🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Musiqa


ድምጻችን ለተዋህዶ ሐይማኖታችን ለኢትትዮጲያ አገራችን

የእግዚአብሔር ሰላም የእናታች የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ፀሎት የመላእክት ጥበቃና የቅዱሳን በረከት ከናንተ
ጋር ይሁን አሜን!
📣ለማስታወቂያ ሥራ👉 @Mane_tekel21

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Musiqa
Statistika
Postlar filtri


ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ


◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇


ሰበር ዜና
ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶ የነበረው
የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው ታግዷል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚሰሩ ኦርቶዶክሳውያን የሚዲያ ተቋማት በአንድ ማዕከል  እንዲያገለግሉ፣ የመረጃ ፍሰቱ ወጥነት ያለውና ተቋማዊ መሆን ይችል ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቶ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብረው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ ማከናወን የሚችሉበት ፈቃድ ከመምሪያው መሰጠቱ ይታወሳል።

ከእነዚህ የሚዲያ ተቋማት መካከልም የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን አንዱ ሆኖ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት "ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም።" በሚል ርእስ  የተላለፈው ትምህርትን ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያችን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን እንገልጻለን።

                ሚያዚያ ፲፭ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
                     አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ

          የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
                      ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

#ድምፀ_ተዋህዶ
#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ


በከመ ተብህለ" ሰናይ አርዝ ይፈሪ ሰናየ ፍሬ" ናሁሰ ፈረየት ጉባኤነ ሰናየ ፍሬ!
"መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራል" እንደተባለው  መልካሟ ግቢ ጉባኤያችንም መልካምን ፍሬ ማፍራቷን ቀጥላለች!
ጥዑም ዜማ: መዝገበ ርህራሄ
በዘማሪት ነፃነት ሲሳይ ፡የአንጋፋው ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ግብርና ግቢ ጉባኤ አገልጋይ                                                                                                                                          
እሁድ ሚያዚያ 19 በ"ጊዜ" ሚዲያ ይለቀቃል።
ሁላችንም እናበረታታት🙏


ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቅድስት ድንግል ማርያምን በማስመልከት ባስተላለፉት ትምህርት ዙሪያ ተወያየ !

ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ ማለዳ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ባሳለፍነው አርብ በስቅለት ዕለት በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ ያስተላለፉትን ትምህርት በተመለከተ ውይይት አድርጓል።

በብፁዕነታቸው  የተላለፈውን ትምህርት ዝርዝር ሁኔታን በመመርመርም ውሳኔ ለማስተላለፍ  ይቻል ዘንድ ሁሉም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት በተገኙበት  ለአርብ ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞል።

በተያያዘ ዜና የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በሆኑት በፖፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ቤተ ክርስቲያናችንን በመወከል እንዲገኙ ተወስኗል።

©የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ
#ድምፀ_ተዋህዶ


ብፁዕ አባታችን። ድንግል ማርያም ቤዛዊት አትባልም ብለው ድምዳሜ ሰጥተው ሲያስተምሩ ሰማሁ። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አይባልም ብለን ከምንደመድም እንዲህ ብንል አይሻልምን?

🥀እናታችን ድንግል ማርያምን ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም እንላታለን። ክርስቶስን ቤዛችን ስንለው በመስቀል ተሰቅሎ እኛን ስላዳነን ነው። ድንግል ማርያምን ቤዛዊት ስንላት ግን ቤዛኩሉ ክርስቶስን ስለወለደችልን ነው። ከእርሷ ተወልዶ ዓለምን አድኗልና ነው። ምክንያተ ድኂን ስለሆነች ነው። ልጇ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ ብሎ እንዳስተማረን እሱን ብርሃን እርሷን ደግሞ የብርሃን እናት እንላታለን። ልጇ አምላክ ስለሆነ እርሷ እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ትባላለች። አምላክን የወለደች የአምላክ እናት ማለት ነው። ቤዛዊት ናት ስንል በጸጋ እንደሆነ ልብ እናድርግ። ምናልባት በባሕርይው ቤዛ ሆኖ ያዳነን ክርስቶስ ብቻ ነው ለማለት ፈልገው ከሆነ መልካም ነው።

🥀ንስጥሮስን ክርስቶስ ላይ ያለው የምንታዌ (Dualism) እይታ ድንግል ማርያምን ወላዲተ ሰብእ ከማለት አደረሰው። ድንግል ማርያም የወለደችው ሰው የሆነ አምላክን አምላክ የሆነ ሰውን ነው እንጂ ዕሩቅ ብእሲ (ሰው ብቻን) አልወለደችም። ነገረ ክርስቶስን ከድንግል ማርያም በበለጠ የሚያውቀው ፍጡር የለም ። እርሷ ልጇን ይዛ ከሀገር ሀገር ተንከራታለች። በመስቀልም ጊዜ ከጽንዐ ፍቅሯ የተነሳ ከመስቀሉ ሥር አልቅሳለች። ድንግል ማርያምን እናከብራታለን፣ እናመሰግናታለን፣ እንሰግድላታለን። ነገር ግን ለእርሷ የምናቀርበው ስግደት እና ምስጋና የአክብሮት ስግደትና ምስጋና ነው እንጂ እንደ አምላክ የአምልኮ ስግደት አይደለም።  

🥀ድንግል ማርያም ዓለም ጣዖትን በማምለክ ጨለማ ውስጥ ሳለ ብርሃንን የወለደችልን እናታችን ናት። ድንግል ማርያም ዓለም ለሰይጣን በመገዛት ባርነት ውስጥ ሳለ በመስቀል ተሰቅሎ የእኛን ሞት ሞቶ ነጻነት የሚያጎናጽፍ ጌታን ወለደችልን። ዓለም ተርቦ ነበር። እሷ ግን የሕይወት እንጀራን ወለደችልን። ድንግል ማርያም የትሕትና እናት ናት። ምሥጢራዊም ናት።ማርያም ግን ይህንን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ነበር ተብሏል። እውነትን ይዛ ሳለ በሐሰተኞች ወደ ግብጽ እንድትሰደድ ሆነች።

የቤዛነትን ትርጉም ንገረን ላላችሁኝ እነሆ

ቤዛነት ምንድን ነው?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች በሰው ልጆች ምትክ ያደረገው ሥራ ቤዛነት ይባላል። ቤዛ በአገባቡ "ስለ" ነው። ምሥጢሩ ምትክነትን፣ መቤዠትን ይገልጻል። ቤዛ "ቤዘወ-አዳነ" ከሚለው ግሥ ሲወጣ መድኃኒት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። በሁለቱም ለክርስቶስ ቢነገር ያስኬዳል። መድኃኒታችንም ነውና። ቤዛ-ስለ በሚለው አገባብ ከተተረጎመ ስለእኛ በመስቀል ተሰቅሎ ማዳኑን ይነግረናል። ክርስቶስ ያደረገው ሥራ ሁሉ ስለእኛ ነው። በትርጓሜ በሐተታ በእንቲኣነ (ስለእኛ) እየተባለ የሚገለጸው እንደ ኃጥኣን ስቶ፣ እንደ ሰማዕታት ዕሴትን ሽቶ ያደረገው አለመሆኑን ለመግለጽ ነው።

ይህ ክርስቶስ ያደረገው የቤዛነት ሥራ የባሕርይ ሥራ ነው። ቅዱሳን ደግሞ አምላካቸው ክርስቶስን መስለው ስለሌላው ሰው ብለው የሚቀበሉት መከራ ቤዛነት ነው። ግን የጸጋ ቤዛነት ነው። "ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" የሚለው ቃል ሰዎችም በአቅማቸው አንዱ ለአንዱ ቤዛ መሆን እንዲችሉ የተነገረም ጭምር ነው። ግእዙ "አልቦ ዘየዐቢ ወይኄይስ እምዝ ፍቅር ከመ ብእሲ ዘይሜጡ ነፍሶ ቤዛ ነፍሰ ቢጹ" ይለዋል (ዮሐ.15፥13)። ቅዱሳን ክርስቶስን አብነት አድርገው ስለሌሎች ሰዎች ሲጸልዩ፣ ሲጾሙ፣ ሲሞቱ አይተናል። ጌታም የእነርሱን ፍቅር አይቶ ኃጥኣንን ሲምር በብዛት ተጽፏል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሐዲስ ኪዳን ላይ ስንገባ በሰፊው እንመለከተዋለን።

©በትረ ማርያም አበባው

#ድምፀ_ተዋህዶ


“ወእምግርማሁ ተሀውኩ ወኰኑ ከመ አብድንት እለ የአቅቡ መቃብረ [ እርሱን ከመፍራት የተነሣ መቃብሩን የሚጠብቁት ታወኩ እንደ በድንም ሆኑ] ” (ማቴ 28፥4)

🌿 ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤

                በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ 🌿

🌿 አሰሮ ለሰይጣን፤

                   አግዐዞ ለአዳም፤🌿

🌿ሠላም፤

                   እምይዕዜሰ፤ 🌿

🌿ኮነ፤

             ፍስሐ ወሠላም፡🌿



እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ !! ✝️🌿


የማርያም ለቅሶ

ልጄ ወዳጄ ሆይ ለእኔ ወዮታ አለብኝ ... በጦር ሲወጉህና ሲገድሉህ ዓይኖቼ ከምያዩ ይልቅ ልጄ ወዳጄ ሆይ ነፍሴን ከስጋዬ ትለያት ዘንድ እማልድሃለሁ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ ይህ በራስህ የተቀዳጀኸው የእሾህ አክሊል ምነው እኔ በተቀዳጀሁትና የመከራህ ተሳታፊ በሆንኩ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ አንተን በእሱ ላይ በሰቀሉበት መስቀልህ በሰላም እሰናበትሃለሁ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ አይሁድ መራቃቸውን በተፉበት ብርሃንንም በተሞላ ፊትህ እሰናበትሃለሁ: ንጉስ ሆይ በሁለት ወንበዴዎች መካከል እርቃኑን ለቆመው አካልህ እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ እጣ በተጣጣሉበት ክብር ልብስህ እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ።
ልጄ ወዳጄ ሆይ አክሊለ ሶክክን ለተቀዳጀ እራስህ ሰላም እያልኩና እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ።

ምንጭ ግብረ ሕማማት

#ድምፀ_ተዋህዶ
#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ




በዓለ ስቅለት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መሪነት ሲፈጸም በምስል

ሚያዝያ 10 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ፎቶ:- AMN

#ድምፀ_ተዋህዶ


በሰሞነ ሕማማት የጸሎተ ሐሙስ ሕጽበተ እግር በግብጽ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ቅዱር ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታውድሮስ ዳግማዊ በተገኙበት ተከብሯል።

#ድምፀ_ተዋህዶ



12 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.