💜...ማርያምን ...🕯


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮን
የጠበቁ መዝሙሮች ና የቅዱሳን ገድል
ይገኙበታል
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"
''የቅዱሳንን ክብራቸውን እናገር ዘንድ ፍቅር ያስገድደኛል''
✍️ግሩፑ ላይ መዝሙር ብቻ አይደለም
የተለያዩ ነገሮችንም ታገኙበታላችሁ
🙏 ኑ በጋራ ሁነን እንማር
👇
❷❶ ማርያም ሆይ እኖድሻለን

ለማንኛውም አስተያየትና ሀሳብ
@Tsegii_yene
👆👆

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
❤️...ቸርነትህ ነው...🕯

ቸርነትህ ነው ያደረሰኝ እስከዛሬ
ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከዛሬ
ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ/2/

አዝ
አንዳች እንደሌለኝ አውቀዋለሁ
ባንተ ቸርነት ግን እመካለሁ
የከበደው ሸክሜ ይቀለኛል
ይቅርታ ለባርያህ ይደርሰኛል
በመቅደስህ ቆሜ ለመዘመር
ስራህን ለትውልድ ለመመስከር
እኔ ማነኝ ብዬ አስባለሁ
አምላክ ቸርነትህን አደንቃለሁ

አዝ
በሰው እጅ መመካት አቁሚያለሁ
እረዳቴ አንተ ነህ አውቄያለሁ
አንተ ከጠበከኝ በህይወቴ
ቅጥሬ አይደፈርም መድኃኒቴ
የኔን ስራ ተወው ተግባሬንም
የመስቀሉን ነገር መርሳቴንም
አዚሜን አንስተህ አንተን ልይህ
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነህ
                                         
ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

@Mezmure_tewahdo


✝️✨ ጾመ ነነዌ ✨✝️

ነነዌ የአሦር ጥንታዊ ከተማ ነበረ። ፍርስራሹ በጤግሮስ ወንዝ ምሥራቅ ዳርቻ በሞሱል ዙሪያ አሁን አለ። ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትሆን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ የምትጀመረው ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አትለቅም ቀኑ ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር 17 ድረስ ነው ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ እስከ የካቲት 24 ቀን ይረዝማል፡፡

በእነዚህ 35 ቀናት ውስጥ ስትመላለስ ከፍ ዝቅ ስትል ትኖራለች ከተጠቀሱት ዕለታት አባቶች እንደ ደነገጉት አትወርድም አትወጣም በዚህ ዓመትም የካቲት 03 ቀን ትጀመራለች፡፡ አጭርና የሦስት ቀን ጾም ብትሆንም እንኳ እጅግ ብዙ ጥቅምን የምታስገኝ ጾም ናት፡፡ ይህም "በመባጃ ሐመር ከፍና ዝቅ ስለሚል ቊጥሩ ከአጽዋማት ሐዋርያት ነው፡፡ አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል፡፡" ታዲያ ነነዌ ማን ናት? ነነዌ በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ ናምሩድ በተባለው ሰው ተመሠረተች፡፡ ለአሰራውያን መናገሻ ከተማ ነበረች፡፡ ሰፊና ውብ ከተማ ሆና የተገነባች ናት፡፡ [ዘፍ. 10:1] አስር ከእስራኤላውያን ጋር ጠላት ሆነው በተቀናቃኝነት የኖሩ መንግሥታት ናቸው፡፡ ዮናስ የተላከው ተቀናቃኝ ወደ ሆኑት ሕዝቦች ነው፡፡ ከተማዋ ውብና ብዙ ሕንፃዎች ነበሩባት የከተማዋ ቅጽር ርዝመት 12 ኪ.ሜ እንደነበር በውስጧ ብዙ ሕንፃዎች ተሠርተውባት ነበር፡፡ የባቢሎን መንግሥት ከክርስቶስ ልደት በፊት ከተማዋን አፈረሳት፡፡ [ዮና.4.1]
 
ሕንፃዎቿን የሠራቸው ሰናክሮም ሲሆን በስተመጨረሻ በ621 ዓ.ዓ የባቢሎን መንግሥት አፍርሷታል፡፡ ነነዌ ዛሬ የኢራቅ ከተማ ምሱል ናት በኩሽ ልጅ ናምሩድ በ1800 ዓ.ዓ ተቆረቆረች፡፡ ሽታር ወይም አስታሮትን ያመልኩ ነበር በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ገጥሟታል፡፡

ታዲያ ለነነዌ ሰዎች የተላከው ዮናስ ከአባቱ አማቴ እና ከእናቱ ሰና እንደተወለደ ታሪኩ ይነግረናል፡፡ ዮናስ ኤልሳዕ ያዳነላት የሰራጵታዎ ሴት ልጅ ነው የሚሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን ይነግሩናል፡፡ ነገር ግን ስለ ነቢዩ ዮናስ ጥልቀት ያለው ታሪክና መረጃ በስፋት አልተገለጸም፡፡ የስሙ ትርጉምም ቢሆን በእብራይስጥ ቋንቋ ርግብ የሚለው ትርጉም እንደሚገልጸው መተርጉማኑ ይገልጻሉ፡፡

ከእግዚአብሔር ዘንድ ለዮናስ የመጣው መልእክት "ክፋቷ በእኔ ፊት ወጥቷልና ወደ ታላቂቷ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ፣ በእርሷ ላይ ስበክ፡፡" [ዮና. 1.1] የሚል ነበር፡፡ ዮናስ ግን ጥሪውን መቀበል ባለመፈለጉ ኮበለለ፡፡ ከእግዚአብሔር መኮብለል አያዋጣምና ነብዩ ዮናስ በትልቅ አሣ እንዲዋጥ ተደረገ፡፡ በዚህ ውስጥ ዮናስ የትንቢት ቃሉን ለነነዌ ሕዝብ ማድረስ እንዳለበት ተረዳ፤ እግዚአብሔር ለኹለተኛ ጊዜ የነገረውን ድምጽም ሰምቶ ወደ ነነዌ ሄደ፡፡

በወቅቱ ነነዌ እጅግ ታላቅ የሆነች ከተማ ነበረች፡፡ በአርኪዮሎጂ ግኝት እንደተረጋገጠውም ከተማዋ ነቢዪ ዮናስ እንዳለው የሦስት ቀን መንገድ ያህል እጅግ ታላቅ ከተማ (ዮና.3.3) ነበረች፡፡ በአሁኑ ወቅት እንዳሉ ከተማዎች ሁሉ ሕዝብ የበዛበት ነበረች፡፡ ከመቶ ሃያ ሺህ በላይ ሕዝብ ይኖርበት እንደነበረም በዚያው በነቢዩ ዮናስ መጽሐፍ ላይ ተጠቀወሶ እናነባለን፡፡ [ዮና.4.1] ሆኖም ግን በዚህ ሁሉ ውስጥ እግዚአብሔርን እጅግ የሚያሳዝን ኀጢያት ይሠራ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ነብዩ ዮናስ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ነነዌ ሕዝቦች ይዞ ሄደ፡፡ ነነዌ እንደምትገለበጥም ተነገራቸው፡፡ 

በዚህ ታሪክ ውስጥ ትልቁን ትምህርት የምናገኘው እዚህ ጋር ነው፡፡ እግዚአብሔር የንስሐ ጥሪን ለኁሉም ያደርጋል፡፡ ከየሰው በኩል የሚሰጠው ምላሽ ግን የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ የነነዌ ንጉስ ከተማይቱ እንደምትጠፋ በሰማ ጊዜ "ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሱንም አወለቀ፤ ማቅም ለብሶ በዐመድ ላይ ተቀመጠ፡፡" [ዮና.3.6] ከዚህም በኋላ በነነዌ ሕዝብ ዘንድ ጾም እንዲታወጅ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- "ማንም ሰው ወይም እንስሳ፣ ከብትም መንጋም ሆነ የበግ መንጋ፤ ምንም ነገር አይቅመስ፤ አይብላ፤ ውሃም አይጠጣ፡፡ ነገር ግን ሰውም እንስሳም ማቅ ይልበስ፤ ኁሉም አጥብቆ ወደ እግዚአብሔር ይጩህ ሰዎችም ኁሉ ክፉ መንገዳቸውንና የግፍ ሥራቸውን ይተው፡፡ እና እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ራርቶ ከጽኑ ቁጣው ይመለስም እንደሆነ ማን ያውቃል" [ዮና. 3:7-9] በዚህም ጥሪ ምክንያት ሕዝቡ በጾም ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ተመለሰ፡፡ 

እግዚአብሔርም ለዚህ የሰጠው ምላሽ እንዲህ ነው፡- "እግዚአብሔርም ምን እንዳደረጉና ከክፉ መንገዳቸውም እንዴት እንደ ተመለሱ ባየ ጊዜ ራራላቸው፤ በእነርሱም ላይ ሊያመጣ ያሰበውን ጥፋት አላደረገም፡፡" [ዮና. 3:10]

ነነዌና አንዳንድ ነገሮች
ሀ. በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የዚህ ጾም ስም "የዮናስ ጾም" ይባላል፡፡ ሆኖም ግን ቀደምት መዛግብት ላይ የሠፈሩ መረጃዎች (የነነዌ ጾም) በሚለው ይሄዳሉ፡፡ እዚህ ጋር የምንዘክረው የነነዌ ሰዎች የጾሙትን ጾም ብቻ ሳይሆን ነብዩ ለሦስት ቀን በአሣው ሆድ ውስጥ መቆየቱን እናሳስባለን፡፡

ለ. የዚህን ጾም ታሪክ ወደ ኋላ ይዘን ስንሄድ የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እናገኛለን፡፡ ይህ ጾም በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲጾም የነበረ ነው፡፡ በዚህም ጾም ምክንያት ብዙዎች ከአደጋ ለመዳን ችለዋል፡፡   
 
ሐ. ለመሆኑ ነብዩ ዮናስን የዋጠው የባሕር እንስሳ ምንድር ነው; ግእዙ (ዐንበሪ) ይለዋል፡፡ ብዙዎች (ዐሣ ዐንበሪ) በማለት ዛሬ ላይ በተለምዶ የምናውቀው ትልቅ ዐሣ ዮናስን እንደዋጠው ይናገራሉ፡፡ ግሪኩ (ኬቶስ) ይለዋል፤ ትርጉሙም ታላቅ የባሕር እንስሳ ማለት ነው፡፡ ሊቁ ኒቆዲሞስ ገዳማዊ st. Nicodemus the hagiorite ስለዚህ (ኬቶስ) የተባለ የባህር እንስሳ ሲናገር እንዲህ ይላል፡-
ዕውቀትን እና መማርን ለሚወዱ ሰዎች ስለ ኬቶስ እንዲህ ብለን እንናገራለን፡፡ ቴዎክለስ እንዳለው ከሆነ ኬቶስ ከአስር መርከብ የበለጠ ነው፡፡ አሊያንስ እንደተናገረው ደግሞ ከዝሆን ዐምስት ጊዜ ይበልጣል፡፡ ኤራቶስቴንስ ሲናገር ደግሞ ሀምሳ ኪውቢት (23 ሜትር) በላይ ርዝማኔ አለው ይለናል፡፡ --- እነዚህን ጥንታዊ ሰዎች በመከተል ታላላቅ አባቶች ስለ ኬቶስ ግዙፍነት ይናገራሉ፡፡ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ኤቶስ ሰውነቱ እንደ ትልቅ ተራራ ያለ እንደሆነ እና ደሴት እንደሚመስል ይነግረናል፡፡ (አክሲማሮስ ዘባስልዮስ ድርሳን ሰባት) ታላቁ አምብሮስ ደግሞ ሲናገር ኬቶስ ሲዋኝ ቀና ቢል ሰማይን እንደሚነካ ሁሉ ግዙፍ እንደሆነ እና ትልቅነቱ እንደ ደሴት ወይም እንደ ተራራ እንደሚመስል ይናገራል፡፡ ኤውስጣቴዎስ ዘአንጾኪያ ደግሞ በአክሲማሮስ ሲነግረን አስፒዶኬሎን የታለው ኬቶስ እጅግ ግዙፍ ከመሆኑ የተነሣ ሰዎች ሲያዩት ደሴት እንደሚመስል ተናግሯል፡፡

ሐዋርያትም ሰብአ ነነዌ የተነሣህያን አብነት ናቸውና ሥርዓቱም ጾሙም አይቀር ብለው ሠርተውታል፡፡ እኛም በጾምና በጸሎት ከፈጣሪያችን ምህረትና በረከት ለማግኘት ስንል እንጾመዋለን፡፡ በተጨማሪም ይህ ጾም ለዐብይ ጾም መዘጋጃ በመሆን ያገለግላል፡፡

የፊታችን ሰኞ የሦስት ቀናቱ ጾም ጾመ ነነዌ ይገባል።
ጾሙ ከመግባቱ አስቀድሞ ኦርቶዶክሳውያን ሁላችን ንስሓ እንግባ።
ከዚህ ንስሓ ጋር የታወጀውን የየነነዌ ጾም ጠዋት በኪዳንና ከሰዓት በቅዳሴ ማታ ደግሞ በጸሎተ ምሕላ በየአጥቢያችን እየተገኘን አምላካችንን እንማጸነው።


@Mezmure_tewahdo


የካቲት 🕯.... ❶ ...ልደታ

እናታችን እመቤታችን  ቅድስት ልደታ ለማርያም ናት።

ድንግል አዛኚቱ የአምላክ እናታችን ወቶ ከመቅረት ከክፉ ነገር ሁሉ ትጠብቀን።🙏❤


አንቺን የያዘ ሰዉ ምን ይጎልበታል በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል።

🌷እመብርሃን ትጠብቃችሁ🌹🤲


@Mezmure_tewahdo


🙏...አቤቱ አምላኬ ሆይ
የመጠሪያዬን ዘመን አላውቀውምና
ኃጢዓቶቼን አስታውዬ የማይበትን
ከፊትህ ተደፍቼ ይቅርታን የምጠይቅበትን አንደበት ስጠ
ኝ🙏

ወር በገባ በ30 ነቢይ ባህታዊ ድንግል  መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንዲሁም ወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ናቸው።🌷

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውሩን።🙏


@Mezmure_tewahdo


"ዛሬ_በዓለ_ወልድ_ነው_29
በዓለ ወልድ ማለት ወር በገባ
በ 29ኛው ቀን የሚከበር በዓል ነው።

የስሙ ትርጓሜም የወልድ በአል ማለት ነው።ይህም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዲያብሎስን ስራ ለማፍረስ፣የሰውን ልጅ ነፃ ለማውጣት ሲል ከእናታችን ከድንግል ማርያም መጋቢት 29 ቀን የተፀነሰበት ታህሳስ 29 ቀን የተወለደበት ቅዱስ እለት ስለሆነ በየ ወሩ ይታሰባል።

እኛን ለማዳን እንደ ሰው ዘር ብሄር ሳይል ለኛ ሀጢያት እርሱ ዋጋውን ሊከፍል ሊገረፍ ሊሞትልን ወደዚህች ምድር መጣ ቅዱስ በዓለ ወልድ ከክፉ ጥበቃው አይለየን🙏


@Mezmure_tewahdo


ዛሬ ጥር 28 ቅዱስ አማኑኤል ነው አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ምስሌነ /እግዚአብሔር ከእኛጋ ሆነ ማለት ነው እርሱ ከእኛ ጋር ባይሆን በከበበን መከራ እስካሁን በጠፋን ነበር። እኛን ለማጥፋት ዘወትር በሚተጋው ጥንተ ጠላታችን ከይሲ እስካሁን ጠፍተን ነበር።

ነገር ግን "እግዚአብሔር ምስሌነ" የሰራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ በመልካም ጥባቆትህ ጠብቀህ ለሊቱን በሰላም እንዳሳደርከን እንዲሁም ደግሞ መልካም ጥባቆትህ ሳይለየን ቀኑንም በሰላም ጠብቀህ ታውለን ዘንድ ያንተ መልካምና ቅዱስ ፍቃድ ይሁንልን

ቅዱስ አማኑኤል በቀኝ ያውለን ጥበቃው ማዳኑ አባትነት ጌትነቱ አይለየን


@Mezmure_tewahdo


🕯....➋❼....❤️

"አልብየ ኃይል ለተናግሮ"
"ይህን ለመናገር አቅም የለኝም"

