የኢስላም ጀግና ወጣቶች ቻናል


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ቢስሚላሂ በአላህ ስም የተከበራችሁ ሙስሊም !ወንድምና እህቶች አሰላሙ አለይኩም አላህ≈ በተከበረዉ ቃሉ እንዲህ ይለናል*[ወዘኪር ፈኢነዚክረ ተንፈኡል ሙእሚኒን]* እና በዚህ#ቻናል ላይ አንዳድ ሙስሊሙን የሚመለከት በተለይም#ወጣቱን የሚመለከትትምህርቶችን እናስታዉሳለን!!

ሀሳብ አስተያየት ካለዎት ስለቻናላችን ያጋሩ
@shebabelmuslimin_bot
@shebabelmuslimbot

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


❝በርካታ በሽታ የሚያሰቃያቸው ሰዎች ምንም ዓይነት መድኃኒት ሳይጠቀሙ ይሽራሉ። ይኼም የሚሆነው ተቀባይነት ባለው ዱዓ ወይ ጠቃሚ በሆነ ሩቃ ወይ በልብ ጥንካሬና በአላህ ላይ በመመካት ነዉ።❞

ኢብኑ ተይሚያ

t.me/shebabelmuslimin


የዙልሒጃን 10 ቀኖች መፆም የፈለገ‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
✍የዙል ሒጃ ፆም ነገ ሐሙስ ይጀምራል።
1⃣✏️ ሐሙስ
30/ 7/ 2022

2️⃣✏️ ጁሙዓ
1/ 7/ 2022

3️⃣✏️ቅዳሜ
2/ 7/ 2022

4️⃣✏️እሁድ
3/ 7/ 2022

5️⃣✏️ ሰኞ
4/ 7/ 2022

6️⃣✏️ማክሰኞ
5/ 7/ 2022

7️⃣✏️ሮብ
6/ 7/ 2022

8️⃣✏️ሐሙስ
7/ 7/ 2022

9️⃣✏️ጁሙዓ አረፋ ላይ ለመቆም ያልበቃ ጁሙዓ ይፆመዋል 8/ 7/ 2022
የአረፋ ፆም የሚመጣውን ያለፈውን የአመት የሚመጣውን የአመት ወንጀላችን የማበስ ፈድል አለው።

🔟 ቅዳሜ የውሙል አረፋ ኢዱል አድሀሙባረክ 9/ 7/ 2022

የዐረፋ እለት ፆም ከዚህ አመት ቀድሞ ያለውንና የቀጣዩን ኣመት እንደሚያስምርልን ከአላህ ኣስባለሁ»።
ረሱል(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
📒ሙስሊም ዘግበውታል

✅ መልዕክቱ እናንተ ጋር እንዲቀር አትፍቀዱ ሌሎችን አሰወታውሱበት በትኑት!!
||
t.me/YasinMuhammed1


Репост из: ኢስላማዊ ግጥም
💦የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ እንድህ አሉ፣
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
▪️ሰባት አጥፊ የሆኑ ወንጀሎችን ራቁ
ሶሃቦችም አንቱ የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ እነርሱ እነማን ናቸዉ? ረሱልም ﷺ

▪️ በአሏህ ማጋራት
▪️ ድግምት [መተት]
▪️በሃቅ ቢሆን እንጂ አሏህ ሓራም ያደረጋትን ነፍስ መግደል
▪️ወለድ መብላት [ሪባ]
▪️ የየቲምን ገንዘብ መብላት
▪️ በጦር ግዜ ማፈግፈግ
▪️ጥቡቅና (ከዝሙት)ዝንጉ የሆነችን ምዕምናት (በዝሙት) መስደብ‼️
[البخاري{2615} ومسلم {89}]
/Sadik_Ibnu_Heyru


Репост из: Poetess hayuzi offical…📖
ክብር ለሙእሚናት!

እናትህ...
ጀነትን ከእግሮቿ ስር መፈለግ እንዳለብህ አስብ

ሴት ልጅህ...
በአኼራ ከእሳት ከለላ (ሲትር) መሆኗን አትዘንጋ

ባለቤትህን ካየህ፣
«ከእናንተ ውስጥ የተባለው ሰው ለሚስቱ መልካም የሆነው ነው» የሚለውን አስታውስ

ክብር ለሙእሚናት


Репост из: Poetess hayuzi offical…📖
💦አቡሁረይራ رضي الله عنه እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል።

✅ ሰኞና ሀሙስ ስራዎች ወደ አላህ ይቀርባሉ። እኔ ደሞ ስራዬ ፃመኛ ሆኜ (ወደ አላህ) እንዲቀርብልኝ እፈልጋለሁ።

📚(ኢማም አህመድ ዘግቦታል)


Репост из: 🌴ለወጣቶች ምክር🌴
«ለሱ ብቻ ተዋቢ»

የአላህ መልዕክተኛ { ﷺ } እንዲህ ብለዋል፦

«መልካም ሴት ባለቤቷ ወደ እሷ ሲመለከታት የምታስደስተው ናት!»ብለዋል።

ዛሬ አብዛኛዎቹ ሴቶች የሚዋቡት ለሠርግ አሊያም ለፕሮግራም ጭራሽ ደግሞ አንዳንዶች መንገድ ላይ እንዲሁም በየሱቁ ላሉ ወንዶች ለመታየት ይዋባሉ።

እንዲህ አይነቶቹ ደግሞ ለባሎቻቸው መዋብን በቤት ውስጥ ፍፁም የዘነጉ ናቸው ።

ሷሊህ የሆነች ሴት የትና መቼ መዋብ እንዳለበት ታውቃለች።

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇

@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir


Репост из: Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
«የሰው ልጅ ወንጀል ሲሠራ የሚበድለው ራሱን ነው። አላህ የከለከለውን ተከልክሎና ያዘዘውን ታዞ ጀነት መግባት እየቻለ፤ ይህን ባለማድረግ ለጀሀነም መዳረጉ ራሱን መበደል ነው።»

[ቃል በቃል ባይሆንም ማታ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ የተፍሲር ፕሮግራሙ ላይ ሲነገር የሰማሁት]

ራስን ከመበደል አላህ ይጠብቀን‼


Репост из: Poetess hayuzi offical…📖
💦የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል።

✅ አንድ ሰው ሶስት ጊዜ አላህን ጀነት ከጠየቀ፦ ጀነትም አላህ ሆይ ይህ ሰው እኔ ውስጥ አስገባው ትላለች። ሶስት ጊዜ ከጀሀነም እሳት ጠብቀኝ ካለ፦ እሳትም አላህ ሆይ ይህ ሰው ከኔ ጠብቀው ትላለች።
📚(ቲርሚዚና ነሳእይ ዘግበውታል)

اللَّهُمَّ إنِّي أَسْأَلُكَ الْجَنَّةَ وَأَسْتَجِيْرُ بِكَ مِنَ النَّارِ
اللَّهُمَّ إنِّي أَسْأَلُكَ الْجَنَّةَ وَأَسْتَجِيْرُ بِكَ مِنَ النَّارِ
اللَّهُمَّ إنِّي أَسْأَلُكَ الْجَنَّةَ وَأَسْتَجِيْرُ بِكَ مِنَ النَّارِ


Репост из: "ኡማ ቲቪ " Tv
እንዴት ይረሳል⁉️
============

✍ ቤታቸውን ጥለው እየተሰደዱ ነበር። ትንሽ እንደተጓዙ ቦርሳዋን ስትፈትሽ መታወቂያዋን እንዳልያዘች አወቀች። እናቷን እና እህቷን "ጠብቁኝ" ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች፥ ዘገየች፣ ቀረች። እናት እና እህት ወደፊት አይሄዱ ልጅ እና እህታቸው ቀርታለች፥ ተመለሱ።
እናት ወደ ቤት ስትገባ ልጅ በጉልበቷ ተንበርክካለች። እናት ግራ ገባት። እጇን ይዛ ልታነሳት ብትሞክር ነገሩ አልሆነም። ልጅቷ የደረሰባት ግፍ ብዛት እንባዋን አድርቆታል። ግፈኞች የጣሉባትን ዱላ መሸከም ያቃተው ሰውነቷ እንባዋን እና ህመሟን ውጦ ግራ አጋብቷታል።

እናት ተናገረች

"ልጄ ምን ሆነሻል? እስኪ ተነሽ" አለቻት
ልጅቷ አንገቷ ደፍታ ቀረች፥ አቀርቅራም
"ወገቤን በሰደፍ ሰብረውታል" አለች!
እንደምንም ለሁለት ክንዶቿን ይዘው አነሷት፣ እናት እና እህት አይናቸው ያየውን ማመን አቃታቸው።
ሁለቱ ጭኖቿ በጩቤ ተወግተዋል፣ ደሟ ይፈሳል።

"ለሶስት መድፈራቸው ሳይበቃ በጩቤም ወግተውኛል" ብላ ተነፈሰች። ከዛ በኋላ እስካሁን ከአፏ ቃል አልተሰማም።

ይሄ የሆነው መርሳ ነው። የተፈፀመውም በጅልባቢስቷ ታዳጊ ወጣት ነው።

የህወኃት ሃይሎችን መጋደል ፅድቅ ነው።

ያሲን ሙሐመድ


ዶ/ር አብዱረህማን አስ-ሱመይጥ እንዲህ ይላሉ:-
"በአፍሪካ የሰብአዊ እርዳታና የዳዕዋ እንቅስቃሴ ላይ በነበርንበት ሰዓት አንዲት
አፍሪካዊት እናት ወደ አንድ ዶክተር ጋር ቀርባ አምርራ እያለቀስች
ስትለማመጠው ተመለከትኩ።ዶክተሩ የህፃናትን የህክምና ጉዳይ የሚከታተል
ነበር።
ሁኔታው በጣም ስሜቴን ስለነካኝ ዶክተሩን ስለምታለቅስበት ምክኒያት
ጠየቅኩት።ዶክተሩም:-
"በአንቀልባ ላይ የሚገኘው ጨቅላ ልጇ በሞት አፋፍ ላይ ነው የሚገኘው።እኛ
ጉዳያቸውን ከምንከታተላቸው ህፃናት ጋር አንድ ላይ ጉዳዩን እንድናይላት ነው
የምትፈልገው።ነገር ግን ለእሱ የምናፈሰው ገንዘብ ጥቅም አልባ ነው።ጥቂት
ቀናትን እንጂ መኖር የማይችል ልጅ ነው።ለህክምናው የምናወጣውን ገንዘብ
ለሌላ ልጅ ብናወጣው ይሻላል" አለኝ።
እኔም ወደ እናትየው ተመለከትኩ።ዶክተሩን በእምባ ተሞልታ የምትልማመጥበት
ሁኔታ ልቤን ነካው።
ለተርጓሚውም በየቀኑ ምን ያክል ገንዘብ እንደሚያስፈልጋት እንዲጠይቃት
ነገርኩት።እሷም ገንዘቡን ነገረችው።ገንዘቡ በጣም ጥቂት ነበር።በሀገራችን
ለለስላለሳ መጠጥ ለምናወጣው ያክል ነው!
ለዶክተሩም:-"ችግር የለውም የሷን ገንዘብ ለኔ ተውልኝ።ሙሉ ገንዘቡን እኔ
ችለዋለሁ።"አልኩት።
እናትየው በደስታ እጄን ልትስም ፈለገች።እኔም ነገሩ ቀላል እንደሆነ አበስሪያት
ከለከልኳት።
ከህክምናው በተጨማሪም ለልጇ የሚያስፈልገውን የአመት ወጪ
ሰጠኋት።ድንገት ካለቀባትም በስፍራው የስራ አጋሬ ወደነበረው ሰው
እየጠቆምኳት ከሱ የሚያስፈልጋትን ሁሉ ማግኘት እንደምትችል ነገርኳት።
በእውነቱ ያረኩት የእናትን ልብ የማረጋጋትና ልቧን የመጠገን እንጂ የልጁን
ህይወት ይመልሳል ከሚል ሃሳብ አልነበረም።በተለይ እናት ኢስላምን ከተቀበለች
አዲስ በመሆኗ በሷ ላይ ፈተናን ከመፍራትም የተነሳ ነበር ለመርዳት
ያሰብኩት።በመሆኑም ከክስተቱ በኃላ ጉዳዩን አስታውሼውም አላውቅም ነበር።
በዚህ ሁኔታ ወራት አልፈው አመታት ነጎዱ።ነገሩ ከተከሰተ ከ12 አመታት በኃላ
በምሰራበት ድርጅት ውስጥ ሳለሁ ከድርጅቱ ሰራተኞች አንዱ፤ አንዲት
አፍሪካዊት እናት አጥብቃ እንደምትፈልገኝና ከዚህ በፊትም ብዙ ጊዜ ፈልጋኝ
እንደተመላለሰች ነገረኝ።ወደ ቢሮው እንድትገባም ነገርኩት።
አንዲት እናት ከቆንጆ ህፃን ልጅ ጋር ወደ ቢሮዬ ገቡ።
"ይህ ልጄ አብዱረህማን ይባላል።ቁርአንን በሙሉ ሃፍዟል።በርካታ ሃዲሶችንም
በቃሉ አጥንቷል።ከናንተ ጋር የኢስላም ተጣሪ መሆን ይፈልጋል።" አለችኝ።
እኔም በጣም የልጁ ህፃን መሆንና የእናትን ስሜት ስለመተከት ተገርሜ:-"ለምን
ከኛ ጋር እንዲሰራ ፈለግሽ?" ስል ጠየኳት።
ስለ ጉዳዩ ምንም የተረዳሁት ነገር አልነበረም።ወደ ልጁም ተመለከትኩ።እሱም
በዐረብኛ እኔን ማናገር ጀመረ:-
"ኢስላምና እዝነቱ ባይኖር በህይወት ኖሬ ፊት ለፊትህ አልቆምም ነበር።እናቴ
ካንተ ጋር የነበራትን ታሪክ በሙሉ ነግራኛለች።ተስፋ በቆረጠችበት ሰዓት
የህፃንነቴን ቀለብና የህክምና ወጪ በሙሉ እንደቻልክለኝ ነግራኛለች።አሁን ላይ
እኔ አድጊያለሁ።አረቢኛን መናገር እችላለሁ።የሀገሬንም ቋንቋ እናገራለሁ።ካንተ
ስር ሆኜ ወደ ኢስላም መጣራት እፈልጋለሁ።ከናንተ ምግብን እንጂ ምንም
አልፈልግም።ከፈለክ ቁርአን ልቅራልህ።ስማኝ.." አለኝና የተወሰኑ አናቅፅቶችን
በውብ ድምፅ አነበበልኝ።አይኖቹ ጥያቄውን እንድቀበለው የሚጠይቁ ይመስል
ነበር።
የዚህኔ የልጁ ታሪክ ትዝ አለኝ።ለእናትየውም:-
"ይህ ልጅ ዶክተሮቹ የህክምና ወጪውን አናባክንም አንቀበለውም ያሉት ነው
እንዴ?" ስል ጠየቅኳት።
እናትም:"አዎን" ብላ መለሰችልኝ።
ልጁም ከእናት ቀበል አድርጎ:-"እናቴ ለዚህ ነው ካንተ ጋር ሆኜ እንድሰራ
የፈለገችው።ስሜንም አብዱራህማን ብላ ያወጣችለኝ ከዚያ በኃላ ነበር።" አለኝ።
በሁኔታው እራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ ድረስ ተደሰትኩ።ለአሏህም የምስጋና
ሱጁድ አደረኩ።የአንድ ለስላሳ መጠጥ ዋጋ በአላህ ፍቃድ እንዴት ተስፋ
የቆረጠች ነፍስን ህያው እንደምታደርግ በማሰብ ተደነቅኩ።
በኃላም ይህ ህፃን በአፍሪካ ላደረግነው የዳዕዋ እንቅስቃሴ የጀርባ አጥንታችን
ሆኖ ከኛ ጋር አሳለፈ።
ጥቂት ምፅዋት የሰው ደስታን መፍጠር፤ህይወትንም መቀየር ትችላለች
.............................
ዶ/ር አብዱረህማን በአፍሪካ የዳዕዋ እንቅስቃሴያቸው ከ11 ሚሊየን በላይ
ሰው የኢስላምን ሂዳያ እንዲያገኝ ሰበብ ሆነዋል።
Ibrahim Taj Ali


በህልሙ ሚያስፈሩ ነገራቶችን በማየት ለተቸገረ ሰው ነብያዊ መድሀኒት

🍂አንድ ሰው ወደ መልእክተኛው ﷺ ዘንድ መጣና በህልሙ ስለሚያየው አስፈሪ ነገራቶች ስሞታ ነገራቸው።

ከዛም የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት ወደ መኝታህ ስትሄድ ይህንን በል:

((أعوذُ بكلماتِ اللَّـهِ التامَّةِ ، من غضبِهِ وعقابِهِ ، ومِن شرِّ عبادِهِ ، و من همزاتِ الشياطينِ ، و أنْ يحضرونَ ))

((አኡዙ ቢከሊማቲላሂ ታማቲ ሚን ገደቢህ ወኢቃቢህ ወሚን ሸሪ ኢባዲህ ወሚን ሀመዛቲ ሸያጢን ወአያህዱሩን))

📒አልባኒ ሀሰን ብለውታል
📚 ሲልሲለቱ ሰሂህ- ሀዲስ ቁጥር (2644)

@alfiqhulmuyser


የሙዚቃ መሣሪያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31፥6 ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት *”አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ”*፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْتَرِي لَهْوَ الْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا ۚ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ

መልእክት በመልካም ንግግር ግጥም አድርጎ ለአገር፣ ለባልና ሚስት፣ ለወላጅ ማቅረብ እና ስንኝ መሰኘት ይቻላል። ነገር ግን መልእክት በመጥፎ ንግግር ግጥም አድርጎ ለአገር፣ ለባልና ሚስት፣ ለወላጅ ማቅረብ እና ስንኝ መሰኘት ከግብረገብ ውጪ ነው። ታዲያ ዘፈንሳ? አዎ ዘፈን በሙዚቃ እና በመሳሪያ የታጀቡ እንጉርጉሮ ነው፥ ዘፈን ሙዚቃ፣ የሙዚቃ መሳሪያ እና እንጉርጉሮ የታጀበት ስለሆነ ከሸይጧን ነው፦
31፥6 ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት *”አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ”*፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْتَرِي لَهْوَ الْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا ۚ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 31፥6
“ኢብኑ መሥዑድ እንደተናገረው፦ *”ከሰዎችም ከአላህ መንገድ ሊያሳስት ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ” የሚለው ወሏሂ እርሱ “ዘፈን” ነው”*። كما قال ابن مسعود في قوله تعالى : ( ومن الناس من يشتري لهو الحديث ) قال : هو – والله – الغناء .

“ለህወል ሐዲስ” لَهْوَ الْحَدِيث ማለትም “አታላይ ወሬ” ማለት ሲሆን “ጊናእ” ነው፥ “ጊናእ” غِنَاء የሚለው ቃል “ገና” غَنَّى‎ ማለትም “ዘፈነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ዘፈን” ማለት ነው። አምላካችን አላህ ኢብሊሥ የሚከተሉትን በድምጹ እንደሚያታልላቸው ተናግሯል። ይህም ድምጹ መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣ እና ስላቅ ነው፦
17፥64 *ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል*፡፡ وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 17፥64
*”ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል” የተባለው እርሱ ዘፈን ነው፥ ሙጃሒድም አለ፦ “ድምጽ የተባለው መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣና ስላቅ ነው”*። واستفزز من استطعت منهم بصوتك قيل هو الغناء قال مجاهد باللهو والغناء أي استخفهم بذلك

"ሐላል” حَلَال ማለት “የተፈቀደ” ማለት ሲሆን “ሐራም” حَرَام ማለት “የተከለከለ” ማለት ነው። ዝሙት እና አስካሪ መጠጥ ሐራም እንደሆነ ሁሉ ሙዚቃም ከዝሙት እና ከአስካሪ መጠጥ ጋር ተያይዞ ክልክል መሆኑ በነቢያችን”ﷺ” ሐዲስ ተነግሯል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 16
አቡ ዐሚር ወይም አቡ ማሊኩል አሽዐሪይ እንደተረከው፦ “ወሏሂ አልዋሸውም! ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦ *”ከኡመቴ ውስጥ ጥቂት ሰዎች ለራሳቸው ዝሙትን፣ ሐር ልብስን፣ አስካሪ መጠጥን እና የሙዚቃ መሣሪያ ሐላል የሚያደርጉ ይሆናሉ”*። قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو عَامِرٍ ـ أَوْ أَبُو مَالِكٍ ـ الأَشْعَرِيُّ وَاللَّهِ مَا كَذَبَنِي سَمِعَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ “‏ لَيَكُونَنَّ مِنْ أُمَّتِي أَقْوَامٌ يَسْتَحِلُّونَ الْحِرَ وَالْحَرِيرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِفَ

አሏህ በሙዚቃ መሣሪያ የሚነሽዱትን ሰዎች ሂዳያህ ይስጣቸው! አሚን።
----------------------------------
ለአስተያየት ወይም ጥያቄ ብቻ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@Yasinnurubot

@yasin_nuru
@yasin_nuru


በአማርኛችን፦
አንድ የቀዶ ጥገና ባለሙያ አንድ ድንገተኛ ታማሚ ስለመጣ ከሆስፒታል አስቸኳይ ጥሪ ተደወለለትና መጣ።

ቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ ከመግባቱ በፊት በር ላይ የታማሚው ልጅ አባት ጠበቀውና «ለምን ዘገየህ? ልጄ አደጋ ላይ ነው!፣ ትንሽ እንኳ ርኅራሄ የለህም?» አለና ጮኸበት።
ዶክተሩም ፈገግ አለና በተረጋጋ መንፈስ «ተረጋጋ! ሥራዬን ልሥራበት። ልጅህ በአላህ ጥበቃ ስር መሆኑን እወቅ!» አለና መለሰለት።
እኚህ አባትም «እንደት ልትረጋጋ ቻልክ? አሁን ይህ ያንተ ልጅ ቢሆን ኖሮ እንዲህ ትረጋጋ ነበር? ሌሎችን መምከር ቀላል ነው!» አሉት ለዶክተሩ።
ዶክተሩም ዝም አላቸውና ወደ ቀዶ ጥገና ክፍሉ ገብቶ ለሁለት ሰዓታት የቆዬ ቀዶ ጥገና ካካሄደ በኋላ ሲወጣ «አል-ሐምዱ ሊላህ! ቀዶ ጥገናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። ልጅህ በጣም ደህና ነው። አሁን ሌላ ቀጠሮ ስላለብኝ ይቅርታ አድርግልኝና ልሄድ ነው ብሎት ምንም ጥያቄ ለማዳመጥ ሳይሞክር ሄደ።

ነርሷ ከቀዶ ጥገና ክፍሉ ስትወጣ «ይሄ ጨካኝ ዶክተር ምን ሆኖ ነው?» ሲል ጠየቋት እኚህ አባት።
እርሷም «ልጁ በመኪና አደጋ ሙቶበታል። አስቸኳይ የስልክ ጥሪውን መልሶ የመጣው ልጅዎ ያለበትን ሁኔታ ስለተረዳ ነው። እናም አሁን የርስዎን ልጅ ካዳነ በኋላ የልጁን ቀብር ለመታደም በአስቸኳይ መሄዱ ነው።» ብላ መለሰችለት!


✔ bከዚህ ምን ትምህርት እንወስዳለን፦
አንተ ትክክል ነህ ማለት ሌሎች ተሳስተዋል ማለት አይደለም።
ህይዎትን ከሌሎችም አንፃር ለመመልከት እንሞክር‼
ልጅህ ሙቶ ሳትቀብር የሌላውን ልጅ ለማከም መምጣት ትልቅ ሞራል ይጠይቃል።
|


"No reason to stay is a good reason to go!" Unknown

«ለመቆየት ምክንያት አለመኖር፤ ለመሄድ ጥሩ ምክንያት ነው።»


በሆነ ቦታ ላይ የምትቆይበት ምክንያት ከሌለህ፤ ከዚያ ቦታ ለመውጣት በቂ ምክንያት ነው።

ከአንዳንድ ሰዎች ልብ ውስጥም የምትቆይበት አሳማኝ ምክንያት ከሌለህና እነርሱ ካልፈለጉህ፤ ውጣ ከሰው ልብ ውስጥ! ካልፈለጉህ ምን ታደርጋለህ?

በግድ ነው እንደ¡

ሐቢቢ! የሚፈልግህን እየሸሸህ፤ የማይፈልግህን አትከተል!
ጊዜህን አታባክን‼

ደግሞ ከኔ ህይዎት ጋ የሚያገናኘው ነገር የለም። ለናንተ ልንገራችሁ ብዬ ነው! እንዳትፈላፈሉ! ብትፈላፈሉም የምታገኙት ነገር የለምና!


"No reason to stay is a good reason to go!" Unknown

«ለመቆየት ምክንያት አለመኖር፤ ለመሄድ ጥሩ ምክንያት ነው።»


በሆነ ቦታ ላይ የምትቆይበት ምክንያት ከሌለህ፤ ከዚያ ቦታ ለመውጣት በቂ ምክንያት ነው።

ከአንዳንድ ሰዎች ልብ ውስጥም የምትቆይበት አሳማኝ ምክንያት ከሌለህና እነርሱ ካልፈለጉህ፤ ውጣ ከሰው ልብ ውስጥ! ካልፈለጉህ ምን ታደርጋለህ?

በግድ ነው እንደ¡

ሐቢቢ! የሚፈልግህን እየሸሸህ፤ የማይፈልግህን አትከተል!
ጊዜህን አታባክን‼

ደግሞ ከኔ ህይዎት ጋ የሚያገናኘው ነገር የለም። ለናንተ ልንገራችሁ ብዬ ነው! እንዳትፈላፈሉ! ብትፈላፈሉም የምታገኙት ነገር የለምና!


ከማንም ምንም አትጠብቅ! ብዙ ጊዜ ሰዎች ውስጣቸው የሚጎዳው፤ ከሌላው ብዙ ስለሚጠብቁ ነው።
"The best way to avoid disappointment is to not expect anything from anyone." - Unknown

No one is coming to save you. Do not depend on others if you want to be wealthy.

This life is 100% your responsibility. If you want to become wealthy, depend on yourself.


📌 የሆነ ነገር ሲረሳ ለማስታወስ ተብሎ አሏሁመ ሶሌ አላ ሙሀመድ ማለት⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች❓
♻️ : ክፍል 152

📌ጥያቄ📌
📌ብዙ ጊዜ ሰዎች እቃም ይሁን የሆነ ነገር ሲጠፋቸው #ለማስታወስና ትዝ እንዲላቸው ብለው "#አሏሁመ_ሶሌ_አላ_ሙሀመድ" ይላሉ ለዚህም ደግሞ #ሀዲስ አለ ይላሉ ይህ እንዴት ነው⁉️

✅መልስ✅
✅ መርሳት አላህ በቁርአኑ እንደጠቀሰው ከሸይጧን የሚመጣ ጉትጎታ ነውና አንድ ሰው የሆነ ነገርን ለማስታወስ ሲቸገርና #ሲረሳው ማድረግ ያለበት #አላህን ማስታወስና አላህ ትዝ እንዲያስብለው አላህን #ዱዓ ማድረግ ነው።ለዚህም አላህ እንዲህ ይላል:—
🔵"በረሳህም ጊዜ ጌታህን አውሳ"
📚ሱረቱል ከህፍ ፣ 24

📌 ነገር ግን በዚህ ፈንታ #ሶላዋት [አሏሁመ_ሶሌ_አላ_ሙሀመዲን] ማለት በሸሪዓችን መሰረት #የሌለው ተግባር ነው። በዚህ ዙሪያ የመጣውም #ሀዲስ በጣም ዶዒፍና #ቅጥፈት ነው።

♻️ ምንጭ :— 📚ተፍሲሩል ቁርጡቢ ፣ 10/386 ፣ 📚ኢብኑል ጀውዚይ ፣ ኪታብ ዛዱል ሙየሰር ፣ 5/128 ፣ 📚ኢብኑ ኡሰይሚን ፣ ፈትዋ ኑሩን አለደርብ

◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•◈
🖋ሙሀመድ ሀሰን (ጁድ)

@yasin_nuru
@yasin_nuru


ሙስሊሟ እህቴ ሆይ!!👉ሂጃብ የሰው ውሻ ከሆኑ እና የልብ በሽታ ካለባቸው ሰዎች ከሚያመነጩት መርዛማ እይታ ይጠብቅሻል ።ሒጃብሽን በፅናት ከያዝሽው የተቃጠለ ስሜትን ካንቺ ይነቅልልሻል ።ሂጃብን ለምትዋጋ ወይም የሂጃብን ጉዳይ ቀለል አድርጋ ለምታይ አላማ አዘል ተጣሪ ቦታ አትስጪ።እርሷ ላንቺ የምትመኝልሽ #ሸርን ነው ።አላህም እንዲህ ይላል ፦"እነዚያም ፍላጎታቸውን የሚከተሉት ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ"(አን-ኒሳእ:27)

ተንቢሃት መፅሐፍ 4ተኛ እትም ላይ ገፅ 50 ላይ የተወሰደ

ይህ ክታብ የተፃፈው በተላቁ ዓሊም በዶ/ር ሸይኽ ሷሊሕ ኢብኑ ፈውዛን ኢብኑ አብደላህ አል ፈውዛን ነው ።(ሀፊዛሁላህ ሸይኻችን)


ከቤት ሲወጣ እና ወደ ኢንተርኔት
ዓለም ሲገባ…

የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) ከቤት ወደ ገሃዱ አለም ሲወጣ ተውሂድን በተግባር አስተምረዋል። በዚህ ዓለም ከፍጥረታት ጋር ከሚገጥሙን ጉዳዮችና ግንኙነቶች ውስጥ በዘመናችን የለው የኢንተርኔት ዓለም አንዱ ነው። እውነቱ ፣ሀሰቱ ፣ አዋቂው ፣ ጃሂሉ፣ ፈተኙ ፣ አራሚው ፣ አስተካካዩ፣ አጥማሚው፣በዳዩ ፣ ተበዳዩ ወዘተ ያሉበት የተደበላለቀ ዓለም ነው።

እነዚህን ውድ ዱዓዎች ልብ እንበል

عَنْ أُمِّ سَلَمَةَ قَالَتْ : مَا خَرَجَ النَّبِيُّ صَلَّى
اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مِنْ بَيْتِي قَطُّ إِلَّا رَفَعَ طَرْفَهُ إِلَى السَّمَاءِ فَقَالَ : " اللَّهُمَّ أَعُوذُ بِكَ أَنْ أَضِلَّ أَوْ أُضَلَّ، أَوْ أَزِلَّ أَوْ أُزَلَّ، أَوْ أَظْلِمَ أَوْ أُظْلَمَ، أَوْ أَجْهَلَ أَوْ يُجْهَلَ عَلَيَّ ".
الألباني: (صحيح أبي داود 5094)

አይንን ወደ ላይ ቀና በማድረግ
1⃣《አላሁመ አዑዙ ቢከ አን አዲለ አው ኡደለ ፣ አው አዚለ አው ኡዘለ ፣ አው አዝሊመ አው ኡዝለመ ፣ አው አጅሀለ አው ዩጅሀለ አለየ》ማለት።

አላህ ሆይ
በራሴ ከመጥመም ወይም ሌላው ከሚያጠመኝ ፣ ከሀቅ በራሴ ከመንሸራተት ወይም ሌሎች ከሚያንሸራትቱኝ ፣ ሌሎችን ከምበድል ወይም በሌሎች ከመበደል ፣ የአላወቂን ተግባር ከመፈፀም ወይም ከሚፈፀብኝ በአንተ እጠበቃለሁኝ።

عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ ، أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : " إِذَا خَرَجَ الرَّجُلُ مِنْ بَيْتِهِ فَقَالَ : بِاسْمِ اللَّهِ، تَوَكَّلْتُ عَلَى اللَّهِ، لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللَّهِ " قَالَ : " يُقَالُ حِينَئِذٍ : هُدِيتَ وَكُفِيتَ وَوُقِيتَ. فَتَتَنَحَّى لَهُ الشَّيَاطِينُ، فَيَقُولُ لَهُ شَيْطَانٌ آخَرُ : كَيْفَ لَكَ بِرَجُلٍ قَدْ هُدِيَ وَكُفِيَ وَوُقِيَ ؟ ".
الأباني (صحيح الترمزي 4326)
وأخرجه أبو داود والنسائي وابن حبان وابن السني .

2⃣…ቢስሚላሂ ተወከልቱ አለላሂ ፣ ላ ሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ…

ይህን ዱዓ ያደረገና የተገበረ
📣ወደ ሀቅ ተመራ

📣 ለሚያሳስበው ጉዳይ ዋስትና
ተሰጠው

📣 ከክፉት ተጠበቀ

📣 የሰው፣የጂን አና የእንስሳት ሸይጣኖች ሁሉ ፈርተውት ሸሹ

በጣም ያስፈልገናል ‼️

✍ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያ)


◾️ሸህ ኢብኑ ባዝ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።

✅ የተቀደደ ወይም የበሰበሰበ ጥቅም መስጠት የማይችል የቁርአን ወይም (የኪታብ) ወረቀት ስናገኝ፦
👉ማቃጠል ወይም
👉ንፁህ በሆነ ቦታ ላይ መቅበር ነው።

📚: فتاوى نور على الدرب 11337

Показано 20 последних публикаций.

1 188

подписчиков
Статистика канала