❓
ቁርዓን ድምፄን ሳላወጣ በእይታ ብቻ እያስተነተንኩ ቢቀራ አጅር አገኝበት ይሁን?==========================
ኢማም ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ ከተጠየቋቸው ጥያቄዎች መሃል እንዲህ የሚል ይገኝበታል
📮 #
ጥያቄ :-ክቡር ሸይኽ ሆይ አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ
#
ከፊል ሰዎች ቁርዓንን ሙስሀፉን ይይዙና ከንፈራቸውን ሳያንቀሳቅሱ ያነባሉ ይህ ሁኔታ ቁርዓን መቅራት የሚላው ስያሜ ይሰጠዋልን ? ወይስ ቁርዓን የመቅራቱን አጅር ያገኝ ዘንድ የግድ ቁርዓን ሲቀራ ማውራት ማሰማት አለበት ? ሰውየው ቁርዓኑን በማየቱ ብቻ አጅር ያገኛል ? ይመልሱልን ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን
👜 #
ምላሽ :- ወአለይኩም ሰላም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ
#
ሳያስተነትኑ እና ትርጉሙን ሳይረዱ ቁርዓንን በእይታ ብቻ ከመቅራት ምንም ከልካይ ዬለም ነገር ግን ይህ ሰው ቃሪዕ ቁርዓን የሚቀራ አይባልም ቁርዓን በመቅራት የሚገኘውም ምንዳ አጅር አይገኝለትም ምንዳውን የገኝ ዘንድ በዙሪያው ያሉ ሰዎች ባይሰሙት እንኳን የግድ ቁርዓንን ማውራት አለበት ። ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ :
(اقرءوا القرآن فإنه يأتي يوم القيامة شفيعا لأصحابه). رواه مسلم.
ቁርዓንን ቅሩ እርሱ (ቁርዓን) እኮ የቂያማ ቀን ለባለቤቱ (ለሚቀራው ሰው) አማላጅ ሆኖለት ይመጣል ።
የነቢዬ ﷺ ፍላጎት "ለባለቤቱ" ሲሉ የሚሰሩበትን ነው በሌላ ሃዲስም እንዳለው :-
(
من قرأ حرفًا من القرآن فله به حسنة ، والحسنة بعشر أمثالها) خرجه الترمذي ، والدارمي بإسناد صحيح
ከቁርዓን አንዲትን ፊደል የቀራ በሷ በቀራት አንድ ሀሰና መልካም ምንዳ አለው ሀሰናዎች መልካም ምንዳዎች ደሞ በአስር ነው የሚባዙት ።
የእውቀት ባለቤቶች እንዳሉት ደሞ አንድ ሰው ሲናገር ድምፅ ሲያሰማ እንጂ ካልሆነ አንባቢ ቃሪዕ አይባልም ።
💼 #
ምንጭ :-ኢማም ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ ከተጠየቋቸው ጥያቄዎች የወሰድኩት
✍ጅብሪል ሱልጣን
ከረመዷን ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፈትዋዎች ለማግኘት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ
✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan