🤓 ሰው ሲኖር-Sew Sinor‍


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


💟 እንኳን በደህና መጡ። 🙏 ቸር አይለፋችሁ ክፉ አያግኛችሁ
😊😍 ገፁን ከተቀላቀሉበት ሰከንድ አንስቶ እጅጉን ጠቃሚ ነገሮችን ያገኙበታል።
በተጨማሪ📚 በpdf ማግኘት የሚፈልጉት ማንኛውም መፅሐፍ ካለ 👉 @Sewsinor1_bot ይጠቀሙ።
ማስታወቂያ ለማሰራት፣ማንኛውም ጥያቄ ፣ ሀሳብ ፣ አስተያየት ለመስጠት👇 Inbox 👇
👉 @Sewsinorbot
👉 @CheramlakT

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


✝️እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው #ማኅቶት_ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥታል ለመቀላቀል ከስር Join የሚለውን ንኩት።

https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk
https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk


🙋‍♂አንድጥያቄ

✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ⁉️✟

         


" ዓለማት ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ሁነ ተብለው በቃሉ እንደተፈጠሩ፣ በቃሉም ጸንተው እንደሚኖሩ ኋላም በቃሉ እንደሚያልፉ ሁሉ የስው ሕይወትም በዚህ ቃል ይወሰናል፤ እንጀራ ኖረም አልኖረ ቃሉ በቃ ካለ ያበቃል፣ ኑር ካለ ደግሞ እንጀራ ባይኖርም ይኖራል፤ ስለዚህ በሕይወታችን ወሳኝ ሥልጣን ያለው የእግዚአብሔር ቃል እንጂ፣ እንጀራ ብቻ አለመሆኑን ጌታችን በዚህ አስተምሮናል። "

ከቅዱስ ፓትርያርኩ የጾመ ኢየሱስ መልዕክት የተወሰደ።


#የሕሊና_ዓይነቶች 

በቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም በአዲስ ኪዳን ይባስ ብሎም ደግሞ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት "#ሕሊና" የሚለው አሳብ ተደጋግሞ ይነሳል። ለምሳሌ ሐዋርያው እንዲህ ይላል፦

“ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።”
           ሐዋርያት 24፥16

ከታች ከተዘረዘሩት ለአንድ ክርስቲያን የሚያስፈልገውና የግሉ ሊያደርገው ሊጋደልበት የሚገባው የቱ ነው? ለምን?

1. ክፉ ሕሊና

ክፉ ሕሊና ተበላሽቶ ወደ ሥነ ምግባር ዝቅጠት የሚመራ ነው። ይህ ሕሊና የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚጻረር እና የኃጢያት ባህሪን የሚያበረታታ ነው። (ዕብ. 10፥22)

2. የረከሰ ሕሊና

የረከሰ ሕሊና በኃጢአት የረከሰና ግልጽ የሆነ የሞራል ልዩነት ማድረግ የማይችል ነው። ትክክል እና
ስህተት መካከል ወደ ግራ መጋባት ይመራል። (ቲቶ. 1፥15) 

3. የደነዘዘ ሕሊና

የደነዘዘ ሕሊና ማለት በድግግሞሽ ኃጢአት የተዳከመ ወይም የደነደነ ነው። ከጊዜ በኋላ
ሰውየው ለጥፋተኝነት ወይም ለጥፋተኝነት ግድየለሽ ይሆናል። ኃጢአትን እንደ ስህተት አይገነዘብም። (1ኛ ጢሞ. 
4፥2) 

4. ደካማ ሕሊና

ደካማ ሕሊና የሚያመለክተው ኃጢአት በሌለበት አካባቢም እንኳ በቀላሉ ሊኮነን የሚችል ያልበሰለ
ወይም ከልክ ያለፈ ስስ ሕሊና ነው። ይህ ሊሆን የሚችለው አንድ ሰው በተፈጥሮ ኃጢአተኛ ያልሆኑ የሥነ ምግባር ጉዳዮች ላይ እርግጠኛ ካልሆነ ነው። (1ኛ ቆሮ. 8፥7)

5. ንጹሕ ሕሊና

ንፁህ ህሊና ማለት ከጥፋተኝነት እና ከነቀፋ በጸዳ መልኩ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መኖር ፣ በታማኝነት እና በመታዘዝ መመላለስ ማለት ነው። (ሐዋ. 24፥16)

6. በጎ ሕሊና

በጎ ሕሊና ከእግዚአብሔር እውነት ጋር የሚስማማ እና ወደ ጽድቅ ሕይወት የሚመራ ነው። ግለሰቡ
ይቅርታን እንዲጠይቅ እና የሞራል ህይወት እንዲጠብቅ የሚገፋፋው ለኃጢያት እና የጥፋተኝነትን ድንበር በማወቅ ለእነዚህ ነገሮች ንቁ የሆነ ነው። (1 ጢሞ. 1፥19)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Sewsinor


┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹 ••✿•• 🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
     ሁሉም ሰው የራሱ ታሪክ አለው

ብዙ ጊዜ በሰዎች ላይ ለመፍረድ እና ሰዎችን ለመተቸት እንቸኩላለን ምን እንደገጠማቸው ምን አልፈው እንደመጡ ግን ለማየት አንሞክርም ነገር ግን ብዙ ሰዎች በርካታ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የገጠማቸው በውስጣቸው ያለውን ጦርነት ለማስቆም እየታገሉ ያሉ፣ በሆነ ነገር ውስጣቸው የተጎዳ ሰዎች ናቸው፡፡

እነዚህ ሰዎች ምናልባት ካላቸው የህይወት ልምድ በመነሳት ከመልካም ስነ-ምግባር ወይም ከደግነት እርቀው ሊሆን ይችላል ምክንያቱም በእነርሱ አስተሳሰብ አሁንም ድጋሚ እንዳይጎዱ በመፍራት በዙሪያቸው ከሚገኝ ማንኛውም ታሳቢ አደጋ እራሳቸውን በመከላከል ላይ ናቸው፡፡

እኛም እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ሲገጥሙን ወይም ስንመለከት ለፍርድ፣ ለትችት እና ለወቀሳ ከምንቸኩል ነገሮችን በተለያየ አቅጣጫ ተመልክተን በፍቅር፣ በመልካምነት እና በደግነት ቀርበን ውስጣቸው የተፈጠረውን ፍርሃት እና የተዛባ አመለካከት ማስወገድ እንችላል፡፡

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ።
@Sewsinor
@Sewsinor


DO NOT LOSE A GOOD MAN BECAUSE HE IS BROKE:

Wise words!

Don't lose a good man because of temporary financial struggles. Here's why:

Good Character is Rare

1. Kindness, empathy, and compassion are valuable traits.
2. Integrity, honesty, and loyalty are essential.
3. A good heart and positive attitude are priceless.

Financial Struggles are Temporary

1. Financial situation can change quickly.
2. Hard work and determination can lead to success.
3. Support and encouragement can help overcome challenges.

Wealth isn't Everything

1. Money can't buy happiness or love.
2. Material possession don't guarantee fulfillment.
3. Relationship built on trust, respect, and communication last.

Good Men are hard to Find

1. Loyalty, commitment, and dedication are rare.
2. Emotional intelligence and maturity are variable.
3. A partner who values you beyond material possessions is precious.

Focus on shared Values

1. Emotional connection and intimacy.
2. Similar goals, interests, and passions
3. Mutual respect, trust, and communication.

Support his Goals and Aspirations

1. Encourage his passion and interests.
2. Help him overcome obstacles and challenges.
3. Celebrate his successes and progress.

Build a Strong Foundation

1. Develop emotional intimacy and connection.
2. Establish open and honest communication.
3. Foster trust, respect, and loyalty.

Remember

1.Love is not measured by bank accounts.
2. True wealth lies in relationships and experiences.
3. A good partner is worth more than gold.

Don't let temporary financial struggles cloud your judgement. Focus on the qualities that truly matter in a partner.

Please foll0w my page 👉 @Sewsinor read more


✍️ .................ትዝብት ..........✍️.።

።...ዓለም እንደዚህ ናት...።

ጎል ባስቆጠርክ ጊዜ ቁማ ታጨበጭብልሃለች።ሪከርድ በሰበርክ ጊዜ በስምህ ቲሸርት ታሳትምልሃለች።በስምህ ድርጅት ትከፍትልሃለች። ለክርስቶስ ያልገለጠችውን ፍቅሯን ላንተ ትገልጥልሃለች። ነገር ግን ይህንን ያህል የወደደችህ ዓለም! ለጎል የተቃረበ ኳስን ተሳስተህ ብታበላሽ በስምህ ያሳተመችውን ቲሸርት ወዲያው ትቀደዋለች። የድርጅቷን ስምም በሌላ ትለውጣለች። ሰው ነው እና ይሳሳታል ማለቷን ትታ ለምን ተሳሳተ እያለች ታማታሃለች። የተሳሳተ ቢሠራ ነው። ያልተራመደ እንቅፋት አይመታውም።
ምክንያቱም ተኝቷል" በማለት አትረዳልህምም።
በዚህ ውስጥ ዓለም የዘነጋችው ቢኖር ? ለስሂት መኑ ይሌብዋ ያለውን የመዝሙር ጥቅስ ነው።

✍️ በዚህ ሰሞን የታዘብኳቸው ጉዳዮች ብዙዎች ናቸው ።በዋናነት ሶስት መሠራታዊ ነጥቦችን
በአክሊል ዙሪያ በኋላ አነሳለሁ። በሶሻል ምድያው ላይ በርካታ ትምህርቶች እየተሰጡ ነው።ሰውም ከዐውደ ምሕረቱ ይልቅ ሶሻል ምድያው ላይ ሰፍሯል። የምድያው አላማ አማኙን ምድያው ላይ ማስቀረት ሳይሆን ምድያው ላይ የሰፈረውን ምእመን ወደ ዐውደ ምሕረቱ መሳብ ነው። ንቦችን ዛፍ ላይ ፤ አጥር ላይ ልናሰፍራቸው እንችላለን። ኋላ ግን አውራቸውን ይዘን መዓር ወደ ሚሠሩበት ቀፎ እናስገባቸዋለን ።ምክንያቱም አሳ የሚጠመደው ባሕር ላይ ነው። ቆቅም የምታያዘው ዱር ላይ ነው ። የሚከሸኑት ግን ከቤት ውስጥ ነው።

✍️ ምእመናንንም ከሀገር ከሀገሪት ፤ ከሀቃል ከሮቢት፤ ከዱር ከገደሉ ከሶሻል ምድያው የወንጌል መረብን በመጣል ልናጠምዳቸው እንችላለን።የክርስቶስ አካል ብልት የሚሆኑት ግን የጸጋ ግምጃ ቤት በሆነችው በቤተ ክርስቲያኗ ነው።ይህንን ሥራ ደግሞ አሁን በምድያው ውስጥ ያሉ ወጣቶቻችን እየሠሩት ነው ። ይህንን ማበረታታት ግድ ነው ።

✍️ከጥቂት ዓመታት በፊት ምድያው ላይ ሙስሊሞች ንጽጽር ሠራን እያሉ መጽሐፍ ቅዱስን እያጋጩ የእኛ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚጣላ እንደሚጋጭ አስመስለው ያሠራጩ ነበር። እኛ ደግሞ እንደ ከዋክብት የበዙ ሊቃውንት ቢኖሩንም ምድያው ላይ እንደ አሁኑ የሚሞግቱ የሚከራከሩ ወጣቶች ግን ብዙም አልነበሩንም ። ምድያው ላይ ማለቴ ነው ።

...........✍️ ፕሮቴስታንቶችም ".......

ኦርቶዶክስ ? ሥዕል ታመልካለች፥
☝️ታቦት ታመልካለች ፤
☝️ድንግል ማርያምን ታመልካለች፤
☝️ቅዱሳንን ታመልካለች እያሉ አንድ አምላክ ማምላኳን ክደው በሀሰት ሲኮንኗት ፤ ሲጽፉባት ፦በየምድያው ሲያቀረሹባት እንደ ኮከብ ተወርውረው እንደ አድማሱ ጀምበሬ፤ እንደ ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ የመሳሰሉት ውሃ በእሳት ላይ እንደሚነሳሳ ሁሉ እነርሱም በቅናት ተነስተው የመናፍቃንን ምንፍቅና እልም ድርግም የሚያደርጉ ጽሑፎችን ሲጽፉ አይተናል ።ይሁን እንጅ ምድያው ላይ ግን ብዙም አልተራመድንም ነበር ።ታላላቁ ምድያዎች እንኳን እስከ አሁን ሁለት ናቸው ። ይህ ስንፍናችን አሳዛኝ ቢሆንም እንኳን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በርካታ ወጣቶች በምድያው ላይ ተሠራጭተዋል ።

እኔ እንኳን በመጠኑ የማያቸው ወጣቶች ብዙዎቹ ዲ/ን እንኳን አይደሉም።ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሱን እንደ ውሃ ይጠጡታል ። ከላይ የጠቀስኳቸው የሙስሊም ኡስታዞች እና የፕሮቼስታንት ፓስተሮች ሊከራከሩ ቀርበው ላብ በላብ ሲሆኑ መልስ አጥተው ሲያቃትቱ አይቼ ተደንቄያለሁ ።የሳቁባቸው እና የተሳለቁባቸው የገድላትን፥ የቅዱሣት ሥዕላትን፤ የታቦትን ፤የቅዱሳን ምልጃን በተመለከተም ብዙዎች እንዲህ ነው እንዴ ? ብለው ሲመለሱ ታይተዋል።ብዙዎች ደግሞ ደንግጠው ከመንቀፍ አፋቸውን ሲቆጥቡ ተመላክቷል። ሌሎች ደግሞ በዚህ ተበሳጭተው በወጣቶቹ ላይ ፖለቲካ ሠርተዋል። በዋናነት ወጣቶቹን እኔ በግሌ የቤ/ክርስቲያኗ የደስታ ፍሬዎች ናቸው ብየ አምናለሁ ።በጣም ይቅር በሉኝ እና? እኔ በትርጓሜ ጉባኤ ቤት ብዙ ዓመታትን ደክሜያለሁ።ሰባኬ ወንጌል ሁኜም በማገልገል 10 ዓመት ሞላኝ። አሁንም የመጨረሻው ትምህርቴ መጽሐፈ ሊቃውንትን እየጨረስኩ ነው ። ግን ስንት መናፍቃን አሳመንክ ብትሉኝ ከነአኬ ጋራ ሲነጻጸር መልስ የለኝም ። ቀጥታ ሲከራከሩ ሲወያዩ ባይገጥመኝም። የተወያዩትን በፌስቡክም በሌላም ተለቆ ሳያው ግን በእጅጉ ደስተኛ ነው የሆንኩት። ሂደት ላይ ሊሳሳቱ ይችላሉ። በየቀኑ ማስተማርና በየ ቀኑ መከራከር ይለያያሉ። ወጣቶቹ ብዙ ጊዜ ከኢአማንያን ጋራ ከመከራከራቸው የተነሳ ዳኅጸ ልሳንም ዳኅጸ ልቡናም ሊገጥማቸው ይችላል። ዳጥ ደግሞ አንገዳግዶ ይጥላል። ወጣቶቹ እንዳይወድቁባት ቤ/ክርስቲያኗ ልትደግፋቸው ይገባል። ምድያ ደግሞ የዳጥ መንገድ ነው።ብዙ ሰዎች በርሱ እየተራመዱ ወድቀዋል። ምናልባትም ለመውደቅ ሲንገዳገዱ በመደገፍ ፈንታ ከገፋናቸው መውደቅ ብቻ ሳይሆን አወዳደቃቸው የከፋ ይሆናል ። ይህ እንዳይሆን ቤ/ክርስቲያኗ፤ ሊቃውንቱ ከጎናቸው ቁመው በምሥጢር በምክር እና በሀሳብ በሞራልም ጭምር መርዳት አለባቸው ፥

✍️አኬ ስለ ተባለው ወንድማችንም ባለፈው አንድ ነገር ጽፌ ነበር። አሁንም ልጁ ብዙ ጊዜ ከካቶሊኮች ጋራ፤ ከፕሮቴስታንቶች ጋራ፤ ከተሀድሶዎች ጋራ ሁልጊዜ የሚከራከር ከሆነ የቋንቋ የሀሳብ የምልከታ የእይታ ግጭት ሊፈጠር ይችላል ። በእስክንድርያ ከተነሱ ሊቃውንት እንደ ኦሪገን (አርጌንስ) ለመናፍቃን መልስ የሰጠ ፦ከመናፍቃን ጋራ የጨበጣ ውጊያ ያደረገ የለም። ለሌሎች መልስ እየሰጠ ሲሰቃይ ኑሮ እርሱ ግን የአስተምህሮ ግጭት ተገኘበት። ብዙ ሊቃውንት ለመናፍቃን መልስ ለመስጠት ሲታገሉ ከጥረታቸው ብዛት የተነሳ በትምህርታቸው ላይ እንከን ሊመጣ ይችላል ።
ይሄ ደግሞ በሁሉም ቤተ እምነት ባሉ መምህራን ዘንድ ያለ ነው ። ልጁ በርካታ አድማጮች ስለነበሩት የልጁ እንዲህ መባል ለብዙ ምእመናን በተለይ ለወጣኒዎች ጭንቀት ይሆናል። አንድ ነገር ግን እንመን። ልጁ ላይ ያሉት ሀሳቦች" እይታዎች ፤ ምልከታዎች ናቸው እንጅ በፍጹም ምንፍቅናዎች አይደሉም። እነዚህን የመሰሉ ሀሳቦች ደግሞ በጉባኤ ቤት ሁልጊዜ ይነሳሉ።ሁልጊዜ ግን መልስ ይሰጣል።ሀሳቡ ምድያ ላይ ስለተነሳ ክርክሩም ምድያ ላይ ሆነ እንጅ በጉባኤ ቤት አኬ ካነሳቸው የበለጡ የሚያስደነግጡ ሀሳቦች ሁልጊዜ ይነሳሉ።ሁልጊዜ ያከራክራሉ።ወዲያው ምላሽ ያገኛሉ። የአኬ ሀሳብም እንደዚሁ ነው ብየ ተስፋ አደርጋለሁ ።ስለሆነም .....።

🥡 ፅጌ አስተራይ

@Sewsinor
@Sewsinor


የአኬ ነገር... በፅጌ አስተራይ ዕይታ


ፍርሃት የገዛው ትውልድ!

ይህ ትውልድ ፍርሃት የገዛው ትውልድ ነው፡፡ ፍርሃት የገዛው ትውልድ በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ፍርሃት ያገኘዋል፡፡

ሰዎች አይወዱኝም ብሎ ይፈራል፤ የሚወደው ሰው ሲያገኝ ደግሞ የወደደው ሰው መልሶ እንዳይጠላው ይፈራል፡፡

ተቀባይነት አጣለሁ ብሎ ይፈራል፤ ተቀባይነት የሚሰጠው ሰው ሲያገኝ ደግሞ መልሶ እንዳይገፋው ይፈራል፡፡

ከሰው ጋር መሆን ይፈራል፤ ከሰው ሸሽቶ ብቻውንም ቢሆንም ይፈራል፡፡

የቀረበው ሰው እንዳይጎዳው ይፈራል፤ ሰውየው ከጎዳው ደግሞ እንደገና ላለመጎዳት ሲል ከዚያ ሰው መለየትን ሲያስብ ሰውየውን እጎዳዋለሁ ብሎ ደግሞ ይፈራል፡፡

ሳላገባ ብቻዬን ልቀር ነው ብሎ ይፈራል፤ ካገባሁ ግን እጎዳለሁ ብሎ ስለሚያስብ ማግባትን ይፈራል፡፡

ስለሚፈራ እንቅልፍ አይወስደውም፤ እንቅልፍ ስላልወሰደው ደግሞ ይፈራል፡፡

እንዳይነግድ ክስረትን ይፈራል፤ እንዲሁ ቁጭ እንዳይል ድህነትን ይፈራል፡፡

ደፍሮ ከወጣ አደጋን ይፈራል፤ ፈርቶ ከቀረ ደግሞ ሰዎች ፈሪ ነው ብለው ያስባሉ ብሎ ይፈራል፡፡

ከፍርሃት የተነሳ መሆንና ማድረግ ያለብህን ሳታደርግ አንድ መቶ አመት ከምትኖር ፍርሃትህን ተጋፍጠህና ቀና ብለህ አስር አመት በዓላማ ኖረህ ብታልፍ ይሻልሃል፡፡

ከፍርሃት ነጻ የሆነ ሕይወት ሊኖር ያለመቻሉን ያህል ፍርሃትን ተጋፍጦ ከመኖር ውጪ ስኬት የለም!

ምንጭ : Dr. eyob

@Sewsinor
@Sewsinor


አሜን እግዚአብሔር ይመስገን!


👉ሶስት ወንድማማቾች አባ መቃርስን ለመጠየቅ ይሄዳሉ

እንዳገኙት ሁለቱ በጥያቄ ያጣድፉታል አንደኛው ግን የአባ መቃርስን ዓይን እያየ ዝም አለ

አባ መቃርስ ዘወር አለና ለምንድነው አንተ የማትጠይቀው ይለዋል

ምን እንዳለ ታውቃላችሁ ጥያቄ የሌለው ሁኖ እንዳይመስላችሁ ወይም ለመጠየቅ ፈርቶ አይደለም ለእሱ አባ መቃርስን ማግኘት ወይም ማየት በቂ ስለሆነ ነው

ታዲያ ይህ ሰው አባቴ አንተን ማየት ለእኔ መልስ ነው ይላል

ቅዱሳን የሕይወት ጥያቄ መልሶች ናቸው በታሪክ መጻሕፍት
በድርሳናት ከተጻፉት በላይ በሕይወት ያለነው እኛ ምስክሮች ነን

የቅዱሳን ጸሎት ግዳጅን ትፈጽማለች ብሎ መጽሐፍ እንደተናገረ በቅዱሳን ምልጃ ቅዱሳንን ተማጽኖ ግዳጁ ያልተፈጸመለት የሕይወት ቋጠሮው ያልተፈታለት ጥያቄው ያልተመለሰለት የለም

ቅዱሳን መፍትሔዎች ናቸው

ቅዱሳንን የሰጠን ለቅዱሳን አምላክ ክብር ምስጋና ይድረሰው አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏


የሆነ ቦታ የሆነች የተረጋጋች ሴት ያለች ይመስለኛል። የሰውን ትኩረት የማትፈልግ ፤ ሰዎች እንዲወዷት የተለየ ነገር የማታደርግ የራሷን ኑሮ የምትኖር...

ህይወቷ በእውነት እንጂ በፈጠራ ድራማ ያልተሞላ ፤ ሰዎች እግረመንገድ ላይ ድንገት ዋነኛዋ ሴት የምትሆን ። የተሰማትን የፈለገችውን ደስ ያሰኛትን የምታደርግ ፤ ምታደርገው የማይፀፅታት ...

ምድር ላይ ያለውን የህይወት ብሶቷን አልያም ችግሯን ለመደበቅ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ወ'ታ ከመንዘባዘብ ይልቅ ከአምላኳ ጋር የምትነጋገር። ስለራሷ እሷ እና አምላኳ ብቻ የሚያውቁ። ይህቺ ሴት ብርቱ ናት....

ለጓደኝነት ትመቻለች። ነፃነት ትሰጣለች። ለጊዜያዊ የፍቅር ግንኙነት ታስፈራለች። ወንዶች ይጠነቀቁላታል። የትኛውም ወንድ ደፍሮ ሌላዋን ሴት የሚያወራበት መልኩ ይቺን ሴት ሊያወራት አይችልም። ልባም ናት። ለዘላቂ ትዳር የምታስተማምን ሴት። የቤቱ ራስ መሆን የሚችል ፣ ሚስቱ እንድትገዛለት ሆኖ መኖር የሚችል ባል የሆነ ወንድ የሚመኛት እና የሚያገኛት ሴት ናት።

ይህቺ ሴት ብርቅ ናት ! ፀሎቷ ልኬት ያለው ይመስለኛል። ከሚያስፈልጋት በላይ እንዲሰጣት አትለምንም። ተመስገንን ታውቃለች በተሰጣት አታማርርም ።

💭 ዘርፉ

ሼር ያድርጉት!
@Sewsinor
@Sewsinor


#ገንዘብ_ደስታን_አይገዛም_ይሉሃል

🤦‍🗣ብድር......ድብርትን እንደሚገዛ
🤦‍🗣ድህነት.......ስቃይን እንደሚገዛ
🤦‍🗣ውጥረት....እንቅልፍ አልባ ሌሊትን እንደሚገዛ ግን አይነግሩህም😏

🤝ብሮ ውሸታሞች በላቸው አንተ ብቻ ወጥረክ ስራ!!!

🗣
ንባብ ለህይወት
@Sewsinor @Sewsinor


"ግፍና መከራ ተንከባሎ በሁሉም ቤት ይደርሳል። "

የምናደርገው ነገር ትርጉም መስጠት ያቆመበት በሚመስልበት ጊዜ ላይ ነን። እዚህ ሀገር ልጅ እንወልዳለን። የምናወርሰው ሀገር ግን ሲዖል ነው። ምሽቶች ባሎቻቸው ድንገት በወጡበት ይቀራሉ። ይታፈናሉ፥ ይታገታሉ። ልጆች ያልጠገቡትን፥ በውል ያለዩትን አባቶቻቸውን ባልጠበቁት ቅጽበት ይሰናበታሉ። ለሀገራቸው ውለታ የዋሉ ዋርካ ሰዎች በልጅ እግሮች ይገደላሉ። ደም ይፈሳል —በየመንገዱ፥ በየጫካው።  አድባራት አንድ ባንድ ይፈርሳሉ። ማንም ምንም ማምጣት የሚችል አይመስልም። ድንገት ኢምንትነት እንዲሰማህ ትሆናለህ።

ሞት እየጠራህ ትማራለህ? ሞት እያነፈነፈህ ታከማቻለህ? በደጅህ ሞት እያደባ ታገባለህ? ሀገር እየተቃጠለ ትሰርጋለህ? ቆንጆ ቆንጆ ልጆች የጥይት እራት እንዲሆኑ ትወልዳለህ? መሣሪያ የታጠቀ ወንበዴ ቤትህን እየሠረሠረ ታንቀላፋለህ? የዓለም ምጽዓት አንተ ጋር እስከሚደርስ ትተኛለህ?

ሀገሩ የባለጌ ነው። ማን ጌታ እንደሆነ አይታወቅም። በመንገድ ስታልፍ ረግጦህ የገላመጥከው ሰው ዘመደ ብዙ ነው። የጦር መሣሪያ አለው። ባታውቀውም የጎበዝ አለቃ ነው። ትንሽ መንግሥት ነው። ሕይወትህን ከአፈር ይደባልቀዋል። ያየህ እስከማይገኝ ድረስ ድራሽህ ይጠፋል። ወዝህ ያስቀናው ሰው ዳር ሊያስይዝህ ይችላል።

ሀገርህ ከየት እስከየት እንደሆነ አታውቅም። እግርህ ከቤት ወጣ እንዳለ የጠላት ሀገር ነህ። በካርታ ባይከለልም የተበጀ ድምበር አለ። ድንገት  ትጨመደዳለህ፥ እጅ ትሰጣለህ። ብትማረክም ትገደላለህ። ከቀን ውሎህ ተርፈህ፥ በሰላም ወጥተህ ከገባህ እድለኛ ነህ።  ከሄድክበት ስትመለስ ቤትህን በገነባህበት ስፍራ ላታገኘው ትችላለህ። ግፍና መከራ ተንከባሎ በሁሉም ቤት ይደርሳል። እስከዚያው ያንተ ተራ እስኪደርስ  ታንቀላፋለህ? ወይ የተኛህ ትመስላለህ? ዝም ካልከው በራፍህን አንኳክቶ መምጣቱ አይቀርም
አልነገሩኝም እንዳትል!!

@Sewsinor @Sewsinor


በአፍላ ትጀምራላችሁ.....በወረት ትተውታላችሁ።

ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ....ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ።

የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ....የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ።

ምኞታችሁ ልክ የለውም...አምሮታችሁ ብዙ ነው።

ያማራችሁን ስታገኙ ወድያው ይሰለቻቹሃል...ተው የተባላችሀትን ትሽራላችሁ።

የተከላከላችሁትን ትደፍራላችሁ...የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ።

ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደ ፊት ቤተ መቅደሱን በመስታወት ሠርታችሁ መቅደስ ባትገቡም እንኳን ሁሉን ከውጪ ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ።

ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ....በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም። ሁሉ አላችሁ ግን ባዷችሁን ናችሁ።

ሃይማኖት እንጂ እምነት የላችሁም ቀጥሉ አባ...ሰውነታችሁ እንደ ቅኔ ዘራፊ በስሜት ይናጣል።

📕እመጓ....ገፅ 162

🗣
ንባብ ለህይወት
------------------------------------------------
ቤተሰብ ሁኑ👇👇
@Sewsinor @Sewsinor


አንድ ናይጄሪያዊ የሂሳብ መምህር፣ለማስተማር ወደ ክፍል ሲገባ፣ተማሪዎቹ መቀመጫ ወንበሩን ጣሪያ ላይ አንጠልጥለውት ይመለከታል።

ምንም እንኳ የተማሪዎቹ ተግባር ቢያበሳጨዉም፣ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ፣በፈገግታ ሰላምታ ከሰጣቸዉ በኋላ፣ለፈተና እንዲዘጋጁ ነግሯቸዉ፣ወደ ሰሌዳዉ በመዞር  ''ጣሪያዉ ላይ የተሰቀለዉን ወንበር መሰረት በማድረግ ከታች ያሉትን ጥያቄዎች መልሱ '' በማለት ይፅፋል....

  #ጥያቄ 1. በወንበሩና በወለሉ መሃል ያለዉን ርቀት አስሉ??   (1 Mark)

  #ጥያቄ 2.  በወንበሩና በጣሪያዉ መሃል ያለዉን ግንኙነት  አግኙ ?  (1 Mark)

    #ጥያቄ 3. ወንበሩን ጣሪያዉ ላይ የሰቀለዉን ተማሪ እንዲሁም ወንበሩን በመስቀል የተባበሩትን ተማሪዎች ስም ዘርዝሩ (16 Mark)

ተማሪዎቹም 3ተኛው ጥያቄ ብዙ ነጥብ መያዙን ተመልክተዉ፣ወንበሩን ጣሪያ ላይ የሰቀለዉን ተማሪ እስከነ ተባባሪዎቹ ፃፉ።

መምህሩም "መምህር የሆንኩት ተምሬ እንጂ በእድል አይደለም!!!!"በማለት፣ወንበሩን ጣሪያ ላይ የሰቀሉትን ልጆች ከክፍል አስወጣቸው።

.......  Always use your mind, to solve  problems!!!!!

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
         @Sewsinor
         @Sewsinor


ከጅብ መንጋጋ ልጇን ያስጣለችው እናት‼️
በሀዲያ  ዞን በሆሳዕና ከተማ በጀሎ ናራሞ ቀበሌ መንደር 16 ነዋሪ  ወይዘሮ  ደንባሌ አሥራት ጥር 11/2017  ዓ/ም  ከጠት 3 ስዓት  አከባቢ ላይ  ሽላንሻ  ወንዝ ልብስ ለማጠብ  የ12ዓመት ሕፃን አሥከትላ በመሄድ ሥራዋን  መከወን ላይ እያለች  ጅብ ወደ እነርሱ  ይመጣል። በአጠገብ ከነበረች  ከሌላ ሴት  ጋር  በመሆን  ይህንኑ  ህፃን በመሀል አሥገብተዉ ቆመው  ያያሉ ።

ይህ ጅብ  ማለፍ  ይቅርና በ2ቱም  ሴቶች  መከከል  ያለውን  ህፃን ዘሎ ቀኝ እግሩን ነክሶ  በመያዝ ለመውሰድ ሲሞክር   ወላጅ እናት ቀኝ እጇን  በጅብ  አፍ  ውሥጥ  በመክተት  የጅቡን ጉሮሮ በግራ እጅ  አንቃ በመያዝ በላዩላይ ትወድቃለች  አብረው   የነበረችው  ሴት ከጅብ አፍ ህፃኑን   ነጥቃ  በማውጣት   ትታደጋለች ።  በጩኸት   የወጡ ሰዎች ህፃኑን ሊባላ  የቋመጠውን ጅብ  ብዙም  ሳይሄድ  በአካባቢው ሰዎች ርብርብ መገደሉን ከሀዲያ  ዞን  ፖሊስ  መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
=======================
አዩ ዘ ዘበሻ

@Sewsinor




ዮሐንስ ክርስቶስን ያገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ አልነበረም፡፡ ከሠላሳ ዓመታት በፊት ሁለቱም በእናቶቻቸው ሆድ ውስጥ ሆነው ተገናኝተዋል፡፡

‘’በእናትህ ሆድ ሳለህ አውቄሃለሁ’’ ብሎ የተናገረውን ፈጣሪውን እኔም ‘’በእናትህ ሆድ ሳለህ አውቄሃለሁ’’ ብሎ ማነጋገር የሚችል ከመጥምቁ ዮሐንስ በቀር ማን አለ? ‘ከማኅፀን ጀምሮ ባንተ ታመንሁ ከእናቴ ሆድ ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ‘’ ብሎ የዳዊትን መዝሙር ለመዘመር የሚችል እንደ መጥምቁ ያለ ማን አለ?

ቅዱስ ያሬድ ‘እምከርሠ እሙ አእመረ ሰገደ ወአንፈራዓፀ’’ ‘በእናቱ ማኅፀን አወቀ ሰገደ ዘለለም’ ብሎ በድጓው የዘመረለት ዮሐንስ ለጌታው ለመስገድ ከእናቱ ማኅፀን እስኪወጣም አልታገሠም፡፡ ጉልበቱ ሳይጸና መስገድ የጀመረ ፣ በዓይኑ ማየት ሳይፈልግ አምልኮ የጀመረ ከዮሐንስ በቀር ማንም የለም፡፡

አሁን በእናቱ ማኅፀን ያገኘውን ጌታ ሁላችንን ወደምትወልደው ወደ ማኅፀነ ዮርዳኖስ ሲመጣ አየው፡፡ ዮሐንስና ጌታ ከሠላሳ ዓመት በፊት ተገናኝተዋል ግን አልተያዩም ነበር ፣ መልእክት ተለዋውጠዋል ነገር ግን አልተነጋገሩም፡፡ ለዚህ ነው ዮሐንስ ስለ ጌታ ‘’አላውቀውም ነበር‘’ ያለው፡፡ /ዮሐ 1፡31/ አሁን ግን ጌታውን አየው፡፡ ወደ እርሱ ሊጠመቅ መምጣቱን ተመለከተ፡፡

እንኳን አደረሳችሁ!


​​የሞት ማምለጫ.....

አዲሱ ቴክኖሎጂ ሰዎች ከሞቱ በኋላ ዳግም ህይወት ሊዘሩ ይችላሉ በሚል የተፈጠረ ነው😎

አዲሱ የሞት ማምለጫ ቴክኖሎጂ ይሳካለት ይሆን?

የሰው ልጅ በየጊዜው ህይወትን ቀለል የሚያደርጉ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

በእስካሁኑ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች አስደማሚ እና ሊሆን አይችልም የተባሉ ፈጠራዎች በሰው ልጆች ተሰርተዋል።

ይሁንና እስካሁን ሞትን ማምለጥ የሚያስችሉ ፈጠራዎችን መስራት ያልተቻለ ሲሆን ቱሞሮ ባዮ የተሰኘ ኩባንያ ግን ባልተሞከረውን መንገድ እየሄደ ይገኛል።

ይህ ኩባንያ አንድ ቀን ይሳካልኝ ይሆናል በሚል መሞታቸው በሐኪሞች የተረጋገጡ ሰዎችን አስከሬን በማጠራቀም ላይ ነው።

የዚህ ኩባንያ ዓላማ ሰዎች ህይወታቸው ከላፈ በኋላ በበጎ ፈቃደኝነት አስከሬናቸውን እንዲሰጡት ካደረገ በኋላ ወደ ማቀዝቀዣ ቦታ ይወስዳል።

የአስከሬኑ ቅዝቃዜ ዜሮ ድግሪ ሴንትግሬድ ከደረሰ በኋላ አስከሬኑ በቅዝቃዜ እና በሌሎች ተፈጥሯዊ ምክንያቶች እንዳይበሰብስ የሚያደርግ የተለያዩ ኬሚካሎችን ተጠቅሞ ባለበት እንዲቆይ ያዱርጋል።

ኩባንያው ይህን የሚያደርገው ሟቾች ወደ ዳግም ህይወት መመለስ ይቻላል የሚል ዕምነት ስላለው እና ሰዎችም ረጅም እድሜ በህይወት የመኖር ፍላጎት አላቸው በሚል ነው።

ሰዎች ይህን አገልግሎት ለማግኘት 200 ሺህ ዶላር መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን አብዛኞቹ ከፋዮች ምን አልባት ቴክኖሎጂው ከሰራ ብለው የሚያምኑ ናቸው ተብሏል።

ከኩባንያው መስራች አንዱ የሆኑት ኢምል ኬንድዚዮራ ለቢቢሲ እንዳሉት ሀሳቡ የተጀመረው አንዲት ስዊድናዊ በልብ ህመም ህይወቷ አልፏል ተብሎ በማቀዝቀዣ ውስጥ ከቆየት ከሁለት ሰዓት በኋላ ዳግም ዳግም ህይወት መዝራቷን ተከትሎ ነው ብለዋል።

እንዲሁም የሞተ የአይጥ አዕምሮን በዚህ የማቀዝቀዝ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ዳግም እንዲመለስ እና በቀዶ ጥገና መልክ በሌላ አይጥ ካይ ተገጥሞ መስራቱ እንደተረጋገጠም ተገልጿል።

ይህ ተስፋ ሰጪ ምልክት በሰዎች ላይ ሊሰራ ይችላል በሚል እየሞከርነው ነው የሚሉት የኩባንያው መስራች የደንበኞቻቸው ቁጥር እየጨመረ እንደሆነም ተናግረዋል።

በተለይም በኮሮና ቫይረስ ወቅት ሞት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቅርብ መሆኑን ተከትሎ ከቫይረሱ መከሰት በኋላ የደንበኞቻቸው ቁጥር ጨምሯልም ተብሏል።

የአንድን የሰውነት አካል በቀዶ ህክምና ወደ ሌላ ሰው መተከት ህክምና ሲጀመር ሰዎች ብዙ ተገርመው ነበር የተባለ ሲሆን ምን አልባት ከ10 ወይም ከ100 ዓመት በኋላ የሞቱ ሰዎችን ዳግም ወደ ህይወት መመለስ ሊጀመር እንደሚችልም ተስፋ ተደርጓል::

ዘገባው የአልዐይን አማረኛ ነው::
ጉርሻ
😎😎😎

🌴🌴🌴

@Sewsinor

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.