Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ቁርኣን ወይም ኪታብ በማስተማር ላይ የተሰማራሀው ወገኔ ሆይ! እራስህን ለመቻልና ከሰው እጅ ላለመጠበቅ የምትችለውን ሰበብ አድርስ። አላህ ካገራልህ የማንንም እጅ ሳታይ ተብቃቅተህ አስተምር። ኑሮህን ለመደጎም፣ ቤተሰብህን ለማኖር የምትቸገር ከሆነ ህዝብ ለማስተማር የምታውለውን ጊዜ ቀንሰህ ስራ ላይ ተሰማራ። አዎ ቀንሰው። ሳምንቱን ሙሉ ታስተምር ከነበረ ሁለት ቀን፣ ሶስት ቀን አድርገው። ሶስት፣ አራት ሰዓት ታስተምር ከነበረ አንድ፣ ሁለት ሰዓት አድርገው። ምክንያቱም ከጥገኝነት መውጣት አለብህ። ያለበለዚያ ይሄ ከዲን ጋር ሲነፃፀሩ እዚህ ግባ ለማይባሉ ነገሮች አእላፍ የሚመነዝር ወገን ከሰፈር ነዋሪ በጣር አጠራቅሞ ለሚሰጥህ ሳንቲም በምላስ ጦር ይወጋሃል። በነፃ አታስተምር ነገር አትችል። በክፍያ ስታስተምር ነገሩ መከራ። "ለቁርኣን እያስከፈሉ" እያለ ባደባባይ ሲወቅስ ትንሽ እንኳን አይሰቀጥጠውም። አንተም እንደሱ ህይወት፣ ቤተሰብ እንዳለህ ሊያስብ አይፈልግም።
ሆድ እንዲብስህ አይደለም የማወራህ። ከማስተማር ራቅ እያልኩህም አይደለም። ለአላህ ብለህ የምትሰራውን ስራ "ምን አገባኝ?!" ልትል አይገባም። ይሄ ፈፅሞ መሆን የለበትም። ብቻ በየትም በየትም ብለህ ከሰው ጥገኝነት ለመውጣት ጥረት አድርግ። ይሄው ነው።
የብዙ ኡስታዞችን ህይወትና የህዝባችንን ሁኔታ በማሰብ ነው የፃፍኩት። መነሻ የሆነኝ እያስከፈሉ የሚያስተምሩ ወንድሞችን የሚወቅሱ ሰዎችን ማየቴ ነው። ወይ ራሳቸው በነፃ አያስተምሩ፤ ወይ የሚያስተምሩትን አያግዙ። እንዲሁ የሚሰሩትን ማሰናከል ብቻ!! ቆይ እንዴት ሆነው እንዲኖሩ ነው የምንጠብቀው?! ወላሂ በዚህ አያያዛችን ወደፊት አስተማሪ እንዳናጣ ያሰጋል። ሱብሓነላህ!!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor