Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
የሰዎችን ውዴታ መፈለግ የማይገኝ (የማይሳካ) ግብ ነው!!
—————
ሰዎችን እንዲወዱኝ ብለህ መልፋትህ የማይሳካ ግብ ነው። ዛሬ እንዲወዱህ ብታስደስታቸው ያመሰግኑህ ይሆናል፣ ነገ ስታስከፋቸው ግን ያወግዙሃል። ታዲያ እድሜህ ሁሉ በሰዎች ማመስገንና ማውገዝ መሃል ሆኖ ያልቃል።
ከሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ቀደሰላሁ ሩሀህ) ባልደረባ የሆኑት ኢማም ኢብን ሀብ-ባል አል-በዕሊይ (ረሂመሁላህ) ወደ አንድ ተማሪያቸው በፃፉት ፅሁፍ ላይ በወርቅ ውኃ የሚፃፍ ድንቅ ንግግር እንዲህ በማለት ይናገራሉ:-
= ከዚህ ቀደም ነግሬህ ነበር፣ ታላቃችን የሆነው ሸይኹል ኢስላም ተቂዩዲን አቡል ዐባስ አሕመድ ኢብኑ ተይሚየህ (አላህ ያግዘው፣ ወደርሱም መልካምን ያድርግ!) አንድ ጊዜ 703 አመተ ሂጅራ ላይ ድካ የደረሰ የሆነን ምክር መክሮኛል። ከእርሷም እንዲህ ማለቱን ሸምድጃለሁ:-
“በንግግርህም ሆነ በስራህ የሰዎችን ውዴታ አታስብ። የሰዎችን ውዴታ መፈለግ የማይገኝ (የማይደረስበት) ግብ ነው። ዛሬ ሰዎችን ብታስደስት ያመሰግኑሃል፣ በነጋታው ደግሞ ታስቆጣቸውና ይወቅሱሃል፣ እድሜህ እነሱ ሲያመሰግኑህና ሲቆጡብህ ያልቃል። ለየትኛውም (ለመውቀሳቸውም ሆነ ለማመስገናቸው) እውነታ የለውም። ይልቅ አላህን የምትታዘዝበት የሆነ ነገር ከቀረበልህ የሚያወግዙህ አንድ ሺህ ቢሆኑ እንኳን እሱን አስቀድም፣ ምክንያቱም የላቀው አላህ ሸራቸውን ይበቃሃል።
ይህም ከዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) በተረጋገጠው ነቢዩ ﷺ እንደሚከተለው በተናገሩት ሀዲስ በመተግበር ነው:-
“ሰዎችን አስቆጥቶ አላህን ያስወደደ ሰው አላህ ከሰዎች ቁጣ ይጠብቀዋል።” [ትርሚዚይ 2414 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒይ ሶሂህ ብለውታል]
አላህን በማመፅ ላይ የሆነ ነገር ከቀረበልህ ከፊትህ የሚያወድሱህ ሺህ ሰዎች እንኳ ቢኖሩ ወየውልህ ተጠንቀቅ!! ተጠንቀቅ!!። የላቀው አምላካችን አላህ የሚያወድሱህ የነበሩ ሰዎችን መልሶ አንተው ላይ ይሾምብሃል። ነቢዩ ﷺ ይህን አስመልክተውም እንዲህ ብለዋል:- “አላህን በማስቆጣት ሰዎችን ያስደሰተ ሰው አወዳሾቹን ወቃሽ አድርጎ ይመልስበታል።” በሌላ ዘገባ እንዲህ ብለዋል:- “አላህ ጉዳዩን ወደ ሰዎች አስጠግቶ ይተወዋል፣ ሰዎች ደግሞ አላህ ዘንድ ካለው ነገር አንዳችም አያብቃቁትም።” [ትርሚዚይ፣ ኢብን ሂባንና እንዲሁም ኢብን አቢል ዒዝ በሸርህ ጦሃዊያ ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]
ወላሂ በእድሜ ቆይታዬ ለዚህች ምክር ብዙ አስገራሚ ፍሬዎችን አግኝቻለሁ!! አላህ ልባችንን እርሱን በመታዘዝና እርሱንም በመውደድ ይሰብስብልን!! እርሱም ለጋሽና ቸር የሆነ ጌታ ነው።” [አን-ነሲሀት አል-ሙኽተሶህ 42-43]
አንተ ሐቅ ላይ መሆንህ እርግጠኛ ከሆንክ ለሰዎች ውዴታና ጥላቻ አትጨነቅ!! ሰዎችን ለሰዎች ጌታ ተዋቸውና በምትችለው መልካም ነገር ሁሉ ወደፊት ብቻ ተጓዝ!! አላህ በትክክለኛው መንገድ የእርሱን ፊት ፍለጋ ለመልፋት ይወፍቀን!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa