📮
የልጅዎን ስብዕና እንዴት ማጥፋት ይችላሉ?ልጆች በልዩ እንክብካቤ ሊያድጉ የሚገባ ዕንቁ ፍሬዎች ናቸው!
እነዚህ ውድ ስጦታዎች በአግባቡ ተኮትኩተው ካላደጉ ገና በጠዋቱ መቀጨታቸው አይቀሬ ነው።
በዛሬው መልዕክታችን የልጆችን ስብዕና የሚያቀጭጩ አስር ነጥቦችን እንመለከታለን!
1- በሁሉም ጉዳዮችቻቸው ውስጥ ጣልቃ በመግባት የሚሠሩትን ሁሉ ይቆጣጠሩ።
2- ከሌሎች ልጆች በተለይም ከወንድምና እህቶቹ ጋር ያነፃጽሯቸው።
3- ያለፈውን ስህተታቸውን ሁል ጊዜ በመደጋገም እያስታወሱ ይውቀሷቸው።
4- “በራስህ እፈር” እና የመሳሰሉትን የማነወሪያ ቃላቶችን በመጠቀም የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማቸው በማድረግ ያሸማቋቸው ።
5- (እንዳንተ አይነት ደደብ አይቼ አላውቅም) እያሉ ህፃኑ ራሱን እንዲጠላና የበታችነት ስሜት አብሮት እንዲያድግ ያድርጉ
6- በቤት ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች ሁሉ መንስኤው እነርሱ እንደሆነ እንዲሰማቸው ያድርጉ
7- በድርጊታቸው ሁሉ ራሳቸውን ችለው እንዳይሠሩ በመከልከል ደካማና ሁል ጊዜ በእናንተ ላይ ጥገኛ እንዲሆን ያድርጉት።
8- ስለ ወደፊታቸው ጨለማ የሆነ ምልከታ እንዲኖራቸው፤ ህይወታቸው በፍርሃትና በጭንቀት የተሞላ እንዲሆን አሉታዊ ነገሮችን ብቻ ደጋግመው ያስተምሯቸው።
9- በመምታት እና በመጮህ ይቅጧቸው።
10- ዘወትር ወቀሳ ያዝንቡባቸው፤ ተግሳጽም በሌሎች ፊት ይስጧቸው።
#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች #ምክር_ለተርቢያ
📮
የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው!
መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!💫
https://t.me/HidayaTerbiya 💫