሉንም ሰው አስደስታለሁ ብለህ መጣርህ የማይደረስበት ህልም ነው፡፡ ይልቅ የሚደረስበትና የሚፈለግ ግብ አለ፡፡ የሰውን ሁሉ ውዴታ ማግኘት የማይደረስበት እና የማይፈለግ ግብ ነው፡፡ የጠራውን ጌታ ውዴታ ማግኘት ግን አላህ ላደለውና ውዴታው ላጋጠመው የሚገኝ ግብ ነው፡፡ እናም ውዴታው የሚገኝና የሚፈለግ ግብ ነው፡፡ ስለዚህ ዳዒያህ የሆነ ሰው ወደ ደዕዋ አደባባይ ሲወርድ ሀሳቡ ይሄ ነው መሆን ያለበት፡፡ ይህን ማድረግ ያልቻለ ከቤቱ ይቀመጥ!!”
[ሸርሑ ሹሩጢ ላኢላሀኢለላህ፡ 102-103]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በቡድን የመጥጠርነፍ ጣጣ
~
በደዕዋ ላይ የተሰማራ ወይም ወደ ደዕዋ የተጠጋ ሰው ለሌሎች የሚያሳድረው ውግንናም ይሁን ጥላቻው ቡድናዊ ተፅእኖ የተጫነው እንዳይሆን ሊጠነቀቅ ይገባል። በተቋማትና ማህበራት የታቀፉም ይሁኑ በሆነ የጋራ አመለካከት የተሳሰሩ አካላት ጥንቃቄ ካላደረጉ ስብስባቸውን ያማከለ ቡድናዊ ዝንባሌ (ተሐዙብ) የሚይዙበት ሁኔታ ሰፊ ነው። ስብስቡን ወይም የጭፍራውን ቁንጮዎች በጭፍን የመከተል ጥፋት ሊኖር ስለሚችል መጠንቀቅ ይገባል። ብዙ ጭፍራዎች የፖለቲካ ፓርቲዎች አይነት ጥርነፋ አላቸው። በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በአብዛኛው አባላት ባያምኑበት እንኳ የፓርቲውን እንጂ የግላቸውን አቋም ባደባባይ አያንፀባርቁም። በኢስላም ስም የሚደራጁ ስብስቦችም ይሄ ባህሪ የሚታይባቸው በብዛት ይገጥማሉ። ማዶና ማዶ ከሚኖሩ አሰላለፎች ሁለት ምሳሌ ልጥቀስ።

1ኛ፦ መፅነፍ፦

የፀነፈ አቋም ለደዕዋ እንደማያዛልቅ፣ የትም እንደማያደርስ፣ በመጨረሻም እርስ በርስ መበላላትን እንደሚያስከትል የታወቀ ነው። ይሄ ከጥንት እስከ ዛሬ ያሉ ፖለቲካዊም ይሁን ሃይማኖታዊ አደረጃጀቶችን ያየ ሁሉ የሚያስተውለው ነው። በዚያ ላይ በተመሳሳይ አጀንዳ አንዱን መውጋት፣ ሌላውን ማለፍ አይነት መርህ የለሽነት ላይ ይጥላል።

ነጥቤ ምንድነው? በዚህ አይነት ስብስብ ታቅፈው ግን ውስጥ ላይ ችግሮች መኖራቸውን እያወቁ "ለምን?" ለማለት በመንጋው እንዳይወገሩ ፈርተው በዝምታ የሚጓዙ አካላት አሉ። "ለምን?" ያሉ ለታ የሚወሰድባቸው እርምጃ ማዶ ላይ ካሉት የከፋ ስለሚሆን በቡድን ተጠርንፈው፣ በፍርሃት ተሸብበው፣ ውስጣቸው ያለውን እምነት መኖር አቅቷቸው ካቦዎቹ በቀደዱላቸው ቦይ ይፈስሳሉ። ይሄ በብዙ ፅንፈኛ ቡድኖች ውስጥ ያለ ተጨባጭ ነው።

2ኛ፦ መላሸቅ፦

በዚህም ላይ አንዳንዶች የተጨመላለቀ አካሄድ በጭፍራቸው ሲፈፀም ሲያዩ ከመሸማቀቅ ውጭ "አልበዛም ወይ?" ለማለት ቡድናዊ ትስስር ወይም ጥቅም ያሰራቸው ብዙ የውስጥ ቆዛሚዎች አሉ። መላሸቁ በበዛ ቁጥር ቁዘማቸው ይረዝማል። ውስጣቸው ይታመማል። ቢሆንም ራሳቸውን መሆን መወሰን አይችሉም። ራሳቸውን ችለው ቢንቀሳቀሱ ከዚህ ሰቀቀን ነፃ ይሆኑ ነበር። ችግሩ ቀድመው በቡድን ተጠርንፈዋል። የጭፍራው ካቦዎች በተጣጠፉ ቁጥር ያለምርጫቸው ይተጣጠፋሉ። በወረዱበት ቁልቁለት ሁሉ ይወርዳሉ። በማያምኑበት መድረክ ሲያሰማሯቸው ይሰማራሉ። ወይ ራሳቸውን ከጥፋቱ አግልለው ሰላም አያገኙ። ወይ ጭንቅላታቸውን እንደ ካቦዎቻቸው ደፍነው አይገላገሉ። እንዲሁ ከሁለት ያጣ ጎመን።

በየትኛውም ቡድንተኛ ጭፍራ ውስጥ መጥጠርነፍ የህሊና ሰላም፣ የልቦና ረፍት ያሳጣል። ከኢኽላስ ያርቃል። አስመሳይነትን ያላብሳል። መርህ የለሽ ያደርጋል። ስለዚህ ከራስህ ጋር ተጣልተህ የሌሎች አጫፋሪ ከምትሆን ራስህን ነፃ አውጣ። ከአጉል ስብስብ አግልል። መንጋ ጋር አትጓዝ። እንዲህ አይነት ስብስብን በተመለከተ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
فَاعْتَزِلْ تِلكَ الفِرَقَ كُلَّهَا، ولو أَنْ تَعَضَّ بأَصْلِ شَجَرَةٍ، حتَّى يُدْرِكَكَ المَوْتُ وأَنْتَ علَى ذلكَ!
"ከነዚህ አንጃዎች በሙሉ ራቅ። የዛፍ ስር ነክሰህ መያዝ ቢኖርብህ እንኳ! (ያን አድርገህ ራቅ።) በዚህ ላይ ሆነህ ሞት እስከሚያገኝህ ድረስ።" [አልቡኻሪይ፡ 3606] [ሙስሊም፡ 1847]

የሚገርመው በሁለቱም ጫፎች ተሰልፈው ከነሱ የማይሻሉ አካላት በቀደዱላቸው እየፈሰሱ አበሳቸውን የሚያዩ ክፍሎች መኖራቸው ነው። ወንድሜ ጉዳዩ ከዘላለማዊ ህይወትህ ጋር ይገናኛል። የኣኺራህ ጉዳይ ላይ ሌሎች እንዲወስኑ አትፍቀድ። ከሰመመንህ ውጣ። አይንህን አሸት አሸት አድርግና ከማን ኋላ እንደተሰለፍክ ተመልከት። ልጅ ቢጎትተው፣ ጅል ቤጎትተው ሳያቅማማ የሚከተለው ግመል ነው። ሰው ተደርገህ ተፈጥረሃልና በተግባር ሰው ሁን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus
የብዙዎቻችሁ መልክት ደርሶኛል ለሁላችሁም ጀዛኩሙሏህ ኸይረን ለዱዓችሁ ለሁሉም የሱና ወንድም እህቶቻችን አሏህ ያቆይልን አላህ ይጠብቅልን እናንተንም !

አሏህ ምንም ሳያጎድለን መልሶ ላገናኘን አልሃምዱሊላህ !


Репост из: ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎

ያጀመዓ እንዴት ናችሁ ...?

በአሏህ እገዛ ትላንት ከእስር ቤት ተፈተናል አልሃምዱሊላህ !

ወንድማችሁ ጀማል እንድሮ አቡ መርየም

اللهم لك الحمد

ولله الحمد والمنة


Репост из: ጃዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ የዳዕዋና የቂርዓት ማዕከል {Official Channel }
የደዕዋ ድግስ በደሴ ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ


ታላቅ የምስራች ለደሴ እና አከባቢዋ ሙስሊም ማህበረሰብ  በሙሉ እነሆ የፊታችን እሁድ በቀን 25/05/2017 ዓ·ል  በአላህ ፍቃድ የወሎ መናገሻ እና እንብርት በሆነችው  ደሴ  ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ  ከአድስ አበባ ፣ ከአፋር፣ ከኸሚሴ፣ እና  ከሌሎችም ሀገራት በሚመጡ ብርቅዬ መሻይኾችና ኡስታዞች   ከጧቱ 3:00 ጀምሮ  እጅግ በደመቀ እና ባማረ መልኩ  የደዕዋ ድግስ ተዘጋጅቶ ሲጠብቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው
 
የዕለቱ ተጋባዥ መሻይኾችና ኡስታዞች


① ሸይኽ አወል አህመድ አል ኸሚሴ
ርዕስ:– ረመዷንን እንዴት እንቀበለው

② ኡስታዝ አብዱረህማን ሰዒድ(አቡ ሒዛም)
ርዕስ:–ሱናን አጥብቆ መያዝና ቢድዓን መራቅ(መጠንቀቅ)

③ ኡስታዝ አቡል አባስ (ናስር)
ርዕስ:– የተውሂድ አሳሳቢነትና የሽርክ አደገኝነት እንድሁም በምን ላይ ነው  አንድ የምንሆነው

④ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (ሙሀመድ አህመድ)
ርዕስ:–ኢልምን በመፈለግ ላይ መበርታት፣የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀማችን ምን መምሰል አለበት እና መልካም ስነ ምግባር

ማሳሰቢያ:–ለሴቶችም በቂ ቦታ አለ‼

N·B :– የቻናልና የግሩፕ ባለቤቶች በሙሉ ሼር በማድረግ ተደራሽ አድርጉት 

አዘጋጅ፦ የጀዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ የደዕዋና የቂርዓት ማዕከል


URGENT: - የደሴ ከተማና በዙሪያዋ ያላችሁ ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ ፕሮግራሙ ዘንድ ትታደሙ ዘንድ ጥሪ አድርገንላችኋል።

ጆይን ይበሉ ቻናል

t.me/yedesse_selfyochi_yedewa_channel
ግሩፕ

https://t.me/yedesse_selfyochi_group


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ቅደመ ሁኔታ ላይ የተንጠለጠለ ፍቺ
=
1- ቅደመ ሁኔታ ላይ የተንጠለጠለ ፍቺ (الطلاق المعلق) ማለት ለምሳሌ ሚስቱ ከሆነች ጓደኛዋ ዘንድ መሄዷ ችግር እየፈጠረ እንደሆነ ተረዳ። "አትሂጂ" ቢላት ልትቆም ፈቃደኛ አልሆነችም። በዚህን ጊዜ "ዳግመኛ እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" በማለት ተናገረ። ይህንን ካለ በኋላ ብትሄድ ኒካሑ ወርዶ ፍቺው ይቆጠራልን?
=> ይህንን ሸርጥ የተናገረው ብትሄድ የእውነትም ሊፈታት ወስኖ ከሆነ በመሄዷ ብቻ ኒካሑ ይወርዳል። ፍቺ ተፈፅሟል።
=> ሸርጡን ያስቀመጠው መፍታትን አስቦ ሳይሆን ለማስፈራራት ከሆነ ኒካሑ አይወርድም።

2- ያስቀመጠው ቅድመ-ሁኔታ ቀድሞ በተፈፀመ ጉዳይ ላይ ይሰራልን? ለምሳሌ "እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" የሚል ሸርጥ አስቀመጠ። ይህን ከማለቱ በፊት ቀድማ ሄዳ ከሆነ ፍቺው ይቆጠራልን?

=> ቅድመ ሁኔታውን ሲያስቀምጥ ሃሳቡ ቀድማ ሄዳም ከሆነ "ፈትቻለሁ" የሚል እሳቤን የሚያጠቃልል ከሆነ ፍቺው ይቆጠራል። ከዚህ በኋላ ቢከሰት የሚለውን ብቻ ነይቶ ካወራ ግን በቀደመ ተግባር ፍቺ አይታሰብም።

3- "ይህንን ካደረግሽ ፍቺ ነሽ" ቢልና አውቃ ሳይሆን ረስታው ያንን ነገር ብትፈፅም ኒካሑ ይወርዳልን?
=>አይወርድም።

4- ካስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ መመለስ ይችላል? ለምሳሌ "እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" የሚል ሸርጥ አስቀምጦ ነበር። ያስቀመጠውን ሸርጥ አንስቶ ቢፈቅድላትና ከዚያ በኋላ ብትሄድ ኒካሑ ይወርዳል?
=>ትክክለኛው አቋም አይወርድም የሚለው ነው።

5- ሚስቱን በሆነ ሰበብ ከፈታ በኋላ ሰበቡ ልክ እንዳልሆነ ካወቀስ? ለምሳሌ፦ ሚስቱ በሆነ ጉዳይ ላይ እንደዋሸችው ወይም ከቤቱ ወንድ እንዳስገባች ተረድቶ ፈታ። ሲያጣራ ግን ጉዳዩ እሱ እንዳሰበው እንዳልሆነ አወቀ። ኒካሑ ይወርዳል ወይ?
=>ኢብኑ ተይሚያ፣ ኢብኑ ባዝ እና ኢብኑ ዑሠይሚን ኒካሑ አይወርድም ብለዋል።
=
ከሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም ፈትሑል ዐላም ኪታብ (8/543 - 554) ተጨምቆ የቀረበ።
ማሳሰቢያ:- መልእክቱ እንዲህ አይነት ጉዳይ ከገጠመ ሑክሙ ምን እንደሆነ ለማስታወስ የቀረበ እንጂ የኒካሕ እና የፍቺ ጉዳይ በሃላፊነት ሊያዝ ተገቢው ክብደት ሊስሰጠው ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኢብኑ ሐዝም እንዲህ ይላሉ፦
"ወደ ጓደኛህ ነፍሱን የሚያሳምመው እና በማወቁ የማይጠቀምበት የሆነን ነገር አታድርሰው። ይሄ የወራዶች ተግባር ነው።" [ረሳኢሉ ኢብኒ ሐዝም፡ 106]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል
(من رأى منكم منكرا فليغيره بيده فإن لم يستطع فبلسانه فإن لم يستطع فبقلبه وذلك أضعف الإيمان).
"ከናንተ መጥፎን ነገር የተመለከተ በእጁ ይቀይረው (ያስወግደው)። ካልቻለ በምላሱ። ካልቻለ ደግሞ በልቡ። ይሄ ግን ደካማው ኢማን ነው።" [ሙስሊም: 186]
ከሐዲሡ የሚወሰዱ ቁም ነገሮች:–

① ከመጥፎ መከልከል ነፍስ ወከፋዊ ሃላፊነት እንደሆነ፣
② ከመጥፎ መከልከል የተለያዩ ደረጃዎች ስላሉት ሁኔታዎችን እና ተገቢ እርምጃዎችን መለየት እንደሚያስፈልግ፣
③ በእጅ ወይም በአንደበት ጥፋትን ለማስወገድ አቅም እንደሚያስፈልግ፣
④ ጥፋትን በልቡም የማይጠላ ሰው ኢማኑ ከዝቅተኛ ወለልም በታች በመውረዱ ከባድ አደጋ ላይ እንደሆነ
⑤ ኢማን ከልባዊ እምነት ባለፈ ተግባርንም እንደሚጨምር
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የደዕዋ ፕሮግራም
~
ዛሬ ቅዳሜ ቀጥታ ከዙህር ሶላት በኋላ
ቦታ፦ አፍንጮ በር ፣ አቅሷ መስጂድ

ተጋባዥ እንግዶች
አቡል ዐባስ
እና
ኢብኑ ሙነወር

በ 6ኪሎ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማ0 የተሰናዳ


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ካለመማር የማይሻል መማርማ አለ
~
አዎ አለመማር ያሳፍራል፣ ያስቆጫል እንጂ አያኮራም። በተለይ በዚህ ዘመን ያለው አለመማር ቀደም ባለው ዘመን ከነበረው አለመማር የከፋ ጉዳት አለው። ቆም ብሎ ያስተዋለ ብዙ ሰበዞችን መምዘዝ ይችላል።
መማር የአስተሳሰብ አድማስን ያሰፋል። የማስተዋል አቅምን ያዳብራል። ሌላው ቀርቶ በሃገራችን ተጨባጭ የዲን ሰዎች እንኳ አካደሚ ትምህርት መማራቸው ይህንን ካላገኙት የተሻለ ብስለትና አቀራረብ ሲንፀባረቅባቸው፣ ያልተማሩት ደግሞ በዚህ ረገድ የጎላ ክፍተት ሲታይባቸው ያጋጥማል። ሁሉን ማለቴ አይደለም።
ግን መማር ምንድነው? ካምፓስ ደርሶ መመለስ ነው መማር? ዲግሪ መቁጠር ነው መማር? እንግሊዝኛ መቀላቀል ነው መማር? መማር ምንድነው?
በርግጥ መማር ብዙ እርከን አለው። ቀለም መቅመስ፣ ክፍል መቁጠር፣ ዲግሪ መደርደር ብቻውን መማር አይደለም። መማር መለወጥ ነው። መማር ለህይወት ዋጋ መስጠት ነው። መማር በህሊና መኖር ነው። መማር ለወጡበት ማህበረሰብ ቅን መሆን ነው። መማር ለራስ የማይወዱትን ነገር ሌሎች ላይ አለማድረስ ነው። ይሄ ደግሞ ጥልቅ ንባብ፣ ማሰላሰል፣ አእምሮን ማስፋት፣ የተማሩትን ሆኖ መገኘት ይጠይቃል። በሃገራችን ተጨባጭ አብዛኛው "ምሁር" በዚህ ረገድ ሲታይ ተምሯል ለማለት ይከብዳል።

የትምህርት ስርአታችን በራሱ በሳል ትውልድ የሚመረትበት ከመሆን ይልቅ ለሃገር ፀር፣ ለወገን ጠንቅ የሆኑ መርዛማ ትውልዶችን ወይም ሻል ካለ ካንገት በላይ ሳይሆን ካንገት በታች የሰፉ ሆድ አደር አድር ባይ የሃገር ሸክሞችን ነው እያመረተ ያለው። የትምህርት ስርአታችን አባት አጥቷል። የተቋቋመበትን አላማ ዘንግቷል። በርካሽ ጥቅማጥቅም ፍትህ እየሸጠ ያለው ዳኛ፣ ethicሱን የረገጠ ሃኪም፣ የህዝብ እንባ የማይገርመው civil servant፣ የሃገርን እድገቱ በራሱ የተንጣለለ ቪላ እና የተንደላቀቀ ህይወት የሚመዝን ሹመኛ፣ ጥላቻ እየቸርቸረ በህዝብ ስም የሚነግድ የደም ነጋዴ የሆነ ፖለቲከኛ፣ ሚዲያን ያክል ትልቅ የለውጥ መሳሪያ ይዞ ሳለ ድባቡን እንዳለ በክፋት፣ በአድር ባይነት፣ በአርቲቡርቲ የሞላው ጋዜጠኛ፣ ... የትምህርት ስርአታችን እንዲህ አይነት ጃርቶችን ነው ያፈራውና እያፈራ ያለው።

የማህበረሰብን ለዘመናት የዘለቀ በሰላም አብሮ የመኖር እሴት የሚንድ፣ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ፣ በህዝብ መሃል መርዝ የሚዘራ መርዝ ትውልድ ቢማርም አልተማረም። ይህ ዘር እየመነዘረ ለተማሪዎቹ ውጤት የሚሰጥ "ምሁር" ተምሯል ሊባል አይችልም። ይሄ ሃይማኖት እየለየ ታዳጊ ልጆችን ከትምህርት ገበታ እየገፋ ያለው ገ ልቱ ፍጡር ለስሙ ካምፓስ ተመላልሷል እንጂ አእምሮው የሸረሪት ድር ያደራበት ኦና ቤት ነው። አልተማረም። የገዛ ወገኑ በኑሮ ስንክሳር ጎብጦ፣ በመከራው ላይ መከራ፣ በችግሩ ላይ ችግር የሚደራርብ ህሊና ቢስ ፖለቲከኛ ከተማሩት የሚቆጠር አይደለም። ወጣቱ ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ሲሄድ እየተመለከተ እውነቱን የማይጋፈጥና መንጋ የሚፈራ አድር ባይ ምሁር ከመሀይም አይሻልም። ከወጣበት ማህበረሰብ ይልቅ ለአላፊ ስርአት ጥብቅና እየቆመ በወገኑ መከራ ላይ አይኑን ጨፍኖ ምናባዊ የተድላ ዓለም ያለን ያህል ሰርክ የሚያሰኩር "ሊቅ" ሞኑን ተማረው?! ይሄ መደ ንቆር እንጂ መማር አይደለም።

እና ምን ለማለት ነው? ሰው በሃገራችን ተጨባጭ መማርን ቢወቅስ አትፍረዱበት ለማለት ነው። ሃሳቡ ልክ ባይሆንም ጤነኛ ምሳሌ አጥቷል። ከተማሩት የሚያየው ሁሉ ግራ የሚያጋባ ነው። የመማር ትርጉሙ ምን እንደሆነ እንዲደበዝዝበት ተደርጓል። ተምሯል፣ ተመራምሯል፣ ለሃገር ለወገን ይጠቅማል ብሎ ተስፋ የጣለበት አካል ጭራሽ ተስፋውን የሚነጥቅ ሲሆንበት እንዴት ግራ አይጋባ?!
"እዩልኝ ስሙልኝ ሰው ይፈርዳል በኔ
በግንቦት አግብቻት ወለደች በሰኔ" አለ ግራ የገባው። ግራ የገባው ሰው ብዙ ይላል። እውነት ለመናገር የኢትዮጵያ ምሁር ነገር ላልተማረው ቀርቶ ህሊና ላለው ሁሉ ግራ የሚያጋባ ነው። እና ያልተማረው ምን ያድርግ? ባየው ፈረደ። ቢሆንም! ቢሆንም! ቢሆንም አለመማር አያኮራም። አለመማር ይሻላል እያልክ በነውርህ እንዳትመፃደቅ። አለመማር ስንኩልነት እንጂ ጌጥ አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor




Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ስለ ክብርህ ስትል ተዋቸው
~
የሰው ልጅ አመል እንደ መልኩ ብዙ አይነት ነው። ብዙ ደግ የመኖሩን ያህል በየትኛውም ሁኔታ መጥፎህን ብቻ ለማውራት ያሰፈሰፈ አለ። ልቡ በክፋት የተሞላ። በጎህን ሲያይ ይከፋዋል። ሰዎች በመልካም ቢያነሱህ ያመዋል። ያለ ስምህ ስም ይሰጥሃል። ያለ ግብርህ ያሸክምሃል። በሌለህበት ያውልሃል። ያለህን መልካም ይገፍሃል። ክፉህን ቢያይ ይቦርቃል። ሰዎች ቢያወግዙህ አታሞ ይመታል። ይቅርታህ አይዋጠውም። ዝምታህ አይጥመውም። ምላሽህም አይመቸውም። የቱንም ብታደርግ አታስደስተውም። ስህተት ቢያገኝ ጭራና ቀንድ አውጥቶለት ቆርጦ፣ ቀጣጥሎ ጭራቅ ያደርግሃል። ንግግርህን ፈፅሞ ባላሰብከው መልኩ ተርጉሞ ራሱ አጣሞ በተረዳው ላይ ተመርኩዞ ነብር ግስላ ሆኖ ይነሳብሃል።

በቃ! አንዳንዱ ባህሪው የውሻ አይነት ነው። ባለፍክ ባገደምክ ቁጥር ይጮሃል። "ዋው!" ማለትን የመተንፈስ ያህል ኖርማል አድርጎታል። ብትነካውም ይጮሃል። ብትተውም ይጮሃል። እንዲያውም ውሻ ሲያይህ ነው የሚጮኸው። ይሄኛው ሳያይህም ይጮሃል። "አትርሱኝ" ባይ ነገር ነው። በሌለህበትም፣ ሳታስታውሰውም ይጮሃል። በየትኛውም ሁኔታ ሊነድፍህ ስለተዘጋጀ ተያያዥ ጉዳይ እስከሚያገኝ አይታገስም። ይበላዋል። ያሳከዋል። ስለ ጦሃራ ስታወራ "ዋው!" ስለ ተውሒድ ስትናገር "ዋው!" ስለ ራስህ ብታነሳ "ዋው!" ራሱ የሚደግፈውን ሃሳብ ብታነሳም "ዋው!" ከማለት አይመለስም። ብትመልስለት አገር በጩኸት ያቀጣጥላል። ዝም ስትለውም ወይ አጀንዳ ፈጥሮ፣ ወይ "አሸነፍኩ" ብሎ ይጮሃል።
እና ምን ይሻላል? ጩኸቱን ላታስቆመው ነገር አትጨነቅ። እርሳው። ሰላምህ ያለው እሱን ከመርሳት ነው። ሊፈትንህ ይችላል። ከዚህ ውጭ ያለው ምርጫ ግን የበለጠ ፈታኝ ነው። አሕመድ ሻኪር - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦

"የማያውቅ ሁሉ ይወቅ! ምድር ላይ ሞኞች ብዙ ናቸው። እና አንድ ሰው ከሞኝ ለሚንፀባረቅ ሞኝነት ሁሉ የሚበሳጭ ከሆነ በብስጭቱ ሰበብ ብሶት መከፋቱ ይራዘማል። ሞኞችን ያሻቸውን ይበሉ ተዋቸው። ለክብርህ ስስት ይኑርህ። ክብርህ ለሞኞች ምላስ ተብሎ የሚመነዘር ከመሆን በላይ ውድ ነውና።"
[መጅሙዑል መቃላት፡ 1/579]
=
Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሴኩላሪዝም ማለት መንግስትን ከሃይማኖት መነጠል ማለት ነው። ኢትዮጵያ ሲደርስ ግን ትርጉሙን ይቀይራል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሴኩላሪዝም ማለት ሙስሊም ተማሪዎችን እምነታዊ አለባበሳቸውን ሰበብ እያደረጉ ከትምህርት ማእድ ማራቅ ነው። ሴኩላሪዝም ለሽፋንነት ይነሳል እንጂ አላማው በአፄው ዘመን የነበረውን ሙስሊሞችን ከትምህርት ማእድ የማራቅን ክፋት ማስቀጠል ነው። ሴኩላሪዝም ማመሀኛ ብቻ ነው። ከድሮው በተሻለ ወደ ትምህርት የዞረው የሙስሊም ቁጥር በአንፃራዊነት ጨምሯል። ይሄ ሐቅ እንቅልፍ የሚነሳቸው፣ የተማረውን ሙስሊም እንደ ስጋት የሚያዩ አካላት ታዲያ ስልጣናቸውን በመጠቀም ሰበብ እየፈለጉ ሙስሊሙን ከትምህርት ለማራቅ የማይፈነቅሉት ድንጋይ ነው።

ፈተናዎቹን ሁሉ እንደ ምንም ተቋቋመህ ተማር ወገኔ። ጠላት መማርህን እንደ ስጋት ቆጥሮ በዚህ ልክ ተግቶ ከትምህርት ሊያፈናቅልህ የሚተጋው ለምን እንደሆነ ይግባህ። ራስህንም ሆነ ልጆችህን ከትምህርት ገበታ በማራቅ ባላሰብከው አቅጣጫ የጠላት አጀንዳ እያሳካህ እንዳይሆን ተጠንቀቅ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ትራንስፖርት ላይ ሆኖ የሶላት ወቅት እንዳያልፈው የሰጋ ሰው ምን ያድርግ?
~
1- በመጀመሪያ በወቅቱ ለመስገድ መጣር አለበት። ለምሳሌ ከመሳፈሩ በፊት መስገድ ከቻለ ይሰግዳል። ወይም ጉዞውን ቀደም ብሎ በመፈፀም ከዚያ ሶላቱን በወቅቱ ይሰግዳል። ባጭሩ እስከቻለ ድረስ ጉዞውን ከሶላቱ ወቅት ጋር በማይጋጭ መልኩ ያመቻች። ሾፌሩን አናግሮ ወርዶ የሚሰግድበት እድል ካለ የአፈፃፀም ስርአቶቹ ያልተጠበቀ ሶላት መኪና ውስጥ ሊሰግድ አይገባም። ስለዚህ ለሶላቱ ትኩረት ይስጥ።
2- በወቅቱ ለመስገድ ካልቻለስ? ጀምዕ ማድረግ የሚቻል ሶላት ከሆነ ለምሳሌ ዙህር እና ዐስር ወይም መግሪብ እና ዒሻእ ከሆኑ በማስቀደም ወይም በማዘግየት ሁለቱን ሶላት በአንደኛው ወቅት በስርአት መስገድ ይችላል። ሙሳፊር ቢሆንም ባይሆንም። ወይ ወደ መጓጓዣው ከመግባቱ በፊት አስቀድሞ ወይ ደግሞ ከመጓጓዣው ሲወርድ አዘግይቶ በስርአቱ ይሰግዳል። በስርአቱ ስል በወቅቱ ለመስገድ ብሎ መኪና ውስጥ አርካኖችን ሳያሟላ እንዳይሰግድ ነው።
3- ሶላቱ ጀምዕ ለማድረግ የማይመች ከሆነስ? ለምሳሌ የሱብሕ ሶላት ወቅት ሳይገባ ተሳፈረ። ወይም ከዙህር በኋላ ቀድሞ ያልታሰበ ጉዞ ጀምሮ ትራንስፖርት ላይ እያለ የዐስር ወቅት ሊወጣበት ሆነ። መኪናው ወቅት ሳይወጣ የማይቆም ከሆነበት ምን ያድርግ? ወቅቱ ሳይወጣ መኪናው ላይ ይሰግዳል። መኪናው ላይ መቆም ከቻለ ይቆማል። ካልቻለ በተቀመጠበት ሆኖ ይሰግዳል። ሩኩዕ እና ሱጁድ ለማድረግ ካልተመቸ ጎንበስ እያለ ይፈፅማል። ለሱጁዱ ከሩኩዑ ይበልጥ ዝቅ ይላል። ውዱእ ከሌለው ተየሙም ያደርጋል።
4- ቂብላን በተመለከተ በሙሉ ሶላቱ ወደ ቂብላ መዞር ከቻለ ለግዴታ ሶላት ቂብላን መቅጣጨት ግዴታ ነው። ካልቻለ ሶላቱ ሲጀምር ወደ ቂብላ ዙሮ ይጀምራል። ከዚያ በኋላ መኪናው ቂብላውን ቢለቅም ባለበት ይሰግዳል።

