[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa] dan repost
የጥመት ቡድኖች በአላህ ዲን ያለ እውቀት ይከራከራሉ!!
———
የጥመት አንጃዎችና ቡድኖች በአላህ ዲን ላይ ባጢልን የበላይ ለማድረግ ሐቅን የበታች ለማድረግ ያለ እውቀት ይከራከራሉ። አምላካችን አላህ ይህን አስመልክቶ ሲናገር በተግባራቸውም አመፀኛና ሞገደኛ የሆነውን ሸይጧንን እንደሚከተሉ እንዲህ በማለት ተናግሯል:-
وَمِنَ النَّاسِ مَن يُجَادِلُ فِي اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّبِعُ كُلَّ شَيْطَانٍ مَّرِيدٍ ۞ كُتِبَ عَلَيْهِ أَنَّهُ مَن تَوَلَّاهُ فَأَنَّهُ يُضِلُّهُ وَيَهْدِيهِ إِلَىٰ عَذَابِ السَّعِيرِ
«ከሰዎቹም ያለ እውቀት በአላህ ነገር የሚከራከር፤ ሞገደኛ ሰይጣንንም ሁሉ የሚከተል ሰው አለ፡፡ እነሆ! የተከተለውን ሰው እርሱ ያጠመዋል፡፡ ወደ ነዳጅ እሳት ስቃይም ይመራዋል ማለት በርሱ ላይ ተጽፏል፡፡» አል-ሐጅ 3 - 4
ታላቁ ሊቅ ሸይኽ ዐብዱረህማን ናስር አስ-ሰዕዲይ (ረሂመሁላህ) ይህን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል:-
“ከሰዎች የጥመትን መንገድ የተጓዙ ቡድንና አንጃዎች አሉ። ሐቅን በባጢል መከራከርን ተግባራቸው የደረጉ፣ ባጢልን የበላይ ለማድረግ (ለማረጋገጥ) ሐቅን ደግሞ ውድቅ ለማድረግ የሚከራከሩ አሉ። ሁኔታቸው ድካ በደረሰ አላዋቂነትና ከእውቀት ምንም የሌላቸው ናቸው። እነርሱ ዘንድ ያለው ግብ የጥመት መሪዎችን መከተል ነው። ከአላህና ከመልእክተኛው አፈንጋጭ ሞገደኛና አመፀኛ ከሆነው ሸይጧን ጋር ናቸው። አላህንና መልእክተኛውን ያመፀና ወደ ጀሀነም ከሚጣሩ የጥመት መሪዎች ሆኗል። ˝እነሆ! የተከተለውን ሰው እርሱ ያጠመዋል…˝ማለት:- ሸይጧን ከትክክለኛው መንገድ ያርቀዋል፣ በትክክልም የሸይጧን ምትክ ነው። ይህ በአላህ መንገድ ላይ ያለ እውቀት የሚከራከር አካል ሁለት ጥመቶችን ሰብስቧል። አንደኛው እራሱን ማጥሙ ሲሆን ሁለተኛው ሰዎችን ከሀቅ መንገድ ዘግቶባቸው ማጥመሙ ነው። እርሱም ለአመፀኛና ለሞገደኛው ሸይጧን ተከታይና በጭፍን ተጎታች ነው። ይህ ደግሞ አንዱ በአንዱ ላይ የተደራረበ ጨለማ ነው። በዚህ ላይ አጠቃላይ ከሀዲዎችና የቢድዐ ባለ ቤቶች ይካተታሉ። አብዘሃኞቹ ጭፍን ተከታዮቻቸው ያለ እውቀት ይከራከራሉ።” [ተፍሲሩ ከሪሚ ረህማን ሊሸይኽ ናስር አስ-ሰዕዲይ - ረሂመሁላህ]
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa