ሰው ማገት/ገንዘብ መጠየቅ‼️
ሰው አግተው ገንዘብ የሚጠይቁ ወይም የሚረሽኑ በራሳቸው ቤተሰቦች ላይ እንደወሰኑ ይቆጠራል‼️
በአማራ ክልል እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በስልክ message ይሄን ያህል ብር አስገባ ካልሆነ ግን በልጅህ፣በሚስትህ፣በመኪናህ...ወዘተ ከሚሉ ማስፈራሪያዎች ጋር የደረሳቸው ሰዎች እንዲሁም ባለሃብቶች በርካቶች ናቸው።
ለምሳሌ ከሰሞኑ ከደረሰኝ ጥቆማ ውስጥ አንዱ "እኔ ኮንትራከተር ነኝ፣በባለፈው ጥቅምት ወር መጨረሻ አካባቢ ይሄን ያህል ብር አስገባ ካልሆነ ግን እንገልሃለን" የሚል message ደረሰኝ። በኋላ Text የተላከበት ስልክ ሲጣራ ራሱ ኮንትራክተሩ የሚያሰራዉ ቀኝ ሰራተኛ ሆኖ ተገኘ። ልጁ አሁን ሲነቃበት ሸሽቷል።
"ግርግር ለሌባ ያመቻል እንደሚባለው" አሁን ያለውን የፀጥታ ችግር ሰበብ በማድረግ ገንዘብ መጠየቅ የተለመደ የመዝረፊያ መንገድ ያደረገ ግለሰቦች አሉ።
ይሄ ጉዳይ ቀስ በቀስ የለየት ማህበራዊ ቀውስ ከማስከተሉ በፊት የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ገንዘብ በሚጠይቁ/በሚረሽኑ ግለሰቦች ላይ ከሰሞኑ አዲስ እቅድ መንደፋቸው ተሰምቷል።
በዚህ መሰረት ማንኛውም ግለሰብ ወይም ቡድን ሰው አግቶ ገንዘብ የሚጠይቅ/የሚረሽን ከሆነ በምትኩ የአጋቹን የቅርብ ቤተሰቦች/ዘመዶች አግቶ በመውሰድ አጋቹ የፈፀመውን ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወሰድ እወቁልን ማለታቸውን ከሰሞኑ በነበረ ህዝባዊ ውይይቶች ከፍተኛ የመከላከያ አመራሮች ተናግረዋል።
ከዚህ ከእገታ/ገንዘብ መጠየቅ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ በተለይ በአማራ ክልል ዋና ዋና ከተሞች በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
አዩዘሀበሻ
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇⬇️⬇️
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2shttps://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s