Ibnu Munewor (ሃፊዘሁላህ)
መኖር እንደ ዘበት
የቱን ነበር … “አለ” ያልከኝ?
እኔ እራሴ ባዶ ሆኜ … በባዶዎች የኮፈስከኝ
“ጥራኝ ቅርብ ነኝ” የሚል … ሀያል ጌታውን ጥሎ
“ማን አለ የሚጠይቀኝ” ሲል … አርረሕማንን ችላ ብሎ
ሙታን ሰፈር የሚኳትን … ጨርቁን ማቁን አግተልትሎ
ለመቃብር የሚሐጅጅ … ፍየል በጉን አስከትሎ
እጣን ከርቤ መጋረጃ … ጂኒ ቁልቋል ዘባተሎ፡፡
ስማኝ እስኪ … አንድ በለኝ
ይህን ነበር … “አለ” ያልከኝ?
ግሳንግሶች ሆነን ሳለ … በግሳንግስ የፎገርከኝ?
በቢድዐ ህብረ-ድግስ … የሺርክ ቅኝት የሚቀኝ
ከሙታን የሚቀላውጥ ከድኩማን የሚመኝ
ይሄን ነው “አለ” ‘ምትለኝ?
እንደሌለ እየነገረኝ
በተግባሩ እያሳመነኝ?
ካሉት ጋራ የሚጋፋ
ከሞቱት ዘንድ የሚደፋ
ተንቀሳቃሽ በድን ሆኖ … “አለ” ሲሉት የሚጠፋ
ቀብሩን በእጁ የሚቆፍር … ለጥፋቱ የሚለፋ፡፡
ምኑ ላይ ነው ህልውናው … የቱስ ላይ ነው ሰውነቱ?
በሺርካሺርክ ተወሮ … ከራስ ጥፍሩ እስከ ‘ግር ጣቱ!!
ይልቅ ፉገራህን ተውና … እጁን ያዘው ከጥፋቱ
በነብዩ ብሩህ ሱና … ይመለስ ዘንድ ህይወቱ፡፡
ይቺን ነበር “አለች” ያልከኝ … በቁሟ የሞተች ምስኪን?
ከደካማው ጠንቋይ ሰፈር … ልጅ ፍለጋ የምትኳትን
ጥራ ግራ ለፍታ አፍርታ … ለገሪባ የመትበትን
ለሺርክ አውራ እጅ ነስታ … የሺርክ ጋን የምታጥን
ለንቶ ፈንቶ የምትከንፍ … ለኹራፋት የምትፈጥን
ይሄ ነው ወይ ህይወት ያለው … የሚባዝን ያለፋይዳ
“ሸይኽ አትጥራ” ስትመክረው … “ሸይኹን ጥላ” የሚረዳ
ለተውሒድ ጀርባውን ሲሰጥ … በህሊናው የተከዳ፡፡
በሺርክ እግሩን የሚያቀጥን … ገታ መጂት አና ዳና
በዳንግላ በቃጥባሬ … ጫሊ አብሪቲ አናጂና
ካሸለቡት በላይ ሞቶ … ከቀብር ደጅ የሚጠና
ከቁርኣን ጋር ተኳርፎ … ከሐዲሥ ጋር ከህሊና
ይሄ ነው ወይ … መኖር ማለት?
ኑሮ እንዲሉት … እንደዘበት
ይሄው ሆነ ወይ ጥቅሙ?
የመኖራችን ትርጉሙ
መኖር “መሄድ” ቢሆንማ … ሳያጣሩ እያጋሩ
ከመቃብር ለሚያንኳኩ … ሙታኖችን ለሚያዋሩ
ላንቃቸው እስኪበጠስ … ላይሰሙ ለሚጣሩ
ቤሳ ቤስቲን የሌላቸው … ጣኦታትን ለሚያባሩ
ሰማያዊ ቅዱስ ቃሉን … የማይሰሙ እማይማሩ፡፡
መኖር እንዲህ ቢሆንማ … ለጠፋበት ቅጥ አንባሩ
“ላትስሚዑልመውታ” ብሎ … ባልሰየማቸው ጀባሩ፡፡
ኢብኑ ሙነወር፣
ታህሳስ 2007
t.me/abdu_rheman_aman