#የፍርድ ባለመብትና የፍርድ ባለዕዳ በማንኛውም ጊዜ ተስማምተው ጉዳያቸውን #በእርቅ መጨረስ እንደሚችሉ እና በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.427 የአማርኛ ቅጂው #ገዢ ሰለመሆኑ የተወሰነ አሰተማሪ የአፈጻጸም ውሳኔ
#አፈፃፀም ለአፈፃፀሙ መነሻ የሆነውን መሰረታዊ ፍርድ/ውሳኔ የሚከተል በመሆኑ አፈፃፀሙን የሚመራው ፍርድ ቤት ፍርዱን የሚያስፈፅመው በስነስርዓት ህጉ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት እንደ ፍርዱ ይዘትና መንፈስ ውጤት ባለው መልኩ ሊሆን ይገባል፡፡(የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.372፤378፤392(1) ድንጋጌዎችን መረዳት ይቻላል
በመሰረቱ የሀራጅ ሽያጭ ስለሚቆምበት ወይም ስለሚቋረጥበት ሁኔታ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.427 የተመለከተ ሲሆን የዚህ ድንጋጌ አማርኛ እና እንግሉዘኛ ቅጂ ልዩነት ያለው ሲሆን በአማርኛው ቅጂ መሰረት የሀራጅ ሽያጩ የሚቆመው የሀራጅ ማስታወቂያ ከመውጣቱ በፊት የፍርድ ባለዕዳው የተፈረደበትን ገንዘብ ወጪና ኪሳራውን ጨምሮ ለሀራጅ ሻጩ አልያም ሽያጩን ላዘዘው ፍርድ ያስረከበ መሆኑ ሲረጋገጥ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን እንግሉዘኛው ቅጂ ደግሞ የሀራጁ ሽያጭ የሚቆመው ሀራጅ ባዩ የጨረታውን ከፍተኛ ዋጋ ከመግለፁና ጨረታውን ከማቆሙ በፊት በማናቸውም ጊዜ የፍርድ ባለዕዳው የተፈረደበትን ገንዘብ ወጪና ኪሳራውን ጨምሮ ለሀራጅ ሻጩ አልያም ሽያጩን ላዘዘው ፍርድ ያስረከበ መሆኑ ሲረጋገጥ መሆኑን“…before the lot is knocked down…” የሚለውን ሀረግ በመጠቀም ለፍርድ ባለዕዳው የሰፋ የመክፈያ ጊዜ የሰጠ መሆኑን ከድንጋጌው ይዘት ለመረዳት ይቻላል ከሁለቱ ቅጂዎች የአማርኛ ቅጂው ገዢ በመሆኑ
#ለፍርድ ባለዕዳው የመጨረሻ የእዳው መክፈያ ጊዜ የሀራጅ ማስታወቂያ ከመውጣቱ በፊት ያለው ጊዜ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን ይህ በሌላ አኳኋን እንዲፈፀም ካልታዘዘ በቀር ማናቸውም ሀብት ወይም ንብረት የሚሸጠው የሽያጭ ስርዓት እንዲያስፈፅም ፍርድ ቤቱ በተለይ ባዘዘው ሰው አማካኝነት ወይም በፍርድ ቤቱ ሰራተኛ አማካኝነት ግልፅ የሀራጅ ሽያጭ በማድረግ መሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.422(2) መመልከቱ
#በተለይም “በሌላ አኳኋን እንዲፈፀም ካታዘዘ በቀር…” በሚል የተከተው የህጉ ሀረግ እንዲሁም በፍርድ አፈፃፀም ምክንያት በሀራጅ እንዲሸጥ የተወሰነውን ንብረት ፍርድ ቤቱ በግል ወይም በስምምነት እንዲሸጥ ትዕዛዝ ለመስጠት የሚችል መሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህቁ.422(2) መመልከቱ የሀራጅ ሽያጭ የአፈጻጸም ሂደት ፍርዱን ለማስፈጸም የተቀመጠ የመጨረሻ አማራጭ መሆኑን የሚያሳዩ በመሆናቸው በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.427 የተመለከተው ድንጋጌ አፈፃፀምም ከዚሁ ድንጋጌ አግባብነት አንፃር ሊቃኝ የሚገባው መሆኑን ያሳያል፡፡
# የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.427 የፍርድ ባለዕዳው የተፈረደበትን ገንዘብ ኪሳራውንና ወጪውን በሙለ መክፈለን ማረጋገጡን የሀራጅ ሽያጩን ለማስቆም መስፈርት አድርጎ ማስቀመጡ ድንጋጌው በአንድ ፍርድ ከንብረት ክፍፍል ጋር በተያያዘ ሁለቱም ወገኖች ባለመብት የሆኑ ወገኖችን የንብረት ክፍፍል ሂደት ለመምራት ከተቀመጠ የአፈፃፀም ድንጋጌ ይልቅ የፍርድ ባመብት በፍርድ ባለዕዳውበፍርድ የተጎናፀፈውን መብት የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር አፈፃፀሙን ከሚያደናቅፈው የፍርድ ባለዕዳ ለመጠበቅ የተቀመጠ ጥብቅ ድንጋጌ መሆኑን እያሳየ፤ከንብረት ክፍፍል ጋር በተያያዘ በግልጽ ሀራጅ ሽያጭ ክፍፍለን ማስፈፀም የመጨረሻ አማራጭ መሆኑን ለግራ ቀኙ መብትን ካጎናጸፈው ውሳኔ እና ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.422 ድንጋጌ ለመረዳ ይቻላል👇👇👇
https://t.me/ethiolawtips