      እንዲል አረጋዊ መንፈሳዊ

ስወድቅ ትደግፈኛለህ ስደክም ታበረታኛለህ በቃው ሲባል ኧረ ገና የምትል የእንደገና አምላክ ነህና ያደረግልኝን የባረከኝን ለመናገር ቃል የለኝም

ተሸሽጎ የሚያለቅሰውን የምታይ መንገድ ለጠፋው መንገዱን እውነት ለራቀው እውነቱ ላሰጣጥህ መስፈሪያ የሌለህ...ሳትሰማ የማትበይን! ደግሞ ምን ፈለግሽ?ብለህ የማትሰለቸኝ ቸሩ መድኃኔዓለም ክብር ምስጋና ይግባህ ተመስገን 🤲🌹

አቅሜ አንተ ስለሆንክ መድኃኔዓለም አባቴ ምስጋና ይግባህ  ለደቂቃ እንኳን አትለየኝም እና አብዝቼ

አመሰግንሃለሁ እንኳን አደረሰን።


@Mezmure_tewahdo


➋❹...ተክለ ሃይማኖት...🕯


...የአባታችን ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓላት

❶...ኅዳር 24 (ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር ያጠኑበት)

➋...ታኅሳስ 24 (ልደታቸው)

❸...ጥር 24 (እግራቸው የተሰበረበት

❹...መጋቢት 24 (ጽንሰታቸው)

❺...ሚያዝያ 22 (6 ክንፍ የተቀበሉበት)

❻..ግንቦት 12 (ፍልሰታቸው

❼...ነሐሴ 24 (ዕረፍታቸው)

🕯...ዛሬ በዚህ ዕለት አባታችን ተክለ ሃይማኖት ለ22 ዓመታት በጸሎት የቆሙበት ቀኝ እግራቸው መሰበሩንና በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመታት ቆመው መጸለያቸውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስባለች::


ከጻድቁ በረከት አምላካቸው ይክፈለን
....🙏

@Mezmure_tewahdo


ወር በገባ በ23

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕት ነው።

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ  ሁሉ ይሰውረን።🙏


@Mezmure_tewahdo


🕯...ጥር ....➋❶

❤️ ...እንኳን አደረሳችሁ ....🙏

ድንግል ሆይ ያንቺ ባርያ ነው የሚል በልጅሽ በደሙ ቀለም በልቤ ሰሌዳ ላይ ይፃፍልኝ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ ዝገቴን በቅድስናሽ በንፅህናሽ ወልውለሽ ንፁህ አድርጊኝ
አንቺ ከወደድሽኝ ልጅሽ አይጠላኝም


( አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ )


እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እረፍት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ቤተሰብ መልካም በዓል ይሁንልን🥰🌷🧎‍♀

@Mezmure_tewahdo


🕯 ...ቅዱስ ገብርኤል...❶❾

ደረሰልኝ ቀኑ ደሞ ላመስግነው
የህይወት መሪ ስሙ ገብርኤል ነው።

፲፱ እንኳን አደረሳችሁ🌷


@Mezmure_tewahdo


በምን እፅናናለሁ ከሌለኸኝ
በምን ልበረታ ካላገስከኝ
አንተ ስላለህ ነው መድኃኒቴ
    ቆሜ መታየቴ /2/

ሸክም ለከበደ ማረፊያ ነህ
እጅግ የቀለለ ቀንበር ያለህ
ፍቅርህ ነው የሚያሰማራኝ
በለምለም መስክ ያቆመኝ /2/

ቸር አምላክ የእውነት ዳኛ
አማኑኤል የኔ መታመኛ

ጨለማን አላውቅም በጉዞዬ
በህይወቴ ሁሉ ነህ መሪዬ
ተጓዝኩኝ ሌቱን በብርሀን
ባንተ አየሁኝ መሻገርን

ቸር አምላክ የእውነት ዳኛ
አማኑኤል የኔ መታመኛ

ማቀርቀሬን ሰበርክ አልኩኝ ቀና
በርትቼ ተራመድኩ እንደገና
ቃልህ ኃይሌ የሚያጸናኝ
በአለት ላይ የተከልከኝ /2/

ቸር አምላክ የእውነት ዳኛ
አማኑኤል የኔ መታመኛ

እንባዬ ታበሰ ስታፅናናኝ
ግን የሆነው ሆኗል ስትረዳኝ
በጠላቴ ፊት ሞገስ ሆንከኝ
ለባህሪያህ ድል ሰጠኸኝ /2/

ቸር አምላክ የእውነት ዳኛ
አማኑኤል የኔ መታመኛ

👇👇
@Mezmure_tewahdo


የልቤን ችግር ላዋይሽ
ከስዕልሽ ፊት ቆሜ
እንባየ ቀድሞ ዝም አልኩኝ
"ሳልነግርሽ ስለምታውቂኝ
....🙏🙏🙏


ኪዳነ ምህረት ....❶❻...🕯

የት እሄዳለሁ
አልልም ሲከፋኝ
ኪዳነ ምህረት አንቺ እያለሽልኝ
ኪዳነ ምህረት የረዳችዉ አሜን ይበል❤🙏

➝⓰እናቴ ሚስጢረኛዬ♥️

@Mezmure_tewahdo


♡ አንተን ማገልገል ♡

አንተን ማገልገል መባረክ ነው
ምርጫ ነው ዕጣ ነው
ክብር ነው እድል ነው

ገና በማለዳ ብላቴና ሳለሁ
የሰማሁት ዜማ ዛሬም ከልቤ ነው
የጸናጽሉ ድምጽ የሸተተኝ ዕጣን
ካንተ ጋር አስሮኛል በዝማሬ ኪዳን

አፈር ትቢያ ስሆን ከሁሉ ያነስኩኝ
እንዳገለግልህ በአንተ ተመረጥኩኝ
የአንተ ስምና ክብር በአፌ ላይ አለፈ
በባሪያህ ተጠቅመህ ስንት ሰው አረፈ
ዓለም ሳትወስድብኝ ያንተን ውድ ጸጋ
ለክብርህ እንደዘመርኩ እየመሸ ነጋ
የዜማ ጠጠሬ ያለህ በወንጭፌ
ሺ ጠላት ቢከበኝ ምስጋና ነው ሰልፌ

ተከፍቼ አላውቅም እኔ በአንዳች ነገር
ስምህን አንግቤ ስሄድ አገር ስአገር
ሰላደረክልኝ ባዕዳነነ ዘመድ
ሞገስ ክብር ሆንከኝ ባለፍኩበት መንገድ
ዘመኔ የደስታ የሐሴት ሆነልኝ
ስትረዳኝ ስላየሁ አቤኔዘር አልኩኝ
ስለ እጅህ ስጦታ አሜን ብዬሃለሁ
የስምህ አወዳሽ የልጅ ልጅ አያለሁ

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
♡ ሼር👉 

@Mezmure_tewahdo
@Mezmure_tewahdo


❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

             ጥር ፲፪ (12) ቀን

           በዓለ ቅዱስ ሚካኤል
               /ቃና ዘገሊላ/


❤ እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ በሠርግ ቤት ተገኝቶ የመጀመርያውን ተአምር ላደረገበት መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል፣ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል እስራኤል ወደ ተባለ ቅዱስ ያዕቆብ ለተላከበት ከወንድሙ ከኤሳው ፈርቶ ሳለ ላዳነበት ለወራዊ በዓሉ፣ ለታላቁ ሰማዕት ለምሥራቅ ሰው ጽኑዕ ኃይለኛ ለሆነ ለቅዱስ ቴዎድሮስ በናድሌዎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍት በዓልና ለቅዱስ ይስሐቅም ልጅ ለቅዱስ ያዕቆብ ለልደቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

@Mezmure_tewahdo


ዛሬ ጥር 10 የከተራ በዓል ነው እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን💙🙏

ከተራ ማለት?

✍️ከተራ ማለት "ከተረ" ከምለው ከግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ዙርያውን ከበበ፣ አጠረ፣ ገደበ ማለት ነው።

🥀ከተራ ማለት ከተረ፣ አጠረ፣ ሰበሰበ ማለት ሲሆን ይኸውም ወራጁን ውሃ ሰብስቦ ወይም ገድበው በየሰበካው ተለይቶና ተከልሎ ለጥምቀት የምዘጋጁበት ዕለት ነው።

➻ታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረዳቸው - ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን አስከትሎ ሊጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ የመወረዱ ምሳሌ ነው። ታቦታቱ የጌታችን ምሳሌዎች ናቸው።

✍️ታቦታቱን ያከበሩ ካህናት የመጥምቁ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ምሳሌዎች ናቸው።
ባህረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ምሳለ ነው።

🥀ታቦታቱን አጅበው የምሄዱ ምዕመናን ወደ መጥምቁ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ እየሄዱ ንሰሃ እየገቡ የንሰሃን ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩ የእኔሱ ምሳሌዎች ናቸው።

መልካም የከተራ በዓል💚💛❤️✝️🙏

@Mezmure_tewahdo


ነገ ቅዳሜ ጋድ ነውይጾማል::



እንዴት ይጾማል…?

ነገ ጥር 10 ቀን የጥምቀት ጋድ ነው፡፡ አባቶቻችን እንዳይረሳ ጥምቀት ረቡዕ ወይም ዓርብ ሲውል ብቻ ሳይሆን ሁሌም በየዓመቱ  እንዲጾም ወስነዋል፡፡ ከሰባቱ አጽዋማት ገብቶ መቆጠሩም ለዚህ ነው፡፡

ቅዳሜ (ቀዳሚ ሰንበት) ባይሆን እስከ ምሽት አንድ ሰዓት ጾሙ ይቆይ ነበር፡፡ እናቶች በጥምቀተ ባሕሩ ተገኝተው "የጥምቀት እራት" እያሉ ታቦት አክባሪ ካህናትን መመገባቸው ለምን እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡

ግን ዘንድሮ ቅዳሜ ጋድ በመሆኑ እንደ ዐቢይ ጾም ቅዳሜ ከጥሉላት መባልት (ሥጋ፤ ቅቤ፤ ወተት...) እንከለከልባታለን.... (ስንክሳር ጥር 10)

መልካም በዓለ ጥምቀት ይሁንላችሁ


@Mezmure_tewahdo


ዛሬ ጥር.... 7....🕯


ቀን ቅድስት ሥላሴ በኃጢያት የተገነባውን የሰናኦር ግንብ ያፈረሱበት ቀን ነው የእኛንም በኃጢዓት የደነደነ ልባችንን አፍርሰው ይስሩልን🙏

በጨነቃችሁ ጊዜ ሁሉ ፈጣሪያተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ አለው ይበሏችሁ

🥰🙏🥰


@Mezmure_tewahdo


#ተባረኩኝ ጠራኝ ጸሎቷ

ተባረኩኝ ጠራኝ ጸሎቷ
ልሳለማት ልሂድ እቤቷ
ፍቅሯ ልዩነው ደግነቷ
እናቴ አርሴማ ሰማእቷ
  
እግሩ ያነከሰ ክንዱ የዛለበት
ደስታ የራቀው ሰው ህመም የጸናበት
ልቡ የደከመ መንገድ የጠፋበት
አፍሮ አይመለስም ደጅሽ የመጣለት

ያንሁሉ ቁልቁለት ያንሁሉ ጋራ
እንዴት ልጓዝ ብዬ ስፈራ ስፈራ
ድረሽልኝ ብዬ ላንቺ ስናገር
እንደእንቦሳ ጥጃ እዘለው ጀመር

ላይድን መችይመጣል ላይለቀው ችግሩ
አንቺስ መችልጠሪው ሲነሳ ከክብሩ
አቤት ቃል-ኪዳንሽ እንዴት ይገለፃል
አምኖ የመጣ ሰው ድኖ ተመልሶል

የውስጥ ደዌውን ህመሙን ደብቆ
ገስግሶ የመጣ ካለሽበት ዘልቆ
ድኖ ተመለሰ ዝናሽን አሰማ
ሰማቷ እናቴ እያለሽ አርሴማ

አንደበትን ስጪኝ እመሰክራለው
በሶስት ፍሬቆሎ ስታድኚ እያየው
ነግሬሽ ነበረ ችግሬን በሙሉ
አላሳፈርሽኝም ተፈታልኝ ሁሉም

👇👇
ለመቀላቀል
     @Mezmure_tewahdo
     @Mezmure_tewahdo
    
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊

Показано 20 последних публикаций.