Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሰው መሳይ በሸንጎዎችን እየተጠነቀቅን
~
ከሸሪዐ አንፃር የፖለቲካና አስተዳደር ርእስ ከፊቅህ ርእሶች የቀለለ አይደለም። ስለ ጦሀራ፣ ስለ ዘካ፣ ስለ ... የረባ ግንዛቤ እንደሌለን አውቀን ፀጥ ብለን እያሳለፍን ፖለቲካው ላይ ሲደርስ ነብር፣ ነብር የሚሰራን በሁለት ምክንያቶች ነው።
1ኛው ምክንያት ስለ ፖለቲካ ማውራት፣ የሃገራት መሪዎችን ማብጠልጠል የንቃት ማሳያ ስለሚመስለን ነው። "ሁሉም ስለ ፖለቲካ እያወራ ነው። እኔ ከማን አንሳለሁ" አይነት ስሜት። በዚህ ግልብ ድምዳሜ የተነሳ ከኛ የተለየ ሃሳብ የያዘውን ሁሉ ዑለማኦችን ጭምር በአሸርጋጅነት፣ በአሽቃባጭነት በመፈረጅ "ችሎታችንን" ልናሳይ እንጋጋጣለን።
ሁለተኛው ምክንያት አለማወቃችን እየሰጠን ያለው ድፍረት ነው። ፖለቲካ 1 + 1 = 2 አይነት የልጅ ሂሳብ አይደለም።
* ፖለቲካ ጥልቅ ንባብ ይፈልጋል። ዛሬ ስለ ፖለቲካ የሚፈተፍተው ግን ጥልቅ ንባብ ሊኖረው ቀርቶ ዘለግ ያለ የፌስቡክ ልጥፍ ጨርሶ ለማንበብ ትእግስት የለውም።
* ፖለቲካን በኢስላም መነፅር ለመመልከት ጥልቅ የሸሪዐ ግንዛቤም ይፈልጋል። ግንዛቤው ግልብ የሆነ ሰው ደግሞ አቅሙን ሊያውቅ ይገባል። ከጋዜጠኛ፣ አክቲቪስት እና ተንታኝ ኋላ ሳይሆን ከዓሊሞች ኋላ ነው መሰለፍ ያለበት። አላህ እንዲህ ይላል:-
{وَإِذَا جَاۤءَهُمۡ أَمۡرࣱ مِّنَ ٱلۡأَمۡنِ أَوِ ٱلۡخَوۡفِ أَذَاعُوا۟ بِهِۦۖ وَلَوۡ رَدُّوهُ إِلَى ٱلرَّسُولِ وَإِلَىٰۤ أُو۟لِی ٱلۡأَمۡرِ مِنۡهُمۡ لَعَلِمَهُ ٱلَّذِینَ یَسۡتَنۢبِطُونَهُۥ مِنۡهُمۡۗ وَلَوۡلَا فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَیۡكُمۡ وَرَحۡمَتُهُۥ لَٱتَّبَعۡتُمُ ٱلشَّیۡطَـٰنَ إِلَّا قَلِیلࣰا}
"ከጸጥታ ወይም ከፍርሃት አንዳች (ወሬ) በመጣላቸውም ጊዜ እርሱን ያናፍሳሉ። ወደ መልክተኛውና ከእነርሱ ወደ ትዕዛዙ ባለቤቶች (ወደ ዐዋቂዎቹ) በመለሱት ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ (ነገሩን) የሚያውጣጡት ባወቁት ነበር። በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከጥቂቶች በስተቀር ሰይጣንን በተከተላችሁ ነበር።" [አኒሳእ፡ 83]
አንዳንዴ ሁላችንም የምናውቀው ግልፅ እውነታ የሚይያዝበት መንገድ ሊለያይ ይችላል። በወቅታዊ ወሳኝ ክስተቶችና ሃይሎች የተነሳ፣ በሚታዩ ስጋቶችና ተግዳሮቶች ሳቢያ፣ በአቅም ውስንነትና ጥንካሬ ምክንያት፣ ባጭሩ በተለያዩ ለኛ በሚታዩንም ይሁን በማይታዩን ሃገራዊም ይሁን ህዝባዊ መስለሐዎች እና መፍሰዳዎች የተነሳ ጉዳዮች የሚያዙበት እና የሚተነተኑበት አቅጣጫና መጠን ከጊዜ ጊዜ፣ ከቦታ ቦታ የሚለያይበት ብዙ ሁኔታ አለ። “Politics is more difficult than physics” ይላል አይንስታይን። ፖለቲካ ከፊዚክስ ይከብዳል ማለቱ ነው። ብዙዎቻችን ዘንድ ደግሞ ፖለቲካ ከፊዚክስ ይቀላል። የእውነት ቀሎን ሳይሆን ድንቁ - ርናችን የወለደው ድፍረት ነው።
የምስል ማስታወሻ፦
ሰብሎችን ለመጠበቅ በማለም ከሩቅ ሲያዩት ሰው እንዲመስል ተደርጎ የሚሰራ ነገር በሸንጎ ይባላል። "ሰው መሳይ በሸንጎ" የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር እንደሚታየውና እንደሚታሰበው ያልሆነ አስመሳይ፣ ወስላታ ማለት ነው። ኢስላምን እየታከኩ የሚጽፉ ብዙ ሰው መሳይ በሸንጎዎች አሉ። እነዚህን ቃላት እየከሸኑ ፖለቲካ በመፈትፈት የተጠመዱ አካላት ዑለማእ ላይ ሲዘምቱ እየተከተልን ባንሸወድ መልካም ነው። አብዛኞቹ ከሩቅ እንደሚታዩት አይደሉም። ነገሮች በሸሪዐ ሚዛን እንዴት እንደሚያዙ አያውቁም። መሰረታዊ የተውሒድና የሺርክ ግንዛቤ የላቸውም። ስለ ጀናባ ቢጠየቁ ውሃ የሚያነሳ ነገር መናገር አይችሉም። ዜና በመለቃቀም በድፍረት ከመለቅለቅ ባለፈ መሬት ላይ ያለውንም ተጨባጭ አይረዱም። ለራሳችን ስንል ብንጠነቀቃቸው መልካም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor