AYA Media || አያ ሚዲያ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


AYA Media || አያ ሚዲያ
ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት በ @Haicrosoft ይላኩልን! እናመሰግናለን!
★ ኢስላማዊ መልዕክቶች
★ ማህበራዊ ጉዳዮች
★ ጠቃሚ መረጃዎች
የሚቀርቡበት ቻናል!
#አያ_ሚዲያ
https://m.youtube.com/user/haiderrkedirtv

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


🌙 🌙 ፆም የተደነገገበት የቁርአን ምዕራፍ የትኛው ነው〽️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

ከትክክለኛው መልስ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና ⬇⬇

⚡️መልሱን በመንካት ውሰዱ 🎁😬🎁🎁


〽️〽️ ሱረቱል ማኢዳ〽️ سورة المائدة 〽️

🌼〽️ ሱረቱል ዒምራን 〽️سورة آل عمران 〽️

⚡️〽️ ሱረቱል በቀራ〽️ سورة البقرة 〽️

🌟〽️ ሱረቱል ኒሳእ 〽️سورة النساء 〽️




ነጋዴ ወደ ማምሻ ላይ ሱቁን ይዘጋል፣ ስለ ዕለት ውሎውም ሒሳብ ይሠራል፤ መክሰር ማትረፉን ይገመግማል፣ ዕዳና ብድሩን ያወራርዳል …
እስኪ ሁላችንም ውሏችንን እናወራርድ ፣ ዛሬ ለአኺራችን ምን ሠርተን ዋልን?

ــــــ ❁ ❁❁ ❁ ــــــ

👥 Join ↘ Me

🔁 ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!

📧Telegram: https://t.me/hidayaTerbiya

🎞 YouTube: https://m.youtube.com/user/haiderrkedirtv


Hidaya Info dan repost
ልጆችን በማሳደግ ረገድ ጠቃሚ ምክሮች

1. ለልጆቻችሁ የሚፈልጉት ነገር ስታሟሉላቸው እግረ መንገዳችሁን አመስጋኝ እንዲሆኑ አስተምሯቸው።

2. ፍፁም እንዲሆኑ አትጠብቁ፤ ሁሉም የአደም ልጅ ተሳሳች ነውና ስህተት ሲሠሩ ከስህተታቸው እንዲማር ፍቀዱላቸው።

3. ፍላጎታቸውን መቆጣጠር እንዲማሩ አንዳንድ ጊዜ የጠየቁትን ነገር "አይሆንም" በሏቸው

4. በገፍ ሲቀርላቸው ተራ ነገር እንዳይሆንባቸውና እጃቸው ላይ ያለውን ነገር ዋጋ በአግባቡ ይረዱ ዘንድ የጠየቁትን መጠን ብቻ ያሟሉላቸው

5. የሕይወት ጉዟችሁን ተርኩላቸው፤ ያሳለፋችሁትን ውጣ ውረድ ንገሯቸው እንዲሁም ልምዳችሁን ለእነርሱ በሚመጥን መልኩ አካፍሏቸው

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው!
መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!


💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫


ታላቁ ዓሊም ኢማም ኢብኑ ሐጀር አልዐስቀላኒይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦

«ማንኛውም ሰው... መልካምን ነገር ጥቂትም ቢሆን ከመፈፀም፤ መጥፎን ነገርም ጥቂትም ቢሆን ከመራቅ ችላ ሊል አይገባውም።

ምክኒያቱም

አላህ በየትኛው መልካም ሥራው
ምህረትን እንደሚለግሰው፤ በየትኛው ወንጀልም እንደሚቆጣበት አያውቅምና!»


(አልፈትሕ 11/321)

❁ ❁❁ ❁

👥 Join ↘ Me

🔁 ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!

📧Telegram   🎞 YouTube


Hidaya Info dan repost
የዱዓእ ኃይል!

ልጆቹን ኣደብ ማስያዝ የተቸገረ ... በዱዓእ ይበርታ!

ልጆችን በተርቢያ ኮትኩቶ ማሳደግ ሰበብ እንጂ ብቻውን ውጤት የሚያመጣ እንዳልሆነ ሁሌም መዘንጋት የለበትም! ሁሉም ነገር ውጤቱ የሚያምረው የአላህ ተውፊቅ ሲጨመርበት ብቻ ነው!

ለዚህም ተከታዩ አስደናቂ ታሪክ ጥሩ ማሳያ ይሆነናል

ልጃቸውን በመልካም ስነምግባር ለመሳደግ ያደረጉት ጥረት ፍሬ አላፈራ ብሏቸው የተቸገሩት ታላቁ ዐሊም ፉደይል ኢብኑ ዒያድ (አላህ ይዘንላቸው) ያደረጉት ዱዓእ እና ያስገኘ አስገራሚ ውጤት በቀደምት ድርሳናት ላይ ሰፍሮ እናገኛለን!

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ ዐሊይ የተባለ ትንሽ አስቸጋሪና ግድ የለሽ ቢጤ የሆነ ልጅ ነበራቸው፤ ታዲያ ይህን ልጃቸው አላህ ያስተካክልላቸው ዘንድ ተከታዩን ዱዓእ ያደርጉ ነበር፦

﴿اللهم إني اجتهدت أن أُؤدب علياً فلم أقدر علىٰ تأديبه ، فأدّبه لي﴾

“አላህ ሆይ! ዐሊይን ኣደብ ለማስያዝ ብዙ ታገልኩ፣ ነገር ግን ኣደብ ላስይዘው አልቻልኩም፤ (አንተ) ኣደብ አስይዝልኝ።"

ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ አላህ፤ አባት ለልጁ ያደረገውን ዱዓእ ሰምቶ ልጃቸውን ወደ ቀጥተኛው ጎዳና መራው፤ ከምርጥ ባሮቹም መካከል አንዱ አደረገው።

ኢማሙ አዝ-ዘሀቢይ አላህ ይዘንላቸውና ዐሊይ የደረሱበትን የልቅና ማማ አስመልክተው ሲገልፁ እንዲህ ይላሉ፡-

"ዐሊይ ቢን አል-ፉደይል ከታላላቅ የአላህ ወዳጆች አንዱ ነበሩ፤ ለአላህ ታዛዥና አላህን የሚፈሩ፤ ልቅና የነበራቸው፤ ረባኒይ (ዕውቀትን ከአምልኮ ጋር ያጣመሩ) ታላቅ ክብር (ደረጃ) ያላቸው ነበሩ።"


📚 ሲየር አዕላም አን-ኑበላእ (7/408)

**

ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ቻናሉን ያስተዋውቁ!

ምርጥ አባት I #ለአባቶች I

🪴 https://t.me/HidayaTerbiya 🪴


Hidaya Info dan repost
📮 በልጆች መካከል ፍትሀዊ መሆን

በልጆች መካከል ፍትህን ማስፈን እንዲሁም በመካከላቸው ከማዳላትና በደል ፈፃሚ ከመሆን መታቀብ ልጆችን በመልካም ለማሳድግ አንገብጋቢና ወሳኝ ከሚባሉ ምሰሶዎች መካከል አንዱ ነው።

አንድ ወላጅ በልጆቹ መካከል ፍትሀዊ የማይሆን ከሆነ በልጆች መካከል እርስ በእርስ መጠላላት ፣ ምቀኝነትና ጥላቻ እንዲፈጠር ያደርጋል።

በተቃራኒው ደግሞ በመካከላቸው ፍትሀዊ ለመሆን ጥረት ባደረጉ ቁጥር በልጆች መካከል መዋደድና መፋቀር እንዲኖር እንዲሁም ለወላጆቻቸው መልካም እንዲሆኑ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል።

ይህን ወሳኝ መርህ አስመልክተው  የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ 

«فَاتَّقُوا اللَّهَ وَاعْدِلُوا بَيْنَ أَوْلاَدِكُمْ»

"አላህን ፍሩ! በልጆቻችሁ መካከል ፍትሀዊ ሁኑ"

(አል’ቡኻሪይ ሰሒሓቸው ላይ በቁጥር 2587 ዘግበውታል።)


📚 "መልካም የልጆች አስተዳደግ" በሚል ርዕስ በሂዳያ ተርቢያ ከተዘጋጀ ያልታተመ መጽሐፍ የተወሰደ!

ምርጥ ወላጅ I #ለወላጆች I
ምርጥ እናት  I #ለእናቶች I
ምርጥ አባት  I #ለአባቶች I

🪴 https://t.me/HidayaTerbiya 🪴


Hidaya Info dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
💡 ጁሙዓን በሰላዋት አድምቋት💡

﴿ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ﴾.


• اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ.

• اللَّهُمَّ بَارِك عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكتَ عَلَى إِبرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ.

• اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّم وبَارِك عَلَى نبيِّنا مُحَمَّدٍ.

ምርጥ ልጅ I #ቁርኣን #ጁሙዓ I

I #ሂዳያ #Hidaya #ተርቢያ #Terbiya I

🪴 https://t.me/HidayaTerbiya 🪴


Hidaya Info dan repost
መርከቧ ከመስጠሟ በፊት … በጋራ እናድናት!

እባክዎ ሼር ያድርጉ!

መልዕክቶቻችን የበለጠ ተደራሽ እንዲሆን ቻናልና ግሩፕ ያላችሁ በማስተዋወቅ ተባበሩን!

የትውልድ ኃላፊነት የሁላችንም ነው!
ሁላችንም በጠበቅነው እንጠየቃለን!
ከጠያቂነት የመዳኛውን ዘለበት እንጨብጥ!
መዳኛው እምነት መልካም መሥራትእውነት እና በትዕግስት ላይ አደራ መባባል ነው!

ይህን ሊንክ በመጠቀም ቤተሰብዎ እና ወዳጆችዎ ወደዚህ ቻናል እንዲቀላቀሉ ይጋብዟቸው።

መጪውን ትውልድ በጋራ እንገንባ!

#ሂዳያ_ተርቢያ
የመልካም ትውልድ ማፍሪያ!


🪴https://t.me/HidayaTerbiya 🪴


Hidaya Info dan repost
ተግባራዊ ትምህርት…

ውድ አባት ሆይ! ለልጅህ ምርጥ አባትና መልካም አርዓያ መሆን ከፈለግክ፤ ለልጅህ ይህን አድርግ ይህንን አታድርግ የሚሉ ትዕዛዛትን ብቻ ከማስተላለፍ ይልቅ በተግባራዊ ምሳሌ ለማስረዳት ሞክር።

ለምሳሌ የመተባበርን ጥቅም ልታስተምረው ከፈለግክ በቤት ውስጥ አንዳንድ ስራዎችን አንተ መሥራት ጀምርና ልጅህ እንዲረዳህ ጠይቀው። ባለቤትህ እገዛህን ፈልጋ ትብብር ስትጠይቅህ ቀና ምላሽ በመስጠት እድሜ ልኩን የማይረሳውን ትምህርት ስጠው።

ምርጥ አባት I #ለአባቶች I

I #ሂዳያ  #Hidaya  #ተርቢያ #Terbiya I

🪴 https://t.me/HidayaTerbiya 🪴


📒 ለሸሪዓዊ ዕውቀት ቦታ እንስጥ!

ነብዩም ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ እንዲህ ብለዋል፦

📒«من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين»
[رواه البخاري و مسلم ]

«አላህ መልካምን የሻለት ሰው ዲንን እንዲገነዘብ ያደርገዋል››

📃[ቡኻሪና ሙስሊም]


ነብዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ መልካምን ነገር ሁሉ ዲንን ከመገንዘብ ጋር አያይዘውታል፡፡

ይህ የሚጠቁመው ወሳኝነቱንና ከፍተኛ ደረጀ ያለው መሆኑን ነው፡፡

በሌላም ሀዲስ ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦


" ﺧﻴﺎﺭﻛﻢ ﻓﻲ ﺍﻟﺠﺎﻫﻠﻴﺔ ﺧﻴﺎﺭﻛﻢ ﻓﻲ ﺍﻹﺳﻼﻡ ﺇﺫﺍ ﻓﻘﻬﻮﺍ "

«በጃሂሊያ ዘመን ምርጥ የነበሩት ኢስላም ውሰጥም ግንዛቤያቸው ካደገና ከተማሩ።ምርጦች ናቸው፡፡»

   ዲንን መገንዘብ ኢስላም ውሰጥ ከፍተኛ ቦታ ያለውና ምንዳውም የላቀ ነው፡፡

ምክንያቱም፦

አንድ ሙስሊም ዲኑን የሚገነዘብ ከሆነና የሚኖረውንና የሚኖርበትን መብትና ግዴታ ካወቀ ጌታውን በእውቀት በማምለክ ለዱንያና ለአኺራ እድለኝንትን ይጐናፀፋል፡፡

🔐አላህ ጠቃሚ ዕውቀትንና መልካም ተግባርን ይወፍቀን !

📮 https://t.me/SebahTube


Hidaya Info dan repost
ህፃናት ብዙ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይወዳሉ…

አንዳንድ ወላጆች ደግሞ ይህን አይወዱትም! ምክንያታቸው ምንድን ነው? ስንል የሚያስቸግሯቸውና ረፈት የሚነሷቸው ስለሚመስላቸው ነው!

ግን እላችኋለሁ! በእናንተ ምልከታ አላስፈላጊና እርባን የሌለው  መስሎ ቢታያችሁም ለእነርሱ ግን በጣም ጠቃሚ እና አስፈላጊ በመሆኑ ልጆችን ጥያቄ ከመጠየቅ ከመከልከል ተቆጠቡ።

ይህ የመጠየቅ ባህላቸው የአዕምሯቸውን ግንዛቤ፣ ፈጠራን እና የማሰብ ችሎታቸውን ለማዳበር የሚረዳ ነው። 

ብዙ ጥያቄዎች በኖራቸው ቁጥር ልጆቻችን ወደፊት የበለጠ አዳዲስ ፈጠራዎችን የማስገኘት እድላቸው እየሰፋ ይሄዳል።

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ
#ስኬታማ_ማክረምት

📮 የመጪው ትውልድ ኃላፊነት የጋራችን ነው!
መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫


Hidaya Info dan repost
ትችት ለእድገት ወይስ ለክስረት?

በልጆች ላይ ከልክ ያለፈ ትችት ማብዛት በስነ-ልቦናቸው እና በማህበራዊ እድገታቸው ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ ይሳድራል።

ከእነዚህ ተፅዕኖዎች መካከል፡

1. ዝቅተኛ በራስ የመተማመን ስሜት ይፈጥራል፡

ዘውታሪና የማያቋርጥ ትችት የልጆችን በራስ የመተማመን ስሜት እና ችሎታን ይቀንሳል፤ ይህም ልጆች ብቃት እንደሌላቸው እንዲሰማቸው ያደርጋል።

2. ውድቀትን መፍራት፡

ትችት በበዛባቸው ቁጥር ውድቀትን በመፍራት አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከርና ኃላፊነት ለመውሰድ ፍርሃት ያድርባቸዋል።

3. ከቤተሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያበላሻል፡

የማያቋርጥ ትችት በልጆች እና በወላጆች መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ክፍተት ሊፈጥር ይችላል፤ ይህም ልጆች በወላጆቻቸው ላይ ያላቸውን የመተማመንን ስሜት እንዲያጡ እና ደጋፊ እንደሌላቸው እንዲሰማቸው በማድረግ ነው።

4. በትምህርታቸው ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል፡

ለቋሚ ትችት የተጋለጡ ልጆች በሚፈጠርባቸው ጭንቀት እና ጫና ምክንያት የትምህርት ውጤት ማሽቆልቆል ሊያሳዩ ይችላሉ።

5. ለጭንቀት እና ድብርት ያጋልጣል፡

የማያቋርጥ ትችት ከፍተኛ ጭንቀት ሊፈጥርባቸው አልፎ ተርፎም በልጆች ላይ የመንፈስ ጭንቀት ሊያስከትል ይችላል።

እነዚህን አሉታዊ ተፅእኖዎች ለማስወገድ ትችታችን ገንቢ እና ባህሪያቸውን ለማሻሻል እንጂ ስብዕናቸው ላይ ያነጣጠረ አለመሆኑ ማስተዋል ተገቢ ነው።

በተጨማሪም ትችታችን በአዎንታዊ መመሪያ እና ቀጣይነት ካለው ድጋፍ ጋር ማቆራኘት ተገቢ ነው።

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ
#ስኬታማ_ማክረምት

📮 የመጪው ትውልድ ኃላፊነት የጋራችን ነው!
መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫


Hidaya Info dan repost
ክረምቱን በስኬት ለማጠናቀቅ ጠቃሚ ስንቅ!

ወዳጅ ዘመድዎን የሂዳያ ቤተሰብ እንዲሆኑ ይጋብዙ!

የልጆችዎን የክረምት ዕረፍት ስኬታማ በሆነ መልኩ ለማጠናቀቅ የሚረዱ አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮች እነሆ፡

1⃣ የጊዜ አጠቃቀም፡-

የመጫወቻ፣ የመማሪያ እና የዕረፍት ጊዜን የሚያካትት ዕለታዊ ወይም ሳምንታዊ ፕሮግራም ያዘጋጁላቸው

2⃣ የንባብ ባህላቸውን ማዳበር፡-

ለልጆች ከዕድሜያቸው ጋር የሚስማሙ አስተማሪና አስደሳች መጽሐፍትን በማቅረብ እንዲያነቡ ያበረታቱ

3⃣ ከቤት ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፡-

ልጆች ከቤት ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለምሳሌ ብስክሌት መንዳት ወይም በውብ ተፈጥሯዊ ስፍራዎች መራመድ እንዲለማመዱ ማበረታታት

4⃣ እየተጫወቱ መማር፡

የልጆችን ችሎታ፣ ክህሎት እና ዕውቀት ለማሳደግ የሚረዱ ትምህርታዊ ጨዋታዎችን እና በእጅ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን ማዘጋጀት

5⃣ የበጎ ፈቃደኝነት ስራ፡

ልጆችን የትብብር እና የኃላፊነት መንፈስን ለማሳደግ በበጎ ፈቃድ ተግባራት እንዲሳተፉ ማበረታታት

6⃣ ማህበራዊ ግንኙነት፡

ልጆች ከጓደኞቻቸው እና ከቤተሰብ አባላቶች ጋር በደንብ እንዲግባቡ እና እንዲጫወቱ የዚያራ ፕሮግራሞች ማመቻቸች


#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ
#ስኬታማ_ክረምት

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው!
መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫


Hidaya Info dan repost
ልጆችን በማሳደግ ረገድ ጠቃሚ ምክሮች

1. ለልጆቻችሁ የሚፈልጉት ነገር ስታሟሉላቸው እግረ መንገዳችሁን አመስጋኝ እንዲሆኑ አስተምሯቸው።

2. ፍፁም እንዲሆኑ አትጠብቁ፤ ሁሉም የአደም ልጅ ተሳሳች ነውና ስህተት ሲሠሩ ከስህተታቸው እንዲማር ፍቀዱላቸው።

3. ፍላጎታቸውን መቆጣጠር እንዲማሩ አንዳንድ ጊዜ የጠየቁትን ነገር "አይሆንም" በሏቸው

4. በገፍ ሲቀርላቸው ተራ ነገር እንዳይሆንባቸውና እጃቸው ላይ ያለውን ነገር ዋጋ በአግባቡ ይረዱ ዘንድ የጠየቁትን መጠን ብቻ ያሟሉላቸው

5. የሕይወት ጉዟችሁን ተርኩላቸው፤ ያሳለፋችሁትን ውጣ ውረድ ንገሯቸው እንዲሁም ልምዳችሁን ለእነርሱ በሚመጥን መልኩ አካፍሏቸው

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው!
መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!


💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫


Hidaya Info dan repost
📮 የልጅዎን ስብዕና እንዴት ማጥፋት ይችላሉ?

ልጆች በልዩ እንክብካቤ ሊያድጉ የሚገባ ዕንቁ ፍሬዎች ናቸው!

እነዚህ ውድ ስጦታዎች በአግባቡ ተኮትኩተው ካላደጉ ገና በጠዋቱ መቀጨታቸው አይቀሬ ነው።

በዛሬው መልዕክታችን የልጆችን ስብዕና የሚያቀጭጩ አስር ነጥቦችን እንመለከታለን!

1- በሁሉም ጉዳዮችቻቸው ውስጥ ጣልቃ በመግባት የሚሠሩትን ሁሉ ይቆጣጠሩ።

2- ከሌሎች ልጆች በተለይም ከወንድምና እህቶቹ ጋር ያነፃጽሯቸው።

3- ያለፈውን ስህተታቸውን ሁል ጊዜ በመደጋገም እያስታወሱ ይውቀሷቸው።

4- “በራስህ እፈር” እና የመሳሰሉትን የማነወሪያ ቃላቶችን በመጠቀም የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማቸው በማድረግ ያሸማቋቸው ።

5- (እንዳንተ አይነት ደደብ አይቼ አላውቅም) እያሉ ህፃኑ ራሱን እንዲጠላና የበታችነት ስሜት አብሮት እንዲያድግ ያድርጉ

6- በቤት ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች ሁሉ መንስኤው እነርሱ እንደሆነ እንዲሰማቸው ያድርጉ

7- በድርጊታቸው ሁሉ ራሳቸውን ችለው እንዳይሠሩ በመከልከል ደካማና ሁል ጊዜ በእናንተ ላይ ጥገኛ እንዲሆን ያድርጉት።

8- ስለ ወደፊታቸው ጨለማ የሆነ ምልከታ እንዲኖራቸው፤ ህይወታቸው በፍርሃትና በጭንቀት የተሞላ እንዲሆን አሉታዊ ነገሮችን ብቻ ደጋግመው ያስተምሯቸው።

9- በመምታት እና በመጮህ ይቅጧቸው።

10- ዘወትር ወቀሳ ያዝንቡባቸው፤ ተግሳጽም በሌሎች ፊት ይስጧቸው።

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው!
መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!


💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫


Hidaya Info dan repost
🪷 ልጆችዎን በማሳደግ ረገድ ስኬትዎን የሚወስኑ አምስት ነገሮች፡-

1. ከመስተጋብር አንፃር፡

ልጆች እንዲወዱህ፣ ወዳንተ ሲቀርቡ ምቾት እንዲሰማቸው፣ ሳትኖር ስትቀር እንዲናፍቁህ፣ ምስጢራቸውን እንዲያጫውቱህ፣ ወደ ቤትህ ስትመለስ ደስተኛ እንዲሆኑ አድርግ። በቤት ውስጥ መረጋጋትና ስምምነት እንዲሰፍን ያደርጋል።

2. ከሥነ ምግባር አንፃር:

ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ሥነ ምግባራቸው ለማስተካከል ተገቢውን ጥረት ማድረግ። ይህ ሲባል ልጆች ስህተት እንዳይሠሩና ፍፁም እንዲሆኑ ማድረግ ማለት አይደለም፤ ይልቁን ክፍተቱ ያነሰ እንዲሆን መጣር ነው።

ከውብ ሥነ ምግባራቸው መካከል፡- ጀግንነት፣ ሐፍረት፣ ጥብቅነት፣ ታማኝነት፣ እውነተኝነት፣ ጨዋነት፣ መተናነስ እና ትሕትና ይገኙበታል።

3. ከአምልኮ አንፃር፡

ጠንካራ ኢማን በውስጣቸው ማስረጽ፤ እምነታቸውን ከሽርክ ማጽዳት፣ ዒባዳቸውን በዕውቀት ላይ የተመረከዞ ማድረግ፤ በተለይ በሰላታቸው ላይ ቀጥ እንዲሉ ማበርታት እና የአላህን ቃል ቁርኣን ማስተማር።

4. ወንድማማችነት / እህትማማችነት መፍጠር፡-

በልጆች መካከላል የመከባበር፣ የመተሳሰብ እና የመተዛዘን መንፈስ እንዲኖር ማድረግ።

5. ከትምህርት (ዕውቀት) አንፃር፡-

ልጆች እንደፍላጎታቸው እንደ አቅምና ተሰጥዖዋቸው የሚፈልጉትን እንዲያሳኩ ማገዝ እንጂ የናንተን ሕልም እንዲያሳኩ አለመጫን፤ ስኬትን በዶክተርነት እና ፓይለትነት ብቻ የተገደበ አይደለም።

አላህ ሆይ ልጆቻችንን አስተካክልንን፤ እኛ ማስተካከል አንችልምና።

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው!
መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫


Hidaya Info dan repost
🪴ጥረት እና ውጤት

ለልጆቻችን የምንሰጠው ትኩረት እና እንክብካቤ እንዲሁም ከእነሱ ጋር ያለንን ግንኙነት በጨመረና በጠነከረ ቁጥር የተሻለ ውጤት የማግኘት እድላችን እየሰፋ ይሄዳል።

በተቃራኒው

ትኩረታችን ከልጆቻችን የምንፈልገውን ውጤት ማየት ላይ ብቻ በሆነ ቁጥር ከእነሱ ጋር ያለን ግንኙነት እየቀነሰ ውጤቱም እያሽቆለቆለ ይመጣል።

#የሂዳያ_ትውልድ #የሂዳያ_ትውልድ  #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው!
መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫


Hidaya Info dan repost
ውድ ወላጅ!

ከልጆችዎ ጋር መነጋገር እና ስሜታቸውን እና ሀሳባቸውን አዘውትሮ ማዳመጥ ጠንካራ የቤተሰብ ግንኙነቶችን ለማዳበር ይረዳል።

#የሂዳያ_ትውልድ
#የሂዳያ_መልዕክት

📮 ውድ ቤተሰቦቻችን ብዙዎች ከትምህርቶቹ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ቻናላችንን በማስተዋወቅ ከጎናችን ይሁኑ!

🪷 https://t.me/HidayaTerbiya 🪷


Hidaya Info dan repost
ከትዳር አጋር ጋር የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን እንዴት ማርገብ ይቻላል?

🪶 አለመግባባት በሚፈጠር ጊዜ ቁጣን በተቻለ መጠን ለማፈን መሞከር።

🪶 አለመግባባቱን የሚያባብስ፤ የበለጠ የሚያወሳስብ እና ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚወስድ ቃል ከመናገር መቆጠብ።

🪶 የትዳር አጋርዎን መልካም ሥራ አለመዘንጋት! መልካም ባህሪያቸውንም ማስታወስ! ይህ አንዳችሁ በሌላኛችሁ ላይ ያላችሁን አሉታዊ ስሜት በእጅጉ እንዲቀንስ ያደርጋል!

🪶 ቁጣችሁ ዓይኖቻችሁን ከትዳር አጋራችሁ መልካም ምግባር እንዲያውራችሁ እንዲሁም ፀጋን እንድትክዱና እንድታስተባብሉ እንዲያደርጋችሁ አትፍቀዱ።

🪷 ሁለታችሁም ኢሕቲሳብ አድርጉ! መስተጋብራችሁን ከአላህ መልካም ምንዳን በመፈለግ ላይ የተመሰረተ አድርጉ!

📌 ባል ሆይ! "ከእናንተ መካከል ምርጡ (መልካሙ) ለሚስቱ ምርጥ የሆነ ነው።" የሚለውን ነብያዊ አስተምህሮ በእያንዳንዱ የትዳር ሕይወትህ ቅጽበት አስታውስ!

📌 ሚስት ሆይ! አንዲት ሴት ለባልዋ ያላት መልካም ባህሪ እና ለባሏ ያላት ታዛዥነት የጀነት መግቢያ በሯ መሆኑን በእያንዳንዱ እስትንፋስሽ አስታውሽ!

📝 በተቻለ ፍጥነት የተፈጠረውን ማዕበል በማርገብ ግንኙነታችሁን ወደ መደበኛው ጣፋጭ ሁኔታ ለመመለስ የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ።

⭕ አለመግባባቱ በቆየ ቁጥር በመካከላችሁ ያለው ርቀት እንዲጨምር! ልቦችም እየደነደኑ እና ነፍሶች መራራቅን እየለመዱ እንዲሄዱ ያደርጋል!

📍ይህም የመፍትሄውን ጊዜ እየራቀ እንዲሄድ የትዳር ሕይወት አሰልቺ እንዲሆን ያደርጋል!

⛔️ በዚህም የጋብቻን መረጋጋት እና ቀጣይነት አደጋ ላይ የሚጥል የመጀመሪያው ምክንያትም ይሆናል!


❗️ቻናሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ሰላማዊ ቤተሰብ በጋራ እንገንባ!!!

ምርጥ ትዳር I #ለጥንዶች I

🪴 https://t.me/HidayaTerbiya 🪴

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.