መቆጠብ ወይስ ኢንቨስት ማድረግ
በመቆጠብ እና ኢንቨስት በማድረግ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት! የገንዘብ ነጻነት እና የቀጣይ ህይወት መሰረት ላይ ወሳኝ ነው!
አንዳንዴ ተለዋዋጭ ተደርገው ይወሰዳሉ! ከተቆጠበ ኢንቨስት ይደረጋል! ኢንቨስት ተደርጎ ከተገኘው ይቆጠባል! (ፍጹም የተለያዩ መሆናቸው ማወቅ ግድ ነው!)
በግለሰብ ደረጃ ቁጠባ ምንድን ነው? ኢንቨስትመንት ምንድን ነው? የሁለቱም እድል እና ስጋት ምንድን ነው?
ቁጠባ ምንድን ነው?
ሰዎች ለ2 ምክንያት ገንዘብ ያስቀምጣሉ (የሆነ ነገር ለመግዛት ወይም ለማይታወቅ የአደጋ ጊዜ) ቁጠባ በቤት፤ በባንክ (በወለድ)፤
ቁጠባ ለአጭር ጊዜ ሸመታ ፍላጎት ጥሩ ነው (አልጋ ለመግዛት 4 መቆጠብ! እስከ 1 ዓመት)
ቁጠባ አደጋው ጠባብ! በቤት ከሆነ የወለድ ግኝት የለውም (የዋጋ ንረት ይንደዋል)
ለምሳሌ፡- የ10ሺ ብር አልጋ ለመግዛት ለ10 ወር በየወሩ 1ሺ ብር መቆጠብ! ወይም 10ሺ ብር ተበድሮ በየወሩ ለአበዳሪ 1ሺ ብር መክፈል (ከዘመድ፤ ከጓደኛ፤ ከቤተሰብ….ብድር)
የቁጠባ ጥቅም
በገቢ በአንዴ ለማይገዛ መግዣ ይሆናል
ድንገት ለሚስፈልግ ወጪ መሸፈኛ ይሆናል (ድንገት ሰው ቢታመም፤ ሞባይል ቢጠፋ….)
ከኪሳራ ለመዳን (ቁጠባው በባንክ ከሆነ ወለድ ካለው! ከኢንቨስትመንት አንጻር)
የቁጠባ አደጋ
አነስተኛ ትርፍ ያስገኛል (በባንክ ከሆነ ወለድ! መባዛት አይችልም!
በዋጋ ንረት ይበላል (በቤት ከተቆጠበ፤ በአነስተኛ ወለድ ከተቆጠበ!
ገንዘቡን ኢንቨስት ባለማድረጋችን የምናጣው ነገር (Opportunity costs)
ኢንቨስትመንት ምንድን ነው?
ያለንን ገንዘብ ወደ ሌላ ብር ወደሚመጣ ነገር የመለወጥ ሂደት (መነገድ፤ አክሲዮን፤ ገዝቶ መሸጥ (ወርቅ)፤ ትምህርት መማሪያ፤ የኪራይ ቅድመ ክፍያ መፈጸም፤ ….
ኢንቨስትመንት አደጋ ያለው ቢሆን የረጅም ጊዜ ትርፍ አለው (ለምሳሌ አክሲዮን የገዛ ሰው ድርጅቱ ሲከስር ይቀንሳል (መሸጥ) ሲጨምር ይጨምራል…..(ያልተጠና ቦታ እና አንድ/ ተመሳሳይ ቦታ ኢንቨስት ማድረግ ዋጋ ቢስ ነው!)
የኢንቨስትመንት እድል?
ከቁጠባ በላይ አትራፊ ነው!
የረጅም ጊዜ የፋይናንስ ምንጭ/መተማመኛ ይፈጥራል!
አሰባጥሮ እንቨስት ማድርግ አደጋን ይቀንሳል!
የኢንቨስትመንት አደጋ?
በተለይ ለአጭር ጊዜ የኪሳራ አደጋ (ስራ እስኪጀመር! ቁጠባ ቢሆን ወለድ)
ከፍተኛ ትጋት የሚፈልግ ተግባር መሆኑ (ጸጉር ቤት የከፈተ ተግቶ መስራት አለበት!)
ረጅም ጊዜ ሊያስጠብቅ ይችላል (አክሲዮን ቢሆን ዓመት ሙሉ ተጠብቆ ትርፍ)
መቼ መቆጠብ መቼ ኢንቨስት ማድረግ?
የዚህ ጥያቄ መልስ ከሰውየው የገንዘብ አቅም፤ ካስቀመጠው ዓላማ እና አደጋ ለመጋፈጥ ያለው አቅም ላይ ይመሰረታል!
ምን አልባት መጣት የሆነ ሰው፡ ትንሽ ገቢ እና ትንሽ ወጪ ስለሚኖረው ቁጠባ ላያሳስበው ይችላል (ወጣት አደጋ የመጋፈጥ እድል እና ጊዜ ስላለው ኢንቨስትመንት (መማር፤ መሰልጠን፤ መሞከር፤…
ምን አልባት ትልቅ የሆነ ሰው፡ አጭር ቀሪ ጊዜ ያለው (አደጋ ካለው ኢንቨስትመንት መካከል አክሲዮን ሊመከር ይችላል! ገንዘቡን በካሽ መያዝ ሊሆን ይችላል)፤
ኢንቨስት ከማድረግ በፊት በቂ መጠባበቂያ ቁጠባ (ቢያንስ ከ3-6 ወር ፍጆታ የሚበቃ) መኖሩን ማረጋገጥ ግድ ነው (ለቤት ኪራይ፤ ለወራዊ አስቤዛ፤ !
ለምን ብዙ ሰዎች ኢንቨስት ከማድረግ በላይ ቁጠባ ይመርጣሉ!
አደጋ ይኖራል የሚል ስጋት መኖር (በመጠባበቂያ መተማመን)
ብዙ የወጪ ምክንያቶች መኖር!
ቁጠባ ትጋት ስለማይጠይቅ!
ኢንቨስት በማድግ አስፈላጊነት በቂ ግንዛቤ አለመኖር (ምን ልስራ!)! በምን ያህል!
ኢንቨስት በማድረግ ወስጥ የሚኖርን አደጋ የመቋቋም አቅም አለመኖር (መፍራት!)
ቁጠባው ለየትኛውም ኢንቨስትመንት የማይበቃ ሲሆን (የቀጣይ ገቢ አነስተኛ መሆን!
ከቪዲዮው ላይ የተጻፈ (
@MesBe)