«መንሃጅ» ማለት ምን ማለት ነው⁉️
✍️በቋንቋ ደረጃ:
«መንሃጅ» ማለት (ግልጽ የሆነ) «መንገድ» እንደ ማለት ነው።
አላህ በቁርአን ላይ እንዲህ ይላል፦
{لِكُلٍّ جَعَلْنا مِنْكُمْ شِرْعَةً وَمِنْهاجاً}"
"ከናንተ ለሁሉም ሕግንና መንገድን አደረግን:.."
((አል ማኢዳህ፡ 48))
*
ኢማሙ ጦበሪይ በተፍሲራቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፥
"وأما"المنهاج"، فإنّ أصله: الطريقُ البيِّنُ الواضح، ... ثم يُستعمل في كل شيءٍ كان بيِّنًا واضحًا سهلاً"
"ሚንሃጅ የሚለውማ፦ መሰረቱ ግልጽና የተብራራ የሆነው መንገድ ነው።
ከዚያም በሁሉም ነገር ላይ ይተገበራል፤
ግልጽ፣ የተብራራና ቀላል ሆነ።"
((ተፍሲሩ ጥጦበሪይ፡ 10/384))
*
ገጣሚውም እንዲህ ይላል፤
مَــنْ يـكُ فِـي شَـكٍّ فَهـذَا فَلْـجُ
مَـــاءٌ رَوَاءٌ وَطَـــرِيقٌ نَهْــجُ
*
በእንግሊዝኛው "Methodology", "Syllabus", "Curriculum" የሚሉት ቃላት ይተኩታል።
በአጠቃላይ የሚለውን ቃል መንገድ፣ ፈለግ፣ ፋና፣ ትውፊት፣ አካሄድ የሚሉት ቃላቶች እንደየ አገባቡ ይተኩታል።
*
✍️በሸሪዓዊ ደረጃ ደግሞ፤
````
እውቀታዊና ተግባራዊ በሆኑ የአምልኮ ተግባራቶች እንዲሁም
በሰዎች መካከል ስላለ መስተጋብር ሁሉ የአላህ ህግ (ሸሪዓዊ ብይን) የሚገለጽበት መንገድ ማለት ነው።
الطريق الذي يبين به أحكام الله في العبادات العلمية والعملية وفي المعاملة بين الناس .
*
👉ታዲያ በቃላዊ ደረጃ የተለያዩ መንሃጆች (መንገዶች) አሉ።
ለምሳሌ፦
የፈላስፎች መንገድ (መንሃጁል ፈላስፋ)፣
የሰለፎች መንገድ (መንሃጀ ስሰለፍ)፣
የሙስሊሞች መንገድ (ሚንሃጁል ሙስሊም) ወዘተ ይባላል።
*
✍️ነገር ግን እንደ አጠቃላይ እንደ ሙስሊም እኛ መከተል ያለብንና አርአያ አድርገን መያዝ ያለብን የመልካም ቀደምቶችን የሰለፎችን መንገድ ነው።
እርሱም "መንሃጁ ስ-ሰለፍነ ሷሊሕ" ይባላል።
ይህ መንሃጅ (መንገድ)፡
ነብያችንን ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በመልካም የተከተሉ ሶሐቦች፣
ሶሐቦችን በመልካም የተከተሉ ታቢዒዮች፣
ታቢዒዮችን በመልካም የተከተሉ አትባዑ ታቢዒዮችንና ከዚያም በኋላ ያሉትን መልካም ቀደምቶች ያቀፈ ነው።
✍️ለምሳሌ፦
ሶሐቦች እንዳሉ ሆነው እነ ኢማም አቡ ሐኒፋ፣ ኢማሙ ማሊክ፣ ኢማሙ ሻፊዒይ፣ ኢማሙ አሕመድ፣ ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ ነሳኢይ፣ ኢብኑ ማጃህ፣ አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚይ፣ ሸይኹል ኢስላም ኢቡ ተይሚይያህ፣ ኢብኑ ቁዳማህ፣ ኢብኑ ዓብዱልበር፣ ኢብኑ አቢ ዱኒያ፣ ኢብኑል ቀይዩም፣ ኢብኑል ጀውዚይ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ እና ሌሎችም።
✍️ከዘመናችን ታላላቅ እንቁዎች ውስጥ ደግሞ፥
ኢማም ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ኢማም አልባኒ፣ ሸይኽ ሙቅቢል፣ ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚ፣ ሸይኽ ሰዕዲይ እና ሌሎችም።
✍️አሁን ላይ በህይወት ካሉት ውስጥ ደግሞ፥
ሸይኽ ዶ/ር ሷሊሕ ፈውዛን፣ ሸይኽ ረቢዕ አል መድኸሊይ፣ ሸይኽ ዶ/ር ሙሐመድ ሰዒድ ረስላን፣ ሸይኽ ዶር ፕሮፌሰር ሱለይማን አር-ሩሐይሊ፣ ሸይኽ ዶ/ር ፕሮፌሰር ዓብዱረዛቅ አልዐባድ፣ ሸይኽ ሱሐይሚይ፣ ሸይኽ አሊ አደም፣ አል-ሸይኽ እና ሌሎችም።
*
✍️እነዚህ ከዋክብቶች በመንሃጀ ስሰለፍ (በቀደምቶች ትውፊት፣ ፋና) ላይ ያሉ ናቸው።
ቁርአንና ሐዲሥንም እነዚያ ቀደምቶች በተረዱትና ተግብረውት በነበረው ነገር ይረዳሉ፣ ይተገብራሉ።
አስተምህሯቸውም ከነርሱ ያፈነገጠ አይደለም።
በዚህም የተነሳ አህሉ ሱንና ወልጀመዓ ይሰኛሉ።
ሱንናን አጥብቀው በመያዝ በሐቅ ላይ የተሰባሰቡ ናቸውና።
*
👉ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በእስልምና ሽፋን የተለያዩ የጥመት አንጃወች እንደ አሸን ፈልተዋል።
ከቀደምት ሰለፎች መንሃጅ ውስጥ የሌለን አካሄድ በመሄድ፣
የራሳቸውን መንገድ ቀይሰው እየሄዱ ነው።
ከነዚህ ከተፈለፈሉ መንሃጆች ውስጥ
ለምሳሌ:
~~~~~~~
የሺዓ መንሃጅ፣ የአሕባሽ መንሀጅ፣ የሱፍያ መንሃጅ፣ የኢኽዋን መንሃጅ፣ የተብሊግ መንሃጅ፣ የሐዳድያ መንሃጅ፣ የጀህምያ መንሃጅ፣ የአሻዒራ መንሃጅ፣ የሙዕተዚላ መንሃጅ፣ የኸዋሪጅ መንሃጅ፣ የተክፊር መንሃጅ ወዘተ የመሳሰሉት፣
ሁሉም ከአህለ ሱንና ወል ጀመዓ ያፈነገጡና ከሰባ ሁለቱ ጠፊ ቡድኖች ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።
እነዚህ በውጭ ሃገር ብቻ የሚገኙ አይደሉም።
በሃገራችንም ውስጥ አሉ።
✍️ለምሳሌ፦
ኢኽዋን የሚባሉት ቡድኖች
አንድን ህዝብ በመሪህ ላይ አምጸህ ውጣ ብለው ለከፋ ችግር ሲዳርጉት በየሃገሩ ይስተዋላል።
በሰላማዊ ሰልፍ፣ ከዲን ይልቅ በስልጣን ጥማት የተነሳ የፖለቲካ ፍትጊያ መገለጫቸው ነው።
አብዛኛውን ጊዜ ሚዲያ ያገነናቸውና በሰፊው የዋህ ህዝብ ዘንድ ታዋቂነት ያላቸው ሰዎች በብዛት ይገኙበታል።
*
✍️አህለ ሱንና ወል ጀመዓዎች የተለያዩ መጠሪያዎች አሏቸው።
ለምሳሌ፥
በቀደምቶች ትውፊት ላይ የሚጓዙ ስለሆነ ሰለፍዮች ይባላሉ።
ከእሳት የምትድነዋ አንዷ ብቻ ስለሆኑ ይባላሉ።
"ጧኢፈቱ መንሱራም" ይባላሉ።
ሁሉም መልካም ገለጻዎች ስለሚገልጿቸው ነው።
*
*
✍️ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀው፣
ሁሉንም ከሱንና ያፈነገጡ፣ የሰለፎችን መንሃጅ (መንገድ፣ ትውፊት) የሳቱ ቡድኖችንና ግለሰቦችን በመራቅ፤
በትክክለኛው የቀደምቶች (የሰለፎች) መንሃጅ ላይ ጸንቶ መጓዝ ነው።
ቁርአንና ሐዲሥንም እነርሱ ተረድተው በኖሩበት መንገድ መኖር ነው።
መርሃችን «ቁርአንና ሐዲሥን በመልካም ሰለፎች አረዳድ መረዳት መሆን አለበት።»
መንሃጃችንም የሰለፎች መንሃጅ ይሰኛል።
ለነርሱ የበቃው ይበቃናል።
ወደ ሰለፎች በተግባሩና በንግግሩ የተጠጋም "ሰለፍይ" ይባላል።
አንድ ሰው "ሰለፍይ ነኝ!" ሲል "ሙስሊም አይደለሁም!" ማለቱ አይደለም።
እንዳውም ለሙስሊምነቱ ምንም ጥርጥር የለውም።
"እያንዳንዱ ሰለፍይ ሙስሊም ነው።
እያንዳንዱ ሙስሊም ነኝ ባይ ግን "ሰለፍይ" ሊሆን አይችልም።"
አንዳንዶች ሲባሉ ይደነግጣሉ።
ሰለፍያ ማለት ግን የሰለፎች (ማለትም የሶሐቦችና የታቢዒዮች) መንገድ ነው።
ለሌሎች ሼር ያርጉ ጆይን አይዘንጉ !!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/tewihd