Postlar filtri


መልዕክት
የ2017ዓ.ም የማጠቃለያ ፈተና በሰላም ያጠናቀቅን ሲሆን ተማሪዎች ፈተናዎችን ለመውሰድ የሚመጡት ቀን:-
*26/05/17 ጠዋት 2:30-5:00 ፈተናዎቻቸውን የሚወስዱ ይሆናሉ።
*የውጤት ስህተት ያለባቸው ተማሪዎች በእለቱ ከመምህራኖቻቸው ጋር ተማምነው መጨረስ ይኖርባቸዋል።
*27/05/17እስከ 30/05/17 ለተማሪዎች የእረፍት ጊዜ ይሆናል።
*03/06/17 የሁለተኛ መንፈቀ ዓመት ትምህርት የሚጀመር ይሆናል።




⭐️በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!✅
========================
⭐️ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::

⭐️ከፈተና በፊት ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምንችለበት መንገድ:-
------------------------------------------------
✅ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።

✅ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡

✅ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። 

✅ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።

✅ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።

✅ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። 

✅✅✅✅✅






ለተማሪዎች
የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ነገ የአይ.ቲ ደብተራችሁን ይዛችሁ እንድትገኙ መምህራችሁ ስለሚፈልገው።




ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የአግሪካልቸር እና የአይ.ሲ.ቲ መማሪያ ደብተር መምህራኖቻችሁ ስለሚፈልጉ ነገ (እሮብ )ይዛችሁ እንድትገኙ።
👉ሙከራ ሶስት አግሪካልቸር ት/ት አርብ የሚሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ።
👉 በተደጋጋሚ ጊዜ ከተማሪዎቻችን እና ከወላጆች ጋር ውይይት ብናደርግም መሻሻል ያላየንባቸው የጠዋት የተማሪ መግቢያ ሰዓትን ጠብቆ አለመድረስ እየታየ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ በኃላ እየጨመረ በመምጣቱ ከነገ ጥር8/2017 ጀምሮ ሁሉም ተማሪ 2:00ተጠቃሎ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ መድረስ ይጠበቅባቸዋል ። በሰዓቱ በማይገኝ ተማሪ ት/ቤቱ የማያስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።
👉ለሰርቢስ ተጠቃሚዎች አገልግሎት ሰጪ አካላት በተለያየ ችግር እክል ገጥሟቸው በሰዓቱ የማይደርሱ ከሆነ ቀድመው ለት/ቤቱ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል።ተማሪዎችም ከቤት መውጫ ሰዓት ባስቀመጡላችሁ ጊዜ ሆኖ እንዲተገበር እናሳስባለን ።
ት/ቤቱ


ለተማሪዎች
የሙከራ 3 ለተማሪዎች የሚሰጥበት ጊዜ ከጥር6-9/2017 በመሆኑ ሁሉም ከ9-11 ክፍል ያላችሁ ተማሪዎች እና ወላጆች ዝግጅታቸውን የበለጠ እንዲያከናውኑ ይርዶቸው።


ውድ የአቡነ ጎርጎርዮስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወላጆችና አሳዳጊዎች እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን የሁለተኛው  የተርም ክፍያ የሚከፈለው ከጥር 1 እስከ ጥር 10 /05/2017 ዓ.ም ድረስ  ብቻ መሆኑን አውቃችሁ እንድትከፍሉ እናሳስባለን ።
✍️የሒሳብ ቁጥር፦ በአሀዱ ባንክ 0000582310901[ለኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ  አ.ማ]
✍️ክፍያውን ገቢ ሲያደርጉ በተማሪዎቹ ስም እና መለያ ቁጥራቸው በደረሰኙ ላይ ላይ እንዲገባ ተደርጎ መሆን ይኖርበታል ።


እንኳን ለ2017ዓ.ም ለጌታችን ለመድኃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዐል በሰላም አደረሳችሁ ።










በንፋስ ስልክ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በግንቦት 20 ክላስተር ማዕከል በአቡነ ጎርጎሪዎስ ትምህርት ቤቶች በለቡ ቅርንጫፍ ሁለተኛ ደረጃ በቀን 25/04/17 የልምድ ልውውጥ ተደረገ :: በእለቱ በስሩ የሚገኙ ሁሉም የመንግስት እና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህራን ፣ሱፐርቫይዘሮች እና ክላስተር ማዕከል አስተባባሪ በተገኙበት
1, የት /ቤቱ አሰራር እና የቢሮ አደረጃጀት
2,በአገልግሎት ሰጭ ክፍሎኝ(የት/ማበልጸጊያ ማዕከል፣ቤተ ሙከራ፣የሲ.ቲ.ኢ አተገባበር ) 
3, የቤተ ሙከራ ተግባራት እና የተማሪዎች ስራ፣የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክበብ የመሳሰሉ ጠቅላላ ስራ እና አሰራሮች ላይ ጉብኝት እና እይታ በማድረግ የትምህርት ቤቱ ሂደታዊ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
👉በቀረቡት መርሃ ግብሮች ተጋባዥ ት/ቤቶች ሀሳባቸውን ካጋሩን በኃላ ይህንን ዝግጅት ላዘጋጁልን የትምህርት ቤቱ አመራሮች እና የት/ቤቱ ማህበረሰብ ክላስተሩ ማዕከሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።🙏🙏🙏🙏


የአቡነ ጎርጎሪዬስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቡ ቅርንጫፍ በጎ አድራጎት ክበብ( Charity Club) በስለእናት የህጻናት መርጃ ድርጅት በመገኘት ችግር ላለባቸው ህጻናት እና የአእምሮ እክል ያለባቸውን በመጎብኘት የገናን በዓል በማስመልከት የንጽህና መጠበቂያ፣የተለያዪ አልባሳት፣ጫማዎች፣ደረቅ ምግቦች ድጋፍ አደረጉ።
በልገሳ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የክበቡ አባላት ተማሪዎች በአዩት ነገር የተሰማቸውን ሀሳብ በተማሪ ዮሃና ዳዊት እና ተማሪ አትናቲዎስ ሰለሞን ያጋሩ ሲሆን በቀጣይ የት/ቤታችን ማህበረሰብ በግል ሆነ በት/ቤት ደረጃ ልገሳችሁን
እንድታደርጉ መልዕታቸውን በማስተላለፍ በበጎ አድራጎት ክበብ ስም ለረዳችሁን ተማሪዎች እና ወላጆች ከልብ እናመሰግናለን።




ABG Lebu branch (2017 G12) dan repost
ውድ የስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ቤተሰቦች አቡነ ጎርጎርዮስ ለቡ ቅርንጫፍ ተማሪዎቸ እና መምህራን በዛሬ እለት በድርጅታችን በስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ተገኝታችሁ ስለጎበኛችሁን እና ስላበረከታችሁት ድጋፍ እና  የራሳችሁን ማህበራዊ ሀላፊነቶችን ስለተወጣችሁ  በምናሳድጋቸው እና  በምንከባከባቸው ልጆች ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እያቀረብን በቀጣይም በሌሎች ፕሮግራሞቻችን ላይ እንደምትገኙ እና ሌሎችም የዚህ የበጎ ተግባር ተሳታፊ እንዲሆኑ እደምትጋብዙ  ተስፋ አለን
ስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት የተሻለ የልጅነት ግዜ ለሁሉም ህፃናት

📍አድራሻ አዲስ አበባ ሳር ቤት ቫቲካን ኤምባሲ አካባቢ ዳማ ትሬዲንግ ጎን ሁሌ ቡና ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ
☎️በስልክ ቁጥር
+251 113710770
+251 113712391
+251 940656565
+251
921939393

"የተሻለ የልጅነት ጊዜ ለሁሉም ህፃናት"
A Better Childhood for every child



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.