Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኡዱሒያ ጋር የሚያያዙ ተጨማሪ ነጥቦች
~
1ኛ፦ የሚታረደው እንስሳ ወንድ ብቻ አይደለም የሚሆነው፣ ሴትም ማረድ ይቻላል። ይሄ የዑለማእ ወጥ ስምምነት (ኢጅማዕ) ያለበት ጉዳይ ነው።
የታረደችው እንስሳ ሆዷ ውስጥ ፅንስ ካለ፣ ካልከበዳቸው መመገብ ይችላሉ። ነብዩ ﷺ ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቁ እንዲህ ብለዋል፦
كُلوه إنْ شِئتُم؛ فإنَّ ذَكاتَه ذَكاةُ أمِّه
"ከፈለጋችሁ ብሉት። የእሱ (የሽሉ) እርድ የእናቱ እርድ ነው።" [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 2827]
ማለትም የሷ ክፍል እንደመሆኑ እሷን ሐላል ያደረጋት እርድ እሱንም ሐላል አድርጎታል ማለታቸው ነው። "ከፈለጋችሁ" ነው ያሉት። ያልፈለገ ለሚፈልግ ሊሰጠው ካልሆነም ሊተወው ይችላል።
2ኛ፦ የሚታረደው እንስሳ ቀንድ ያለው መሆኑ ግዴታ አይደለም። በተፈጥሮው ቀንድ የሌለው ከሆነ ምንም ችግር የለውም።
3ኛ፦ ግልፅ ያልሆኑ ትንንሽ ነውሮች ያሉበትን ማረድ ይቻላል። በጣም አጥብቀን ራሳችንን ልናስቸግር ወይም የተሻለ እንስሳ ልናስመልጥ አይገባም።
4ኛ:- ውጭ ሃገር ለሚኖር ሰው በውክልና የምናርድ ከሆነ ባለ ኡዱሒያው አካል ዒድ ሳይሰግድ ቀድመን ማረድ የለብንም። ይቺን ፈትዋ ማየት ትችላላችሁ። https://t.me/ibnhezam/14606
ስለዚህ ባለ ኡዱሒያዎቹ አውሮፓና አሜሪካ የሚኖሩ ከሆኑ ከኛ ጋር በተመሳሳይ ሰዓት ስለማይሰግዱ እናቆየው። እስከ 13ኛ ቀን ድረስ ማረድ ስለሚቻል ስጋት እንዳይገባን።
5ኛ፦ ስጋውን ከፊሉን ቤት ውስጥ ለእለት ምግብ ማዋል፣ ከፊሉን ማስቀመጥ፣ ከፊሉን ደግሞ ሶደቃ አድርጎ ለሰው መስጠት ይቻላል። 1/3ኛ ለእለት ምግብ፣ 1/3ኛ ለሚቆይ፣ 1/3ኛ ደግሞ ለሶደቃ የሚለው መረጃ የለውም። በዚህም ይሁን በሌላ በፈለገው መልኩ ማከፋፈል ይችላል።
ከፊል ዓሊሞች ትንሽም ቢሆን ሶደቃ መስጠቱ ግዴታ ነው ይላሉ። ነገር ግን አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ሙሉውን መጠቀምም ይቻላል።
https://t.me/ibnhezam/14661
ስለዚህ ለምሳሌ ቤተሰብ የሚበዛበት ሰው እዚያው ሊጠቀመው ይቻላል ማለት ነው።
=
Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor