Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
በረጀብ ወር ውስጥ የተለየ የአምልኮ (ዒባዳ) አይነት ምን አለ??
—————
ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“በረጀብ ወር ውስጥ የሚፆም ፆምና የሌሊት ሶላቶች እንዳሉ የሚጠቁሙ ሀዲሶች በሙሉ ውሸትና ቅጥፈቶች ናቸው።” [አልመናሩል ሙኒይፍ 96]
❍
አል-ሃፊዝ ኢብኑ ረጀብ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“በረጀብ ወር የመፆምም ሆነ ሌሊቱን የመስገድን በላጭነት፣ እንዲሁም ከወሩ የተወሰኑ ቀኖችን መፆምም ሆነ የመፆም በላጭነትን የሚጠቁም አንድም ለማስረጃ የሚሆን ሶሂህ ሀዲስ አልመጣም።” [ለጣኢፉል መዓሪፍ 228]
❍
አቢበክር ኢብኑ አቢ ሸይበህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“አቡ ሙዓዊየህ ከአዕመሽ ይዞ፣ አዕመሽ ከወበረ፣ ወበረ ከዐብዲረህማን፣ ዐብዲረህማን ከኸርሽ ኢብኒል ሁር ይዞ፣ እንዲህ ሲል ነግሮናል:- ሰዎች የረጀብ ወርን በመፆማቸው ምክንያት ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ፆማቸውን ትተው ምግብ እስኪበሉ ድረስ እጃቸውን ሲገርፋቸው አይቻለሁ። እንዲህም ይላቸው ነበር:- ረጀብ የቱ ረጀብ ነው? ረጀብማ በጃሂሊያ ዘመን ሰዎች ያከብሩት ነበር እስልምና ሲመጣ ተትቷል።” [አል-ሙሶኒፍ 9758]
አጃዒብ እኮ ነው! ሠለፎቻችን በዲን ላይ አዲስ ፈጠራን ያመጣን ሰው እንዲህ የገረፉበትም ሁኔታ ነበረ፣ ዛሬ ላይ ግን የሱንና ዑለማዎች በቢድዓ ባለ ቤቶች ላይ ጠንከር ያለ ንግግር ሲናገሩ ሙተሸዲድ፣ ተሳዳቢ፣ ተክፊር… ይባላሉ።
❍
ታላቁ የኢስላም ሊቅ ሸይኹ'ል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረህመቱላሂ ዐለይሂ - ወቀደሰላሁ ሩሀሁ) እንዲህ አሉ:-
“የረጀብ ወርን በተለየ መልኩ መፆምን በተመለከተማ፣ ሀዲሶቹ በሙሉ ደካማ (ዶዒፍ) ናቸው፣ እንዲያውም ውድቅ የሆኑ (መውዱዕ) ናቸው። አንድም የእውቀት ባለቤቶች ሊደገፉበት የሚችሉበት ደረጃ ላይ አይደሉም። እንዳው ደካማ ቢሆኑም ፈዳኢል ስለሆነ ይሰራባቸዋል የሚባል ደረጃም ያላቸው አይደሉም። ሁሉም ውድቅ (መውዱዕ) የሆኑ በነቢዩ ـ ﷺ ـ ላይ የተዋሹ ናቸው።” [መጅሙዕ አልፈታዋ 25/290]
❍
ታላቁ የኢስላም ሊቅ ዐብዲ'ልዐዚዝ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
“የረጀብን ወር ‘ሶላተ-ረጘኢብ’ በማለት ወይም 27ኛውን ሌሊት በተለየ ዝግጅት የኢስራእ እና የሚዕራጅ ሌሊት ነው ብሎ ማክበር ሁሉም አዲስ ፈጠራ (ቢድዓ) ነው አይፈቀድም። በሸሪዓችን ምንም አይነት መሰረት የለውም።” [መውቂዑ ሸይኽ - ከዌብሳይታቸው የተወሰደ]
❍
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“የረጀብ ወር ልክ እንደሌሎቹ ወራቶች ነው፣ ከሌሎች ወራቶች በአምልኮ (በዒባዳ) የሚለይ ነገር የለም። ምክንያቱም በሶላት፣ በፆም፣ በዑምራም ሆነ በእርድ በሌሎችም የአምልኮ ዘርፎች ከሌሎች ለየት የሚደረግበት ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የተረጋገጠ ነገር የለም። በረጀብ ወር እነዚህ ተግባሮች ይፈፀሙ የነበረው በጃሂሊያ ዘመን ነበር እስልምና ውድቅ አድርጎታል።
አንድ ሰው በዚህ ወር አምልኮ (ዒባዳ) ከፈጠረ፣ በዚህ ወር የሚሰራ የተለየ አምልኮ (ዒባዳ) ነው ካለ፣ ይህ ሰው በዲን ላይ የሌለን አዲስ ነገር ፈጣሪ (ሙብዲዕ) ይሆናል። ምክንያቱም በዲኑ ያልነበረን አዲስ ነገር ፈጣሪ ነው፣ አምልኮ (ዒባዳ) ደግሞ የተገደበ ነው፣ በመሆኑም ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ከሌለው ምንም አይነት ነገር ፈጥሮ ማስቀደም አይቻልም። ምንም አይነት የረጀብ ወር እንደሚለይ የሚጠቁም ሊደገፉት የሚቻል ማስረጃ የመጣ ነገር የለም። የመጡ ሀዲሶች በጠቅላላ ከነቢዩ ـ ﷺ ـ ያልተረጋገጡ (ዶዒፍ) ናቸው። ሶሃቦች በጠቅላላ ከዚህ ተግባር (ረጀብን) በአምልኮ ለየት ከማድረግ በተለየ የረጀብ ወርን ለየት አድርጎ ከመፆም ይከለክሉ ያስጠነቅቁ ነበር። ነገር ግን አንድ ሰው በሌሎች ወራቶችም የሚያዘውትረው የሆነ የሌሊት ሶላትም ሆነ ፆም ከነበረው እንደሌሎች ወራቶች ረጀብ ወር ላይም መፆሙ ችግር የለውም።” [አል-ሙንተቋ ሚን ፈታዋ 1/222–223]
❍
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ አል-መድኸሊይ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“እኛ ሙስሊሙን የምንመክረው እንዲህ ያለውን ውዳቂ ነገር እንዲተው ነው። የጮሀን ሁሉ መከተልንም እንዲተው ነው። ይልቅ በአላህ ገመድ ላይ እንዲጣበቅ ነው ምንመክረው፣ በአላህ ኪታብ (ቁርኣን) እና በነቢዩ ـ ﷺ ـ ሀዲስ ያልተደነገገን ነገር ሁሉ እንዲተው ነው።” [ከዌብሳይታቸው የተወሰደ]
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa