"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


እንኳን አደረሰን ከትንሳኤ በኃላ ያለው ዓርብ"ቅድስት ቤተክርስቲያን" ተብላ ተሰይማለች፡፡⛪

⛪ከደጀ ሰላሙ አያርቀን🙏❤


"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
☦መልክአ ቅዱስ እስጢፋኖስ🌷


ቅዱስ እስጢፋኖስ ሆይ ሰላም እልሃለሁ/፫/
በጨነቃችሁ ጊዜ ሁሉ ቅዱስ እስጢፋኖስ አባቴ አለው ይበላችሁ።

🥰🙏🥰


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33☦📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ሚያዝያ 17/፲፯

https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊




በሕይወታችን ብዙ ነገሮችን ዐይተናል፡፡ ዐይተናቸው በውስጣችን የቀሩ፣ ዐይተናቸው የረሳናቸው፣ ዐይተናቸው ደግመን ለማየት ያልፈቀድናቸው፣ ዐይተን እንዳላየ ያለፍናቸው፣ ዐይተን የታዘብናቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ጽጌረዳን ዐይተን እሾህን እናያለን፡፡ የተንሰራፉ አበቦች በአሜኬላዎች ላይ ተጐዝጉዘው እናያለን፡፡ ዐይናችን ሁለቱንም ታያለች፡፡ ኅሊና ግን አጥርታና መርጣ ታያለች፡፡ በዐይናችን ብዙ መልካምና ክፉ ነገሮችን እናያለን፡፡ ላየነው ሁሉ ምላሽ መስጠት አያስፈልገንም፡፡ ምላሻችንን የሚፈልጉ ዕይታዎች ግን አሉ፡፡ ማየት ከመስማት በላይ ነው፡፡ ሰምቶ ምላሽ ያልሰጠ ሲያይ ግን ምላሽ ይሰጣል፡፡ ማየት የተግባር አዛዥ ናት፡፡

ሰዎች በቃል ሊገልጹት የሚያንስባቸው የመሰላቸውን ነገሮች መጥታችሁ ተመልከቱ በማለት ይጋብዙናል፡፡ በዐይናችን የሙት ልጆችን ፣ የረሀብ ሰለባዎችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ደጋፊ አጥተው የተጨነቁ አረጋውያንን፣ በግፍ የታሰሩ ምንዱባንን፣ በበሽታ የሚያለቅሱ ድውያንን፣ የመጣልና የመረሳት ፈተና የወደቀባቸውን ኅዙናንን፣ ለቀጣይ አንድ ሰዓት የመኖር ዋስትና የማይሰማቸው ቅቡፃንን አይተናል፡፡ ላየናቸው ነገሮች የሰጠናቸው መልሶች ግን የተለያዩ ናቸው፡፡፡ በአገራችን የመጀመሪያ እርዳታ ብቻ ሳይሆን የመጨረሻም እርዳታ የሆነው ከንፈር መምጠጥ ነው፡፡ ላየነው ነገር ከከንፈር ፉጨት የበለጠ ምላሽ አልሰጠን ይሆናል፡፡ የራሳችንን ችግር ከሌሎች ችግር ጋር አወዳድረን እኔ ያለፍኩትና የማልፍበት ይብሳል ብለን ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ ዓመት ለታሰረው እንዳናዝን የሦስት ዓመት እስራታችን መሰናክል ሆኖብን ይሆናል፡፡ ላየነው ችግርም የእርዳታ መንገድ ጀምረን በትንሹ በመርካት ቆመን ሊሆን ይችላል፡፡

ዓይኖቻችን ለማየት የሚናፍቁትን ያህል እጆቻችን  የወደቀውን ለማንሣት አይዘረጉም፡፡ ጆሮዎቻችን ምሥጢርን ለመስማት እህ የሚሉትን ያህል አንደበታችን ለመሸፈን አይጠነቀቅም፡፡ የማየት ጥማታችን ከፍተኛ ነው፡፡ በአገራችን ዝናብ ሲዘንብ ወደ ቤት፣ ጥይት ሲዘንብ ወደ አደባባይ የምንወጣው የማየት ጥማት ስላለን ነው፡፡ ልንፈታ የምንችለውን ነገር ማየት አንፈልግም፡፡ ልንፈታ የማንችለውን ነገር ለማየት ግን እንጨነቃለን፡፡ መሬት ላይ ወድቆ የሚያጣጥረውን ሰው በየደቂቃው ሃምሳ ሃምሳ ሰዎች ይከቡታል፡፡ ሃምሳው ለደቂቃ አይቶ ሲያልፍ ሃምሳው ይተካል፡፡ የወደቀውን የሚረዳው ግን ከመቶ አንድ ሰው ነው፡፡ የሚከብ ሁሉ የሚረዳ አይደለም፡፡ የወደቀውን የከበቡት ሰዎች፡- ‹‹ምን ሆኖ ነው?›› ‹‹አገሩ እዚህ ነው?›› ‹‹ያመመው ስኳር ነው?›› ‹‹ሌቦች ጐድተውት ይሆን?››  ‹‹ወይ ማሳዘኑ! እኔ እጥፍ ልበል፣ እናቱ እንኳን ይህን አላየች›› ‹‹ፖሊስ አይቶታል …›› ይላሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ዓይኖችና ድምፆች ወደ ሞት እየተጓዘ ያለውን ሰው አይመልሱትም፡፡ ከዚያ ይልቅ ቀዝቃዛ ውሃ በማንኪያ የሰጠው ሰው የሞትን ከባቢ ይበትንለታል፡፡ ከብዙ ትልልቅ ቃሎች አንድ ማንኪያ ውሃ ትበልጣለች፡፡ ትንሽ ተግባር ትልልቅ ቃሎችን ዝም ታሰኛለች፡፡  እነዚህ ሁሉ ድምፆች ከማየት የበለጠ አይረዱም፡፡ ቀርቦ የሚረዳ፣ በቊስል ላይ ዘይት የሚያፈስ ግን ከመቶ አንድ ሰው ነው፡፡

የስልክ እንጨት ሲተከል መንግሥት የቀጠራቸው አምስት ሠራተኞችን እናያለን፡፡ ሾፌሩ አንድ፣ እንጨቱን የሚተክሉ ሁለት፣ ግንዱ ጫፍ ላይ ወጥቶ አምፖል የሚሰቅለው አንድ ሲሆን አንደኛው ግን ከብቦ የቆመውን ሰው የሚበትን ነው፡፡ ቻይናዎቹ ሳይቀር፡- “ኢትዮጵያውያን ሌላ አገር አላቸው ወይ?” እስኪሉ ከሚሠራው የሚመለከተው እንደሚበዛ፣ ለአገራችን የእኔነት መንፈስ፣ ለሥራ ልባዊ ፍቅር እንደሌለን ታውቋል፡፡ አዎ ከሚሠራው የሚያየው ይበዛል፡፡ ማየት ሁሉ መሥራት አይደለም፡፡ ማየት ሁሉ መሥራት ቢሆን ስንት ተቺዎች የተቹትን ነገር በአጭር ታጥቀው ባስተካከሉ ነበር፡፡
   Anyways የተረዳሁት ነገር ሁላችንም በኖርንበት ባሳለፍንበት ባለን ልክ ነው የአስተሳስባችንም ውስንነት!!  በሌላ ሰው አስተሳሰብ ልክ አስቡ ባልልም ቢያንስ የሰውን ሃሳብ  በራሳችሁ ልክ አትመንዝሩ እውነት ነው መቶ ብር ለታክሲ ያጣ ሰው ስለ መቶ ሚሊዮን ቢሰማ ያጥወለውለዋል ተረጋጉ ሁላችንም የተመኘነውን እናገኛለን ቀና ልብ ቀና አስተሳሰብ Positive mind ይኑረን ብቻ 🙏

ያነበብኩትን አካፈልኳችሁ።


☞ከትንሳኤ በኃላ ያለው ዓርብ"ቅድስት ቤተክርስቲያን" ተብላ ተሰይማለች፡፡ ይህ እንዴት ነው ቢሉ፡፡በዚህ ዕለት ቅድስት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ሰለ መመሥረቷ፤ እርሱን ሰለ እርሷ አሳልፎ ሰለመሰጠቱ፤ቤተክርስቲያንም የእርሱ አካል ሰለመሆኗ ።ኤፌ 5፥21)
☞የነበያትና የሐዋርያት መሠረት በሆነው በክርስቶስ ላይ ሰለመመሥረቷ
አንድነቷም በክርስቶስ እንደሆነ(ኤፌ 2፥19-22)
☞በክቡር ደሙ ፈሳሽነት መታጠቧ(ራዕ 1፥6-10)
☞ከነገድ ከቋንቋ መመረጧ በደሙ ተዋጅታ አንድ መንጋ መሆኗ በሰማይ
ሠራዊት በምድራውያን ሰዎች ያላገኘችውን ሕይወት በእርሱ ብቻ ማግኘቷ(ራዕ
5፥1)
☞በወርቅ በብር ያልሆነ በክርስቶስ ኢየሱስ ደም ሰለመዋጀቷ(1ኛጴጥ1-፥1
8-21)
☞ከልዮ ልዮ ቦታ ተሰብስባ ተጠርታ በእርሱ ላይ መታነጿ(1ኛ ጴጥ2፥4-7)
☞ይህንን ሁሉ በማሰብ ከትንሳኤ በኃላ ያለው አርብ የቤተክርስቲያን ከብር
ለማሰብ ቅድስት ቤተክርስቲያን ብላ ቤተክርስቲያችን አሰባ ትውላለች፡።

ቴሌግራም ይቀላቀሉ

https://t.me/Orthodoxtewahdoc


ስለ እናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት

🥰✝🥰


"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
🌹#ቅዱስ_እስጢፋኖስ_ማለት📚

♨እስጢፋኖስ የግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም «አክሊል»ማለት ነው።ቅዱስ እስጢፋኖስ በግሪክ ሀገር እንደተወለደ የሚነገርለትና ከክርስቶስ እርገት በኋላም አስራ ሁለቱም ሐዋርያት በጋራ ተሰብስበውና ለአገለግሎት ከመረጡዋቸው ሰባት ዲያቆናት አንዱና ዋነኛው ነበር። ሕዝቡን በማዕድ ያገለግሉ ዘንድ ሰባት ዲያቆናት ተመርጠዋል።

🌿❤️ ከእነዚህ መካከል ቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ ሲሆን ለስድስቱ ዲያቆናት ደግሞ አለቃ ሊቀ ዲያቆን ሆኖ ተሹሟል። ቅዱስ እስጢፋኖስ በማዕድ አገልግሎት ሕዝቡን ከማገልገሉ በተጨማሪ ወንጌልን ይሰብክ ነበር ። ተዐምራትን የማድረግ ጸጋም ተሰጥቶት ነበር በዚህም አገልግሎቱ ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሷል።

🌿❤️ በዚህም አይሁድ በቅናት ተነሳስተው በሐሰት ከሰሱት ከከተማውም ወደ ውጭ አውጥተው ቄዳር በተባለ ቦታ በድንጋይ ወገሩት በሚወግሩትም ጊዜ ሰማያት ተከፍተው ምሥጢረ ሥላሴን እግዚአብሔርን በሦስትነቱ ተመለከተ።

🌿❤️ ኢየሱስ ክርስቶስንም በአብ ቀኝ ተቀምጦ አየ ። ለሚወግሩትም ሰዎች ከአምላኩ እንዲህ በማለት ምሕረትን ለመነ «ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው» በመጨረሻም «ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል»ብሎ ነፍሱን ሰጠ።

🌿❤️ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት። ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ። እስጢፋኖስም። ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። ተንበርክኮም። ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር። 《የሐ ሥራ 7፥58—60》
🌿❤️ የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት በረከትና ምልጃው አይለየን ለዘለዓለሙ አሜን
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን




"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
🌹አባ ገሪማ (ይስሐቅ )ማለት⁉🌹

«#ወር በገባ በ17 የአባ ገሪማ ዘመደራ ወርኀዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው አባ ገሪማ (ይስሐቅ) ዘመደራ🌹
📌•••አቡነ ገሪማ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሮም ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸው መስፍንያኖስና ሰፍንግያ እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ:: ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ::

+እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን #ይስሐቅ ብለው አሳደጉት:: ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ:: ለ7 ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ : መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል::

+አንድ ቀን ግን ከግብፅ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው:: ላኪው #አባ_ዸንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና" የሚል ነበር::

+ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ:: ድንገት ግን #ቅዱስ_ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ዸንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው::

+እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ #ኢትዮዽያ መጡ:: ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ (ገሪማ) ናቸው:: ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር::

+አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ዸንጠሌዎን አዘኑ:: ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ" አሉ:: አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም:: ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ ተጠራርጎ ሸሸ::

+ይሕንን የተመለከቱት አባ ዸንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ" (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ) አሏቸው:: ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "#አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ::

+አቡነ ገሪማ ወደ #መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል:: ይህም የተደረገው በዚህች ቀን (መስከረም 30) ነው::

+ጻድቁ ወንጌልን : ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:-

1.ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር::
"ነግሃ ይዘርዕ ኪነቶ:: ወሠርከ የዓርር ገራኅቶ::" እንዲል::

2.ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር::

3.አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ::

4.ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች::

5.አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ (ወንጌለ ዮሐንስን ሲጽፉ) ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን አቁመዋታል::

+ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በሁዋላ #ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው:: "ስምሕን የጠራ : መታሰቢያህን ያደረገ : እስከ 12 ትውልድ እምርልሃለሁ:: አንተ ግን ሞትን አትቀምስም" ብሏቸው ተሰወረ:: ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ #ብሔረ_ሕያዋን አድርሰዋቸዋል::

=>ቸሩ አምላካችን ከታላቁ ቅዱስ ጸጋ በረከት ይክፈለን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን::

=>+"+ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ::
ግርማው በእሥራኤል ላይ : ኃይሉም በደመናት ላይ ነው::
እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው::
የእሥራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን : ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል::
እግዚአብሔርም ይመስገን:: +"+ (መዝ. 67:34)

>https://t.me/Orthodoxtewahdoc




"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
♥#ወለተ_ጴጥሮስ_ማን_ናት⁉🌹
➖━⊱✿⊰━➖

📒☞ወር በገባ በ17 የእናታችን የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ወርሀዊ መታሰቢያዋ ነው፡፡ይቺ ደገኛ ሴት አባቷ ባሕር ሰገድ እናቷ ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ፡፡ ☞የትውልድ ሀገሯ ጎንደር ደዋሮና ነው፡፡ ይቺ የተቀደሰች እናታችን ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ በሕግ በሥርዓት በሊቀ ጳጳስ ትዕዛዝ የንጉሥ ሱስንዮስን የአማካሪዎች አለቃ የሆነው መላክአ ክርስቶስን አግብታ ሦስት ልጆችን ወልዳለች፡፡ ባሏም ታላቅና እጅግ ባለጸጋ ነበርና ከልጆች ጋር በተድላ በደስታ መኖር እንደጀመረች፡፡ አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ እነዚህ ሦስት ልጆቼ አንተን የሚያስደስቱ ከሆነ በሞት ውሰዳቸው፡፡ ብላ ከጸለየችበኃላ እንደፋላጎቷ ሦስት ልጆቿ በሞት ተወስደውላታል፡፡

☞ባለቤቷ እጅግ እየወደዳት እርሷ ግን ይህን ዓለም እንደ ጤዛ ያልፋል፡፡ ብላ
ከሞላ ሀብቷ ከሞቀ ቤቷ ተለይታ ወጥታ በመመነን ጣና ገባች፡፡ በዚያም
በተጋድሎ ስትኖር ባሏ አበምኔቱን ለምን ገዳም አሰገበሀት ብሎ ከሰሳቸውና
ከገዳሙ አስወጣት፡፡ እርሷ ግን ተደብቃ አክሱም ሄዳ ደብረ በንኮል ገዳም
ገባች፡፡ ተመልሳም መጥታ በጣና ባሕር ላይ ቆማ መጸለይ ጀመረች፡፡
በዘመኗ የነበረው ገዢ ጨካኝ ለጣዎት የሚሰግድ ሰለነበረ በትልቅ ገደል
ወረውረው እንዲጥሏት አደረጋት፡፡ ነገር ግን መልአኩ ቅድስ ሚካኤል
ከእግዚአብሔር ተልኮ መጥቶ በክንፋ ተቀብሏት ወስዶ ብሔረ ብፁዓን አሳይቶ
መልሶ አምጥቶ ዋልድባ አደረሳት፡፡

☞ቅድስት እናታችን ወለተ ጴጥሮስ ወደ ጉምዝ ሀገርም ተስዳ ሳለ በነደደ አሳትውስጥ ቢጨምሯት ምንም ሳያቃጥላት ወጥታለች፡፡ ተመልሳም በጣና ባሕርላይ ቆማ ስትጸልይ ልብሷ ለገዳሙ ያበራ ነበር፡፡ ቧላም እምነቱን ቀይሮ
ከካቶሊኮች ጋር ሰለተዛመደ ቅድስ እናታችን ካቶሊኮቶችንና ባሏን አጥበቃ
ሰለተቃወመች በገመድ አሰረዋት በጎንንደር ከተማ ጎዳና ላይ ጎትተው አሠቃያት፡

☞ቅድስ ወለተ ጴጥሮስ ሰባት ገዳማትን ያቀናች ሲሆን ከ700በላይ በሚሆኑ
ወንዶች መነኮሳትና ሴቶች መነኮሳት ላይ እመ ምኔት ሆና ተሹማ
አገልግላለች፡፡
☞ከመነነችበት ጊዜ ጀምሮ ምግቧም የመረረ ቅጠል፤ኮሶና አመድ ነበር፡፡
ቅድስት እናታችን ታላቁን የራማ መድሀኒአለም ቤተ ክርስቲያን ሠርታ ሙታንን
እያነሳች ድውያንን እየፈወሰች በታላቅ ተጋድሎ እያገለገለች ሳለ ኅዳር 17ቀን
በታላቅ ከብር ዐርፋለች፡፡ ወርሐዊ የመታሰቢያ ዕለቷ ወር በገባ በ17 ነው፡፡
በዕረፍቷም ጊዜ የብርሃን ምስሶ ከምድር ሰማይ ተተክሎ ታይቷል፡፡

☞የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዐፅሟ በራሷ በመሠረተችው በሬማ መድኃኔአለም
አንድነት ገዳም ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል ፡፡በዚህ ገዳም ውስጥ በቅድስ ሥላሴ ምሳሌ የተሠሩ ሦስት የተለያዩ ድምፆችን የሚያወጡ ደወሎች ይገኛሉ፡፡ ሦስቱም ደውሎች የሚያወጡት ድምጽ ፍጽም የተለያየ ነው፡፡

☞የእናታችን የወለተ ጵጥሮስ አማላጅነት አይለያችሁ፡፡
☞የጽሁፍ ምንጭ☞መዝገበ ቅዱሳን
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

ቤተሰብ ይሁኑን ብዙ የቅዱሳንን ታሪክ እናቀርብለወታለን https://t.me/Orthodoxtewahdoc




"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
††† እንኩዋን ለታላቁ "ሐዋርያ ቅዱስ ያዕቆብ" ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

+*" ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ "*+

=>በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከእመቤታችን
በቀር ከቅዱሳን ሐዋርያት የሚበልጥ አልተነሳም::
"ሐዋርያ" ማለት "ፍንው: ልዑክ: የተላከ: የጽድቅ
መንገደኛ" እንደ ማለት ነው:: በምሥጢሩ ግን "ባለሟል"
ብለው ሊቃውንቱ ተርጉመውታል::

+ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:-
¤የፍጥረታት ሁሉ ጌታ: የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም
ከድንግል ማርያም ተወልዶ: አድጐ: ተጠምቆ: ጾሞ:
ከገዳመ ቆረንቶስ ሲመለስ ቀዳሚ ሥራው ያደረገው ደቀ
መዛሙርቱን መጥራት ነበር::

+ከተከተሉት የ5 ገበያ ሕዝብ መካከል "ወሐረየ እምሰብአ
ዚአሁ አሠርተ ወክልኤተ ሐዋርያተ" እንዲል በመጀመሪያ
12ቱን ሐዋርያት መረጠ::

+እሊህም:-
1.ዼጥሮስ የተባለ ስምኦን
2.እንድርያስ (ወንድሙ)
3.ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
4.ዮሐንስ (ወንድሙ)
5.ፊልዾስ
6.በርተሎሜዎስ
7.ቶማስ
8.ማቴዎስ
9.ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ
10.ታዴዎስ (ልብድዮስ)
11.ናትናኤል (ቀናተኛው ስምዖን) እና
12.ማትያስ (በይሁዳ የተተካ) ናቸው:: (ማቴ. 10:1)

+እነዚህን 12 አርድእቱን ከጠራ በሁዋላ ለ3 ዓመታት ከ3
ወራት ከዋለበት ሲማሩ ይውሉ ነበር:: ሌሊት ደግሞ
ምሥጢር ሲያስተረጉሙ ያድሩ ነበር::

+ጌታ እንደሚገባ ካስተማራቸው በሁዋላ ከፍ ያለ
ኃላፊነትን ሾማቸው:: ለዓለም እረኞች: የእርሱም
ባለሟሎች ሆኑ:: እጅግ ብዙ መከራ እንደሚገጥማቸው
ነገራቸው:: (ማቴ. 10:16, ዮሐ. 16:33) በዚያው ልክ
ክብራቸውንም አከለላቸው:: (ማቴ. 19:28)

+ሥልጣናቸው ደግሞ እስከዚህ ድረስ ሆነ:: "በምድር
ያሠራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል: በምድር የፈታችሁት
በሰማይ የተፈታ ይሆናል::" (ማቴ. 18:18) "ይቅር
ያላችሁዋቸው ኃጢአታቸው ይቀርላቸዋል: ያላላቹሃቸው
ግን አይቀርላቸውም::" (ዮሐ. 20:23)

+የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ (ማቴ. 16:19):
እረኝነትን (ዮሐ. 21:15) ተቀበሉ:: ጌታ በንጹሕ አንደበቱ
ሐዋርያቱን እጅግ ሲያከብራቸው "ጨው: የዓለም
ብርሃናት" (ማቴ. 5:13) አላቸው:: ወንድሞቹም ተባሉ::
(ዮሐ. 7:5) ከዚህም በሚበልጥ በሌላ ክብር
አከበራቸው::

+ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ በጌታ ሕማማት ጌዜ ገና
ነበሩና አንዳንዶቹ ፈርተው ተበተኑ:: ተመልሰው ግን
በጽርሐ ጽዮን ሲጸልዩ ሰንብተው የጌታን ትንሳኤ
ተመለከቱ:: እጆቹን: እግሮቹንም ዳስሰው ሐሴትን አደረጉ::

+ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓት: ሌላም
በፍጡር አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢራትን ተምረው:
ጌታ ሊቀ ዽዽስናን ሹሟቸው ዐረገ::

+ለ10 ቀናት በእመ ብርሃን ሥር ተጠልለው ሲጸልዩና
በአንድ ልብ ሲተጉ ሰንብተው መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው::
በአንዴም ከፍርሃት ወደ ድፍረት ተመልሰው ፍጹማን:
ብርሃናውያን ሆኑ:: 71 ልሳናትን ነስተው በአንዲት ስብከት
ብቻ 3ሺ ነፍሳትን ማረኩ:: (ሐዋ. 2:41)

+ቅዱሳን ሐዋርያት በኅብረት ለአንድ ዓመት ያህል
በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ እየተመላለሱ አስተምረው ብዙ
እሥራኤላውያንን ወደ ክርስትና ማርከዋል:: ከዚህ በሁዋላ
ግን እንደ ትውፊቱ በዚህች ቀን ዓለምን በእጣ ለ12
ተካፈሏት::

+ይህ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ አብሯቸው ነበርና
ለእያንዳንዳቸው እንደሚገባቸው አሕጉረ ስብከቶች
ደረሷቸው:: እነርሱም ደቀ መዛሙርቶቻቸውን አስከትለው
ለታላቁ መንፈሳዊ ዘመቻ ወረዱ::

+በሔዱበት ቦታም ከተኩላ: ከአንበሳና ከነምር ጋር
ታገሉ:: በጸጋቸውም አራዊትን (ክፉ ሰዎችን) ወደ በግነት
መልሰው ለክርስቶስ አስረከቡ:: በየሃገሩ እየሰበኩ
ድውያንን ፈወሱ:: ለምጻሞችን አነጹ:: እውራንን አበሩ::
አንካሶችን አረቱ:: ጐባጦችን አቀኑ:: ሙታንንም አስነሱ::
እልፍ አእላፍ አሕዛብንም ወደ መንጋው ቀላቀሉ::

+ስለዚህ ፈንታም ብዙዎቹ በእሳት ተቃጠሉ:: ቆዳቸው
ተገፈፈ:: በምጣድ ተጠበሱ:: ደማቸው በምድር ላይ
ፈሰሰ:: ከአንድ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በቀር ሁሉም
ይህችን ዓለም በሰማዕትነት ተሰናበቱ:: ጨው ሆነው
አጣፍጠዋልና: ብርሃንም ሆነው አብርተዋልና
እናከብራቸዋለን:: "አባቶቻችን: መምሕሮቻችን: ጌቶቻችንና
ሊቆቻችን" እንላቸዋለን::

✞ ቅዱስ ያዕቆብ ✞

=>በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
ሰማዕት ሆኗል:: ቅዱሱ ሐዋርያ አባቱ ዘብዴዎስ: እናቱ
ማርያም ባውፍልያ: ትንሽ ወንድሙ ደግሞ ዮሐንስ
ወንጌላዊ ይባላል::

+ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን አሳ አጥማጅነቱን ትቶ:
ከጌታችን እግር ተምሮ በዓለም ወንጌልን አስፋፍቷል::
(ማር. 1:19) ከሌሎቹ ሐዋርያት በተለየም የእንስሳትን
ቁዋንቁዋ ያውቅ ነበር::

+በመጽሐፍ ቅዱስ በሔሮድስ መገደሉ (ሰማዕትነቱ)
የተነገረለት ከ12ቱ ብቸኛው ነው:: ሰማዕት የሆነውም
በ44 ዓ/ም : ማለትም ከጌታ ዕርገት 10 ዓመታት በሁዋላ
: ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሳይበተኑ ነው::
(ሐዋ. 12:1)

=>እግዚአብሔር ከቅዱስ ያዕቆብና ከቅድስት ቤቱ በረከት አይለየን::

=>ሚያዝያ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ ወልደ ዘብዴዎስ (ከ12ቱ
ሐዋርያት)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዘቆዽሮስ
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ

=>+"+ በዚያም ዘመን ንጉሡ ሄሮድስ መከራ ያጸናባቸው
ዘንድ ከቤተ ክርስቲያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን
ጫነባቸው:: የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ
ገደለው:: አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው አይቶ ጨምሮ
ዼጥሮስን ደግሞ ያዘው:: የቂጣ በዓልም ወራት ነበረ::
+"+ (ሐዋ. 12:1)

>




✝እንኳን አደረሳችሁ!

"" ነጻነትን ሰበከላቸው! "" (፩ኛ ጴጥ. ፫:፲፱)

"የበዓለ ትንሣዔ ትምህርት"

(ሚያዝያ 12 - 2017)

https://t.me/zikirekdusn


የብርሃን እናቱ ሆይ ካንቺ በነሳው ስጋ እኛነታችንን አከበረ፡፡መዐዛሽ ስቦት አንችን በወደደ ጊዜ ድህነታችን ተሰራ፡፡ድንግል ሆይ እውነተኛው የህይወት እንጀራ : ጣፋጩን የነፍስ መጠጥ አማናዊው የፅድቅ ብርሀን የፈነጠቀብሽ ነሽና ከትውልድ መሀል ብፅዕናሽን እንናገራለን፡፡ጥማችንን የቆረጠ ጥዑም ወይን፡ረሀባችንን ያጠፋ እውነተኛው መብል ካንቺ ወጥቶልናልና እንወድሻለን፡፡ምስራቃዊት በራችን ሆይ ከሴቶች አንችን የሚመስል የለም፡፡ባንቺ ላይ ስለተደረገልን ታላቅ ነገር ዛሬም ለዘላለምም ስምሽን እናገናለን፡፡

ዝምተኛይቱ ድንግል ሆይ አንቺ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የአይሁድ ሴቶች አይደለሽም።በትሕትና ተልመሽ በንፅሕና አጊጠሽ የባህርያችንን መመኪያ ያስገኘሽልን የፅድቅ በራችን ነሽ። አንችን ማመስገን የነፍስ ምግብ የህሊና እርካታ ነው።ስናመሰግንሽ እናርፋለን ስናርፍ እናመሰግንሻለን።ክብርሽ ከሰማይ ምስጋናሽም ከአርያም ነውና አንችን ለማመስገን ልቦናችን ይብራ አሜን።🌷


ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተመረጥሽ #እመቤታችን_ሆይ! አንቺን አናመልክም ነገር ግን ከሁሉ በበለጠ እጅግ በላቀ ምስጋና ክብርሽን እንገልጣለን።

#የተመረጥሽ_ድንግል_እመቤቴ_ማርያም ሆይ ሁልግዜ #በዓይን_ልቦናዬ አይሻለሁ . . . በሃሳቤም በየስፍራው ሁሉ አገኝሻለሁ ልጅሽም የዓለም መድሀኒት ነው ። በተኛሁም ጊዜ እኔን ለመጠበቅ የነቃሽ ነሽ ፣ከመኝታዬም ስነቃ እኔን ለማንሳት የተዘጋጀሽ ነሽ ስቀመጥም እኔን #ለመምከር ትደረሻለሽ ፣ በቆምሁም ጊዜ በቀኜ ትቆሚያለሽ ፣ በተናገርሁም ጊዜ አንደቤቴን ለማጣፈጥ ታከናውኛለሽ ፣ በዝምታዬም ጊዜ ለመጠበቄ ማሞገሻ ነሽ ፣ ሀሴትም ባደረግሁ ጊዜ ተድላ ደስታዬ ነሽ
በእውነት ምን ብዬ እንዴት ልገልጥሽ ይቻለኛል።
ዝክርሽን ዘክሬ በበረከትሽ እንድጎበኝ ፈጣሪ ይርዳኝ።
የእናታችን የኪዳነ ምህረት ረድኤት በረከት ፍቅር አይለየን አሜን ።🤲

፲፮❤️ እናቴ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ሆይ በዕለተ ቀንሽ ከክፉ ሁሉ ሰውሪን ሀገራችንን ሰላም አድርጊልን ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ  ሰውሪን።

🌷አሜን በእውነት።🙏

"ላመነባት ለተማፀናት ኪዳነ ምህረት አምባ መጠጊያ ናት🙏


https://t.me/Orthodoxtewahdoc


#"የቃል ኪዳኗ እመቤት ሆይ ለጽድቅ የሚያበቃ በጎ ምግባር ባይኖረኝም እንኳ የገሃነምን ደጅ "እንዳታሳይኝ" እማልድሻለሁ ቃል ኪዳንሽ እንዲሁ በከንቱ አይደለምና፡፡

🌹አሜን በእውነት🙏

❤       ኪዳነ ምህረት እናቴ     ❤


ስምሽ ይጣፍጣል ማር ነው ለአንደበቴ፣
ትውልድ የሚወድሽ ብፅዕት እመቤቴ።
በእጆችሽ የታቀፍሽ የዓለምን ዳኛ፣
ኪዳነ ምህረት የልቤ መፅናኛ❤


 
             🥀 አለው ትበለን 🤲


"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
🌷መልክአ ቅድስት ኪዳነ ምህረት☦

ቅድስት ኪዳነ ምህረት ሆይ በክፉ ሰዎች እጅ ከመውደቅ ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ካልታሰበ አደጋ ሰውሪን።🤲

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.