(ሼር ብታደርጉት ባረከላሁ ፊኩም።)
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ጀምዕ የሚደረጉ ሶላቶች
~
1- ጀምዕ ማለት ሁለት ተከታታይ ሶላቶችን በአንደኛው ወቅት መስገድ ነው። ጀምዕ የሚደረጉት ሶላቶች የሚከተሉት ናቸው፦
- ዙህር እና ዐስርን በአንደኛው ወቅት
- መግሪብ እና ዒሻእን እንዲሁ በአንደኛው ወቅት መስገድ ይቻላል።
ከዚህ ውጭ ጀምዕ የለም። የሱብሕ ሶላት ከየትኛውም ሶላት ጋር ጀምዕ አትደረግም። እሷም ወደ ሌላ ወቅት አትውወሰድም። ሌሎችም ሶላቶች ወደሷ አይውወሰዱም። 0ስርን ከመግሪብ ጋር ጀምዕ ማድረግም አይቻልም።

2- ጀምዕ በሁለት መልኩ ሊፈፀም ይችላል።
1ኛው፦ የኋለኛውን ሶላት ወደ መጀመሪያው በማምጣት። ይሄ ጀምዑ ተቅዲም ይባላል። ዐስርን ከዙህር ጋር በዙህር ወቅት ፤ ወይም ዒሻእን ከመግሪብ ጋር በመግሪብ ወቅት መስገድ ነው።
2ኛው ጀምዑ ተእኺር ይባላል። የመጀመሪያውን ሶላት ወደ ኋለኛው ወስዶ መስገድ ነው። ይህም ዙህር እና ዐስርን በዐስር ወቅት ፤ መግሪብንና ዒሻእን በዒሻእ ወቅት መስገድ ነው።

3- ጀምዕ ከሐጃ ጋር የተያያዘ ነው። መንገደኛም ይሁን በሃገሩ ኗሪ ሶላትን በወቅቱ መስገዱ የሚከብደው ከሆነ ሁለቱን ሶላት በአንደኛው ሶላት ወቅት ጀምዕ ማድረግ ይችላል። ህመምተኛ፣ ነፍሰ ጡር፣ አጥቢ፣ ሌሎችም እያንዳንዱን ሶላት በወቅቱ መስገዳቸው የሚከብዳቸው አካላት በዚህ መልኩ ሊፈጽሙ ይችላሉ። ልብ በሉ! ያለ ተጨባጭ ምክንያት ልማድ እንዲያደርጉ አይደለም።

4ኛ፦ በጀምዕ ጊዜ የሶላቶቹን ቅደም ተከተል መጠበቅ ይገባል። ዙህር እና ዐስርን ጀምዕ የሚያደርግ ሰው ጀምዑ ተቅዲምም ይሁን ጀምዑ ተእኺር መጀመሪያ ዙህርን ያስቀድማል። ካሰላመተ በኋላ 0ስርን ይሰግዳል። መግሪብ እና ዒሻእን ጀምዕ የሚያደርግም ሰው እንዲሁ መጀመሪያ መግሪብን ይሰግዳል። ካሰላመተ በኋላ ዒሻእን ያስከትላል።

5ኛ፦ ጀምዕ እና ቀስር ተያያዥ አይደሉም። ቀስር ማለት ባለ አራት ረከዐ ሶላቶችን ሁለት አድርጎ አሳጥሮ መስገድ ነው። ይሄ ጉዞ ላይ ላለ ሰው ብቻ የሚፈቀድ ነው። በሃገሩ ኗሪ የሆነ ሰው አራቱን ረከዐ ሁለት አድርጎ ማሳጠር አይፈቀድለትም። እንዲሁም ማሳጠር ሱብሕ እና መግሪብን አይመለከትም። በየትኛውም ሁኔታ የረከዐቸው ቁጥር አይቀየርም።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

Показано 20 последних публикаций.