Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በየሰፈሩ ልጆችን በክረምት ቁርኣን ለምታስተምሩ መርከዞች
~
ቁርኣን ላልጨረሱ ልጆች ኪታብ ባታስቀሩ መልካም ነው። ልጆቹ አቅማቸው ገና ስለሆነ ኪታቡን አይዙትም። ለቁርኣን የሚሰጠውን ትኩረትም በእጅጉ ይቀንሰዋል። ቁርኣን መቅራት ያልቻለ ልጅ እንዴት ኪታብ መቅራት ይችላል? ስለዚህ በዚህ የአቅም ደረጃ ላይ ላሉ ህፃናት ሙሉ ትኩረት ለቁርኣን ቢሰጥ ነው የሚሻለው።
አንዳንድ መሰረታዊ ነገሮችን ማስጨበጥ ከተፈለገ በኪታቡ ፈንታ በጣም አሳጥሮ በቃል ብቻ ከእድሜያቸው ጋር የሚሄዱ ቀላል ነገሮችን ጣል ማድረግ በቂ ነው። ለምሳሌ የኢማንና የኢስላም ማእዘናት፣ የውዱእ አደራረግ፣ የሶላት አሰጋገድ፣ በጣም ቀላል አደቦችንና አጫጭር ዚክሮችን ቀለል ባለ መልኩ እየደጋገሙ ለማስያዝ መሞከር በቂ ነው።
ቁርኣን የጨረሱትን ደግሞ አቅማቸውን ባገናዘበ መልኩ ከቀላል ኪታብ ጀምሮ እየያዙ መሆናቸውን እየፈተሹ ቀስ አድርጎ መያዝ ያስፈልጋል። አስተማሪዎች አቀራረባችሁን እየገመገማችሁ አሻሽሉ። ማወቅ ብቻውን ለማስተማር ብቁ አያደርግም። ያወቀ ሁሉ ማስተማር ይችላል ማለት አይደለም። የልጆች አቅምም፣ ባህሪም፣ ትኩረትም አንድ አይደለም። ሁሉንም አንድ ዓይነት አያያዝ መያዝ ውጤማነቱን ይቀንሰዋል። ስለዚህ አቅም በፈቀደ እንደ ሁኔታው መያዝ ይገባል። የልጆቹን የአቀባበል አቅም ማጤን፣ ድክመታቸውን ለይቶ ለመፍታት መሞከር፣ እንዳስፈላጊነቱ ሞራልና ቁጣ፣ ምክርና ማሳሰቢያ መስጠት አስፈላጊ ነው።
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor