የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 1ኛ ልዩ ስብሰባውን ያካሂዳል
እሁድ ጥር 18 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።
ምክር ቤቱ በስብሰባው የግብርና ሚኒስቴርን የ2017 በጀት አመት የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የሚያዳምጥ ሲሆን፤ ሁለት የብድር ስምምነቶችን መርምሮ እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።
የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እንዲሁም የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።
በተጨማሪም የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
አዲስ ማለዳ የምክር ቤቱን ስብሰባ በዩቲዩብ በቀጥታ ስርጭት የምታስተላልፍ መሆኑን እየገለጽን መሰል ጉዳዮችን ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን በመጫን አዲስ ማለዳን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
YouTube ➲
t.ly/vSgSTelegram ➲
t.ly/SOXUFacebook ➲
t.ly/flx8Twitter ➲
t.ly/mxA