ሐሽማል ቤተ-መዘክር


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Kitoblar


👉Only for readers
👋መግቢያ👋
መግቢያ ለመግባቢያ
ገታ አርገነዋል የቃላትን ግልቢያ
እናም በዚህ ሀሳብ ከተስማማህበት
ያንኳኳኸዉን በር የገለፅከዉን ገፅ ፈቅደናል ግባበት
ምንጭ - ካልታወቀ ገጣሚ
Join the group
@amharicbooksforeadersgroup
አድሚኑን በ ቀጥታ ለማናገር ይህንን ቦት ተጠቀሙ @Digitallibraryofhashmal_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


አንዳንድ ሰዎች አለመረሳት እንጂ የእናንተ መሆን አይፈልጉም።


©ሶፊ


ማንነትህን የቀየረው ማን ነው ? ብባል ሳላንገራግር ሽፈራው ነው የምለው ...ሽፈራው ማነው ? ብባል

ዘጠነኛ ክፍል ኮከበ ፅብሃ ስማር ትምህርት ቤታችን በር ላይ ሩጬ አስፋልት ስሻገር በመኪና የገጨኝ ሹፌር ነው እላልሁ .....

እስከዘጠነኛ ክፍል ቆሌ አልነበረኝም ብርር ብርር፣ ጥድፍ ጥድፍ፣ ቅልጥፍ ፣ቅልል፣ ቅልቅል ያልኩኝ ነበርኩ ሽፈራው በሚኪናው እስኪያንከባልለኝ ....

ኳስ ከሚጫወቱ ጋር፣ ጆተኒ ከሚጫወቱ ጋ፣ ሩጫ ከሚሮጡ ጋ፣ ከሚታገሉ ጋ ፣ ዋና ከሚለማመዱም ፣ከሚዋኙም ጋ በየቦታው ነበርኩ

በየቦታው ሰላም የማልለው የለም የሁሉም ጓደኛ ነበርኩ የሁሉም ...

ሽፈራው አስፋልት ስሻገር በመኪናው ገጨኝ

እስከዛሬ ሰው በጣም አሞኛል ሲለኝ ፤ተሰቃየው ፤ ከባድ ነበር ፤ ልሞት ነበር እያለ ሲያብራራ ልቤ ወደ ዘጠነኛ ክፍል ኮከበ ፅባህ ትምህርት ቤት መኪናው ሲገጨኝ ተሸክመውኝ ሲሄዱ ሃኪም ጋ ስሄድ ያለውን መንፈስ ነው የማስተውሰው ...

የሁሉም ጓደኛ ስለሆንኩ በመገጨቴ ዜና ሆነ ...ምንሊክ ሆስፒታል የትምህርት ቤታችን ልብስ የለበሱ ልጆች፣የሰፈር ልጆችም ሳምንቱን ሙሉ ሞሉት

የግራ እግሬ ተሰብሮ ነበር ጀሶ ተጠቀለለልኝ ከሆስፒታል ወጣሁ እቤት የተወሰኑ ጓደኞቼ እየመጡ ጠየቁኝ ...

ጓደኞቼ ጠብ ጠብ እያሉ ጠፉ ። የሁሉም ጓደኛ መሆን ለካ የማንም ጓደኛ አለመሆን ነው የሚለው ጥቅስ ገባኝ ...

ለእናት እና አባቴ ብቸኛ ልጅ ነኝ ሰራተኛ የለንም ሁለቱም ስራ ይውላሉ

ጓደኞቼ ትምህርት ቤት ነው የሚውሉት

ቤት ውስጥ ቀን ብቻዬን እውላለሁ ። ብቻዬን ከራሴ ጋ ተፋጠጥን ....

ረጋ አልኩ ....

ረጋ ብሎ የሆነ ቦታ ቁጭ ማለት ..ሳያወሩ መዋል ..ነገሮችን ረጅም ሰዓት ሃሳብ ሳይሰጡ ማየት ለመድኩ

ቀስስ ብዬ ቴክስት ቡኮችን ለመረዳት ማንበብ ጀመርኩ ...አባቴ የሚያነባቸውን መፅሃፍ ማንበብ ጀመርኩ .....

እግሬ ሙሉ ለሙሉ ስላልዳነ ስራመድ ረጋ አልኩ ...ትንሽ ሳውቅ የማወቅ ፍላጎቴ ዳበረ

እራሴን ተለማመድኩት .... ስለሚደብረኝ የምሄድባቸው ስፍራዎች ቀረው ...

የሆነ የተረጋጋ ልጅ ፦
የሆነ ብቻ መሆን የማይፈራ ልጅ ፦
የሆነ ተረጋግቶ ለመረዳት የሚጥር ልጅ ሆንኩ

ከጓደኞቼ አንድ አመት በትምህርት ዘግይቼ ግን ሲገጭ ከነበረው ልጅ በፍፁም የተለየ ልጅ ሆኜ ዘጠኛ ክፍል ደግሜ ጀመርኩ ...

ትምህርት ጎበዝ የሆነ ልጅ ፣ቧንቧ ሲሰራ ኤሌትርኪ ሲሰራ ፣ፊዚክስ ሲብራራ ፣በትኩረት ሳልሰለች የማይ ልጅ ሆንኩ ...

የወደድኩት የህይወት Turning point የጀመረው ሽፈራው በመኪናው ያንከባለለኝ እለት ይመስለኛል ...

እግር ነስቶ ክንፍ የሚሰጥ መንከባለልም አለ ብንል ላንታመን እንችላለን አለመታመናችን እውነትነቱን አይነጥቀንም እንጂ።
© Adhanom Mitiku


የማንም ጓጆ በእውነት ብቻ አልተሰራም ። እውነት በመውደድ ፊት አቅም የለውም ። እውነት ላይ ክችች ያሉ ሰዎች ቤታቸው ሲፈርስ ፣ ከስራ ሲባረሩ ፣ ስራ ሲበላሽባቸው ነው ያየሁት ....

Undeniable truth !!

የሞቀ ቤት ያላቸው ብዙ ቤታቸውን ሊያቀዘቅዘው የሚችል ነገር ታግሰው ነው !! ሳድግ ያየሁት ጥበብ እሱን ነው ። መኖር ያሳየኝ እውነት ይሄ ነው ።

የሚያኖረው መለሳለሳችን ነው !!

ደረቅ እውነት አያሸንፍም። እውነት ብቻውን አያሻግርም ። እሚያኖረን ጥበባችን ነው ። የጎጆ መሰረት እውነት አይደለም መተላለፍ ነው።

ሁሉም የሞቀ ቤት ውስጥ የታለፈ ፣ይቅር የተባለ አደባባይ የማይነገር፣ ያልተነገረ ገበና አለ ።
እየተላለፍን ! ✋ source - https://t.me/ademeteku
Adhanom Mitiku


አንዳንዶቻችን እኮ መዳን እየቻልን ነው በሕመም ውስጥ መቆየት የመረጥነው ..
የሆነ የወደድነው ሕመምማ አለን

✍️ሔኖክ


ልቤ ሌላ ፤ ወየው ጉዴ ፊት መንሳቴ
ተጠምጥማኝ ባወቀችው ፤ ምን ትል ነበር ለስሜቴ
ሐረግ ብትሆን ምናለበት፤ ከልቤ ብትጠላለፍ
እኔስ ብሆን ከየት ቻልኩት ፤ እያዩ ሳያዩ ማለፍ

✍️ ሔኖክ


የመኖሬን ቅንጣት
በጥርሶችሽ ንጣት
ቀናውን እድሌን
በአይኖችሽ ብሌን
የነገዬን ድምቀት
በውበትሽ ስምረት
አየሁኝ ተስሎ
ነገ አንቺን መስሎ።
                 
By @poetkidus


ነበር.pdf
126.3Mb
📒 ርዕስ: ነበር

✍️ ደራሲ: ገስጥ ተጫኔ (ዘነበ ፈለቀ)

📖 የገፅ ብዛት: 406

🗓 የህትመት ዘመን: 2002
ዓ.ም (6ኛ ዕትም)

📜 ዘውግ:
ታሪክ


አልተዘዋወረችም.pdf
64.9Mb
📒 ርዕስ: አልተዘዋወረችም

✍️ ደራሲ: አሌክስ አብረሃም

📖 የገፅ ብዛት: 240


🗓 የህትመት ዘመን: 2016

📜 ዘውግ: ወግ


ሰርግ እና ቀብር አንድ ናቸው።ልዩነቱ የሰርግ አበባን ባለቤቱ ማሽተት መቻሉ ነው።

📚ርዕስ፦ነፃ ስሜቶች
✍️ፀሀፊ፦ኦሾ

📚 @ በእምነት ላይብረሪ


እሷ የክፍላችን ቁጥር አንድ ጎበዝ ተማሪ ናት። እኔ በቅርብ ርቀት እከተላታለሁ። አንድ ቀን የፊዚክስ የቤት ስራ ተሰጥቶን የኔና የሷን መልስ ስናነጻጽረው እርስበእርሱ ተቃራኒ ነው።

እኔ እሷ ናት ትክክል ብዬ መልሴን ወደሷ መልስ ቀየርኩ። ለካ እሷም ተሳስቻለሁ ብላ መልሷን ወደኔ መልስ ቀይራዋለች።

መምህሩ ደብተራችንን ተቀብሎ መልሱን ሲያመሳክር የሷ መልስ ትክክል፣ የኔ ደሞ ስህተት ሆኖ ተገኘ። ይህ ማለት የኔ የመጀመሪያ መልስ ልክ ነበር። እሷ ደግሞ ስህተተኛ ነበረች።

ታዲያ በአእምሮዬ ሁሌም የሚፈጠር ጥያቄ አለ። እኔ ትክክለኛ የነበረውን መልሴን የቀየርኩት መል,ሷ አሳምኖኝ አልነበረም። በደረጃ ስለምትበልጠኝ ብቻ እሷ አትሳሳትም ከሚል በራስ ካለመተማመን የመጣ ድርጊት ነበር። ይህ አጋጣሚ ታዲያ ትልቅ ቁምነገር አስተማረኝ፦

"መቼም ቢሆን በሰዎች ሃሳብ ልክ ከመሆን በራስ ሃሳብ ስህተት መሆን ተመራጭ ነው"


Yismake Worku dan repost
ከክፋት ዘመን መድረስ እድሜ አይባልም!


ለምን በኋላ አይሆንም ?


★በኋላ - ቀኑ ይመሻል
★በኋላ - ፀጉር ይሸሻል

★በኋላ - ቡናው ይቀዘቅዛል
★በኋላ - ሙዱ ይነፍሳል

★በኋላ - በኋላ የለም
★(ምሥክር አልባ ናት ዓለም )
.
.
አድርገው አሁን
አሁን....... source - https://t.me/ThoughtsAndPoetryChannel


ለሰው አደገኛ ተስፋ አትስጡ !ላትኖሩ አለውልህ አትበሉ፥ላታዳምጡ ንገረኝ አትበሉ፥መሸከም ማትችሉትን እንሸከማለን አትበሉ የማንንም ህመም የማስታመም ግዴታ የለባችሁም !
ከማስመሰል ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት ሰውን ያተርፋል።ለሰው ያልፋል ብቻ ሳይሆን ላያልፍም ይችላል ባያልፍም ግን መኖር ትችላለህ በሉት።ለደከማቸው እውነቱን ንገሩዋቸው ።አንዳንዴ ማንም ላይሰማን ይችላል አንዳንዴ ደግሞ የሰሚ ጆሮ ራሱ ይዝላል።በጣም የቅርብ ጉዋደኛ ቀርቶ ቤተሰብ እንኳን ስለኛ ግድ ላይሰጣቸው ይችላል ።በቃ እንደዚህም ከባድ ይሆናል ህይወት ።ይህንንም ችሎ
መኖር ነው ሁሉም ነገር ደግሞ በንግግር አይፈታም አንዳንዱ ችግር እኛ ጋር ብቻ ሚቀር ነው ።በቃ ለሰው ማውራት እንኳን ማትችለው ይሆናል ።እናት፥አባት፥ወንድም፥ጉዋደኛ ማይራመዱልን መንገዶች ብዙ ናቸው።ሁሉም በራሱ አለም ውስጥ የተጠመቀ ነው ።ለራስህ ራስህ ብቻ አዳኝ ሆነህ ምትቀርብበት ጊዜ አለ።ሳቅህን ከሰው ጋር አድርገው ለቅሶህን ግን አስብበት ወዳጄ.....


Unknown poet


Sponsored by Add'o coffee house ☕

የተቀደደው ማስታወሻ


Sost Kilo dan repost
ኧረ አሸሼ ፥ አሸሼ አሼሸ
አብይ መጣልን ከመሸ ።

[ ልዑል ዘወልደ ]

ወሬ ሁሉ ቲም-ለማ በሆነ ግዜ ቅዱሱን ለውጥ የሚያወድስ ዘፈን እንዲቀመር አቅጣጫ ይቀመጣል ። አቅጣጫውን ከዳላሩ (*በዶክተርዬ አክሰንት) ያስቀመጡት የዲሲ ግብረኃይሎች ናቸው ፤ ሀቅ ለመናገር ከዛ ቀድሞ አላውቃቸውም ።

ዜማና ቅንብሩን ሔኖክ ነጋሽ ሰርቶ በራሱ በ'ሔ - ሄኒ ቲዩብ እንዲለቀቅ ከስምምነት ይደረሳል ፥ ሙዚቃዊ ሀትሪክ ይሏል። ባይሆን ግጥሙ እንኳ የአንጋፋ እጅ ይዳብሰው ተብሎ ለጉምቱ ይልማ ገብረአብ ተሰጠ ።

ዜማ ልምምዱ በጎን ይጧጧፍ ጀመር ። ዘፈኑ ላይ በስቱዲዮ በኩል ያለፉ ሁሉ በአጃቢነት ተሳተፉ ። ፋሲል ደሞዝና ( ዛሬ ለውጡን ሊጠላ ነገር ) አብዮት ካሳነሽ በእንቅጥቅጥ ሸጋ ዱየት ወጣቸው ።

ስራው እየተሳለጠ ሳለ ችግር አይኑ ይጥፋ ችግር ተፈጠረ ። ይልማ የአዝማቹን መግቢያ እንደፃፈ ጨንጓራውን አመመው ። በአራቷ መስመር አረጠ ።

ኧረ አሸሼ ፥ አሸሼ አሸሼ
አብይ መጣልን ከመሸ ፤

ኧረ እንድያ ነው እንድያ
ፀሐይ ወጣልን ከወድያ ። (00:21)

ስራው ጊዜውን ጠብቆ ካልወጣ ጭንቅ ሊሆን ነው ። እንደ ደልፊ ሚቲንግ ሁሉም አስተያየቱን ከዛም ከዚ ይወረወር ገባ ። በመሀል ይልማ ጨጓራው ጋብ ሲልለት እየተነሳ የመብል ስንኝ ወርውሮ ይተኛል ።

ሠላም ነው ድግሱ
ኑ ፀበል ነው ቅመሱ - ሃሃ (04:16)

የሆነ ቀን እንዲሁ ከአልጋው ተነስቶ መድሀኒቴን ስጡኝ ሲል ፥ በመድሀኒት አንድ ሌላ አንጓ መጣለት ፤ ወስዶ ሰካው ።

መድኃኒት ወጣልሽ ኢጦቢያ ከጉያሽ
ደመቀ መኮንን ሆኖልሻል ቀያሽ - ሃሃ (5:34)

በዛ አካሄድ ሰባት ደቂቃ ሙሉ መቀጠል ስላልተቻለ ማሲንቆ ገዝጋዡ ዳዊት " እንዲያ እንዲያ " ከሚል ሐረግ ጋር ረጅም ትራክ ተሰጠው ። ነገር ግን ትርፉ የአብዮት ካሳን አንገት በእስክስታ ማዛል ሆነ ። ጀብደኛው አብዮት አንገቱ ከመሸማቀቁ በፊት ፋሲልን ይዞ ደውለለኝ ።

- ኧረ ግጥሙን በምን እንጨርሰው ?

- በመደመር ሃሃ

( ፋሲል በመሃል ገብቶ...)

- ዋ ! አትቀልድ'ዪ አባ ፥ ታሜሪኻ መስሎኝ ምንደውል

- ሰለም ነው ፋሲሎ !

- አለሁ የናቴ ልጅ ፥ ኧረ በጀ በለን?

- እኔ'ኳ ከመሰረቱ አዝማቹ ራሱ ይቀየር ባይ ነኝ ።

ኧረ አሸሼ ፥ አሸሼ አሸሼ
አብይ መጣልን ከመሸ ፤
ኧረ እንድያ ነው እንድያ
ፀሐይ ወጣልን ከወድያ ። (02:40)

- አይ እድሌ ፥ ምኑ ይቀየራል ይሄ አሁን ?

- አንደኛ " ፀሐይ ወጣልን ከወዲያ " ማለት ትልቅ ስተት ነው ። ፀሐይ እኮ አትወጣም ፋሲሎ ፥ የሌትና ቀን ፈረቃ ምድር መሽከርከሯ ያመጣው ሁነት ነው ።

- አሯ ፥ ለያ ኖሯል ምራብ ተ'ምስራቅ ምንከላወሰው ? አፈር በበላሁ ፥ ሁለተኛውስ ?

- " አሸሸ አሸሸ ፥ አብይ መጣልን ከመሸ " ማለት ከምሽት ለጥቆ ያለው እንግዲህ ለሊት ነው ። ከጨለማው ዘመን ይባስ ወደ ድቅድቁ ገባን መሆኑ እኮ ነው ።

- ማነህ ልዑል

- አቤት

- በደሞዝ ሞት ፥ ወያኔ ነህ አደል ?


🔥 "እናሲዝ"" አለቺኝ የማርያም ጣቷን ዘርግታ "እናሲዝ" አልኳት አስያዝን ካሸነፈች አዝያት ልዞር ተስማማን

🌟 የሆነ ቀን ቀጥሬያት ተገናኝተን እያወራን "እዩዬ" አለቺኝ የያዘችውን ትንሽ ሻይ ያለበትን ብርጭቆ በሁለት እጇ እያሽከረከረች፥መጨነቋ ፊቷ ላይ ያስታውቃል።

የምትለውን ነገር ሳትለው አስጨነቀኝ "ወዬ እናትዬ" አልኳት

"አንዳንዴ ጓደኞች ሆነን በቀረን ብዬ የምመኝበት ጊዜ እየበዛ ነው" አለቺኝ ሰውነቴ ቅዝቅዝ አለ "ምነው እናቴ ያጎደልኩት ነገር አለ" አልኳት ይሄ ነው የምትለኝ ነገር ቢኖር እና ማስተካከል ብችል ብዬ

💥 "አያይ በፍፁም እንደሱ አይደለም... በቃ ጓደኛሞች እያለን የነበረንን ነፃነት እወደዋለሁ... ቅርበታችን... ምንም አለመደባበቃችንን... ሳቃችን... ቀልዶቻችን መተፋፈር አልነበረውም አሁን ግን ተመልከተን... ድሮ አፈር መስለን እንዳልተገናኘን አሁን ልብሳችንን ፀጉራችንን ስንጠበብበት ያናድድኛል። እንደድሮ ነፃ አይደለንም አሁን ቃላት መርጠን ነው የምናወራው ተቆጥበን ነው የምንስቀው። ..."

"ስለዚህ...?!"  አልኳት ድምፄ ከጠበኩት በላይ ሻክሮ ምክንያቱም ከተናገረችው አንዱም ስህተት የለውም
🌟 "እዩዬ እንዳሰብከው አይደለም የእውነት አሁን ያለንን ነገር እወደዋለሁ ግን ደሞ ውልብ ሲልብኝ ጓደኝነታችን ይናፍቀኛል" አለች እጆቼን ይዛ

አየኋት... አይኖቿን አየኋቸው... እንዳልከፋበት ፈርታለች "እዩ አላስደበርኩህማ በእማማ ሞት" አለቺኝ "ብትሞክሪ ራሱ ልታስከፊኝ አትቺይም" አልኳት "ለምን ያን ያህልማ ሰነፍ አይደለሁም" አለች እየፈገገች "ተፈጥሮሽ አይደለም ማንንም በተለይ እኔን ማስከፋት አትቺይም አልኳት"

"እናሲዝ"" አለቺኝ የማርያም ጣቷን ዘርግታ "እናሲዝ" አልኳት አስያዝን ካሸነፈች አዝያት ልዞር ተስማማን

ከዛ ግን ተመኘሁ ሁሉም እንደኛ ጉድለቶቹን ፊትለፊት መነጋገር ቢችል ብዬ ምናልባት ብዙ ፀቦች ፍቺዎች ይቀንሳሉ።

Nani እንደፃፈችው✍


"የሚፈልጉትን አይፈልጉትም "
short story




ግልጽ ሰው እወዳለሁ አለችው

ህይወቱን ግልጽ ነገራት ጠላችው

ቀላል ሰው ደስ ይለኛል አለችው

ቀለል ሲል ረከሰባት ሸሸችው

ኩሩ ሰው ምርጫዬ ነው ስትለው ኮራ አለ

ጠበርክ ብላው ሄደች።

የተረጋጋ ሰው እወዳለሁ አለችው

ሲረጋጋ ተንቀራፈፍቅ ብላው ሄደች

የማይጨቃጨቅ ሰው ነው ምርጫዬ አለች

ስህተቷን ሲያልፋት ባትወደኝ ነው ግድ ያለሰጠህ አለችው

አስሬ መገናኘት መደዋወል ምናምን አልወድም አልችው።

መደወሉን ሲቀንስ ብትፈልገኝ ኖሮ ይሄንንም ብልህ ገፍተህ ትመጣ ትደውል ነበር። በቃኸኝ አለችው።


ምን እንዳጠፋ አሰበ።

እስካሁን አልገባውም።

ለአባቱ ነገረው ሁሉንም። አባቱ መለሰለት።

"ሰው ወዳለሁ ያለው ሁሉ አይኮንለትም።

ያለውን ሁሉ የምደረግለት ለአምላክህ ነው።

ሰው እኮ የፈለገውን ነገር ገና መፈለጉን አርግጠኛ አደለም።

የሚወደውን ነገር ለይቶ ያልጨረሰ ፍጡር ነው።

በተለይ እነሱ ወጣቶቹ የሚፈልጉትን ራሱ በቅጡ አይፈልጉትም"

"ምን ልሁንላት?"

"ራስህን ሁንላት!
የምትልህን ትተህ የማትልህን ሁንላት።
ሴቶች ከንግግራቸው ጋ ሩቅ ናቸው።
ያሉህን ትተህ ያላሉህን ስማቸው"

የልጁ ስልክ ጮኸ። እሷ ናት።

~ ~ ~ ~ ~ ~

ኤልያስ ሽታኹን


የበቀደሟ ልጅ ደወለችለት።
ሰፈሩ መጥታለች። ደነገጠ።

ሊዪቅፋት ሲሞክር ሸሸችው።

"ይቅርታ በለኝ" አለችው

"ይቅርታ "

"ድገመው"

"ይቅርታ"

"ድገመው "

"ይቅርታ "

ፀጥ አለች። ከትንሽ ፋታ በኋላ ደገመው

"ይቅርታ" አላት

"በቃ በቃ ስትደጋግመው እየቀለድክ ነው ሚመስለኝ"

"እሺ " ብሎ ጸጥ አለ።

"ምን እያሰብክ ነው"

ግራ ገባው። አሰበ

"አላጠፋሁም እኮ ላንቺ ስል ነው ይቅርታ ያልኩትም ብላት" ትሄዳለች

"ይቅርታ ልልሽ ነበር ብላትም ደጋገምከው ከልብህ አይደለም መሰለኝ ብላ ትሄዳለች"

"ቆይ ምን አርጌሽ ነው ብላትም ጭራሽ ያደረከውንም አታቅም ብላ " ትሄዳለች

"ፀጥ ብላትም ንቀት ነው ብላ ትሄዳለች"
ዝም አለ።

"እኔ ቆሜ እየተናደድኩ ጭራሽ ታስባለህ ንቀት መሆኑ ነው"

ሄደች.. .. ..

በቆመበት ቀረ።
መኪኖች እንደአደባባይ ይዞሩት ጀመር።

አንድ እብድ በጥቅስና በመፈክር መሐል ያለ ወረቀት ለጥፎ አየው።

ወረቀቱ

"ባንተ በኩል ሲያለፍ ያገኘኸውን ሰው
" እኔ ጋ ነው የመጣኸው" ብለህ ለማቆየት አትሞክር።"

~ ~ ~ ~ ~ ~

ኤልያስ ሽታኹን


እሜቴ የማታ ለሁሉም አንድ ቃላት ይመልሳሉ ፡
" ታለ አይቆጠርም"
ጉድ ወደኋላ አደለም ?
- " እንግዲህ አይዞዎ ፥ እግዚሐርም አለዎ ።" ይላል ያ መዝጋቢ ።
- " አይይይ... ምኑን አመጣኸዋ ? "
- " እንዴት ? "
- "ሰው ተተው ቆየ ብዬ "
- " ማን እግዚሐር ? "
- " አዎ ሰው ትቷል ። እርግፍ አርጎ ትቷል"
- " እኮ እግዚሐር ?"
- " አዎ የኔ ልጅ ። እሱም ቢሆን ታለ አይቆጠርም ። "
[ ሸ ሙ ኔ ]





20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.